spot_img
Wednesday, October 4, 2023
Homeነፃ አስተያየትወደብ ፡- አዲሱ የአማራ ምሁራን ማጃጃያ ቁማር!

ወደብ ፡- አዲሱ የአማራ ምሁራን ማጃጃያ ቁማር!

advertisement

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

በመላእክትነት ተመርጦ የነበረው ሳጥናኤል እግዚአብሔርን ከድቶና ክርስቶስን ወደ ተራራ ወስዶ ከተማ እያሳዬ በንብረት ሊደልለው ሞከረ፡፡ የሳጥናኤል ተከታዮች ደግሞ ከዓለም በፊት እግዚአብሔርን እያመለከ የኖረውን አማራ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ ወዘተርፈ በሚሉ የቁማር ካርታዎች ሲያታልሉ ኖሩ፡፡  አማራ ክርስቶስን ስላለሆነ  ተታለለ፡፡

በቁማር መጫዋቻ ካርታ መደለሉ የሰለቸው አማራ ራሱን ለማዳን መሰባሰብ ሲጀምር ደሞ እንደተለመደው ወደብ የሚል የቁማር ካርታ ይዘው ብቅ አሉ፡፡

ሳጥናኤል አዙሮ የሚያይበት አንገትና ይሉኝታ እንደሌለው ሁሉ ተከታዮዎቹም ትናንት የሰሩትን ዞር ብለው የሚያዩበት አንገት፣ እንደ አቡጀዲ የሸረከኩትን ውሽት የሚያፍሩበት ህሊናና ይሉኝታ የሳጥናኤል ያህል እንኳ የላቸውም፡፡

አማራ የኢትዮጵያ ግዛት ከራስ ካሳ እስከ ሞያሌ፤ የባህረ ነጋሽ ሰዎችም ወንድምና እህቶታችችን ናቸው ሲል እነዚህ የሳጥናኤል ተከታዮች ኢትዮጵያ የባህረ ነጋሽ ቅኝ ገዥ፣ ሰዎቹም የተለዩ ስለሆኑ ይገንጠሉ ብለው ያሳደገቻቸውን ኢትዮጵያን ከአስራ ሰባት ዓመታት በላይ ወጉ፡፡  አማራ ሕዝባችንን አትከፋፍሉ አገሪቱንም ወደብ አልባ አታድርጉ ሲል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን በከንቱ በማስጨርገድ ወደብ አልባ አድርገውና ከዓለም በፊትም ኢትዮጵያ ወደብ አልባ እንድትሆን ድምጥ ሰጥተው የሚያሳፍር ወራዳ ሥራ በታሪክ ማህደር ጣፉ፡፡ 

ዛሬም እንደ ወትሮው አዙሮ የሚያዩበት አንገትና ሊያፍሩ የሚችሉበት ህሊና ወይም ይሉኝታ ስለሌላቸው ወደብ የምትል ማታለያ ቁማር ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ዳሩ ዛሬም በዚህ የሳጥናኤል ተከታዮች  ቁማር እንደገና ተጠልፎ የሚወደቅ  የአማራ ምሁር የእንግዴህ ልጅ ያጣሉ አይባልም፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ በሚሉ ይሁዳዊ ሰባኪያን የተንዘላዘሉና የተከንከረፈፉ ጁላጅል ምሁራን በወደብ ስብከትም እንደ ገለባ ተጠርገው የአማራን ሕዝብ ማሳሳቱን አይቀጥሉም አይባልም፡፡ 

መጃጃል የማይሰለቻችሁ ምሁራን ሆይ! የወቅቱ የአማራ ጥያቄ ወደብ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ጅኒጃንካ የሚል ድስኩር ሳይሆን የህልውናና በአገር ሰርቶ የመኖር ጥያቄ ብቻ ነው፡፡ አማራ ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ንብረቱንም ሆነ መንፈሱን ማዋል ያለበት ለራሱ ህልውና ብቻ ነው፡፡ አማራ እንደ ማርያም ጠላት በሚዋከብበት በዚህ ክፉ ዘመን የራሱ ልጅ እየተራበ ሌላውን አጎርሳለሁ የሚል፣ የራሱ እያረረበት የሌላውን የሚያማስል የእንግዴህ ልጅ ነው፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ እያሉ የአማራ ምሁራንን ሲያጃጅሉ የኖሩት ቁማርተኞች ዛሬ ደሞ ወደብ የሚባል የካርታ ጨዋታ የጀመሩት እንደዚህ ዓይነቱን የእንግዴህ ልጅ ሙልጭ አድርገው ቁማር ለመብላት ነው፡፡

ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/06/Abay.pdf

ፈንድ ፈንዳጅ ዲያስጶራ እባክህ ስማ! ለዘራፊዎች የማይነጥፍ ጥገት መሆንህ ይብቃ!   ቦንድ ቦንዳጅና ፈንድ ፈንዳጅ.docx (ethiopatriots.com)

ሰኔ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,733FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here