
በ ያፌት፣ ተ.ብ.ዜ
“ ከጥንት ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣
ሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው። “
ብሎ አስተምሮ፣
የሕዝብን እሮሮ፣
እንዲዳረስ ብሎ ለምሁራን በሙሉ
እርግማን ትቶልን ሄዷል ጀግናው ኃይሉ።
አሁን ግን ይድረስዎት በሳቅ ለሚያፈዙት፣
አገር ሲቀጣጠል ጥርስዎን ለሚያሳዩት
ለጥቅልል ሚኒስቴር ጀርባ አጥንት ላጡት፣
ከዛሬ ጀምሮ ቅንᎅርስ ልበልዎት።
ለመጪው አመት በዓል ለገናው ልደት፣
በግፍ ያሰሩትን ንፁሐንን ፍቱና፣
እኛም በተራችን እንደንግጥ በገና።
ግና ምን ይሆናል ይህ ሁሉ ባልነበር፣
ያለአግባብ ወርሰውት የነቴዎድሮስንወንበር
ጥቅልል ብለው ተኙ ከተረኞች መንደር።
ወንበርሽ፣ ወንበሬ፣ ከሆነ ነገሩ፣
የርስዎን “ዲሞክራሲ” ሚስጢሩን ይንገሩ።
ወይስ ብልግና ነው “ብልጽግና” ማለት፣
ሰው: ሰው: የሚሸተውን፣ ራቁት ማስቀረት።
ስሙን በማሽሞንሞን፣እድገት፣ፍትህ ቢሉ፣
ወጥ መርገጥ ይሆናል ዘር ሲቀላቅሉ።
በዘር የታመሰው የኢትዮዽያን እንጀራ፣
ለዜጎች አይበጅም ይብሉት ከአᎅኪው ጋራ፣
“ዲመንስክራሲ” በዲያብሎስ ተግተን፣
የዕውነት ዲሞክራሲ ወዴት ብለን ባከን።
ዘርን ያስቀደሙ ናዚዎች ፋሽስቶች፣
ዘር፣ ዘር፣ ብለው ሄዱ ከሲዖል በታች።
ፈረሱንም ሰጥተን፣ ሜዳውንም ብለን፣
ጋላቢው ጠፋና በዘር ተጠቀለ ልን።
አንድ ዜጋ ብሎ ያጨበጨበው ጣት፣
ማን ላይ ይቀስራል ኢትዮዽያን ሲያጣት።
መሻገሩ ቀርቶ ወደ መስመጥ ሳንሄድ፣
የቀይ ባሕሩ ትርክት፣የፈርኦን ጉድ፣
ዳግም ይከሰታል በውድሞ በግድ:
“ባለንበት መቆም” አማራ ጭ መንገድ።
ለዐበይት በዓላት መልእክት፣
ለአስደንጋጭ ዜና ብሥራተ-ልደት፣
ለ ፈረንጅ 2 0 2 3 የ ተስፋ ዓመት።
የ እ ም ነ ት መልዕከት 🥀
ያፌት፣ ተ.ብ.ዜ
i.mnet@yahoo.com
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena