spot_img
Monday, June 24, 2024
Homeነፃ አስተያየትየአድዋን 127ኛ በዓል የዐብይ ብልጽግና ሲያራክሰው ዝም ልንል አንችልም

የአድዋን 127ኛ በዓል የዐብይ ብልጽግና ሲያራክሰው ዝም ልንል አንችልም

Adwa _ Addis Ababa

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

“ ከሲኦል ተመልሰንም ቢኾን ኢትዮጵያን እንበታትናታለን”! 
ህወሃት የአማራውን ሕዝብ ለማስፈራራትና ወልቃይትን ለማጠቃለል የሰጠን ማስጠንቀቂያ 

“ጠንካራ ሕዝብ አንድነቱንና ክብሩን በደሙ ያፀናል”  የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ዶር ይልቃል ከፋለ 

“ሞት ሰለቸኝ፤ ውሸት ሰለቸኝ” ኦባንግ ሜቶ፤ የሰብአዊ መብት ጠበቃ 

“ዛሬ የውርደት ቀን ነው” አንዳርጋቸው ጽጌ፤ የአድዋን የድል በዓል ብልፅግናዎች ሲያቃውሱት ተመልክቶ የተናገረው 

“የፋሺስት ጣሊያን ጀነራል ግራዚያኒ ከሙታን ተነስቶ እንደገና አዲስ አበባን ይዞ የየካቲትን ፍጅት ሊድግም ነው? ይኽ ምን ይባላል? አቢይ አሕመድ እንደ ሮማዊው ቄሳር እንደ ኔሮ እንጦጦ ላይ ተሰይሞ ክራር እየተጫወተ በተድላ ደስታ እየተዝናና  ይሆን?”  ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልኪያስ

“He (Abiy Ahmad) intentionally closed his eyes to the TPLF’s maneuver to keep its  modern weaponry and its professional defense forces. It seems that Abiy and the TPLF have  silently agreed that the handing over of old weapons and the disbanding of TPLF recruits is  enough to fool Ethiopians into believing that the TPLF has disarmed. “ 

Journalist Leo Okere, “Abiy Ahmad’s Machinations for Amharafrei,” February 22, 2023 

የዚህ ሃተታና ምክረ ሃሳብ ዋና ምክንያት ህወሃታዊያን፤ ኦህዴዳዊያን/ ኦነጋዊያንና የኦሮሞ ብልጽግና የዘውግ አክራሪዎች፤ ተተኪዎችና መሪዎች በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት በሚያምኑ አካላት፤ በተለይ በወጣቱ ትውልድ አባላት ለይ የሚያካሄዱትን ዘርፈ ብዙ ግፍና በደል የሚፈጽሙት በታቀደና ስልት ባለው ደረጃ እንጅ በዘፈቀደ አለማሆኑን ለማሳየት ነው። 

ለዚህ መረጃ ካስፈለገ የዐብይ ብልጽግና መንግሥት የአድዋን በዓል ፍጹምና አደገኛ ወደ ሆነ ጠባብ ብሄርተኝነት ለመቀየር መሞከሩ ነው። ይህ የፖለቲካ ቁማር አብዛኛውን የኦሮሞን ሕዝብ ይወክላል የሚል እምነት የለኝም። የሚያጠናክረው ክስተት ግን የማዘናጋትና አጀንዳዎችን የመቀያየር ጥበበኛ የሆኑት ጠቅላይ ሚንስትር (The Prime Minister who excels  in the art of deception) ኢትዮጵያን ከአንድ ግጭት ወደ ሌላ ግጭት፤ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እያሸጋገሯት መሆኑን ለማሳየት ነው። ህወሃት እኔ ካልገዛኋት ኢትዮጵያን እበታትናታለሁ ብሎ ፎከረ። ኦህዴድ/ኦነግ/የኦሮሞ ብልጽግና እኔ ኢትዮጵያን አፈራርሸና አድሸ ሙሉ በሙሉ የበላይ ሆኘ ካልገዛኋት ብዙ ሚሊየን ሕዝብ ቢጨፈጨፍ አልጠየቅም የሚል መርህ ይከተላል። 

የበላይነት የፖለቲካ ዘዴው ከፈረንጆች የተቀዳ ከፋፍለህ ግዝው መሆኑን መገንዘብና እኛ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት የምናምን ግለሰቦችና ስብስቦች ከጎጥ፤ ከመንደር፤ ከብሄር፤ ከኃይማኖት መለያ በላይ መጥቆ በመውጣት፤ ያለ ምንም ማመነታታት የምንሰበሰብበት፤ የምንደረጃበትና አማራጮችን የምንቃርብበት ወቅት ነው። ይህ ለነገ የሚተው አይደለም። 

ዛሬ ኢትዮጵያ በፖለቲካ ሥልጣን ፍላጎት የሰከሩ ብሄርተኞች የሚገዟት አገር እንጅ፤ በሕግ የበላይነት፤ በሕዝብ እህትማማችነት/ወንድማማችነት/አንድነት፤ በእውነተኛ እክሉልነትና በፍትህ የሚያምን የመንግሥት አመራር የላትም። መንግሥት አለ ብሎ ለመናገር የሚያስችል ሁኔታም የለም። ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ተንቃለች ብል አልሳሳትም። 

ለምሳሌ፤ እስከ አፍንጫው የታጠቀው የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የሱዳንና የደቡብ ሱዳንን ወረራና ሰፊ መሬት ነጠቃ ሊከላከል አልቻለም። በተጻራሪው ግን ሕዝብን ለማስፈራራት ሲባል በአዲስ አበባ የጦር ጀቶችና ሄሊክፕተሮች ሰማይና ምድሩን ሲቆጣጠሩና ሕዝቡን ሲያስፈራሩ ታይተዋል። ሕዝብ እንደ ጠላት የሚታይባትን አገር በሃያኛ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማየት ያማል፤ ያሳፍራል፤ ያዋርዳል። ጠላቱ ማነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። 

የፖለቲካ ጠበብቱ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለፈው የአድዋን 2023 የድል በዓል ለማየት በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ የአይን ምስክር ሆኖ የተናገረውን ታሪክ ሲጠቅሰው ይኖራል። “ዛሬ የውርደት ቀን ነው” ያለው ወዶ አይደለም። የተናገረው ሃቁን ነው። በኦሮሞ ብልጽግና አቀነባባሪነትና አመቻችነት ኢትዮጵያን የሚገዙት ኦህዴዶች/ኦነጋዊያን ጽንፈኞችና እብሪተኞች ናቸው። 

በሌላ አነጋገር፤ ህወሃትን ተክቶ ኢትዮጵያን በበላይነትና በአምባገነንነት በሚገዛው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲና በህወሃት መካከል ያለው ልዩነት ለይስሙላ ነው። በጋራ ጠላታቸው ላይ ይስማማሉ። የጋራ ጠላታቸው የአማራው ብሄር ለመሆኑ ተጨማሪ መረጃ አያስፈልገውም። 

ግን፤ በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደው ግፍና በደል፤ የዱር አራዊት የመሰለ (barbaric) ግድያ፤ ማፈናቀል፤ ማሳደድና ማዋረድ ቀስ በቀስ በአፋሩ፤ በሶማሌው፤ በወላይታው፤ በጉራጌው፤ በትግራዩና በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ሁሉ እንደሚደርስ አንጠራጠር። የሚካሄደው ፍጹም የሆነ ሁሉን አቀፍ የበላይነት ነው። 

ዋናው ብሄር ተኮር ጭካኔ በአማራው ላይ መሆኑን በተለያዩ ትንተናዎቸ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ አሳይቻለሁ። አማራውን ከእልቂት እንዲድን ተከላክሎ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሚቻለው ግን ሌላውንም በኢትዮጵያ የሚኖር ሕዝብ በመቀስቀስና በማበረታት እንጅ በመለያየት ሊሆን አይችልል የሚል እምነት አለኝ። ከፋፋዩን የኦሮሞ ብልፅግናን መንግሥት ካላጋለጥንና ከብሄር ባሻገር ካልተባበርን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ልትቀጥል አትችልም። 

እኛ የለት የለቱን አጀንዳ ብቻ ስለምናይ ነው እንጅ፤ ለዚህ አማራ ጠልነት ስር እየሰደደ መሄድ መሰረት የሆነው በ60ዎቹ ዓመታት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና በውጭ ስለ የብሄረሰቦች ጥያቄ (The national question) ተብሎ ስለሚጠራው ጉዳይ በሰፊው ንትርክ የተካሄ ትርክት መኖሩንና የተማሪውን እንቅስቃሴ ከሁለት እንደ ከፈለው መርሳት የለብንም። ዛሬ “ከአማራ በላይ አማራ ነን” የሚሉት የአማራው ምሁራን፤ ግራ ክንፍ አባላትና ስብስቦች ይህንን ከስታሊን የተወረሰ ትርክት እንዳስተጋቡትና እንዳጠናከሩት የረሱት ይመስለኛል። ስንት ወጣቶች በፖለቲካ ልዩነት ተጨፍጭፈዋል? በኢትዮጵያ ፋይዳቢስ ንትርክ ምክንያት ያሸነፉት የብሄር ነጻ አውጭ ግንባሮች ናቸው—በተለይ ህወሃትና ኦነግ። ብአዴን እኮ የህወሃት ልጅ ነው። 

በሌላ አነጋገር ህወሃት፤ ኦነግ፤ የኤርትራ ነጻ አውጭ ግንባርና ሌሎች ግንባሮች ይህንን የኢትዮጵያ ወጣቶች እንቅስቃሴና የብሄር ፖለቲካ ግብዓት ተጠቅመውበታል። በወቅቱ “ነጻ የምትወጡት ከማን ነው?” ብለን የጠየቅን ጥቂቶች ነን። ይህ ያለፈ ታሪክ ስለሆነ ወደ ጎን እተወዋለሁ። 

የዐብይ ብልጽግና ዛሬ የሚከተለው የፖለቲካ መስመር መሰረት የብሄር፤ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጥያቄ ነው። እኔ የምገነዘበው፤ ሰሜነኞች (አቢሲኒያዎች) ለሶስት ሽህ ዓመታት ገዝተዋል፤ መዝብረዋል፤ ጨቁነዋል ወዘተ እና አሁን ጊዜው የኦሮሞ ብልጽግና የበላይነት መሆኑን በውድ ሆነ በግድ ተቀበሉ የሚለውን ሃቅ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የዚህ ስር ነቀል ለውጥ ወገንተኛ ናቸው (Abiy is partisan to this tectonic shift).  

በአንድ የዋሽንግተን ስብሰባ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እኔና የኔ ጓደኛ ለመሆኑ “የአንተ ኢትዮጵያዊ ጀግና ማነው?” ብየ የኔ አጼ ቴዎድሮስና አፄ ምንኒልክ እንደሆኑ ነገርኩት። “እኔ ጀግና የለኝ” ያለው ትዝ ይለኛል። 

ስላ ወቅቱ ተደራራቢ ቀውስ ምሳሌዎች ልስጥ። 

አማራው ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ማገብ  

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአማራ ብሄር ጠልነትን በግልጽ በሚያሳይ ደረጃ አማራውን በብሄሩ እየለዩ ልክ በበረት እንደታጎረ እንስሳ “መጤ ነህ፤ ነፍጠኛ ነህ፤ የዱሮውን ናፋቂ ነህ፤ ውጣና አትገባም” ወዘተ እያሉ ከቤትና ከንብረቱ እያባረሩት ነው። ከዚህ የባሰ ግፍና በደል፤ ጭካኔና ዘረኛነት አለ? የለም። 

በውጭ የሚኖረው ግዙፍ አማራ የተከፋፈለና ለዓላማ አንድነት በጋራ ለመቆም ያልቻለ ስለሆነ፤ ይህንን የህልውና ጉዳይ እንኳን ለማስቆም በኣንድ ላይ ሆኖ ጠንካራ አቤቱታ ለተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ ኮሚሽን፤ ለአሜሪካና አውሮፓ ባለሥልጣናት፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ ለሂውማን ራይትስ ዎች፤ ለአምነስቲ ኢንተርናሺናል ለማቅረብ አልቻለም። ባጭሩ፤ ከግራ ክንፉ የወረስነው የእርስ በእርስ ጥላቻ፤ መነታረክና መከፋፈል አማራውን እየጎዳው ነው። 

የኦሮሞ ብልጽግና መንግሥት አማራውን እንደ እንስሳ ማጎር፤ ማሳደድ፤ ማዋረድ፤ መጨፍጨፍና ከቀየው በገፍ ማስወገድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ነው። በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ህግጋት መስፈርት ሲታይ ይህ ተደጋጋሚ ድርጊት የዐብይን ብልጽግና መንግሥት በሕግ ያስጠይቀዋል። ክስ መቅረብ አለበት። ለዚህ ባለሞያዎችን ለይቶ እንዲሳተፉ ማድረግና ገንዘብ መሰብሰብ ወሳኝ ነው። 

ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም። 

አዲስ አበባ ወይንስ ሸገር?  

ባለፈው “Is Abiy a liability or an asset?” በሚለው ድርሰቴ እንዳሳየሁት፤ አዲስ አበባን ለማዳከም፤ ፋይዳ ቢስ ለማድረግና በምትኳ “የሸገር ከተማን” ግንባታ በአስቸኳይ ስኪታማ ለማድረግ የሚደረገው የተቀነባበረ እንቅስቃሴ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ይጎዳል። አዲስ አበባ ስትዳከም የሚጎዳው ማነው? ሸገርን ለመገንባት ፈሰስ የሚሆነውን ወደ አንድ ትሪልየን ብር የሚገመት መዋእለንዋይ ማን ይሸከመዋል? ሸገር የማን ከተማ ይሆናል? የሸገር የመጨረሻ ግብ ምንድን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል። ይህ መሰረታዊ ችግር ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ይመለከታል። 

የኢትዮጵያን ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በብሄር መክፋፈል ለምን?  የኢትዮጵያን ተዋህዶ ቤተክርስትያን በዘውግ ለመከፋፈል የሚደረገው ሴራ፤ የአድዋን አገራዊና ዓለም አቀፋዊ በዓል ታሪክና ገጽታ በማናጋት፤ በማዛባትና የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ በማድረግ ለኦነጋዊያን/ኦህዴዳዊያን/የኦሮሞ ብልጽግና መንግሥት አይን ያወጣ የበላይነት አመች ሁኔታዎችን የመፍጠር ሂደት አፍራሽ ነው። ዘረኝነት ነው።

የአማራው ሕዝብ በመላው የኦሮምያ ክልል፤ በሰሜን ሸዋ፤ በቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ፤ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች በኦነጋዊያን ኃይል በጅምላ እየተጨፈጨፈ፤ ከቀየው እየተባረረ ወደ ደብረብርሃንና ሌሎች የአማራ ከተሞች እንዲሸሺ የሚደረገው ወዘተ የሚካሄደው ሁሉ የተያያዘና በሚገባ የታቀደ የበላይነት ጉዞ ነው። እኔ አንዱን ብሄር ተኮር ሂደት ከሌላው ለመለየት አልችልም። ስር ነቀል የሆነ መዋቅራዊ ለውጥ እየተካሄደ ነው። ይህ ሁሉ አፍራሽ ሂደት ነው (This is the  essence of deconstructing Ethiopian society with intent to create a “new Ethiopia.”).  

እኔ የምከራከረው የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት ለመቀጠል የሚቻለው ታላቁንና የመላውን በዓለም ዙሪያ የሚኖረውን፤ በተለይ በቅኝ ገዢዎች ቀንበር ስር ይሰቃይ የነበረውን ጥቁር ሕዝብ ለክብሩ፤ ለነጻነቱ ከዳር እሰከ ዳር የቀሰቀሰውን በታላቁ፤ በአስተዋዩ፤ በጥበበኛው፤ ሕዝብን ለአንድ አገራዊ ዓላማ በማስተባበር ኢትዮጵያን የነጻነት ተምሳሌት ያደረጉትን፤ ዛሬ ይህች አገር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መዲና እንድትሆን መሰረት የጣሉትን አፄ ምንሊክን በማክበርና በማስታወስ ሊሆን ይገባል የሚል ነው። ታሪክን ለስልጣንና ለጥቅም እየበረዙ (Deconstructing and changing historical facts to fit ethnic  elite supremacy) ኢትዮጵያን ለመታደግ አይቻልም። ታሪክ ለስርቆት አያመችምና እስኪ ሰከን በሉ። 

የአድዋ መንፈስ ወጣቶችን በቲር ጋዝ በማፈን፤ በሰደፍ በመደብደብ፤ በማሰርና በማሳደድ፤ አድዋን በቤተክርስቲያን ሆነው ያከብሩ የነበሩ ወገኖቻችን በመግደል ሊሰረዝ አይችልም። የአድዋ መንፈስ የሚከበርበትን ቦታ በመቀየር ሊኮላሽ አይችልም። የአድዋ መንፈስ የእምየ ምኒልክንና የእቴጌ ጣይቱን ምስሎችና ፎቶግራፎች እንዳይሰራጩ በመከልከል ሊበከል አይችልም። የአድዋ መንፈስ የኢትዮጵያን አረንጓዴ ብጫ፤ ቀይ መለያ ሰንደቅ አላማ እንዳይታይ በማድረግ ሊበከል አይችልም። አድዋ በእያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ልብ የሰረፀ ስለሆነ ማንም ኃይል ሊሰርዘው አይችልም። ዋጋ ግን ያስከፍላል። 

“የትላንት የታሪክ ምርኮኞች” ፋይዳ አለውን?  

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ግፍና በደል፤ ጭቆናና ሌላ ጥፋት አልተሰራም ለማለት አልችልም። የአማራውን ሕዝብ ብቻ ለይቶ ላለፉት ጥፋቶች ተጠያቂ፤ ተከሳሺና ተወቃሽ ለማድረግ የሚያስችል መረጃ የለም። ውጣ ውረድ፤ ግፍና በደል በማንኛውም ሀገረ መንንግሥት ግንባታ ላይ የሚደረግ ክስተት ነው። ከሰራነው ስህተት መማርና ኢትዮጵያን ዘመናዊ አገር ማድረግ ግዴታችን ነው። ይህ ግዴታ ግን የአማራው ብቻ ሊሆን አይችልም። ላለፈው ቂም በቀልን እወጣለሁ፤ መግዛትና መብላት የኔ መብትና ተራ ነው በሚል መርህ፤ አማራውን ለይቶ ወደ መሰረታት ከተማ ወደ አዲስ አበባ አትገባም ማለት ከግፍ በላይ ግፍ ነው። ከፋሽስቶች ድርጊት በምን ይለያል? ወንጀል ነው። አማራውን “ምን ልታደርግ ትችላለህ?” የሚል የትእቢተኞች መልእክት ነው። አገር አፍራሽ ነው። አማራውን ሙሉ በሙሉ ማዋረድ ነው። በመሰረታት አገር ተዋርዶ ለመኖር የሚፈልግ አማራ ሆነ ሌላ ኢትዮጵያዊ የለም። በተጨማሪ፤ ማንነቱን የማይቀበልና ታሪኩን የሚክድ ሕዝብ ሊበለፅግ አይችልም። 

በተደጋጋሚ ለማሳሰብ የምፈልገው የአማራው ሕዝብ በመላው ኢትዮጵያ ከሌላው ብሄር፤ ብሄረሰብና ሕዝብ ጋር ተጋብቶ፤ ተዋልዶ፤ ተቻችሎ፤ የነዋሪውን ባህልና ቋንቋ ተቀብሎ፤ ጥሮ ግሮና ተጋምዶ የሚኖር ታላቅ ሕዝብ ነው። ስለሆነም፤ የአማራው እልቂት የሁሉም እልቂት መሆኑን መቀበል ብልሃተኛነትን ያንፀባርቃል። ኢትዮጵያን ለመታደግ አማራውን መታደግ፤ አማራውን ለመታደግ ኢትዮጵያን መታደግ ያስፈልጋል ማለት ነው። ይህ መርህ የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ነው። 

እንቁ ሃሳብ እንጅ እንቁ ብሄር የለም  

በሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ውስጥ የሚከሰቱትን ደካማ ጎኖች ማስተካከለል እንዳለ ሆኖ፤ የትላንት ታሪኩን ጠንካራ ጎን በሚገባ ለማስተጋባት፤ ለተከታታይ ትውልድ ለማስተላለፍ፤ ለማክበርና ለመጠቀም የማይችል ህብረተሰብና አገር የወደፊቱንም ተስፋና ብሩህ አቅጣጫ ለመቀየስ እንደማይቻል የማሰብ ግዴታ አለብን። ይህም በአንድ ብሄር የሚደረግ ጥረት አይደለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ክብር የሚሰጣቸው የሰው ፍጥረት መሆናቸውን የመቀበል ግዴታም የሁላችንም ነው። 

አፄ ምንሊክን የምናደንቃቸውና የምናከብራቸው የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጀግና መሪ ስለሆኑ ነው። የሚያኮራ ታሪክ አለን እያልን የዐብይን ብልጽግና መንግሥት የምንተቸው ለምን ወራዳ ስራ ትሰራላችሁ በሚል ነው። የሰራችሁት ጥቁር ቀለም ነውና ያስጠይቃችኋል ማለቴ ነው። የዐብይ ብልፅግና ካቢኔ ለምን ከሌሎች አገሮች ታሪክ አይማርም?  

ለእውነት ተገዢ እንሁን!  

አሜሪካኖች ጆርጅ ዋሺንግተንን፤ ቱርኮች ከማል አታተርክን፤ ቻይኒሶች ጀኔራል ዩ ፌን፤ ራሺያኖች ታላቁ ጴጥሮስን (Peter  the Great) ወዘተ ያደንቃሉ፤ ያከብራሉ። መንግሥታታቸውን ይቀያይራሉ። መብታቸው ነው። ታሪካቸውን ግን መንግሥታቸውን በቀያየሩ ቁጥር ታሪካቸውን አብረው አይቀይሩም፤ አይክዱም፤ አያዋርዱም። ግፍና በደል አይፈጽሙም።

የጆርጅ ዋሽንግቶን ቅድመ አያቶች በቅኝ ገዢነታቸው የመጀመሪያውን ደረጃ የያዙ እንግሊዞች ስለሆኑ ጥቁር አሜሪካኖች ውይንም የአሜሪካ ህንዶች (indigenous millions who perished during the formation of the United States)  ዋሽንግተንን አያከብሯቸውም ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ኖሮ አሜሪካ ታላቅ አገር አትሆንም ነበር። 

በአድዋ በዓል አከበባር ላይ ባለፉት አምስት ዓመታት–በተለይ ባለፉት ሁለት– የተከሰተውን ጠብ ጫሪ፤ አማራ ጠል ንትርክ ሳንሰላስል የታዘብኩት የብሄር ፖለቲካ መጋቢ የሆነ አንድ የማይካድ የጋራ ዓላማ ሂደት አለ። ህወሃት አማራ ጠል በሆነው መመሪያው መሰረት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በከፋ ደረጃ አንድ ሚሊየን ንጹህ ዜጎች እንዲሞቱ አደረገ። የኢትዮጵያ መንግሥት ባደረገው ግምገማ መሰረት በአፋር፤ በአማራና በትግራይ ክልሎች ብቻ የወደመውን የመዋእለ ንዋይ ፈሰስ ለመተካት ሃያ ሁለት ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል። የውጭ እዳዋ ከሃያ ሰባት ቢሊየን ዶላር በላይ የሆነችው ኢትዮጵያ ይህንን የካፒታል ክፍተት እንዴት እንደምታሟላው አላውቅም። ጦርነቱ አላስፈላጊና ዋጋ ያስከፈለ መሆኑን ግን በሚገባ አውቃለሁ። ከእብድነት በላይ እብድነት ነው። ተጠያቄነትን አስፈላጊ የሚያደርገው መረጃው ነው።  

ሃላፊነትና ተጠያቂነት የሌለባት ኢትዮጵያ  

On February 28, 2023, ዋሽንግቶን ፖስት የትግራይን ሕዝብ እልቂት በሚመለከት “Hundreds massacred in Ethiopia as  peace deal being reached” የዓለምን ሕዝብ ህሊና የሚቀሰቅስ ርእስ ለእልቂቱ ተጠያቂ የኤርትራ መንግሥት መሆኑን ያበስራል። 

“The agreement between the Ethiopian government and Tigrayan rebels brought about a  cease fire in a two-year war that had made northern Ethiopia one of the deadliest places in  the world. But the deal did not address the status of Eritrean troops. Neither the Ethiopian  nor Eritrean government has made any public statement on how Eritrean soldiers who  perpetrated mass killings like the most recent one near Adwa could be brought to justice. Joint investigations by the Ethiopian Human Rights Commission, whose head is appointed  by parliament, and the Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights  have documented crimes against humanity and war crimes carried out by all sides up  until June 2021. The head of the EHRC, Daniel Bekele, said they had identified many other  incidents requiring investigation and they would be dealt with under a transitional justice  mechanism. 

The U.N. International Commission of Human Rights Experts, a separate body, also  documented war crimes by all sides, and said the government and its allies may have  committed crimes against humanity. In January, the Ethiopian government asked the  United States to support its bid to terminate the commission, calling its work “highly  politicized.” 

ትግሬ ቢሆን አማራ፤ አኟክ ቢሆን አፋር ወዘተ እልቂት በሕግ ያስጠይቃል። ዋሽንግተን ፖስት ቢፈልግና ቢያስብበት ኖሮ  Lemkin Institute for Genocide Prevention February 3, 2023 ያወጣውን “Statement in Support of an  International Investigation of Abiy Ahmed’s Crimes in Ethiopia” ሊጠቅስ ይችል ነበር። ይህንን አላደረገም ብለን  እኛ ጉዳዩን ቸል እንዳንለው አሳስባለሁ።  

በተጨማሪ ዋሽንግቶን ፖስት ሆነ ብሎ ይሁን በሌላ ምክንያት ትኩረት ያልሰጣቸው ጉዳዮች አሉ። ከነዚህ መካከል፤  

• በኦሮምያ ክልል በወለጋ፤ በሰሜን ሸዋ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚካሄደውን የአማራ እልቂት፤ • ለጦርነቱ ምክንያት የሆነውና አሁንም ሌላ ጦርነት ሊቀሰቅስ የሚችለው የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምትና ራያ  ጉዳይና በማይካድራ የተፈጸመው የሚዘገንን የአማራ እልቂት፤ 

• የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የተደረገው ሴራ፤ የታሰሩ አባቶችና ምእመናን፤ የተገደሉ  የእምነት አባላት፤

• የዐብይ ብልፅግና መንግሥት በበላይነት የሚያሽከረክረው የአዲስ አበባ አስተዳደር አማራው ተለይቶ ወደ አገሪቱ  መዲና ወደ አዲስ አበባ ልትገባ አትችልም የሚለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ሊጠቀሱ ይገባ ነበር።  

ይህ ክፍተት መኖሩ እንዳለ ሆኖ ለሁሉም ዜጎች እልቂት የዐብይ ብልፅግናና የኦሮምያ መንግሥት ባለሥልጣናት፤ የህወሃትና የኦነግ/ኦህዴድ አመራሮች በሃላፊነት መጠየቅ አለባቸው።  

ኢትዮጵያ ወደ የት እየተጓዘች ነው? የሚለው ጥያቄ ተመልሷል ለማለት እችላለሁ። የህወሃት ከፍተኛ መሪዎችና ጠቅላይ  ሚንስትር ዐብይ አህመድ በተከታታይ ያካሄዱት የሁለትዮሽ (Bilateral agreement) ስምምነት ለመሸወዳችን ዋቢ ነው።  ኦባንግ ሜቶ “ውሸት ሰለችኝ” ያለውን ሃቅ እጋራለሁ። በኢትዮጵያ ስም ብዙ ውሸት ይነገራል። ከእርቅና ከሰላም ጀርባ  ያለውን ድብቅ ሴራ ማጤን ወሳኝ ነው። የሴራው ይዘት ፍትህ ሳይሆን ፍጹም የሆነ የኦነጋዊያን/ኦህዴዳዊያን የበላይነት  ነው። ዐብይ ከደሙ ንጹህ ናቸው የሚለውን አልቀበልም። አበው “ማነን ይዞ ጉዞ” የሚሉትን ብሂል እናጢን።  

እኔ የማቀርበውን ትችትና ምክረ ሃሳብ ወደ ጎን ትታችሁ ጋዜጠኛ ሊዖ ኦኬሪ በመረጃ ተደግፎ የጻፈውን ደጋግማችሁ  ብታነቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሸውደውታል። ዋሽተዋል ማለቴ ነው። “ኢትዮጵያ!  ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!” ማለት በራሱ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት ስኬታማ ሊያደረገው አይችልም። የኢትዮጵያዊነት  መሰረቱና መስፈርቱ የዜጎች ደህንነት፤ እኩልነትና አንድነት፤ ፍትህ፤ የሕግ የበላይነት፤ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ ስርዓት ወዘተ  ነው።  

ሌዖ ኦኬሪ እንዳስቀመጠው፤ በህወሃት አመራርና በኦሮሞ ኦነጋዊያን የበላይነት በሚመራው የብልፅግና መንግሥት ባለሥልጣናት መካከል የተዋቀረው የበላይነት መጋመድና ስልት ኢላማው አጀንዳዎችን በስልት በመቀያየር የአማራውን ሕዝብ፤ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራርን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ማንበርከክ ነው። “The love making between the  two (TPLF and Abiy) involves the foreplay of banishing from their ethnic heaven the “devil” they fear  most, the one who does not understand that there is no other love but ethnic love: the Amhara. The  Abiy-TPLF love makings in ethnic heaven, he said, are punctuated by the ecstatic cry, “neftenga,  neftegna, neftegna” when they reach their climax. “ 

የህወሃት የበላይ አመራርንና ጠቅላይ ሚንስትሩን ምን ጉዳይ ሊያስማማቸው ቻለ? የሚለውን ጋዜጠኛው ከኔ በበለጠ አንደበት አስቀምጦታል። አንድ ሚሊየን ህዝብ ተጨፍጭፎ፤ አማራው በማይካድራ፤ በደራ፤ በስቴ፤ በመተከል፤ በወለጋና በሌሎች አካባቢዎች በየለቱ እየተጨፈጨፈ፤ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት አትችልም እየተባለ ወዘተ ወዘተ ለዚህ ሁሉ ጭካኔና የሰብአዊ መብት ቀውስ ማን በሃላፊነት ይጠየቃል? ብየ ራሴን ስጠይቅ፤ መልሱ ጋብቻው እኮ የተፈፀመው ሁለቱንም የበላይ አካላት በሚጠቅም ስልት በምስጢር ተስማምቶ ራስን በወንጀለኛነት ከሚያስጠይቅ የዓለም መንግሥታት ክስ ለመታደግ ነው እላለሁ። ጊዜ ይወስዳል እንጅ ይኼ ሸፍጠኛነትና ጮሌነት አያዋጣም። 

በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ህወሃትን ለማጋለጥና የምእራብ አገሮች አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ከፍተኛ ትግል አድርገናል። የገንዘብ እርዳታም አድርገናል። ይህንን ያደረግነው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንጅ ለዐብይ አህመድ አይደለም። አንሞኝ፤ ይህም አስተዋጾ ተረስቷል። ያ ጦርነት ለምን ተካሄደ? ማን አሸንፎ ወጣ? የሚለውን ታሪክ ይመራመረው። ሌዖ ኦኬሪ እንዲህ ሲል ያስቀመጠውን ግን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊያስብበት ይገባል። 

“Abiy is trying hard to create a “free love” relation between Tigray and Oromia, a free love that gives  intense pleasure only when it mobilizes hatred to crush the Amhara. What for? I asked. You fool, he  said. To prevent the Amhara from continuing to be the symbol, the thinkers, and the motive force of  Ethiopian peace and unity. “ 

በአማራው ላይ የሚካሄደው የተቀነባበረ ከእልቂትና ውድመት ጋር የተያያዘ ሴራና መዋቅራዊ ለውጥ ይህንን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት የቆመ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ለመገርሰስ ነው። ጋዜጠኛው እንዳስቀመጠው፤ የማናውቀው፤ ግን ከቃላትና ዲስኩር ውጭ ሆኖ ለገመገመው ቀስ በቀስ ይፋ የሆነው የዐብይ እውነተኛ ገጽታ እንደሚከተለው ነው። 

አብይ የሚናገረው ቃላት እንደ ቅጠል ነው። መስፈርት መሆን ያለበበት የሚሰራው ነው (“Acta non verba.” Words are  leaves, and deeds are fruits. Look at what he does and not at what he says. Not only is he treating the  TPLF as a victor and Ethiopia as defeated, said he, Abiy has also made his own the TPLF hatred of the 

Amhara. He lets the Amhara be massacred systematically in Oromia. He is tacitly cooperating with  ethnicist forces to make Oromia, as the Germans would say, “Amharafrei.” “ 

በሌላ አነጋገር፤ ዐብይ አሕመድ የአማራውን ጭፍጨፋ የማያወግዝበት፤ የአዲስ አበባን እገባና የኦርቶዶክስን ክፍፍል የማይተችበት ዋና ምክንያት የሴራው አካል በመሆኑ ነው። “ In the case of Ethiopia, “Amharafrei” means cleansing  the ethnic kilils of Amharas by all means necessary. Look, he said, not only Abiy has tacitly consented to  make Oromia and other kilils “Amharafrei” by killing and displacing Amharas, he is also quietly  supporting the arch-ethnicist Shimelis Abdissa and Adanech Abeibei’s scheme to make Addis Ababa  “Amharafrei” by preventing Amharas to travel to Addis Ababa. Likewise, he is preparing the ground to  deliver Wolqait and Raya to the TPLF. Ask yourself, my friend continued, why is Abiy not raising a  finger to liberate the hundreds of Amharas captured during the war and are still kept in horrendous  conditions in TPLF prisons, despite the Pretoria Agreement? Why does Abiy still allow the continued  occupation of Aber Gele and adjacent Amhara areas by TPLF forces? Why does Abiy try to disarm the  Amhara Special Forces despite the continued presence of TPLF forces in eastern Amhara, while allowing  the TPLF to keep almost intact the Tigray Defense Forces? Because, for Abiy and the TPLF, every  opportunity to create an “Amharafrei” Ethiopia is not to be missed.” 

እኛ ኢትዮጵያዊያን ለመናገር ያልደፈርነውን፤ አሁንም ቢሆን ብዙዎቻችን ችላ ያላልነውን ጋዜጠኛው በትክክክል አቅርቦልናል። ዐብይ አህመድ ሸውዶናል ማለት በቂ አይደለም። አደጋውን በሚገባ ተገንዝቦ የኦሮሞ ብልፅግና በበላይ ሆኖ የሚመራው መንግሥት በሁሉም መስፈርቶች ለኢትዮጵያ፤ ለአፍሪካ ቀንድና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ኦሮሞውን ጨምሮ የማያዋጣ መሆኑን የምናስተጋባበት ወቅት ደርሷል። 

ምክረ ሃሳቦችን ልጠቁም 

1. የአማራው ክልል ባለሥልጣናት፤ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ አባላት፤ የአማራ ስብስቦችና ተቆርቋሪ ግለሰቦች በሙሉ ከአሁን በኋላ በኦሮሞ ብልጽግና የበላይነት በሚመራው በዐብይ መንግሥት ላይ ያላቸውን እምነት ወደ ጎን ትተው የራሳቸውንን አቅም መገንባት፤ ማጠናከርና እየተናበቡ መስራት ይገባቸዋል። “ባንተባበር ይበሉን ነበር” የሚለው የወጣቱ አማራ ቀስቃሽ መፈክር ወደ አቅም ግንባታ እንዲሸጋገር ሁላችንም ድርሻችንን እንድንወጣ አደራ እላለሁ። ውጭ የምንኖረው ከማውራትና ሌላውን ከመተቸት ወጣ ብለን በአቅም ግንባታው ስራ ላይ እንረባረብ እላለሁ። 

2. የአማራው መንግሥት ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ዘመነ ካሴን፤ ሌሎችን በብዙ ሽይ የሚቆጠሩ የፋኖ፤ የልዩ ኃይል አባላት ጨምሮ በአስቸኳይ እንዲፈታ አሳስባለሁ። 

ከላይ እንዳሳየሁት በህወሃት የበላይ መሪዎችና በዐብይ መካከል የተካሄደውን ስምምነትና ይፋ ያልሆነውን ጸረ-አማራ “ቃል ኪዳን” ስገመግም (ለምሳሌ ያልተፈታው የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምትና ራያ ጉዳይ) የአማራው ክልል ራሱን ከአስከፊ የወያኔ ጥቃት ለመከላከል የሚችለው ፋኖውን፤ ልዩ ኃይሉን ትጥቅ በማስፈታት ሳይሆን ተጨማሪ ኃይል በማሰልጠን ነው እላለሁ።  

3. የኢትዮጵያን ኢህአዴግ/ብልጽግና የፈጠራቸውን ስርዓታዊና መዋቅራዊ ቀውሶች ለጊዜውም ቢሆን ለመፍታት የሚቻለው የአማራና የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች በሚያደርጉት የሁለትዮሽ ውይይት ብቻ ሊሆን አይችልም። የአማራን ብልፅግና አመራር የምመክረው ይህ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የሚመለከት አስቸኳይ ጉዳይ ስለሆነ በውይይቱና በመፍትሄው ድርድሩ ላይ ሁሉም የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እንዲሳተፉ ግፊት እንዲያደርግ ምክሬን እለግሳለሁ። 

4. የዐብይ ብልፅግና አመራሮች በአድዋ በዓል ዙሪያ በቤተክርስትያን ውስጥ ሆነው በዓሉን በሰላም ሲያከብሩ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ለተፈጸመው እልቂት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ዓለም አቀፍ ጥሪ የማድረግ ግዴታ አለብን። 

5. የብልጽግና፤ የኦህዴድ/ኦነግና የአዲስ አበባ ከተማ ባለሥልጣናት የአማራውን ብሄር እየለዩ ወደ አዲስ አበባ ልትገባ አትችልም የሚሉት የሚዘገንን የሰብአዊ መብት ጥሰት ሕገ ወጥ ስለሆነ መላው የዓለም ሕዝብ እንዲያውቀው አናድርግ፤ ክስ እንዲመሰረት ድጋፍ እንለግስ፤ ሰላማዊ ሰልፎች እንጥራ፤ የአፍሪካ አንድነንት ድርጅትና ኢጋድ ጫና እንዲያደርጉ ዘመቻ እንጀምር እላለሁ።

6. ህወሃት በማኒፌስቶው ላይ ያወጣውን ፀረ-አማራ መርህና ኦህዴድ/ኦነግ የአማራውን አስደናቂ የሃገረ መንግሥት ምስረታ ዘርፈ ብዙ ሚና “አፈራርሰን አዲሲቱን ኢትዮጵያን እንመሰርታለን” የሚሉት በሥልጣን የበላይነት የሰከሩ ጽንፈኞች የሚጠቀሙት ሕገ መንግሥት ኢትዮጵያን ያሸጋገራት ከህወሃት የበላይነት ወደ ኦሮሞ ብልፅግና የበላይነት መሆኑ በማያሻማ ደረጃ የመቀበል ግዴታችን ድምጽ በማሰማት እንድንወጣ አሳስባለሁ። 

ይህ የብሄር ልዩነትን መሰረት ያደረገ፤ ግጭቶችን የሚፈለፍል ሕገ መንግሥትና የክልል አስተዳደር በአስቸኳይ መቀየር አለበት። በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የምንኖር አገር ወዳዶች ይህ ሕገ መንግሥት እንዲቀየር የተቀነባበረ የሕዝብ ግንኙነትና የሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ስራ መስራት አለብን። ባለሞያዎችን ሰብስበን አማራጮችን የማቅረብ ግዴታ አለብን። 

7. በዜግነት መብት ላይ ብቻ የሚቀነባበረው አዲስ ሕገ መንግሥት ልክ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንደ ደነገጉት በኃይማኖትና በብሄር የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት ከሕግ ውጭና የዜጎች ግዴታ መሆኑን መደንገግ አለበት። 

በመጨረሻ፤ የኢትዮጵያ መሰረታዊና መዋቅራዊ ተግዳሮቶች እየትባባሱ መሄዳቸውን አብዛኛው የኢትዮጵያና የዓለም ሕዝብ  ይጋራል። ምን እናድርግ በሚለው ላይ ግን ብዙ ስራ ፊታችን ላይ ተደቅኗል። ሁለት ምክረ ሃሳቦችን ልጠቁምና አስቡበት፤ 

• ለሁሉም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ የህብረ-ብሄር፤ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ተወካዮች፤ አገር ወዳዶች፤ ባለሞያዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች በአንድ ላይ ሰብሶብ ምክክር እንዲያደርጉና በፍኖት ካርታ እንዲስማሙ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ፤ አገር አቀፍ ጥሪ ማድረግ እና፤ 

• በኢትዮጵያዊያና ላይ የሚካሄደውን የሚዘገንን አፈና፤ ግድያ፤ ብሄር ተኮር እልቂትና ማፈናቀል በሚመለከት ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎች ማካሄድ፤ አቤቱታዎችን በጽሁፍና በመረጃ እየደገፉ 

ለሚመለከታቸው የተባበሩት መንግሥታት፤ ለአሜሪክና ለአውሮፓ ባለሥልጣናት፤ ለአፍሪካ አንድነት መስሪያ ቤት መሪዎችና ለሌሎች ለሚመለከታቸው ሁሉ ማድረስ፤ በቁርጠኛነት የሚከታተል አካል መመስረት የሚል ሃሳብ አቀርባለሁ።  

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

 

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here