spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeነፃ አስተያየትጠሚ ዶር ዓቢይ እና ፕሪንስፕል

ጠሚ ዶር ዓቢይ እና ፕሪንስፕል

advertisement
Abiy Ahmed _ Principle

ጓንጉል ተሻገር  

ጠሚ ዶር አቢይ በጣም ብዙ “ተከድኖ ይብሰል” ብሎ ጥግ ያስያዟቸው ጉዳዮች ጥግ እስከመቼ? Sidelined till when??? በቃን ብለው ወደፊት መጥተው እያስጨነቋቸው ነው። ሐይማኖት እና ፖለቲካን ከመቀላቀል፣ ከመደበላለቅ፣ ዘይት እና ውሀን ለመቀላቀል ከመሞከር የሞኝ ሙከራ የመጣ ችግር ሊሆን ይችላል ። 

ጠሚ አቢይ አንድ ፕሪንስፕል ኖሯቸው መስመር ሊይዙ አልቻሉም። ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሐል ሆኖ ሁሉቱን ጎራ ሊሾፍሩ ማለትም አንዴ ከጎንደሮች ጋር ሆነው የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴን ያወድሳሉ፣ ችግሩን ወያኔ ለማፈን እንጦጦ ጠብቆ ኮሚቴዌቹን እንዳሰራቸው፣ እንደተገረፉ በመናገር ከወልቃይቴዎች ጎን የተሰለፉ ሆነው ይታያሉ። ትንሽ ቆየት ብለው ደግሞ የወልቃይት ጥያቄ የልማት ጥያቄ እንጂ የማንነት ጥያቄ አይደለም ብለው ከወያኔዎች ጋር መሞዳሞድ ብጤ ይሞክርና ጎንደሬዎች ምን አልክ ብለው ብድግ ሲሉ ልጃችሁ ነኝ ካጠፋሁ ቆንጥጡኝ ብለው ያግባቧቸውና ያልፏቸዋልል። 

በሌላ ጊዜ ደግሞ አንዴ ከethiopianists ጎን ሆነው ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ይሉና  ደስ ብሎን አጨብጭበን ሳንጨርስ ከcessationists  ጋር እየተሞዳሞዱ ለአንድ ክልል ብለን ሕገ መንግስት አንቀይርም ይላሉ። እንደዚህ እንደዚህ እያሉ እንደ ፔንዱለም ሲወዛወዙ ሳያቸው ያሳዝኑኛል። የአገር መሪ ሆነህ ይቅርና ተራ፣ ምክትል ተራ ግለሰብም ብትሆን በዚች ዓለም የምትኖረው ፕሪንስፕል ኖሮህ ቀይ መስመር አስምረህ ነው። ጠሚ ዶር አቢይ ይሄን ማድረግ አቅቷቸዋል ወይም ብልጠት መስሏቸው አልፈለጉም።

የምትቀርቧቸው ተው በሉት፣ ምከሩት።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 

ትዊተር ፡ @zborkena

ፌስቡክ ፡ Borkena 

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,722FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here