spot_img
Wednesday, April 17, 2024
Homeነፃ አስተያየትኢትዮጽያን ና የአፍሪካን ቀንድ ለማዳን የአለማቀፍ ማህበረሰብ ጫና ወሳኝ ሚና 

ኢትዮጽያን ና የአፍሪካን ቀንድ ለማዳን የአለማቀፍ ማህበረሰብ ጫና ወሳኝ ሚና 

Oromummaa’s Inhumanity in Pictures 

(ዶ/ር ዮናስ ብሩ) 

በኢትዮጽያ ሁለት መንግስታት አሉ ። አንደኛ የአድናቆት ስስት በተጠናወተው ለራሱ ከፍተኛ ግምት የሚሰጥ ጠቅላይ ሚኒስትር የምትመራ ኢትዮጽያ አለች ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚመራው ህዝብ ደህንነት ግድየለሽ በመሆኑና የህዝቡን ስቃይ ለመገንዘብ ባለመቻሉ የሀገሪቱን ሀብት ድህነት ተኮር ከሆኑ ጠቃሚ መንግስታዊ የልማት ስራዎች ጭምር በማውጣት በጣት ለሚቆጠሩ እርባናቢስ ፕሮጀክቶች ማስፈፅሚያ እንዲውል አድርጓል።  

ለራሱ የተጋነነ ከፍተኛ ግምት የሚሰጥ ሰው ስብእና የሚገነባው ራሱ በስቀለው ማማ ላይ ወጥቶ በመሆኑ ተጨባጭ እውነቶችን እንደ ረብሻ በመቁጠር ከእውነት ተጣልቶ ይኖራል። ይህም የማስተካከያ እርምጃዎች ለመውስድ የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ እድሉን እንዳይጠቀምበት አድርጎታል። 

ሁለተኛው የኦሮሙማ መንግስት ነው ። ኦሮሙማ ፀረ ኢትዮጽያ ፤ ፀረ ክርስትናና ፀረ እስልምና የሆነ ራሱን የኦሮሞ ብሄራዊ ንቅናቄ ዋና ርእዮተ አለም አድርጎ የሚወስድ የኦሮሞ አሸባሪ አምልኮ ነው ። የንቅናቄው ዶግማ በቅስቀሳ ዘመቻው ፣ በንቅናቄውና ኢሰብአዊ በሆነ ጭካኔው ናዚዎች የተደራጁበትን ስርአት ይከተላል። ከቀን ወደ ቀን የጠቅላይ ሚኒስትሩን መንግስት በመገዝገዝ ላይ ይገኛል። መሪዎቹ ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታና ሺመልስ አብዲሳ ናቸው። እ.ኢ,አ ከ2007 ወዲህ የቲኒሲ ኖክስቬል ዩኒቨርሲቲ የመረጃ መረብ ድህረ ገፅ ለንቅናቄው የጥላቻ ንግግርና የዘር ፍጅት ቀስቃሽ ጽሁፎች ማከማቻ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ። 

ምንም እንኳ ሁለቱ መንግስታት መሳ ለመሳ እየሰሩ ቢሆንም የጋራ ፍላጎቶችና የማይታረቁ ቅራኔዎች አሏቸው ሁለቱም የፖለቲካ ስልጣን መሰረት የሚሆን የኦሮሞ ጎሳን ድጋፍ ለማስባሰብ ባላቸው ፍላጎት ይመሳሰላሉ። ልዩነታቸው የሚመነጨው ከዘላቂ አላማዎቻቸው ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ታላቅ ጉጉት የኢትዮጽያ ንጉስና የአፍሪካ ምርጥ መሆን ነው ። በአንፃሩ ኦሮሙማ በሀገር ውስጥ የተወሰነና ወደ ኋላ የሚያልም በከፊል አምልኮና በከፊል የፖለቲካ ዶግማ የሆነ ሀገሪቱን ወደ 16 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለመመለስ የሚመኝ ነው። 

ምንም እንኳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማን አህሎኝነት እየፎከሩ ቢሆኑም የስልጣን መሰረት የሆናቸው ህዝባዊ ድጋፍና ህጋዊ ተቀባይነታቸው በፍጥነት በመሸርሸር ላይ ይገኛል። የኦሮሙማን አራማጆት ትእዛዝ በመፈፀም ድጋፍ ለማግኘት አብያተክርስትያናትን ና መስጊዶችን እስከ ማፍረስ ደርሷል። ያም ሆኖ እንደ ተአማኒ አጋር እንደማይወስዱት ለመረዳት አያዳግትም። እሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ያበቃውን ለማ መገርሳን ፤ ከትህነግ ወረራ ያተረፈውን ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ከድቷል። እንዲሁም ጠመንጃውን ሊገድሉት ወይም ሊይዙት እየዛቱ ወደ አዲስ አበባ ሲገሰገሱ የነበሩትን የትህነግ ታጣቂዎችን ያቆሙለት የአማራ ህዝብና ፋኖ ላይ አዙሯል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለራሳቸው በሚሰጡት ጤናማ ያልሆነ የተጋነነ ግምት፣ በኦሮሙማ የዘርማጥፋት የህሊና ውቅርና ኢስብአዊ ጭካኔ ሰበብ ኢትዮጽያ በመፈራረስ ላይ ትገኛለች ። አስፈሪ የዘርማጥፋት ዝግጅት ውስጥ ውስጡን እየተብላላ ነው። የዘር ማጥፋቱን የሚያቀጣጥለው የኦሮሙማ ጥላቻ የሩዋንዳን ዘር ማጥፋት ካመጣው ሃይል የማይተናነስ ክፋት አለው። ከሩዋንዳ ዘር ማጥፋት በኋላ ‘ሁለተኛ አይደገምም ‘ የሚል ቃል የገባው አለም አቀፉ ማህበረስብ በ120 ሚሊዮን ኢትዮጽያውያን ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ የመቀልበስ የሞራል ግዴታ አለበት ። በተጨማሪም አለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጽያን መረጋጋት የሚፈልግበት አካባቢያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞች አሉት ምክንያቱም ኢትዮጽያ በአለም ዋና የነዳጅ መተላለፊያ ከሆኑት አንዱ በሆነውና ለአለም አቀፍ የነዳጅ ሃይል አቅርቦት ዋስትና ወሳኝ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ ታላቅ ሀገር በመሆኗ ነው።

የአእምሮና የስነምግባር ብቃት የጎድለው ጠቅላይ ሚኒስትር 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉን አድራጊ ፤ሁሉን አዋቂ፤ በሁሉ ቦታ መገኝት የሚችል መሆኑን ማመኑ የስነልቦና ቀውሱን ማሳያዎች ናቸው ። በሰባት አመት የልጅነት እድሜው እናቱ የኢትዮጽያ ንጉስ እንደሚሆን ና ሀገሪቱን ከድህነት ወደታላቅነት እንደሚመራ እንደነገረችው በአደባባይ ለመናገር ምንም ሀፍረት አልተሰማውም። በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ በእኔ አመራር በ2050 ኢትዮጽያ በአለም ሁለተኛ ልእለ ሃያል ሀገር ትሆናለች ሲል እንዲሁ ሀፍረት አይሰማውም። እናት ለልጆቿ ያላትን በጎ ህልም እንደ የመፅሃፍ ትንቢት ያምናል።  

ለአድናቆትና ዝና የማይረካ ጥም አለው። የእሱን የቅዥት ስኬት በመሬት ላይ ካለው ውድቀቱ ለማስታረቅ ሲያቅተው እውነታውን መሸሽ እንደአማራጭ ይጠቀማል። በምሳሌ ላስረዳ 

በ ዴሴምበር 2022 እ.ኢ.አ አለም አቀፉ ሚዲያ ዮክሬን ስንዴ የተጫነች መርከብ የተራቡ ኢትዮጽያውያንን ለመመገብ እንደሰደደች ሲዘግብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውዝግብ አስነስቷል። በቴሌቪዥን ቀርቦ ‘’መንግስቴ ፈጽሞ ስንዴ አልለመነም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ስንዴ የሚልከውና በአለም አቀፍ ሚዲያ የሚያራግበው በምግብ እህል ራስን በመቻል ያስመዘገብኩትን ስኬት ለማንኳሰስ ነው። ‘’ ሲል ንዴቱን ገልጿል። ‘’ኢትዮጽያ የምግብ እርዳታ ከመጠበቅ አልፋ ምግብ ለውጭ ንግድ ለማቅረብ ተዘጋጅታለች ‘’ ብሏል።  

እ.ኢ.አ በ2023 አሜሪካ ና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለተራቡ ድሆች ሊቀርብ የሚገባው ስንዴ ላይ ከፍተኛ መንግስታዊ ስርቆት ተከስቷል በሚል ለኢትዮጽያ የሚያቀርቡትን ስብአዊ ድጋፍ አቁመዋል። በእርዳታ የተገኘው ስንዴ ወደ ዱቄት ተቀይሮ ኬንያና ሱማሊያ ተልኮ ተሽጧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ በአደባባይ ወጥተው አሜሪካንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብአዊ ድጋፍ ለማቆም መወሰናቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጽያውያንን ለርሃብ አደጋ ያጋልጣል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ይህ የተገለፀው ከስድስት ወራት በፊት ኢትዮጽያ የተትረፈረፈ ምርት አምርታ ስንዴ ለውጭ ገበያ ታቀርባለች ባለው የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥላውን የማያምን ሰው በመሆኑ ሰላማዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለርሱ ፍፁም ስልጣን አደጋ እንደሆኑ አድርጎ ይወስዳል ። እ.ኢ.አ በ2021 በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ስልጣኔን ሊቀሙ እያሴሩ ነው በማለት ከሶ በአንድ ጀንበር በመቶ ሺዎች ሲገደሉ ያያሉ ሲል ዝቷል። 

እ.ኢ.አ በ 2023 እርሱን ከስልጣን ለማውረድ ብጥብጥ የሚያስነሱ ጽንፈኞች በ1970 ከነበረው የቀይ ሽብር እልቂት የበለጠ መዘዝ እንደሚያስከትል ሊያውቁ ይገባል ሲል ዛቻውን ከፍ አድርጎታል ። እንደ አፍሪካ ህብረት መረጃ በቀይ ሽብር ከ700,000 የሚበልጡ ኢትዮጽያውያን ተገድለዋል። 

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ደህንነት ግድየለሽነትና ችግሩን ለመረዳት ፍላጎት ማጣት ለህዝቡ ስቃይ ማዘን እንዳይችል አድርጎታል። ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ከሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በጦርነት፣ ርሃብና የጅምላ ፍጅት አልቀዋል እንዲሁም ከ 5 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግድ ተፈናቅለዋል ። ይህ ሁሉ ሆኖ እሱ ቅድሚያና ትኩረት የሚሰጠው ለታይታ መናፈሻዎችና ቤተመንግስት ግንባታዎች ነው ። የሚገነባው ፈርኦናዊ ቤተ መንግስት ሶስት ሰው ሰራሽ ሃይቆች ፤ የአራዊት ፓርክ ፤ ፏፏቴና በዱባይ ደረጃ ያሉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን ጨምሮ ሊሎች ቅንጡ ግንባታዎችን ያካተተ ነው ። ይህ የርሱ ፕሮጀክት በኢትዮጽያ ታሪክ እጅግ ውድ ሲሆን እስከ 15.3 ቢሊዮን ዶላር ያስወጣል።  

ስለፕሮጀክቶች የሚቀርቡ ሰፊ ወቀሳዎች ሲመልስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጽያ ድህነት ፕሮጀክቶቹን ከማስፈፀም እንደማያግዱት በጥብቅ በመቃወም ተናግሯል። በአሜሪካ በምግብ እርዳታ የሚኖሩና ቤት አልባ የሆኑ ዜጎች የኢትዮጽያን ህዝብ 50 በመቶ (ከ 60 ሚሊዮን በላይ) የሚሆኑ ናቸው ሲል ሞግቷል። መልእክቱ ይህ አሜሪካንን ወደ ማርስ መጓዝን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ከማስፈፀም አላገዳትም ነው።

ይህ ሆነተብሎ የተደረገ ግልፅ ማጭበርበር ነው። በመጀመሪያ በአሜሪካ ቤት አልባ ዜጎች ቁጥር 582,000 ነው በምግብ እርዳታ የሚኖሩ አሜሪካውያን 42 ሚሊዮን ናቸው ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጠቀሰው 60  ሚሊዮን ያነስ ነው። ዋናው ነገር በምግብ እርዳታ የሚኖሩ አሜሪካውያን ያጡ የነጡ አይደሉም። 

ምንም እንኳን የመንግስት የተለያዩ ድጎማዎች ተጠቃሚ ቢሆኑም አብዛኛዎቹ መኪና ፤ የራሳቸው ቤት ፤70  ኢንች ቲቪ ፣ ዘመናዊ አይ ፎን፤ የመሳሰሉት አላቸው። ለምሳሌ 4 አባላት ያሉት (ባል ፤ ሚስት ና ሁለት ልጆች) አመታዊ ገቢው ከ36,084 እስከ 55,512 ዶላር የሆነ አንድ ቤተሰብ ለምግብ ርዳታ ብቁ ይሆናል ። 8  አባላት ያሉት (ባል፤ሚስት ና ስድስት ልጆች) አመታዊ ገቢው 60,624 እስከ 93,264 ዶላር የሆነ ቤተሰብ ለምግብ እርዳታ ብቁ ይሆናል ምክንያቱም በአሜሪካ ደረጃ እነዚህ ከድሃ ስለሚመደቡ ነው ። 

የኢኮኖሚው ቀስ በቀስ መፈራረስ 

የእርስ በርስ ጦርነቱ፤ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ቅድሚያ አለመስጠትና የተሳሳቱ የኢኮኖሚ መመሪያዎች ድምር ውጤት የሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ጂዲፒ 25.9 በመቶ መቀነስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዱባይ ያዩትን ብልጭልጭ የሚደንሱ ውሃዎችና የታላቁ ፒተርን የመሰሉ መናፈሻዎች በመገንባት ለመዝናናት በሚያስቡበት በአሁኑ ወቅት 22 ሚሊዮን ኢትዮጽያውያን አለም አቀፍ የምግብ እርዳታ ጥገኛ ናቸው። እንዲሁም ከ 2.3 ሚሊዮን በላይ ህፃናት በጦርነቱ የወደሙት ትምህርት ቤቶች እስኪሰሩ ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው። ከዚህም አልፎ 3 ሚሊዮን ሰዎች ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ኢትዮጽያውያንን ተቀላቅለዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገንዘብ በማተም በሚያሰራቸው የማይረቡ ፕሮጀክቶች (15.3 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ቤተ መንግስት ጨምሮ) የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እያወደመ ነው ። እ.ኢ.አ በ2018 የኢትዮጽያ የዋጋ ግሽበት 13.8  በመቶ ነበር። በዚሁ ወቅት ከሳሃራ በታች የሚገኙ ሀገሮች አማካይ የግሽበት መጠን 4.1 በመቶ ነበር። እ.ኢ.አ በ ጃንዋሪ 2022 ኢትዮጽያ በአለም የከፋ የዋጋ ግሽበት ከስመዘገቡ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች። የአለም 

የገንዘብ ድርጅት የ2023 የኢትዮጽያ ግሽበት ትንበያ 31.4 በመቶ ነው። በ2024 የግሽበት ትንበያው 23.5  በመቶ ነው ። የአፍሪካ 2024 አማካይ የግሽበት ትንበያ 5 በመቶ ነው። 

ዋናው አሳሳቢ ጉዳይ የ2023/24 የመንግስት የ281.05 ቢሊዮን ብር (5.2 ቢሊዮን ዶላር) የበጀት ጉድለት ነው። የተለያዩ ምክንያቶች ለችግሩ አስተዋፅኦ አድርገዋል። አንዱ ከቀረፅ የሚገኝው ገቢ ለሀገር ውስጥ አጠቃላይ ምርት ሲካፈል ውጤቱ እየቀነስ መምጣቱ ነው ። ከአምስት አመት በፊት 0.11 ነበር በ2022/2023  በጀት አመት 0.07 ነበር ። ከስሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት አማካይ 0.17 ነው። ወደር የሌለው ሙስና ሌላኛው ነው። ወደ መንግስት ካዝና ሊገባ የሚገባው ገንዘብ ወደ ግለሰቦች የግል ባንክ ሂሳብ ይገባል። ከወርቅ የውጭ ንግድ ይገኝ የነበረው ገቢ 59 በመቶ መቀነሱ ለዚህ ምሳሌ ነው። ሶስተኛው ምክንያት አለም አቀፉ ማህበረሰብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስተዳደር ብቃት ላይ እምነት በማጣቱ እርዳታ በከፍተኛ መጠን መቀነሱ ነው። 

ሁለተኛው አሳሳቢ ጉዳይ መንግስት ለዘላቂ ልማት ስራዎች (ለመንገዶች ፤ ድልድዮች ና ለመሳሰሉት)  የሚመድበው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ ነው ። በመንግስት በሚጠቀስ አንድ የ’ሴፈስ ካፒታል’  ሪፖርት በ2018/19 በጀት አመት የመንግስት የዘላቂ ልማቶች ወጪ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 6.5 በመቶ ብቻ ነበር። በ2022/23 ወደ 2.9 በመቶ አሽቆልቁሏል። የኢትዮጽያ የስታስቲክስ አገልግሎት መረጃ ተመሳሳይ ነው። ለ2023/24 ምንም መረጃ አልወጣም ሆኖም በዋጋ ግሽበት ምክንያት በተፈጠረው የመንግስት በጀት መቀነስ ቁጥሩ በ2022/23 ከነበርው በጣም እንደሚቀንስ ይገመታል።  

 “ከፍተኛ ማሽቆልቆል” የሚለው አጠቃላይ የኢኮኖሚውን ሁኔታ የሚገልፅ ይመስላል ። ቱሪዝም አንዱ ማሳያ ነው። ሀገሪቱ በጦርነቱ ና በኮቪድ 19 ምክንያት 2 ቢሊዮን ዶላር አጥታለች ። ። ጦርነቱ ከስድስት ወራት በፊት

አቁሟል።ወረርሽኙ ካለፈ በኋላ አለም አቀፍ ቱሪዝም ሲያንሰራራ የኢትዮጽያ ግን ወደ ቀድሞው ሊመለስ አልቻለም። ይህ በዋናነት በሀገሪቱ ህግ ና ስርአት ባለመኖሩ ምክንያት የመጣ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእውነት እንደተጣላ ዋነኛው ማሳያ ቱሪዝም ነው ። ህግ ና ስርዐት ወደ ሌለበት ዜጎች ህግን በመዳፋቸው ወዳስገቡበት ሀገር ቱሪስት እንዳማይሄድ እየታወቀ ለቱሪስት መስህብ በሚል መናፈሻ መገንባቱን ቀጥሏል። በአንፃሩ ኬንያ በ2022 ቱሪዝምን ወደ ቀደመ ደረጃው መመለስ ችላለች። በ 2022 የቱሪዝም ገቢዋን 83  

በመቶ በማሳደግ ወደ 2.13 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ ችላለች ። በ2023 መጨረሻ ገቢዋ ወደ 3.37 ቢሊዮን እንደሚያድግ ይጠበቃል።  

በከፍተኛ ማሽቆልቆል ላይ ከሚገኙት መካካል ኢንዱስትሪው ይጠቀሳል ። እንደ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በ2022 446 የማምረቻ ኢንደስትሪዎች ምርት አቁመዋል። የገንዘብ እጥረት፤ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፤ የተቀናጀ መንግስታዊ ድጋፍ አለመኖር ና የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት እንደምክንያት ተጠቅሰዋል። የውጭ ምንዛሬ ችግር እንዲሁ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጓዳ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በማግኝታቸው የሀገሪቱ የማምረቻ ና ሌሎች ህዝባዊ ፕሮጀክቶች ከህጋዊው ተመን እስከ እጥፍ በመክፈል ወደ ጥቁር ገበያ ለመሄድ ተገደዋል ።የሃርቫርድ ጥናት እንዳመላከተው አሳሳቢ ደረጃ የደረስው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚፈልጉ አምራች ድርጅቶችን እየጎዳ ነው። በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከቻይና 200 አውቶብሶችን ለመግዛት የጥቁር ገበያ ተመን እንደተጠቀመ ለማመን ተገዷል። ይህ የከተማ መስተዳድሩ ለእያንዳንዱ አውቶብስ ከመደበኛው እጥፍ ዋጋ እንዲከፍል አድርጎታል።  

ምናልባት እጅግ የሚያሳዝነው ማሽቆልቆል ከድህነት ቅነሳ ጋር የተያያዙ የመንግስት ወጪዎች ላይ የታየው ነው። እንደ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት የሩብ አመት የኢኮኖሚ ትንተና ድህነት ተኮር ወጪዎች በ 2022 የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት 2.9 በመቶ ነበር ይህ ከ2017 ወዲህ ዝቅተኛው ነው። የኢትዮጽያ ስታስቲክስ አገልግሎት መረጃ ከ2017/18 እስከ 2020/21 ተመሳሳይ ማሽቆልቆል ያሳያል።  

ብቸኛው ውጤታማ ድርጅት የኢትዮጽያ አየር መንገድ ነው 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢው ሀገሪቱ ከውጭ ምንዛሬ ንግድ ካገኘችው 3.9 ቢሊዮን ዶላር እጅግ ይበልጣል ። የሚያሳዝነው ይህ ፅሁፍ በሚፃፍበት ወቅት ከኢትዮጽያ የሚሰማው ሰበር ዜና የአየር መንገዱ ቦርድ ሊቀመንበር ግርማ ዋቄ በግዳጅ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ነው ታይምስ ኤሮስፔስ የአፍሪካ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አባት ተብለው የሚታወቁትን ሰው አስደንጋጭ የስራ መልቀቅ ‘’ ግርማ የኢትዮጽያን አየር መንገድ የአህጉሩ ታላቁ አየር መንገድ ና ከታላላቅ አለም አቀፍ አየር መንገዶች ተፎካካሪ እንዲሆን ያስቻሉ ናቸው’’ ሲል ዘግቧል ። አክሎም ‘’ምንም እንኳ በአየር መንገድ ስራ ውስጥ የመንግስትን ድጋፍ የሚያደንቁ ቢሆንም የመንግስትን በአየር መንገዱ አስተዳደር ጣልቃ መግባት ይቃወሙ ነበር ‘’ብሏል 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኝህን የአቪዬሽን እንቁ በኢትዮጽያ ፤ በቀጠናውም ሆነ በአለም አቀፍ አቪዬሽን ምንም እውቅና በሌላቸው ወጣት የአየር ሃይል ጄኔራል ቀይረዋቸዋል ። መላምቶች ቢኖሩም በግዳጅ ስልጣናቸውን የለቀቁበት እርግጠኝ ማብራሪያ አልተገኘም ። እንደኔ እምነት ውሳኔው የተደረገው የአየር መንገዱን የአሜሪካ ዶላር ና ዩሮ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቤተ መንግስት ፕሮጀክት ለማዞር ባለ ፍላጎት ነው። እንዲሁም አለም 

አቀፍ የምግብ እርዳታ ተሰርቆ ለውጭ ንግድ የቀረበበት ምክንያት በከፊል መንግስት እንዲሁ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማይረቡ ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሬ ለማቅረብ ካለው ሰቀቀን ጋር የተገናኘ ነው የሚለውን ከግምት ውጭ ለማድረግ አስቸጋሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን ሀብት ምርታማ ና ድህነት ቀናሽ ከሆኑ ተግባራት ወደ ራሱ የማይረቡ ፕሮጀክቶች በማዞሩ የኢትዮጽያ ኢኮኖሚ እየሰጠመ ነው። ከዚህም የከፋው እነዚህን የማይረቡ ፕሮጅክቶች የሚያከናውነው ከ ሀገሪቱ ህግ ማእቀፍ ውጭ ነው።

መልስ የሚያሻቸው ጥያቄዎች አሉ ። አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ና የአለም ባንክ ይህንን እያዩ እንዳላዩ እይሰሙ እንዳልሰሙ መሆን ጆሮ ዳባ ልበስ ሊሉ ይችላሉ? ይህ የድርጅቶቻቸውን የአባል ሀገራትን ኢኮኖሚና የገንዘብ ፖሊሲ ጤንነት በየጊዜው የመመርመር ሃላፊነታቸውን አለመወጣት አይሆንም ወይ? 

የምንሰማው የውጭ ምንዛሬ ተመንን በጣም ለመጨመር ያላቸውን ጉጉት ብቻ ነው ። መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግሮቹ ያሉት ሌላ አካባቢ ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህግ ከተፈቀደለት ውጭ የማይረቡ ፕሮጀክቶችን ሲያቅድ ና ሲያስተገብር ለምን ዝም አሉት? ለምን ከፈተኛ ድጎማ የሚደረግለት ብድር ኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለሚያደርስ አምባገነን ይሰጣሉ ? ይህ የአለም አቀፍ እርዳታ ገንዘብ ለሚያዋጡት አለም አቀፍ ግብር ከፋዮች ያለባቸውን የመተማመን ግዴታ መጣስ አይሆንም ወይ? 

የኦሮሙማ መንግስት 

ቃል በቃል ኦሮሙማ ማለት ኦሮሞነት ወይም ኦሮሞ መሆን ማለት ነው። በተለምዶ የኦሮሞን ባህል የማቀፍ ና መንከባከብ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ክፋቱ ቃሉ የስን ምግባር ና ስነልቦና ድርቀት ባጋጠማቸው የኦሮሞ ጎሳ ምሁራን ተወርሶ ፤ ተጠልፎ ና ተበርዞ እንደ ዋና የኦሮም ብሄራዊ እንቅስቃሴ ርእዮት ሆኖ ቀርቧል ።  

የኦሮሙማ የጡት አባት የሆኑት ፕሮፌሰር አሰፋ ጃላታ እንቅስቃሴው ሁለት መልክ እንዳሉት አረጋግጠዋል። ከታሪክ ፤ ባህል ና ልማድ የወጣው የተለመደው ኦሮሙማ ና የፖለቲካ ና ርእዮተ አለም ፕሮጀክት የሆነው ብሄራዊና አለም አቀፍ ኦሮሙማ ። ኦ ፕራይድ የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ ቃሉን ‘’ የኦሮሞ ፖለቲካዊ ማንነት ‘’  በማለት ገልጾታል ። 

የእንቅስቃሴው ደጋፊዎች የኦሮሙማ ኢስብአዊ ጭካኔዎች እንደ የፖለቲካ ርእዮት ሲጠቀሱ በጣም ይበሳጫሉ። ፍላጎታቸው የፖለቲካ ግቦቻቸውን በኦሮሞ ባህልና ልማድ መጋረጃ መደበቅ ነው። እውነታው በኦሮሙማ መዝገበ ቃላት የቃሉ ፍቺ ‘’ ብሄራዊ ና አለም አቀፍ የፖለቲክ ፕሮጀክት ‘’ የሚል ነው ። 

ኦሮሙማን አደገኛ የሚያደርገው ለዋናው ፖለቲካዊ ፍላጎቱ ማህበራዊ ና ሃይማኖታዊ መልክ መጨመሩ ነው ። በዚህም የተነሳ ፖለቲካዊ ና ሃይማኖታዊ አመራሩን መቆጣጠር ለኦሮሙማ እንቅስቃሴ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ክርስቲያኖች ና ሙስሊሞች በኦሮሞ መሬት ሃይማኖታቸውን የመከተል መብት እንዳላቸው እስከ መጠየቅ አድርሷቸዋል ። ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በተደረገ ጥናት እንደተመላከተው ፕሮፌሰር ጃለታ ‘’ ኢስላም በኦሮሞ ማንነት ውስጥ ትክክለኛ ቦታ እንዳለው ለመቀበል አመንትተዋል ‘’ እንዲሁም ‘’ኦሮሞዎችን ክርስቲያን የማድረግ ሂደት ዘረኝነት ነው ‘’ ሲሉ ይከሳሉ።  

እንደ የፖለቲካ ና ሃይማኖት እንቅስቃሴ ፣ ኦሮሙማ አመጽን ይጠቀማል እንዲሁም ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር በቅርበት ይሰራል ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በጅምላ ግድያ ና ኢትዮጽያውያን ና የውጭ ሀገር ዜጎችን በማፈን ገንዘብ በመጠየቅ ይታወቃል ። የኦሮሙማ ምሁራን ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ገንዘብ ይሰበሰባሉ ፤እንዲሁም መንግስት ና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በታንዛኒያ ድርድር ሲቀመጡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ልኡክ አባል ነበሩ። 

የኦሮሙማ እንቅስቃሴ ዋና ኢላማ ‘’ የኢትዮጽያ ቅኝ አገዛዝ ‘’ ና እንደ ቅኝ ገዢ ተቋማት ና ግዛት አስፋፊ የሚታዩት ቤተክርስትያኖች ና መስጊዶች ናቸው ።ምንም እንኳ ኦሮሙማ የኢኮኖሚ ፤ፖለቲካ ና ባህል እንቅስቃሴ ነኝ ቢልም አትኩሮቱ ሃይማኖት ላይ ነው። ከሚያቀርቧቸው ክሶች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ 

• የሃበሻ ገዢዎችን ሃሳቦች ና ሃይማኖት አስተዋውቀዋል 

• ኦሮሞዎች የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ና ራሳቸውን እንዲጠሉ አድርገዋል 

• የኦሮሞን ጥንታዊ ሃይማኖት በመቀየር ና የሃበሻ ና አረብ ስሞችን ፣ ሃይማኖትን ፤ ወግ ና ስርዐት መውረስ

• ኦሮሞዎች የተውሶ ሃይማኖት ማንነትና ንዑስ ማንነት መጠቀም መጀመራቸው 

የኦሮሞ ህዝብ ክርስትና እና እስልምናን እንዳይከተል ጫና ማድረግ 

የኦሮሙማ እንቅስቃሴ ባህላዊ ገፅ ሲፋቅ ና በጥልቀት ሲፈተሽ አላማው ዋቄ ፈና የተባለውን የኦሮሞ ሀገር በቀል ሃይማኖት እንደ መንግስታዊ ሃይማኖት እውቅና መስጠት ነው። እንደ 2007 ህዝብ ቆጠራ 3.3 በመቶ ኦሮሞ ብቻ ዋቄ ፈናን ይከተላል። በተቃራኒው 96 በመቶ የኦሮሞ ህዝብ ክርስትናን ና እስልምና ይከተላል ክርስትና ና እስልምና የሚከተሉና የሚያመልኩ ኦሮሞዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው። በቴኔስ ዩኒቨርሲቲ የመረጃ መረብ ድህረ ገፅ የታተሙ ሁለት ጽሁፎች ኦሮሞ ክርስቲያኖችን ና ኦሮሞዎችን የገለፁት እንደሚከተለው ነው  

 ‘’እንደ ሀበሻ ጌቶቻቸው የሃበሻ ባህልን ሃይማኖትን ና የአማረኛ ቋንቋን የሚያስጠብቁ ና የኦሮሞን ታሪክ ፣ ባህል ና ተቋማት የሚጠሉ ኦሮሞዎች ናቸው እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ከኦሮሞ ልማድ የተገለሉ ና የበታችነታቸውን ባሳመኗቸው ገራፊዎቻቸው ሃሳቦች ና እውቀት የሚደመሙ ናቸው።’’ ሃበሻ በሰሜን ኢትዮጽያ የሚኖሩ ህዝቦችን ለመግለፅ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። የኦሮሞ ክልል ፕሬዝዳንት አማራዎችን ‘’ጠላት ‘’ በማለት በተደጋጋሚ ሲገልፁ ተሰምተዋል። 

የኦሮሙማ እንቅስቃሴ ምሁራዊ ሙከራ አይደለም ። የሃይማኖት ማፅዳት ቅድመ ዝግጅት ነው። ለዘር ማጥፋት ዘመቻ ፅንስ ነው ። በ ጃንወሪ 2023 የአሜሪካ ድምፅ እንደዘገበው ከኦሮሞ ጎሳ መሬት የተፈናቀሉ አማሮች ወደ አንድ ሚሊዮን ይደርሳሉ። ሰዎቹ ክርስቲያኖች ና እስላም ናቸው። በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን በደል በመዘከር ፖፕ ፍራንሲስ ተከታዮቻቸውን ‘’በኢትዮጽያ ለተገደሉ ክርስቲያኖች እንዲፀልዩ’’ ጠይቀዋል 

ዘ ጋርድያን ‘’ ከሁለት መቶ የሚበልጡ አማራዎች በ ኦሮሞ ፅንፈኞች ተገድለዋል ‘’ ሲል ዘግቧል አብዛኛዎቹ ሙስሊም ነበሩ ። የ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ‘’ ከፍተኛ ትጥቅ ያነገቡ ገዳዮች ሴቶችን ና ህፃናትን ጨምሮ 400 ሰላማዊ አማሮችን ገድለዋል ‘’ ሲል እንዲሁ ስለ ሌላ ዙር ጅምላ ጭፍጨፋ ዘግበዋል ። በሪፖርቱ የሚያለቅሱ ሙስሊም አባት ተጠቅሰዋል ። 

 ‘’ የ 8 ወር ልጄ ማልቀስ ጀመረች ። ወደኛ ከመተኮሳቸው በፊት አንድ ታጣቂ ‘ ወደ እዚህ ተመልከት ‘ወደ እዚህ ተመልከት ‘ ሲል ሰማሁት … ህፃን ልጄን ተኩሰው ገደሉት ። ሬሳውን በለበስኩት ልብስ ሸፈንኩት ። ሌላዋ ልጄ ከጀርባ ተመታች ጥይቱ በአንገቷ አካባቢ ወጣ ። የቆሰለች ልጄን ወደ ደረቴ አስጠግቼ አላህ ህይወቷን እንዲያተርፍልኝ ፀለይኩ “ 

ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ የኦሮሞ መንግስት ከ200 በላይ ቤተክርስትያኖች ና መስጊዶች አፍርሷል ፕሬዝዳንት ሺመልስ ለክርስቲያን ና ሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች በቴሌቪዥን የተቀርፀ ሁለት ገለፃ ሰጥቷል አንደኛው የፈረሱት የአምልኮ ቦታዎች ህገወጥ ግንባታዎች ነበሩ የሚል ነው። የኢትዮጽያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይህንን ክስ ተቃውሞታል ። 

ሁለተኛው የአምልኮ ቦታዎቹ በፈርሱበት መሬት ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ያሉት የኦሮሞ ታላቅ ከተማ ይገነባል የሚል ነው። ገለፃው ተቃውሞ ሲገጥመው ፕሬዝዳንት ሺመልስ ያስከተለው የሚረብሽ መልስ ነው ‘’  ጠላቶቻችን አላማችን ገብቷቸዋል ‘’ አላማው መስጊዶች ን ና ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ እንደ ምክንያት አዲስ ታላቅ ልብወለድ ከተማ መጠቀም ነው ። ‘’ ሸገር ከተማ ና ገዳ የኦሮሙማ የሰማይ ቤተመንግስት ቅዠት ናቸው”  

በስብሰባው የታደሙ የሃይማኖት መሪዎች ላይ ማሾፍ በሚመስል አይነት ፕሬዝዳንቱ ወደፊት ለመስራት የሚፈቀድላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የውጭ ጎብኝዎችን መሳብ የሚችሉ ህንፃዎችን ብቻ ነው ብለዋቸዋል። ‘’  ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች ና መስጊዶች መስራት አይፈቀድም ‘’ሲሉ አስረገጥዉ ተናግረዋል ። የውጭ ጎብኝዎችን የሚስቡ እንደ ቅዱስ ጼጥሮስ ካቴድራል ወይም በዱባይ ክሬክ ሃርቦር ያለው ታላቅ መስጊድ አይነት ካልገነቡ ምንም የማምለኪያ ስፍራ አይኖራቸውም ።

ጉዳዩ የግንባታ ደረጃን መጠበቅ አይደለም ።ድሃ ክርስቲያን ና ሙስሊሞችን በኦሮሞ መሬት የአምልኮ ስፍራ የመከልከል ስልት ነው። በወሎ አንድ አባባል አለ ‘’ ቤተክርስቲያኑ ወይም መስጊዱ ሲያንስ ፈጣሪ ይቀርበናል’’ ቁምነገሩ በቤቱ ያለው መንፈስ ነው እንጂ የህንፃው ማሸብረቅ አይደለም የሚል ነው። ‘  

የፕሬዝዳንት ሺመልስ ና የሃይማኖት መሪዎቹ በቴሌቪዥን የተቀርፀ ስብሰባ የሕዝብ ግንኙነት ድራማ ነበር ። በመሬት ላይ ያለው እውነታ በኦሮሞ የሚኖሩ ከርስቲያኖች ና ሙስሊሞች ኢሰብአዊ ለሆነ አሰቃቂ ጭካኔ የተጋለጡ መሆናቸው ነው። አለም ከስብአዊ መብቶች ጥሰት ሪፖርቶች የኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሪዎችን ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ የቀሳውስትና ኢማሞች መደበደብ አንብቧል ። አረጋዊ ሙስሊም እናት እያለቀሱ በዚህ ከቀጠለ ለመቀበሪያ ቦታ እንኳን አናገኝም በማለት ምህረት ሲለምኑ አለም ሰምቷል ።  

አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በምክርቤት መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው ኦሮሞ ያልሆኑ የምክርቤት አባላት ‘’  የአማሮ ህዝብ በሶስት አቅጣጫ በኦሮሞ የተከበበ ነው። ከሌሎች ክልሎች እንዳንገናኝ ተከልክለናል። ሆስፒታሎቻችን ቤተክርስቲያኖቻችን ተቃጥለዋል ። የደረሰብንን መከራ በቃላት ለመግለፅ ያስቸግራል። ተወረናል ፤ ተጨፍጭፈናል ና ጎሳችን የህልውና ስጋት ተጋርጦበታል። ‘’ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍትህ ሲማፀኑ ሰምቷል 

ከዚህም የከፋው ምእመናን በፀሎት ና ዝማሬ ላይ እያሉ የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ውስጥ አስለቃሽ ጭስ ሲወረውሩ አለም በድንጋጤ ታዝቧል። እነዚህ ኦሮሙማን ና ዋቄ ፈናን በኢትዮጽያ መንግስታዊ መመሪያዎችና ሃይማኖት ለማድረግ የሚወስዱ ጥቃቅን እርምጃዎች ናቸው።  

ፕሬዝዳንት ሺመልስ የኦሮሞ ብልጽግና ለወደፊቷ ኢትዮጽያ ያቀደላት የገዳ ስርዐት ነው ብለው ሲናገሩ ቃላት ለመምረጥ አልተቸገሩም ። ገዳ ሃይማኖታዊ (ዋቄ ፈና) ና ሃይማኖታዊ ያልሆኑ ተግባራትን የያዝ የኦሮሙማ ፍልስፍና መሰረት ና ዋና መመሪያ ነው ። ችግሩ ገዳ በቁራን ና ነቢዩ መሃመድ ትምህርት ከተመሰረተው ከእስልምና ህግ ከሽሪያ ይቃረናል። የፕሮፌሰር ጃለታ አቋም ክርስትና ና እስልምና ከብሄራዊው ኦሮሙማ መስማማት አለባቸው የሚል ነው  

ፕሬዝዳንት ሺመልስ በኦሮሞ ጎሳ መሬት የሚኖሩ ክርስቲያኖች ና እስላሞች ኦሮሙማ ከሃይማኖታቸው እንደሚበልጥ መገንዘብ አለባቸው በማለት ይሄንኑ ደግሞታል። ፕሬዝዳንት ሺመልስ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው መንግስታቸው በአዲስ አበባ የኦሮሙማን ምልክቶች ለማኖር በቢሊዮኖች እያወጣ ነው ሲሉ አክለዋል። ከአዲስ አበባ ነዋሪ ኦሮም 19 በመቶ ብቻ ነው ። 

እ.ኢ.አ በ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ክርስቲያኖች ና እስላሞች በጋራ የአዲስ አበባን ሕዝብ 99 በመቶ ይሆናሉ ። በአንፃሩ የዋቄ ፈና ተከታዮች 0.05 በመቶ ብቻ ናቸው ። ዋቄ ፈና በአዲስ አበባ ድሃጣን ነው። በህዝብ ብዛትም አናሳ ነው። ነገር ግን ክርስቲያኖች ና ሙስሊሞች ወደ ኦሮሙማ ና የኦሮሙማ ሃይማኖት ወደ ሆነው ዋቄ ፈና እንዲዞሩ ተነግሯቸዋል። ይህ የተነገረው ከዋነኞቹ የአሜሪካ ዮኒቨርስቲዎች በአንዱ ድህረ ገፅ ነው።  

መጽሃፍ ቅዱስን ክኦሮሞ ማንነት ለማስማማት በሚያደርጉት ጥረት የኦሮሙማ ምሁራን ኢትዮጽያ የሚለውን በ ኩሽ በመቀየር አዲስ የመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም አሳትመዋል። ኦሮሙማው መፅሀፍ ቅዱስ ምሳሌ 68፡31  እንዲህ ይነበባል ‘’ኩሽ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች “

የኦሮሙማ ኢሰብ አዊነት ሰእላዊ ማሳያ 

የኦሮሞ መንግስት ና የኦሮሙማ ወሮበሎች የሚፈፅሙት ወንጀል ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የሚደረግ ነው። (1)  በፎቶው የሚታየው የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ የሆነች እናት ና የልጇ ሬሳ ነው። (2) የአምኒስቲ ኢንተርናሺናል ሪፖርት (3) የኢራን ጋዜጣ (ታስኒም) ባለስልጣናት በመቶ የሚቆጠሩ ቤቶች በማፍረሳቸው የተነሳው ቁጣ በሚል ርእስ ያወጣው ዜና ። (4) የክርስቲያኖችን ና ሙስሊሞችን በብዛት መፈናቀል የሚያሳይ (5) በፈረሰ መስጊዳቸው የሚፀልዩ ሙስሊሞች (6)ቤታቸው ከፈረሰና ንብረታቸው ከተጣለ በኋላ ከትንሽ ወንድሟ ጋር በጎዳና የተቀመጠች ህፃን 

የኦሮሙማ ወንጀሎች ጭካኔ ምንጭ ና የዘርማጥፋት ምልክቶች 

የኦሮሙማ ወንጀሎች ና ኢሰብአዊ ድርጊቶች የሚፈፀሙት በኦሮሞ ወጣት ካድሬዎች ፤ የአካባቢ ታጣቂዎች ና የፖሊስ አባላት ነው ። እነዚህ ቁጣን ና ብቀላን ለማነሳሳት ታስቦ በተደርጉ የዘመናት የኦሮሙማ የውሸት ቅስቀሳ አእምሮቸው የተበረዙ ወጣቶች ናቸው። በጥላቻ የተሞሉ ወጣት ኦሮሞዎች ቤተክርስቲያን ና መስጊድ ሲያዩ የሚታያቸው ‘የኢትዮጽያ ግዛት አስፋፊዎች ና በሃይል የተጫነባቸው ባህላዊና ሃይማኖታዊ ማንነት ነው ‘’  

አብያተ ክርስትያናትን ና መስጊዶችን ሲያዩ የሚያስቡት የኦሮሞ ጠላቶች ክርስትናን ና እስልምናን ለማስተዋወቅ የተጠቀሙት ሶስት ደረጃዎች ያሉት ሂደት የሚለውን የኦሮሙማ ትርክት ነው ።. የመጀመሪያው የኦሮሞን መሬት መውሰድ ነው ‘ መሬቱን መውረር ‘ ። ሁለተኛው በሃይል ወይም ማግባባት የሃገሬውን ሰው አእምሮ ክርስትናን ወይም እስልምናን በመጠቀም መለወጥ ነው ። ወቀሳው ሃይማኖት ኦሮሞን ለማንጻት ና መቀደስ ጥቅም ላይ ውሏል ምክንያቱም የኦሮሞ ህዝቦች እንደ እርኩስ ይቆጠሩ ስለነበር ነው የሚል ነው። ሶስተኛው ና የመጨረሻው ደረጃ ለተወረሩት ህዝቦች አዲስ ታሪክ መፍጠር ነው። 

በጥላቻ የተመረዙ ወጣት ኦሮሞዎች ከሰሜን ኢትዮጽያ አካባቢ የመጡ ሰዎችን የሚያዩቸው ኦሮሞን በስነልቦና ለመቆጣጠር ና ለመጨቆን የኦሮሞን ሃይማኖት አጥፍተው እስልምናን ና ክርስትናን የጫኑባቸው የ ቱርክ፣ ሀበሻ፤ አና አውሮፓ ወኪሎች አድርገው ነው

ወጣቶቹ ጠላቶቻቸውን የሚጠሉት አምርረው ነው። ንዴታቸውን ና የበቀል ስሜታቸውን የሚያነሳሱት ‘’ በ 19ኛው ምዕተ አመት መባቻ የጀመረው የኢትዮጽያ የቀኝ አገዛዝ ሽብር ና የዘር ማጥፋት ዛሬም በ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቀጥሏል ‘’ የሚለውን የሃሰት ትርክት በማመን ነው ። 

በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በ አፕሪል 3,2023 የዛሬይቱ ኢትዮጽያ ሩዋንዳ በዘር ማጥፋት ዋዜማ በነበረችበት መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ሲሉ አለምን ያስጠነቀቁት ትክክል ነበር። ከሚኒስትሩ መግለጫ ጥቂት ጊዜ በኋላ ለምኪን ኢንስቲትዩት ፎር ጄኖሳይድ ፕረቨንሽን ‘’ አማራዎች (ኦሮሙማ ቀንደኛ ጠላት የሚሏቸው ህዝቦች) በቀላሉ ወደ ዘር ፍጅት ሊቀየር የሚችል አደገኛ መስመር ላይ ይገኛሉ’’ በማለት አፅንኦት ሰጥቶ ለዘር ማጥፋት ወንጀል የቀይ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል ። 

ኦሮሙማ ጉዳት ያደረሰው በክርስትያን ና እስላም ላይ ብቻ አይደለም የመረዛቸው ና ወደ ዞምቤ ገዳይ የቀየራቸው የኦሮሞ ወጣቶች እንዲሁ ተጠቂ ናቸው። 

አለም አቀፍ ጫና ብቸኛው አማራጭ ነው 

ከሩዋንዳ የዘር ፍጅት በኋላ አለም አቀፉ ማህበረስብ ‘’አይደገምም ‘’ ሲል ቃል ገብቶ ነበር። የሩዋንዳ የዘር ፍጅት በፍጥነት የተፈፀመ ነው ። የኦሮሙማ የዘር ፍጅት ቀስ በቀስ እየተብላላ ነው። አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ የመግባት የሞራል ሃላፊነት አለበት ። ቀደም ብለው በተጠቀሱት ምክንያቶች አለም አቀፍ ማህበረሰቡ የአፍሪካን ቀንድ መረጋጋት የሚፈልግበት ፖለቲካዊ ና ከባቢያዊ ፍላጎቶች አሉት ። 

እየተባባሰ የመጣውን የኢኮኖሚ ቀውስ ና የኦሮሙማ የሃይማኖት የዘር ፍጅት የሚያስከትል ጦርነት ለማስቆም የሚያስችሉ አዋጭ እርምጃዎችን ከማየታችን በፊት ሁለት ወሳኝ ነጥቦችን መረዳት ይኖርብናል ። የመጀመሪያው መሰረታዊ ነጥብ ጠቅላይ ሚኒስትሩና የኦሮሙማ አስተሳሰብ መሪዎች ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ኃይል ሁሉ እየተጠቀሙ መሆኑ ነው። ለኢኮኖሚው መውደቅ ና እየቀረበ ለመጣው የኦሮሙማ ዘር ፍጅት ምልክቶች በፍጥነት እየታዩ ነው። 

ሁለተኛው ኢትዮጽያውያን በሁለት ግንባር በኢኮኖሚው ና ሃይማኖት ንቅናቄ ማድረግ ይገባቸዋል የሃይማኖቱ ያለፖለቲካ አክቲቪስቶች ጣልቃ ገብነት በሃይማኖት ተቋማት ብቻ መመራት አለበት የኢኮኖሚው ንቅናቄ ከሃይማኖቱ ተለይቶ መደረግ አለበት አለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ና ሃይማኖታዊ ንቅናቄዎች አትኩሮት እንደሚስቡ ማስታወስ ያሻል። 

ኢኮኖሚው 

ኢኮኖሚው ቀስ በቀስ ከውስጥ ወደ ውጭ እየፈረሰ ነው ። የኢኮኖሚው እያንዳንዱ ክፍል የሞት ጣር ላይ ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት ቀውሱ በከፍተኛ መጠን በፍጥነት ሲባባስ እየታዘብን ነው። መንግስቱ የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን በጥይት ና በጅምላ እስር ለማፈን ይሞክራል ። 

እንደ የኢትዮጽያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መንግስቱ የውሃ አቅርቦት ለወራት ከተቋረጠ በኋላ የውሃ እጥረት በማጋጠሙ ሰልፍ የወጡ ስዎችን ተኩሶ ገድሏል። የኮሚሽኑ ረፖርት እንዳመለከተው ‘’ሶስት ሰዎች በጭንቅላታቸው ና በደረታቸው ላይ በጥይት ተመተው ሞተዋል። እንዲሁም ከ30 በላይ ሰዎች በተለያየ ደረጃ ቆስለዋል ‘’ 

በተመሳሳይ የአዲስ ስታንደርድ ሪፖርት ፖሊስ በደቡብ ህዝቦች ክልል ሃድያ ዞን መንግስት የሶስት ወር ደመዎዝ ባለመክፈሉ ሰልፍ በወጡ የመንግስት ሰራተኞች ላይ ድብደባ ፈጽሟል ። ሪፖርቱ አንድ የአይን እማኝ መረጃ ይዞ ወጥቷል ‘’ ሰልፉን ለመበተን በፖሊስ ክፉኛ የተደበደቡ ሶስት ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ‘’ በተቃውሞው ሳቢይ ከ 40 በላይ ሰዎች ታስረዋል ። 

በተጨማሪም በኑሮ ውድነት የተነሳ የሚጠየቁ የደመወዝ ጭማሪ ተቃውሞዎች በድንብ ና ማስፈራሪያ ይከለከላሉ። የኢኮኖሚ ቀውሱ ሀገሪቱን ና የቀንዱን አካባቢ ወደ ኢኮኖሚ ውድመት ሊያስገባቸው ጫፍ ደርሷል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ለማስገደድ የገንዘብ አቅም ያለው ብቸኛው ሃይል አለም አቀፉ ማህበረስብ ነው ። 

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዋና መሳሪያ ማእቀብ ነው ። ሰብአዊ እርዳታ ሲቀር ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ መዋል አለበት ። አንዳንድ ሰዎች ማእቀብ ከገደል አፋፍ ያለውን ኢኮኖሚ ክፉኛ ይጎዳዋል ይላሉ ‘ ያልተረዱት ጉዳይ ጣልቃገብነቱ ከቀረ ኢኮኖሚው እንደሚጠፋ ነው። እኔ የማምነው ‘’ የተመርጡ ማእቀቦችን መጣል የሚያመጣው ጉዳት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀመሩት መንገድ ሄደው ከሚመጣው የኢኮኖሚ አጠቃላይ ውድቀት ያነሰ ነው።’’  

ማእቀብ በጣም አስፈላጊ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ በማሳጣት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጉራ ና ቅዥት ፕሮጀክቶች ለማሰናከል ብቸኛው አዋጪ አማራጭ ነው ። የሀገሪቱን ሀብት ወደ ምርታማ የኢኮኖሚ ክፍሎች በማዞር ኢኮኖሚውን ከአጠቃላይ ውድቀት ወደ ማገገም ማምጣት ያስችለናል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትህነግ ጋር የሰላም ስምምነት ሲፈራረም ። ከኦሮሙማ ሸኔ ጋር ለድርድር ሲቀመጥ አይተናል ማእቀብ አይሰራም ና እንደ አማራጭ መወሰድ የለበትም የሚለው ጅላ ጅል ሃሳብ ነው ። ማስተካከያ ፤ ከ ደነዞቹ ‘’# ይበቃል’’ መደርደሪያ የሚገኝ የደነዞች ሃሳብ ነው። ቁጭ ብሎ ተአምር መጠበቅ አንድ ውጤት ብቻ ያመጣል ‘የማይቀለበስ የኢኮኖሚ ውድቀት 

ለቤተሰብ ከሚላክ አስፈላጊ ርዳታ በቀር ወደ ሀገር ቤት የሚላክ ገንዘብን ማስቆም 

የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት በኩል ከአለም አቀፍ እርዳታ ና የውጭ ንግድ ይልቅ ትውልደ ኢትዮጽያውያን ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ ና ወደ ሀገር ቤት የሚያደርጉት ጉዞ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ። በደንብ ከተቀናጀ ትውልደ ኢትዮጽያውያኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን እንዲቀይሩ የማስገደድ በቂ አቅም አላቸው።  

ስለማእቀብ ና ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት መላክ የበለጠ መረጃ የኔን “Averting Civil War in Ethiopia:  An Emergency Manifesto.” የሚል ጽሑፍ ይመልከቱ 

ፀረ፟ክርስትና ና ፀረ እስልምና የሆነውን ኦሮሙማ ለመቋቋም መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች 

በምድር ላይ ማንም ሕዝብ ኦሮሙማን ኢትዮጽያውያን እንደታገሱት ሊታገስ አይችልም ። አንድ ቃል የኛን ድክመት ይገልፀዋል ‘’ በድነናል ‘’ እጅግ የሚያስገርመው በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢው ብቻ ከ60 በላይ አብያተ ክርስትያናት ና ብዙ መስጊዶች እያሉ ክርስቲያኖች ና ሙስሊሞች ይታረዳሉ ፤ የአምልኮ ስፍራዎቻቸው ይፈርሳል ፤ልጆቻቸው ከትምህርት ወይም መኖሪያ ቤት ውጭ ይሆናሉ ። እንዴት አለም አቀፍ ተቃውሞ ማቀጣጠል አቃተን ? በድነናል 

አሜሪካ ከመጀመሪያው የባፕቲስት ቸርች አንድ ኢትዮጽያዊ መርከበኛ ለጥቁሮች በተለየው መቀመጫ እንዲቀመጡ ሲጠየቁ ተቃውሞ ሲወጣ በ 1808 የተመሰረተው የአቢሲኒያን ባፕቲስት ቸርች የሚገኝባት አገር ነች። ኢትዮጽያውያኑ ጥለው ሲወጡ አፍሪካ አሜሪካዊያን ተከተሏቸውና የራሳቸውን ቤተክርስቲያን አቋቋምው አቢሲኒያን ባፕቲስት ቸርች ብለው ሰየሙት ። ቤትክርስትያኗ በአሜሪካ ካሉት ተፅዕኖ ፈጣሪ

ቤተክርስቲያኖች አንዷ ነች ። በምርጫ ወቅት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች የቤተክርስትያኗን ድጋፍ ለማግኝት አዘውትረው ወደዛ ይሄዳሉ ። እንዴት የእነሱን ድጋፍ መጠየቅ ተሳነን ? በድነናል ። 

የአብያተ ክርስትያናት ና መስጊዶች መፍረስ እየጨመረ ና አየተፋጠነ የመጣው አለም አቀፉ ማህበረሰብ እሮሮ ከማሰማቱ በፊት ስራውን ለመጨረስ ነው ። ፕሬዝዳንት ሺመልስ በኋላ የሃይማኖት መሪዎቹን አግኝተው ቤተክርስቲያን ና መስጊድ ወደፊት መስራት ትችላላችሁ ብለዋቸዋል መቼ እንደሆነ አልተናገሩም እስከዛው ያለ አምልኮ ስፍራ ይቆያሉ ። 

የኦሮሞ መንግስት አብያተ ክርስትያናትን ና መስጊዶችን እያፈርስ የተሻለ ጊዜ ይመጣል እንዲለን መፍቀድ የለብንም። ፍትህ ና ተጠያቂነት የፈረሰውን ወደ ነበረበት መመለስ ይጠይቃል ። ከዚህ ያነስ ነገር አንቀበልም። 

በመቀጠል ከዚህ የሚከተሉት እርምጃዎች እንዲወሰዱ እጠቁማለሁ 

የክርስቲያኖች ና ሙስሊሞች የጋራ ኮሚቴ በማዋቀር በሙስሊሞች ና ክርስቲያኖች ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን የሚያስቆም ፤ ለፈርሱ መስጊዶችና ቤተክርስቲያኖች እንዲሁም ለጠፋው ህይወት ሙሉ ካሳ የሚያስከፍል አለም አቀፍ ዘመቻ ማስጀመር ። የፖለቲካ ማህበረሰብ አንቂዎች ጣልቃ ላለመግባት ጥረት ማድረግ አለባቸው። የጋራ ኮሚቴው አባላት የታዋቂ የሃይማኖት ድርጅት አባላት ብቻ መሆን አለባቸው። 

ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ከኋይት ሃውስ ፊት ለፊት እሁድ እሁድ በሃይማኖት አባቶች የሚመራ ጉባኤ ማዘጋጀት ። ይህ ስብሰባ በፖለቲከኞች መመራት የለበትም ። ሁሉም በዲሲ አካባቢ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች ና የሃይማኖት ተከታዮች መገኘት አለባቸው ። አላማው የጋራ የፀሎት ፕሮግራም ማድረግ ና ፕሬዝዳንት ባይደን የሚከተሉትን እንዲያስፈጽሙ ግፊት ማድረግ ነው (1) አሜሪካ ለኢትዮጽያ ለምታደርገው እርዳታ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ በተጨማሪ እንድታስቀምጥ ፤ 

የቤተክርስቲያኖችን ና መስጊዶችን ፈረሳ ፤የክርስቲያኖችን ና ሙስሊሞችን ጅምላ ግድያ ና የክርስቲያን ፤ ሙስሊሞችና ኦሮም ያልሆኑ ዜጎችን ከኦሮሞ መሬት በግዳጅ መፈናቀል በአለም አቀፍ አካላት ማስመርመር (2) አብያተ ክርስቲያናትን ና መስጊዶችን ማጥፋትን ማስቆም (3) ሁሉም የፈረሱ ቤተክርስቲያኖች ና መስጊዶች እንደሚሰሩ ና ሙሉ ካስ እንደሚከፈል ማረጋገጥ (4) የሁሉንም ጥፋተኞች ተጠያቂነት ማረጋገጥ (5) የኦሮሙማን ፀረ ክርስትና ና ፀረ እስልምና ንቅናቄ እንደ ሽብርተኛ ንቅናቄ መፈረጅ።  

በክርስቲያን ና ሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች የስምምነት ፊርማ በማሰባሰብ ለአቢይ አስተዳደር እርዳታ ለሚያቀርቡ ዋና ዋና የፋርስ ባህረ ሰላጤው ና አውሮፓ ሀገራት ከላይ የተጠቀሱትን አምስት ጥያቂዎች በማከል መላክ 

በመረጃ ድህረ ገፁ የጅምላ ግድያ ና የአብያተ ክርስቲያናት ና መስጊዶች መፍረስ ምክንያት ለሆኑ የኦሮሙማ የጥላቻ ፅሑፎች ማስራጫ ና ማከማቻ በመሆን ለሚያገለግለው ለቴኒሲ ዮኒቨርሲቲ የጋራ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መፃፍ። ሁሉንም የኦሮሙማ ፅሑፎች ከድህረ ገፃቸው ባያጠፉ ለክስ ማቅረብ ይገባል ። ጠበቃዎች ይህንን በበጎ ፈቃድ ማድረግ አለባቸው። 

ኢትዮጽያ ታሸንፋለች ! እስልምና ና ክርስትና የኦሮሙማን ጥቃት አሸንፈው ያብባሉ ! ነገር ግን የመከላከያው ጊዜ አስፈሪው የዘር ፍጅት አደጋ ክቁጥጥር ውጭ ከመውጣቱ በፊት ዛሬ ነው ።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here