spot_img
Sunday, July 21, 2024
Homeነፃ አስተያየትሕዝብ ሆይ! ተይሁዳዊ ሽምግልና ፍትህና ሰላምን እየጠበክ መከራህን አታራዝመው!

ሕዝብ ሆይ! ተይሁዳዊ ሽምግልና ፍትህና ሰላምን እየጠበክ መከራህን አታራዝመው!

Abiy _ Getachew

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

እንደ ይህአድግ ቁጥር አንድ ሁሉ በሕዝብ የቁጣ ማእበል የተጥለቀለቀው ይህ አድግ ቁጥር ሁለት ይሁዳዊ ሽምግልናን የወንበር ማስጠበቂያና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀምበት ነው፡፡ ክርስቶስ አእዋፍዋ የሆነውን ቅድስት ቤተክርስትያን ሳይቀር በይሁዳዊ የሽምግልና መሳሪያ ሊያጠፋ የይሁዳ ሽማግሌዎችን እያሰማራ ነው፡፡

በታሪካዊትና መንፈሳዊት ኢትዮጵያ ሽምግልና ከእውነተኛ ችሎት እጅግ የበለጠ ርትኡ ፍርድ የመስጥትና ዘላዊ ሰላምን የማስፈን መለኮታዊ ሀይል ነበረው፡፡ የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች እየጠራረገ የሰይጣንን የቅጥፈት፣ የሌብነት፣ የአውሬነትና የጭራቅነት መንፈስ ሲሰራና ሲተክል የኖረው ይሁዳው ይህ አድግ ከመጣ ጀምሮ ሽምግልና ተበዳይን ከበዳይ እግር የሚያስደፋና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ ሆኗል፡፡ 

ይህ አድግ ቁጥር አንድ ኤፍሬም ይስሀቅን የይሁዳዊ ሽምግልና መሪ ተዋናይ አድርጎ እደተጠቀመበት ሁሉ  በአራት ዓመታት ውስጥ ወድ ሶስት ሚሊዮን ሕዝብ የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈው ከአስር ሚሊዮን ሕህዝብ በላይ ስደተኛ ያደረገው ይህ አድግ ቁጥር ሁለት ደሞ ስለሽምግልና ምንም የማያውቁትን ሆደ ኣደሮች የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ከአለፈው መማር ያቃተው ልብ የለሽም በማያባራ ይሁዳዊ ሽምግልና እየተጠለፈ ታግሎ ማስወገድ ያለበትን መከራ እያራዘመው ነው፡፡   

የውሸት እርቅና ምግልናን የማምታት አባዜ፦ ድርድር እንጅ ሽምግልናን የማያውቁት ምዕራባውያን ሰው ከተፈጠረበት ዘመን ጀምሮ የነበረውን የኢትዮጵያውያን እምነትና ባህል ተሸቀጣቸውና ተእርጥባናቸው ጋር በሚልኩት እንደ ጥንዚዛ በሚያፈናጥር የዳንስ ባህል ከተፈታተኑት በከፋ ሁኔታ ይህ አድግንና እንደ ኤፍሬም ይስሀቅ ያሉ ተላላኪዎች ተጠቅመው የኢትዮጵያን የሽምግልና ሥርዓት ማጥፋቱን አንደቀጠሉ ነው፡፡ ሽምግልናን ድርድር በሚባል ተበዳይን ከበዳይ እግር አስወድቆ ይቅርታ በሚያስጠይቅ ኤፍሬም ይሳቃዊ ወለፈንዲና ኢመለኮታዊ ተግባር ክፉኛ እያጠቁት ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሽምግልና መለኮታዊ ሚዛንን፣ ፍርድንና ፍትህን ያካትታል፡፡ በአንፃሩ ይህ አድግና ኤፍሬም ይሳቅ እንደ ወረርሽኝ ጎትተው ያስገቡት ሳጥናኤላዊ ድርድር መለኮታዊ ሚዛንን፣ ትክክለኛ ፍርድንና ፍትህን በመዳመጫ ደፍጥጦ የተጎዳውን ደካማ ተጎጂው ጉልበታም በደም የከረፋ እግር ሥር ወድቆ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያደርጋል፡፡ 

እምነት ቀርቶ የአውሬ ያህል እንኳ የደመነፍስ ባህሪ ካልፈጠረባቸው የይህ አድግ አረመኔዎች በሽምግልና በኩል እርቅን፣ ፍትህንና ሰላምን መጠበቅ ከሳጥናኤል በረከትን ተጭራቅ ርህራሄን እየጠበቁ ሲንዘላዘሉ እንደመኖር ነው፡፡  

ሕዝብ ሆይ! ጭራቆች ለወንበር መጠበቂያና ለሕዝብ መጨፍጨፊያ ተሚጠቀሙበት ይሁዳዊ ሽምግልና ፍትህና ሰላምን ጠብቀህ መከራህን አታራዝመው፡፡ መፍትሔው  ጭራቅን ደጋግፎ ተወንበር አለማውጣት፤ ከወጣም ዥልጦ ማውረድ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ጥር ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here