spot_img
Friday, July 19, 2024
Homeነፃ አስተያየትለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን መልእክት (ከአልማዝ አሸናፊ)

ለዲያስፓራ ኢትዮጵያውያን መልእክት (ከአልማዝ አሸናፊ)

Ethiopian Diaspora
ምንጭ ፡ ካፒታል ጋዜጣከአልማዝ አሸናፊ
Wyoming, USA

የአገራችን ሰው ሲተርት “ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ” እንደሚለው እኛ በዲያስፖራ የምንኖር : ኢትዮጵያዊነት ጭምብል አጥልቀን አረንጏዴ ብጫ ቀይ ባንዲራን መለያችን አድርገናል የምንል ኢትዮጵያውያን ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአፋችን ሙቀጫ እንደውሃ እንወቅጣለን እንጅ እንደተቀሩት ጠንካራ መጤ ማህበረሰቦች ተባብረን ባለንበት አካባቢ ጠንካራ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች ማቋቋም ያልቻልን ብኩኖች ነን:: ግን የሌሎችን የማይስማሙንና የማይጥሙንን ድርጊቶች ለመወንጀልና ሌላዎችን ለመተቸትና ለማኮሰስ እጅግ ጎበዞች ነን:: መጀመሪያ የሌላውን ጉድፍ ከመጦቆም የራሳችንን ጉድፎችን : አከፋፋይ ሁኔታዎችን : አስተሳሰባችንን : አመለካከታችንና ባህሪያችንን በአምሮአችን መስተዋት ለማየት እንሞክር:: በተለይ በ80ዎቹና በ90ዎቹ ውስጥ በስደትም ሆነ በሌላ መንገዶች ወደ ዲያስፖራ መጥተን የእድሜ ባለፀጋ የሆንን በነዚያ ባለፉት አስርተ አመታት ቀጣዩ ትውልድ የሚወርሰውን የሚኮራበትንና የሚጠቀምበትን ጠንካራ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች በየአካባቢያችን አቋቁመናል ወይ? ለምንድነው ሌሎች መጤ ማህበረሰቦች ማንነታቸውን በማስታወቅ የምንኖርባቸው ህብረተሰቦች አካሎች መሆናቸውን ተደራጅተው ሲያስመሰክሩ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች እድገታቸው ተቀጭቶ ዳዴ ማለት ያልቻሉት? በግለሰብ ደረጃ ኢትዮጵያዊነትን በየቤታችን በየማድቤታችን ልናነሳ ልናጎላ እንችላለን:: ሆኖም ይህንን በየቤታችን የምንዘክርለትን ኢትዮጵያዊነት በአንድነት ጠንካራ ማህበረሰቦች መስርተን እስካላዳበርነው ድረስ ውይይታችን በቻት ግሩፖች ውስጥና በድረ ገፆች የግል ብሶታችን ማስተንፈሻ እንጂ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ክብርና ሞገስ የሚያመጣው ጠቀሜታ የለም:: በማህበረሰብ የመደራጀት ጥቅሙን ለማየት ሊቆጨን የሚገባ ከእኛው ህብረተሰብ ተገንጥለው የወጡትን ሁለት ማህበረሰቦች ለምሳሌ ልጦቅምላችሁ:-

1. የኤርትራ ማህበረሰብ:- ምንም እንኳ ዛሬ በኢሳያስ አፈወርቂ አምባገነናዊ አስተዳደር በመሃላቸው ክፍፍል ቢኖርም በወያኔ ምረቃ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እስክትገነጠል ድረስ ኤርትራውያን ለአመኑበት ዓላማ በአንድነት ፅኑ ሆነው በመቆም ኤርትራን ከእናት አገር ኢትዮጵያ እንድትገነጠል አድርገዋል:: ከመገንጠላቸው በፊት የተቀረነው ተበታትነን ያለነው ኢትዮጵያዊያን ኤርትራውያንን አገር ገንጣዮች እያልን መርገም እንጂ እንደ ኢትዮጵያዊያን ተደራጅተን ያንን መቃወም የሞከርንበትና የቻልንበት ጊዜ አልነበረም:: በእርግጥ የዛሬ 32 ዓመት ሶሻል ሚዲያው ስላልነበረ ውይይቱ በየቢራ ቤቶች በኮፊ ሾፖችና በየግል ቤታችን ሶስት አራት እየሆንን የኤርትራውያንን ንቅናቄ ማንቋሸሽ ነበር:: እነሱ ግን እስኪገነጠሉ ድረስ የነበራቸውን አንድነት ጠብቀው ባሉባቸው የዲያስፖራ አካባቢዎች ጠንካራ ማህበሰሰብ መስርተው የኤርትራ ስም ጎልቶ የሚታዩባቸው ሕንፃዎች ገዝተው የኤርትራ ማህበረሰብ ማዕከሎች ያላቸው ናቸው:: መገንጠላቸው የማይደገፍ ቢሆንም ከእነሱ ምንቀስመው ትምህርት አንድነትን ህብረትንና የዓላማ ፅናትን የሚያንፀባርቅ ነው::
2. የኦሮሞ ማህበረሰብ:- ይህ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ህብረሰብ አካል ነው:: ሆኖም እንደ ኤርትራውያን አንዳንድ የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች እንደማንም ሰው በተማሩት ትምህርት ወይም ሙያ ሰርተው ከመታዳደር ይልቅ ሕዝብን በማበጣበጥና አገርን ሰላም በማሳጣት የሚያገኙትን የፖለቲካ ጥቅም አይተው የኢትዮጵያ ታሪክን እያዛቡ ኦሮሞ ተበድሏል የሚለውን የውሸት አፈትረካ ደጋግመው በመናገር እውነት በማስመሰል በጠባብ ጎሰኝነት ላይ የተመሰረተ የኦሮሞ ማህብረሰብ ድርጅት በኤርትራውያን ፎርም በዲያስፖራው ውስጥ ተቋቁሞ እያየን ነው::

በእነዚህ በሁለቱ የመገንጠልና የመከፋፈል ድርግቶች ባንስማማና ባንደግፍም እንደ ግለሰቦችና እንደ ኢትዮጵያዊያን የምናገኘው አንድ ጥሩ ትምህርት አለ:: ይህንንም መጀመሪያ በተረት ሳቀርበው “ድር ቢያብር: አንበሳ ያስር::” ይህ የሚያሳየን የሰው ልጆች በጋራ ሆነው ለማግኘትና ለማሸነፍ ለሚፈልጉት ነገር ዋና መሰረቱና ምሰሶ የሚሆኑት : ለዓላማቸው ፅኑ ሆነው መቆምና መተባበር ናቸው:: ኢትዮጵያ አንድ እንድትሆን ኢትዮጵያውያን በያለንበት አንድነትን ማዳበር : ማንነታችንን በህብረት ማጎልበስ : ድምፃችንን በአንድነት ማሰማት ይኖርብናል:: ይህንን ማድረግ የምንችለው ጠንካራ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ድርጅቶች በያለንበት አካባቢዎች ስናቋቁም ነው::

አንድ አንባቢዎችን ማስታወስ የምፈልገው ከኢትዮጵያ ምድር የወጣ ማንኛውም ሰው ራሱን መጠየቅ ያለበትን ጥያቄ ነው:: ይህም በምንኖርበት የዲያስፖራ ግዛቶች ተፈቅዶልን : እንደግዛቶቹ ተወላጆች ሙሉ መብት ተሰጥቶን የምኖር መጤዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጎሳ ፖለቲካን በመዋጋት ሰላም ከማስፈን ይልቅ ሕዝብን ለማከፋፈል እሳቱ ላይ የጠባብ ጎሰኝነትና ፅንፈኝነትን ቤንዚን ስናርከፈክፍ “እኔ ሰባዊነት አለኝ?” ወይ የሚለውን ጥያቄ ነው:: ማንም ጎሳውን አገሩን ሃይማኖቱን መርጦ የተወለደ ሳይሆን ሰው ሆኖ የተወለደ ነው:: ዛሬ በዲያስፖራ በምቾት ላይ ተቀምጠን ስለጎሳ የምናጠነጥን የኦሮሞ ትግሬ አማራ ሱማሌ ጉራጌ ወዘተ ኢትዮጵያውያን ማወቅ ያለብን ልጆቻችን እኛ እያለንም ሆነ ካለፍን በሗላ ዛሬ የምንባላበትን ጎሰኝነትን ዞር ብለው አያዩትም: አያሸቱትም:: ሰውነት ተፈጥሮ ሲሆን ጎሰኝነት ብሔራዊነትና አገራዊነት ከቤተሰቦቻችን የምንወርሰው የምናዳብረው የምንጥለውና የምንለውጠው ባለንበትና በምኖርበት አካባቢ የሚገለፅ የማንነት አመለካከትና የልዩነት ማስረጃ እንጂ የተፈጥሮን ማንነት ለዘለዓለም የሚገልፅና በዓለም ካሉት የሰው ልጆች ጋር ያለንን ተመሳሳይነት የሚያሳይ አይደለም:: አንድ አይሮፕላን ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስክሶ ወድቆ ቢቃጠልና ተሳፋሪዎቹ ሁሉ ቢሞቱ : የመጀመሪያ ዜናው አውሮፕላን ወድቆ ይህንን ያህል ሰዎች ሞቱ እንጂ ; ይህንን ያህል ኦሮሞ : ትግሬ : አማራ አይልም:: ስንፈጠር ሰው ነን : ስንሞትም ሰው ነን:: ጎሳ ተፈጥሮ ሳይሆን አመለካከት ነው:: ለሰው ልጆች ደህንነትና ዘለቄታ የማይጠቅመውን አመለካከት አስወግዶ ሰባዊነት የተሞላበትን የአእምሮ እይታ ማዳበር ትልቅ ዕውቀት ነው:: በትምህርት የሚገኝ ዕውቀት የሰውን ልጆች የሚያደርጋቸው ባለሙያተኞች እንጂ አዋቂዎች አያደርጋቸውም:: ምክንያቱም ትምህርታቸውና ሰብዓዊነት በነዚህ የተማሩ መሃይሞች የእስተሳሰብ ማዕክል ውስጥ አብረው መኖር ስለተሳናቸው ነው:: አዋቂ ሰው ለመሆን ዘመናዊ ትምህርት አያስፈልግም:: አዋቂ ሰባዊነት የተሞላበት ስብእና ያለው ሰው ነው:: አዋቂ በስሜት ሳይሆን በሥነአመንኪዮ ይመራል:: አዋቂ ወገናዊነትን ሳይሆን ሰብዓዊነትንና ጋርዮሽነትን ያራምዳል:: ዓለማችንም ሆነች ኢትዮጵያ አገራችን የተበደሉትና የሰው ልጆች ማሰቃያ የሆኑት አዋቂዎች ጠፍተው ባለሙያተኞች አዋቂ ሆነው ስለሚቀርቡ ነው::

የተማሩ በዝተው የአዋቂዎች መጥፋት ወይም እጥረት ኢትዮጵያን የሰዎች አገር ከማድረግ ይልቅ ህግና ስርዓት የሌላት የጎሳዎችና የብሔሮች በረት በመሆኗ የአገር ልዑላዊነት አንድነትና የጋርዮሽነት ትርጉም በማይረዱ ሙያተኛ እረኞች እየተመራች የጥፋት ጎዳና ላይ ትገኛለች:: አዎን በእርግጥም በኢትዮጵያ ጎሳን መሰረት ባደረገ የጥላቻና የክፍፍል ፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ የተለመደው አንድን ጎሳ በተለይ የአማራን ጎሳ የችግሮቹ መንስዔ በማድረግ ኃጢአቱን እያበዙ ማጥቃት የተጀመረው ኤርትራን በመገንጠል ኢትዮጵያን ለመከፋፈል በተደረገው ሂደት ነው:: ይህም በተገንጣይ ኤርትራውያን የተጀመረው በአማራ ላይ የተወረወረው የጥላቻ ዘመቻ በወያኔ ጎሰኞችና ፅንፈኞች ተሻሽሎና ተጣርቶ ለባለተረኞቹ የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች አማራ ኢትዮጵያውያንን ማጥቂያ መሳሪያ ሆኖ ቀርቧል:: በነዚህ አገር አፍራሽና የግል ጥቅማቸውን አስጠባቂ በሆኑት የወያኔና የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ጁንታዎች አማራ ለምን እንደሚጠላ ሳጠነጥን የመጣልኝ መልስ አንድና አንድ ነው:: ይኸም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ጨቁኖ ለረጅም ጊዜ ለመግዛትና ለመበዝበዝ ኢትዮጵያዊነትን ሽፋን በማድረግ በአሁኑ ሰዓት ባለተረኛው የኦሮሞ ፅንፈኛ ቡድን ጁንታ የበላይ ለመሆን የአማራን ጎሳ ሞራሉንና ሃይሉን ማኮላሸት አስፈላጊ ነው ብሎ ጋሻ ጃግሬውን አንስቷል:: አማራ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ምሰሶ መሆኑ አይካድም:: በኢትዮጵያዊነቱም እንደማይደራደር ግልፅ ነው:: በኢትዮጵያዊነታቸው ፀንተውና ኮርተው ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የሚፈልጉትን የተቀሩትን ሱማሌ ኢትዮጵያውያን ደቡብ ኢትዮጵያውያን ጋምቤላ ቤንሻንጉልና ጉሙዝ ትግራይ ኦሮሞ ኢትዮጵያውያንን ከገንጣዮችና ከከፋፋዮች መዳፍ ለማውጣት የአማራ ኢትዮጵያውያን መኖርና መጠናከር ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ የውስጥ ጠላቶች የሆኑ አረመኔ ወያኔና አረመኔው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ጁንታዎች ይገነዘባሉ:: እነዚህ የውድመት ሃይሎች የአማራ ኢትዮጵያውያንን አልበገሬነትና ወኔ አጥብቀው ስለሚያውቁና የያዙትን ዓላማ ለማሳካት የአማራ ኢትዮጵያውያንን ጉልበትና የመቋቋም ችሎታ መፈተሽና መሞከር አለባቸው:: የጠላቴ ጠላት ወዳጄ የሚለውን ምሳላዊ አነጋገር በመከተል አረመኔዎቹ የወያኔና የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ጁንታዎች አማራ ኢትዮጵያውያንን በጋራ ለማጥቃት ቂጥና ሙታንቲ ሆነው ቀርበዋል:: ማን ቂጥ ማን ሙታንቲ እንደሆነ ባይታወቅም የተግማማ ቂጥን የሚሽፍን ሙታንቲ ቆሽሾና ገምቶ እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው:: እነዚህ ሁለቱም የሸተቱ ጁንታዎች መግማታቸውን ራሳቸውን በራሳቸው ካልተረዱና ካላፀዱ እንዳለፉት ውዳቂ መንግስታት በኢትዮጵያ ንፁህ ሕዝብ መፅዳታቸው አይቀርም:: አማራ ኢትዮጵያውያንና ከላይ የዘረዘርኳቸው የአንድነት አጋሮቻቸው እያሉ ማንም ዶማ ራስ ኢትዮጵያን አያፈርስም::

ሆኖም በኢትዮጵያ ሕዝብና አረመኔነትን በተከናነበው በተረኛውና በወጋናዊ የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ጁንታ መንግስት መሃል በሚነሳው ውዝግብ ምክንያት የሚያሳዝነኝ አሳሳቢ ድርጊት ሊፈፀም ይችላል:: ይህም የሰው ልጆች እልቂት ነው:: ይህ አስከፊ ድርጊት ከተፈፀመ ጠቅላይ ሚንስቴሩ ዶ/ር አብይ አህመድ እንደጲላጦስ ከደሙ ንፁህ ነኝ ብለው እጃቸውን እንደማይታጠቡ ተስፋ አደርጋለሁ:: ልታጠብም ቢሉ ውሃና ውሃ እቅራቢ አይኖርም:: በደህንነት ቅጥሮቻቸው : በጎሰኛው በኦሮሞ ልዩ ሃይል :ሰዎች በተገደሉ ቁጥር ጆሮ እንደሌላቸው አልሰማሁም አልሰማም ማለት ልምዳቸው ስለሆነ ኃላፊነትን መቀበል ጠንካራ ባህሪያቸው አለመሆኑ ቢታወቅም : በጎሰኛው የኦሮሞ ክልል አስተዳደር ጎሳ እየተቆጠረ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ቤቶቻቸው በአዲስ አበባና በሸገር ባንቱስታን መሬት በሽዎች እየፈረሰ ዜጎች ቤተአልባ ሲሆኑ ሃዘኔታ የማይሰማቸውና ልባቸው በሰብዓውነት የማይደነግጥ አረመኔ መሪ ሆነው መገኘታቸው ተጠያቂ ያደርጋቸዋል::

ስለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ብዙ ነጥቦች አንስቶ መተቸት ይቻላል:: ያንን ለሌላ ፅሁፍ በመተው አንድ ነጥብ ብቻ ልጥቀስ:: እኝህ አፈጮማ አስመሳይ መሪ ደግመው ደጋግመው ሙስናን የሚጠየፉና የሚቃወሙ እንደሆኑ ይናገራሉ:: ግን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በሙስና ውጊያ ተግባረ ጎደሎ ሆነዋል:: ለዚህ ጉድለታችው ማረጋገጫ : ብልፅግና ፓርቲ ስልጣን ላይ ሲወጣ ሹማምንቶቻቸው ያላቸውን ንብረት በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር:: ያም ትእዛዝ እንዲፈፀም ሳይሆን በማስመሰል የኢትዮጵያን ሕዝብ ማታለያ ነው ብል አልሳሳትም:: 3 ወር ተለውጦ 3 አመት ሆኗል:: የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ትእዛዝ ሹማምንቶቻቸው ሰምተው አልሰማንም ብለዋል:: እንዲህ ነው ማስመሰል:: ሌላው በሙስና ላይ ተግባረ ጎደሎ የሚያደርጋቸው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አባላት በሆኑት የኦሮሞ ክልል አመራሮች ባለፉት አምስት ዓመታት የተፈፀመው የሀብት ዘረፋና ስርቆት የወያኔ አመራሮች በ27 አመታት ውስጥ ከዘረፉት ሀብት ጋር ሲመጣጠን የወያኔ ዘረፋ ለአገሪቱ ሃዘኔታ ያለው ይመስላል:: በተለይ የኦሮሞ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በወንድሞቹ በሚስቱ በሚስቱ ዘመዶችና በሚዜዎቹ ስም ያከማቸው የሲሚንቶ የብረታ ብረት ንግድ የመሬት የሕንፃ ሀብት ዓይን ያወጣ ዘረፋን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልሰሙም አያውቁም ማለት በፍፁም አይቻልም:: ሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማካሪ አዲሱ አረጋና የኦሮሞ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ በሙስናና በሀብት ዘረፋ ጭምልቅልቅ ማለታቸውን ዶ/ር አብይ አህመድ አላወቁም አይባልም:: በደንብ ያውቃሉ:: ታከለ ኩማም የዘረፈውን ሀብት ይዞ በአሜሪካን ቨርጂንያ ውስጥ በሆቴል ውስጥ ተንደላቆ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልሰሙም? እንዴት አይሰሙም? እሳቸው አይደሉም ባርከው ሂድና ተዝናና ያሉት? ድንገት የሳቸውንም ድርሻ እንዲጠብቅላቸው ይሆን? ይህ ነው የተግማማ መንግስታዊ አስተዳደር:: በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርምና እስከዚያ ድረስ በስልጣኑ ይግማሙበት::


ሌላው መታለፍ የሌለበትና መሰመር ያለበት የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የአመራር ዝንባሌ ነው:: ይህም ዝንባሌ ጠባብ ጎሰኝነትንና አምባገነን አመራርን (DICTATORSHIP) የሚያመላክት ነው:: እንዴት ቢባል : ፓርላማ ላይ ኦሮሞ አገር ሊያፈርስ ነው የሚል ዘፈን ይዘፈናል የሚል ትችት ተናገሩና እኛ ኦሮምች ኢትዮጵያን ስለምንፈልጋት አናፈርስም የሚል አስተያየት ከወረወሩ በሗላ በዚያው ትንፋሽ ለማፍረስ ብንፈልግስ ማን ይከላከለናል በማለት ግብዝነት የሞላበት ተንፃራሪ መልስ በመስጠት የጠባብ ጎሰኝነትና ማን ደፍሮን የሚል ስሜት አሳይተዋል:: ይህን ባህሪይ አልነበረም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሳቸው የጠበቀው::ይህ መደበኛ የአፍሪቃ አምባገነን መሪ ባህርይ ነው:: በዚህ አጋጣሚ ሳልጠቅስ ማለፍ የማልፈልገው: እንዴት የኦሮሞ የብልፅግና ፓርቲና ጠቅላይ ሚኒስቴሩ መሞገስና ስልጣን እንደጣማቸው ነው:: ይህንንም የጠቅላይ ሚኒስቴሩን አምስተኛ ዓመት የስልጣን ዘመን ምክንያት በማድረግ የድጋፍ ሰልፍ በኦሮሞ ክልል ውስጥ እንዲደረግ መጥራታቸው ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንቅሮ እየተፋቸው መሆኑን ያሳያል:: የዛሬ አምስት አመት የስልጣን መቀመጫ ላይ ሲቀመጡ እንደዛሬ እስኪመቻቸው ድረስ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያኖች እያሉ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አስመሳይ ቱሉቱላቸውን ሲነፉ የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች አቢይ አማራ እንጂ ኦሮሞ አይደለም በማለት ሲያብጠረጥሯቸው ከረሙ:: ዛሬ እነዚያ የአንድነት መርዘኛ ጎሰኞችና ፅንፈኞች አቢዬ ኬኛ ሲሉ መስማት ፖለቲከኛና ሴተኛ አዳሪ መመሳሰላቸውን ታዘብኩኝ:: በእርግጥ ማንኛውም የማንኛውም ጎሳ ብሔርና አገር ፖለቲከኛ ከሴተኛ አዳሪ አይለይም:: በዚህ አጋጣሚ እነዚህ የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች ለአንድ ጎሳ የበላይነት : ካልሆነላቸው ኢትዮጵያን ለመበተን ሲሯሯጡ : አብላጩ የኦሮሞ ተወላጆች አያቶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው ሕይወታቸውን ሰውተው አንድነቷንና ልዑላዊነቷን ጠብቀው ያወረሷቸውን የጥቁሮች ነፃነት ተምሳሌት የሆነችውን እናት አገራቸውን በአንድነት ከተቀሩት ኢትዮጵያውያን እህቶቻቸውና ወንድሞቻቸው ጋር በመተባበር እንድሚጠብቋት የታወቀ ነው::

ወደ ዋናው መልእክቴ ስመለስ : ከጎሳነት አገራዊነት : ከአገራዊነት አለማዊነትና ከአለማዊነት ሰውነት እንደሚበልጥ በመረዳት በትልቁና በሰፊው ሁላችንም ሰዎች ስለሆንን ሰውነትን እንምረጥ እናራምድ:: በትንሹና በጠባብ ካሰብነው አገራዊነት ማለትም ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከፍ እናድርግ:: ለዚህም በያለንበት አካባቢ : አገርና አህጉር በኢትዮጵያዊነታችን አንድነታችንና ህብረታችን ፀንተን ይዘን በመገኘት ኢትዮጵያዊ ማነታችንን እንጠብቅ እናስከብር:: አንድ ክሆንን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን የመከራና የችግር ቀንበር በጋራ ተሸክመን ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ተባብረን ማምጣት እንችላለን:: ክፍፍላችን ውድቀታችን : አንድነታችን ጥንካሬ ነው::

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here