spot_img
Saturday, September 23, 2023
Homeነፃ አስተያየትየማይሠበረው እስክንድር ነጋ!!! (ከቴዎድሮስ ሐይሌ )

የማይሠበረው እስክንድር ነጋ!!! (ከቴዎድሮስ ሐይሌ )

advertisement

ከቴዎድሮስ ሐይሌ 

በእሳት ቀልጦ ወርቅ የሆነ:: በመከራ ውስጥ በጽናት ያለፈ:: በአገዛዝ ጭለማ ውስጥ ለሚኖረው የተስፉ ጭላንጭል ያሳየ ::ሁሉን ትቶ እራሱን ለአላማው የሰጠ :: ሃገሩን ከእራሱም ከቤተሰቡም በላይ ወዶ የተንከራተተ:: ዛቻ ያላስደነገጠው እስራት ትጥቁን ያላስፈታው ስቃይ ከመንገዱ ያላራቀው::  

የዘመናችን ትውልድ ተምሳሌት : የጽናት አርዐያ ; የብርታት ቀንዲል! ከድርሻው በላይ ዋጋ የከፈለ ; ስለ እውነት የጠቆረ ስለወገኑ የተሰቃየ የመርሕ ሰው ! የውግዘት ፍላጻ የስድብ ወጀብ የሽሙጥ ሰይፍ የተንበርካኪዎች ማውካካት ያላስበረገገው ቆራጥ ! ተመዝኖ የከበደ ተፈትኖ ያለፈ !! 

ሰውዬው ቢጫኑት የማይጎብጥ ብረት ሊሰብሩት የማይቻሉት አለት ነው:: መከራን ገና በእሩቁ ፈርተው ይጠብቁ ዘንድ የተሰጣቸውን መንጋ ጥለው ጻጻሳቱ ሲሰደዱ : ካህናቱ ለገዥዎች ሲያጎበድዱ ሼኮች ምዕመናቸውን ጥለው ሲንበረከኩ ;ምሁራን በአድርባይነት ሲሰለፉ ; ጋዜጠኛው ቴክኖክራቱ ፖለቲከኛው በየፌርማታው ሲንጠባጠብ ብቻውን ለሦስት አስዕርተ እመታት ከመስመሩ ሳይወጣ አንባገነኖችን የታገለ ብርቱ:: ጏደኞቹ በገዥዎች ሙገሳ : በስልጣን ቅልውጥ ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ የካዱት :: ወዳጆቹ በባዶ ፕሮፓጋንዳ የተለዩት::አድናቂዎቹ በውዥንብር የተውት :: ሕወሃትን በብዕር ታግሎ አመድ ያደረገ:: የኦህዴድ ኦነግን የክፉት ድሪቶ የገለጠ :: የመሪውን መቀላመድ ሃሳዊ ተስፉ ያመከነ:: አስመሳዩን ለትዝብት አድርባዩን ለውርድት አጨብጫቢውን ለመናቅ ያበቃ የሃቀኝነት የማዕዘን እራስ ሆኖ በትውልድና በታሪክ ፊት የተገኘ:: 

ኢትዮጵያ ከአመድ አንስታ ያከበረቻቸው ; ሕዝቧ ሳይማር አስተምሮ; እየራበው አጥግቦ ;ለወግ ማዕረግ ያበቃቸው ምሁራን ; ጥቂቶች የጠቡትን ጡቷን ሲነክሱ ; የቀሩትም ሲያሴሩ ; በርካቶችም ለመጣው በማሽርገድ ሲቆሙ ; የተረፉትም ትተዋት ሲፈረጡ በጣት የሚቆጠሩት ብቻ አብረዋት ሁሉን ተጋፍጠዋል::  ከነዚህ ጥቂቶች አንዱናዋናው እስክንድር ነጋ ነው:: 

መከራው ሳይከብደው ስቃዩ ሳያመው ከቤተሰቡ መነጠሉ ሳያሳቅቀው ቀርቶ አይደለም ሁሉን የቻለው:: በሃይማኖቱ ካለው ጽናት ለሃገሩ ካለው ፍቅርና ለመብት ልዕልና ለዲሞክራሲ መረጋገጥ ካለው ፍጽም እምነት በመነሳት ነው:: 

ዛሬም እስክንድር ለዳግም እስር ተዳርጏል:: የሰው በላውን ኦዴፓ የግድያ ሴራ ሸሽቶ ከሄደበት አማራ ክልል ተይዞ ለአራጆች መሰጠቱ ግን እጅግ ልብ ይሰብራል:: አማራን እንደ ሕዝብ ያዋረደ አዴፓ የተባለው ቡድን ሊፈወስ የማይችል ቆሻሻ ድርጅት መሆኑ ፍጹም ያሳየ አጋጣሚ ሆኗል:: የአማራ ልዩ ሃይል ትላንት ለክብር ያበቃውን መሪውን ጀነራል ተፈራና ጏዶቺን አሰረ :: ዛሬ ደግሞ የሕዝብን ልጅ የአማራ ሕዝብን ስቃይ በአለም አደባባይ ያስተጋባውን እስክንድር ነጋን አስሮና አሳልፎ ለአራጆች አቀረበ:: እንዴት አንድ ጀግና አይሆንም የሚል ወንድ ከመሃላችሁ ጠፉ :: እስክንድር ምንም ይሁን ምን በወርቅ የተጻፈ ታሪክ ያለው ታላቅ ሰው ነው:: ይብላኝ ሱሪህን ላወለከው የአማራ ክልል አመራር ይብላኝ ለክልሉ ታጣቂ እራስህን አስንቀህ ክብርህን አዋርደሃል:: የኦሮሙማው ተረኛ መንጋ እስክንድርን በአደባባይ ለማጣጣል ቢሞክርም ከልቡ ግን ያከብረዋል:: ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ስሙ ሲጠራ የሚርዱና ሱሪያቸው የሚረጥበው ሹማምንት ቀላል አይደለም::

እስክንድር ዛሬም ከብሯል ::ለሚያምንበት አላማ ዛሬም ያው ነው:: ቀና ኮስተር እንዳለ ነው የታይው :: አስር ሞት ቢመጣም ሽብርና ፍርሃት በእርሱ ዘንድ ቦታ የላቸውም:: ዛሬም የሽንፈት ስሜት አንገትን መድፉትን አላሳየም:: እስክንድር የማይሰበር ነው:: አላማው ሕዝባዊ መንፈሱ ንጹህ ግቡም እኩልነት ነው::   ይብላኝ ለኛ ቆመን ለቀረንው:: ይብላኝ የማንም አዛባ መጫወቻ ለሆነው ከተሜ:: ይብላኝ ለዚህ አልጫት ውልድ ተስፋውን ለተቀማ እድሉ ለጨነገፈው:: እንደ ሕዝብ ተዋርደናል እንደ ሃገር ደቀናል:: ዘመን በማይዋጁ የጥንታዊ ጋርዮሽ ጉግማንጉ አራዊቶች እጅ ላይ ወድቀናል:: እስክንድርና የእሱ ብጤ ታጋዬች በስቃያቸው ውስጥ ደስታ በመከራቸው ውስጥ የአይምሮ ሰላምና የሞራል ከፍታ ማንም አይነካባቸውም :: 

 ሕዝባችንስ በዚህ ወቅት ምንድን ነው የሚጠብቀው? አዲስ አበቤስ የት ነህ ያለህው?:: አስቀድሞ አደጋውን የጠቆመህ መብትህን ለማስከበር የደከመልህ እስክንድር አላማው ዛሬም አልገባህም? በየልኳንዳና በየመሸታው ከማውደልደል መቼ ነው ለመብትህ የምትቆመው:: በኑሮህ ; በሃይማኖትህ ; በማንነትህ ;በባህልህ እያሸማቀቁህ እየረገጡና እየተፉብህ መኖር ተስማምቶሃል ? ለገጣፎ ሱዳን ድንበር ; ስሉልታ የኬንያ ግዛት ሳይሆን ለአንተው አዲስ አበቤ አዋሳኝ ነው:: የትውልድ ማንነታቸው እየተለየ በሕገወጥ ስም ቤታቸው በላያቸው በተኙበት የሚፈርሰው በጅብ የተበሉትና በተረኞች የተገደሉት ያንተው ወገኖች ናቸው:: የመጣው አደጋ ቤት እስኪመጣ ከሆነ ተመቻችተ ጠብቀው:: ሚስትህ ቀምቶ ሃብትህን ዘርፎ አንገትህን የሚቀነጥህስ ጭራቅ መሆኑ ካልገባህ ይመችህ:: 

 በጋራ ቆመን በድፍረትና በጽናት ለመታገል እስካልቆረጥን ድረስ መከራችን እረጅም ተስፉችንም ጭለማ ነው:: ፍርሃትን ካልፈራን ሞትን ካልደፈርን መጨረሻችን አያምርም:: ጎበዝ የሞትም እኮ አይነት አለው:: አካልህ አንድ ባንድ እየተቆረጠ ብልትህ ተሰልቦ ወይ በቁምህ በር ተዘግቶብህ ከነልጆችህ በእሳት መቃጠልም የሞት ሞት ሞት ይባላል:: በወለጋ ሲደረግ የቆየው ይሄው ነው::  

 በጥላቻ ቅስቀሳ ; በተዛባ ትርክት ; በቁስ ሰቀቀን በስነልቦና ስብራት ; በበቀል ፈረስ የሚጋልብ ጠላት እየከበበህ ነው:: ብትተወው የማይተውህ :: ብትሸሸው የሚከተልህ::ካለጠፉህ አይቆምም ::ካላወደመ አይረካም:: ካልገደለ አይደሰትም:: መርህ ; አላማ ; ሞራል ; ሰብዓዊነት ሕግና ; ስርዐት የማይዳኙት መደዴ ሊሰማራብህ አቆብቁቧል::ጆሮ ያለህ ስማ ሕሊና ያለህ አስተውል:: ለሌላው ሳይሆን ለእራስህ ሕልውናና መብት ዘብ ካልቆምክ የሚያድንህ የለም::  

 በቅዱስ መጽሃፉ ለእራሳችሁ አልቅሱ እንዲል: ሁልህም ለእራስህ አልቅስ:: ትላንት አደጋውን የጠቆሙህ ዛሬ ሲያዙ ከማዘን ለእራስ አልቅስ ለሕይወትህ ዋጋ ከሰጠህ የሚጠበቅብህን አድርግ :: በከንቱ ከንፈር ከመምጠጥና በየሶሾል ሚድያው ከማናፉት መሬት የረገጠ ተግባር ላይ እናተኩር የተደቀነብንን አደጋ ማለፍ የምንችለው በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ ለትግል ስንነሳ ብቻ ነው:: 

ዘላለማዊ ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር!!! 

ምስጋና ለቆራጡ ጀግና እስክንድር ነጋ!!! 

ድል ለዲሞክራሲ!!!

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,676FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here