በውጭ ሃገር የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ድርጂቶች በፋኖ ውህደት ላይ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ለቦርከና የተላከው መግለጫ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ዋሽንግተን ዲ.ሲ.
ኅዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም.
እኛ፣ ስማችን ከታች የተዘረዘረው፥ በመላውዓለም የምንገኝ የሲቪል ማህሕበራት፣ በቅርቡ ከአራቱም ማዕዘኖች የተሰባሰቡ የፋኖ ታጋይ ቡድኖች በጎንደር ክፍለ ሀገር ኅዳር 13/2015 ዓ/ም የዐማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን መሥርተው በአንድ ድርጅት ሥር ለመቀናበር ያሳለፉትን ውሳኔ በፅሞና አጥነትን፣ ይህን የድጋፍ መግለጫ አውጥተናል።
ፋኖ የአገርን ልዕልና ለማስከበር፣ የወገንን ህልውና ለመንከባከብና የአገራችንን ዳር ድንበርን ከጠላት ለመከላከል፣ ለዘመናት ያልተቋረጠ፣ በጀግንነትና ጀብድ ያሸበረቀ አገልግሎት ያስመዘገበና ያስዘከረ፣ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊኮራበትና ሊመካበት የሚገባ ሕዝባዊ ድርጅት ነው።
ከፋሽሽት ጣሊያን እስከ አረመኔያዊው የሕወሓት የጭካኔ ዘመቻ ድረስ፣ ፋኖ ለወገኖቹ የብረት አጥር በመሆንና ዘብ በመቆም ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍሏል። እየከፈለም ይገኛል።
በተለይም በአለፉት ሁለት ዓመታት አገሪቱ በአጠቃላይ፣ በተለይ ደግሞ በዐማራ ሕዝብ፣ በውጭ ጠላቶችና በውስጥ ዘውጋዊ ፅንፈኞች የተቀነባበረ ጥቃት ሲዘነዘርባቸው፣ ከየአካባቢው በራሳቸው አነሳሽነት ቅርሳቸውን ሸጠው እንዲሁም ያለምንም መንግሥታዊ እርዳታ ያበረከቱት አስትዋጽዖና የተጎናፀፉት ድል፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፎ በአድናቆት ሲወሳ የሚኖር ነው።
ሆኖም በዘረኝነት ላይ ተጣብቆ፣ የአገሪቱን ድርና ማግ በመበጣጠስ ላይ የሚገኘው ኋላ-ቀር ስርአት፣ የፋኖ ቡድኖች በአንድነት እንዳይሠሩ እንቅፋት ከመሆንም በላይ፣ የቡድኖቹንም ህልውና የሚያሰጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ስለዚህ በቅርቡ የታወጀው የውህደት ስምምነት ጊዜው የደረሰና እጅግ በጣም አስፈላጊ ሂደት በመሆኑ፣ መደገፍ የሚገባውና በተለያየ አቅጣጫ እርዳታ የሚያስፈልገው ነው ብለን እናምናለን። ውህደቱን በተለይ አንገብጋቢ የሚያደርገው፣ በኦሮሚያ ክልል በዐማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደው አሰቃቂ ጭፍጨፋ እየከፋ መጥቶ፣ ችግሩን ለማገትና ተጠቂዎቹን የዐማራ ተወላጆች ለመታደግ በመንግሥት በኩል ምንም ዓይነት አስተማማኝ እርምጃ ሲወሰድ የማይታይበት ሁኔታ ጎልቶ መፈጠሩ ነው።
በአንፃሩም፣ የዘውጋዊ ፅንፈኞችን ፍላጎት ለማርካት፣ በመንግሥትም ሆነ በወኪሎቹ፣ በፋኖ ላይ በመካሄድ ያለውን አስከፊና አደገኛ ዘመቻ አጥብቀን እያወገዝን፣ በተለይ አገሩን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ ከዚህ አሳፋሪና እኩይ ተግባር ተቆጥቦ፣ ይልቁንም ድርጅቱ ለአገር ደህንነት ያደረገውን አስተዋፅኦ በሚመጥን ደረጃ ድጋፍና እውቅና እንዲሰጥ ጠንካራ ጥሪ እናቀርባለን።
አገር ወዳድና ለፍትህ የቆሙ ኢትዮጵያውያንም፣ ዝምታቸውን ሰብረው፣ ይህን ባለውለታና መመኪያ ድርጅት አቅፈውና ደግፈው፣ እየተሰነዘረበት ያለውን ጥቃት ነቅቶ በመከላክል፣ የድርጅቱ ደጀን፣ አይንና ጆሮ በመሆን፣ አስፈላጊውን የቁሳቁስ፣ የሥነልቦናና ልዩ ልዩ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያለባቸውን የታሪክ ሀላፊነት እንዲወጡ በአክብሮት እናስታውሳለን።
ፋኖ የዐማራ ሕዝብ አለኝታና የመላው ኢትዮጵያ መኩሪያ ነው!!!
ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች:-
1. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
2. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association 3. The Amhara Association in Queensland, Australia
4. Amhara Dimtse Serechit
5. Amhara Well-being and Development Association
6. Communities of Ethiopians in Finland
7. Concerned Amharas in the Diaspora
8. Ethio-Canadian Human Rights Association
9. The Ethiopian Broadcast Group
10. Ethiopian Civic Development Council (ECDC)
11. Freedom and Justice for Telemt Amhara
12. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
13. Global Amhara Coalition
14. Gonder Hibret for Ethiopian Unity
15. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
16. Network of Ethiopian Scholars (NES)
17. Radio Yenesew Ethiopia
18. Selassie Stand Up, Inc.
19. Vision Ethiopia
20. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ