spot_img
Sunday, May 28, 2023
Homeነፃ አስተያየትየጠቅላይ ሚኒስትሩ የእውቀት ሌብነት (plagiarism ) ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ያለው መልዕክት፣

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእውቀት ሌብነት (plagiarism ) ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ያለው መልዕክት፣

- Advertisement -
Screenshot from FBC Video

ከዶ/ር አገሬ አበበ

ሰዎች አማራ ስልሆኑ ብቻ እንደ አውሬ እየተጨፈጨፉ ነው። ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ተፈናቃይ በአማራ ክልል ውስጥ ይገኛል። የኑሮው ውድነት ጣራ ነክቶል። ዜጎች በሰላም ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አልቻሉም። አገራችን በብዙ በከፋ መከራ ላይ ናት። አሁን ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እዉቀት ሌብነት ለምን መጨነቅ አስፈለገ የምትሉ አንደምትኖሩ እገነዘባለሁ። ምንም እንኳ የህዝቡ መከራ በመቀጠሉ ቅድሚያ ትኩረት ቢያሻም፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደጋጋሚ የእውቀት ሌብነት (plagiarism) በቀላሉ ሊታለፍ አይገባም። ምክንያቱም ለአገርና ለትውልድ አደጋ ስለሆነ ነው።

የመቶ ሃያ ሚሊዮን ህዝብና የጥንታዊቷ አገራችን ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ያልሆኑትን ሆኖ ለመቅረብ፣ ያላወቁትን አዋቂ ሆነው ለመታየት፣ ራሳቸውን ከሁሉ በላይ፣ የሁሉም ነገር አዋቂ አድርገው ማየታቸው አደጋው በቀላሉ መታየት የለበትም። ከሸመደዱትና የራሳቸው አስመስለው ካቀረቡ ከሄነሪ ኪሲንጀር ንግግርከቀድሞው ፕሬዘደንት ኦባማ ንግግር ጀምሮ  ሚኒስትሮቻቸውን በሚይሰለጥኑባቸው አቅርቦቶች እና፣  ምንም እንኳ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰራ የወያኔ የውጭ ክንፍ ቢያወጣውም፣ በዶክትሬት መመረቂያቸው የምርምር ጽሁፍም ግልጽ የእውቀት ስርቆት /plagiarism/ ፈጽመዋል። ሚኒስትሮቻቸውን ባሰለጥኑበት አቅርቦት የራሳቸው አስመስለው ለስራው ባለቤት እውቅና ሳይሰጡ ያቀረቡት ስዕልና ሃሳብ ከሌላ ሰው ሥራ የተገለበጠና የተበረዘ ነው። ለዚህም ተገቢው ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። ጠ/ሚ አቢይ በኩራት እንደራሳቸው ስራ አድርገው ያቀርቡትና ሚንስትሮቻቸው በትጋት ኖት ሲይዙ፤

ሙሉውን በፒዲኤፍ ለመጫን እዚህ ይጫኑ

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena 
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena 
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,858FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here