spot_img
Sunday, July 21, 2024
Homeነፃ አስተያየትከታሪክ ማሕደር : ወሎ የሚለው ስም ከየት እንደመጣ ስንቶቻችን እናውቃለን? 

ከታሪክ ማሕደር : ወሎ የሚለው ስም ከየት እንደመጣ ስንቶቻችን እናውቃለን? 

ደሴ ከተማ (በ2011 ዓ.ም. የተነሳ ፎቶግራፍ)

ታአሪክ እንደሚአስተምረን በአስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን መሃል አገር ያለው ሕዝብ በግራኝ ጦርነት ከተዳከመ በኅላ የኦሮሞ መስፋፋት ሲጀመር ለቱ ለማ የሚባለው የኦሮሞ ጎሳ ሽዋን ሲቆጣጠር ሌሎቹ የኦሮሞ ጎሳወች በተለያዪ አቅጣጫ ተከፋፍልው ሌላውን አካባቢ ለመውረር ሄዱ፡፡ አንጎት ተብሎ ይጠራ የነበረውን አካባቢ የወረረው ወሎ የሚባለው የኦሮሞ ጎሳ ስለነበር አንጎትን ወሎ ብሎ ስሙን ቀዪረው ይባላል፡፡ ታዲያ ታሪካችን ይህን ጭምር የሚአጠቃልል ከሆነ ሁሉንም ኬኛ ኬኛ ከማለትና በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን እየኖረን እንዳአስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን ከማስብ በጋራ ሆነን ድህነትን በመዋጋት ማደግ አይሻልምን? 

አንዳንድ የኦሮሞ ጽንፈኞች የኢትዮጲያ ታሪክ የመቶ አመት ብቻ አስመስለው ሊአቀርቡ ቢፈልጉም እውነቱ ግን ከዛ የራቀ ነው፡፡ ለምሳሌ የፋይናንስ እና የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ከዛም በተጨማሪ በተለያዪ ሃላፊነት ላይ ሆነው አገራቸውን ያገለገሉት የተከበሩ አቶ ይልማ ደሬሳ የእኢትዮጲያ ታሪክ በአስራስድስተኛው ከፍለ ዘመን በሚለው መጻህፋቸው እንዲህ ሲሉ ይገልጽታል፡፡

ታሪክን የማነሳው ለመወቃቀስ ሳይሆን የተጎጂ ትርክት ፈጥረው አሁን ጊዜ አገኘን የሚሉ የኦሮሞ ጽንፈኞች ሕዝቡን የሚያሰቃዩትና የኦሮሙማን ፕሮጀክት ለማሳካት የሚያደርጉት እሩጫ ተገቢ እንዳልሆነና ሁላችንም አብረን በሰላም የምንኖርብትን ስርአት ካልፈጠርን አሁን የሚአደርጉት ዘላቂ ሳዩሆን ጊዜያዊ መሆኑን ሊረዱት ይገባል ለማለት ነው፡፡ በተጨማሪም የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌላው ኢትዮጲያዊ ታሪካችንን እና አሁን የደረስንበትን በትክክል ብናውቅ ጥሩውም መጥፎውም ታሪካችን የሁላችንም መሆኑን ለመረዳት ይጠቅማል በማለት ነው፡፡ ሕዝብአችን አንድ የሚያረገው ብዙ እሴቶች ያሉት በመሆኑ አሁን በምናዪው የውሽት ትርክት በመከፋፈል አደጋ ላይ መውደቅ የለበትም፡፡ ጥያቄው መሆን ያለበት አሁን ካለንበት ተነስትን እንደ አገርም እንደሕዝብም እንዴት መቀጠል አለብን ነው እንጂ እንዴት ወደኅላ እንጎተት ሊሆን አይገባም፡ በጽሞና ካዪነው ባለንበት በዚህ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ለማደግ እና ድህነትንም ለማሽነፍ እንደ አገር እና እንደ ሕዝብ በአንድ ላይ ከመቆም ሌላ የተሻለ አማራጭ የለንም፡፡ 

አሁን ከሚካሄደው የኦሮሙማ ፕሮጀክት ተጠቃሚው ማነው?  

አዲስ አበባ ላይም ሆነ፤ ሽገር ከተማ ለመስራት ባፈረሱት የድሆች መኖሪያ ቤቶችእና የእምነት ተቋማት፤ ተጠቃሚው በኦሮሞ ሕዝብ የሚነግድ ጽንፈኞች ብቻ ናቸው፡ በየጊዜውም ከሚያፈናቀሉት፤ ከሚያፍኑትና ከሚገደሉት ሕዝብ ባአጠቃላይ አሁን እየተገበረ ባለው የኦሮሙማ ፕሮጀት ከኦሮሞ ጽንፈኞች ገዚአዊ ጥቅም በስተቀር ሌላው የህብረተሰብ ክፍል የኦሮሞ ሕዝብንም ጨምሮ ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌላው ሰላምና እድገት የሚፍለግ ኢትዮጲያዊ ሁሉ በአንድነት በመቆም ይህን የጽንፈኞች ቡድን በቃ ሊለው ይገባል፡፡ 

እሬሳ በአደባባይ ተጎትቶ ሲሰቀል ድምጳችንን ከፍ አርገን ሁላችንም ለፍትሕ ቆመን ቢሆንና መንግስትን ተጠያቂ አርገን ቢሆን አሁን የደረስንበት ባልደርስን ነበር፡፡ አሁንም የኦሮሙማን ፕሮጀክት መታገል አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ በመሆኑና ለኦሮሞውም፤ ለአማራውም፤ ለጉራጌውም፤ ለትግሬውም፤ ለሁሉም ኢትዪጲያዊ በሙሉ የሚአዋጣ ስላልሆነ ተባብረን ልናስቆመው ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን መጭው ጊዜ አስፈሪ እና አሳዛኝ መሆኑን ከወዲሁ ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል፡፡ 

ካክብሮት ጋር 

ሺመልስ

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here