spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeነፃ አስተያየትይድረስ ለትግራይ ህዝብ (ዳን ታደሰ )

ይድረስ ለትግራይ ህዝብ (ዳን ታደሰ )

People in Tigray
ፎቶ ምንጭ ፡ የትግራይ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን

ከዳን ታደሰ

የዚህ ጽሁፍ አላማ የትግራይ ምሁራን ጳጳሶች ካድሬዎችና ወጣቶች ቆም ብለው እራሳቸውን እንዲመረምሩ ለመኮርኮር ነው። እውነት አንዳንዴ መራር ነውና ብዙ ሰዎችን ሊያስቆጣ ይችላል። አለባብሼ በዙሪያ ጥምጥም ከመ ዞር ቀጥተኛውን መርጫለሁ። ይቅርታ ካስቀየምኩ። 

የኢትዮጵያ ችግር ሊፈታ የሚችለው የትግራይ ፓለቲከኞች ስለ አማራ የሚባለው መሀበረሰብ ያላቸው ግንዛቤ ሲቀየር ነው። ተታሎም የሰቆጣ፣ ጉግና፣ ጠገዴአካባቢ ከብት ሲጠብቁ ወጣቶች ከህወሀት ጋር ተቀላቅለው ባይታገሉ፣ ሌላውም የአማራ ህዝብ ከደርግ ይሻላሉ ብሎ ባያበላ፣ ባያክም ባያስጠልል ኖሮ አማራን ተሻግሮ ህወሓት አድስ አበባ ባልገባ ነበር። 

ይሁንናብ አብሮ ታግሎ ለስልጣን ያበቃን የአማራ ህዝብ ህወሓት ስልጣን ከያዘ ቦሀላ ከስልጣን አባረርነው፣ አከርካሪውን ሰብረናል፣ ዳግም እንዳይነሳ ቀብረነዋል ብለው ነበር። በጥላቻሽቅስቀሳም ህዝብ እያነሳሳም፣ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በወተር፣ በጉራ ፈርዳ፣ ደሀ ገበሬዎችን አሳረደ። ከጠገዴ፣ ከሁመራብደግሞ ዘር ማጥፋትና ማፈናቀል ስራው ሆነ። እነ ቴዎድሮስ አድሀኖም ደግሞ የአማራ ወጣቶች ዘር እንዳይተኩ እያታለሉና እያስገደዱ ቋሚ የወሊድ ምቆጣጠርያ በትምህርት ቤት በልጅች ክንድ ላይ ተከሉ። 

አማራን መስደብ፣ ማፈናቀል፣ መግደል እና ዘር እንዳይተካ ማድረግ የትግራይን ህዝብ እንዴት ሊጠቅም እንደሚችል የገባው የለም። ከዛም የህወሀት ጸረ አማራ ፓሊሲ ከስልጣን ሲባረርና ስልጣኑን እነሱ ያሳደጓቸው የኦፒዲኦ ካድሬዎች እነ ኮ/ል አብይ አህመድ፣ ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ፣ እነ ጄ/ል ይልማ መርዳሳ፣ ኮምንደር ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሪፓብሊካን ሰራዊት አዛዥ ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ፣ የስለላው ኢንሳ ዳንኤል ጉታ እና ሌሎችም የኦፒዲኦ ካድሬዎች አለቆቻችውን አብረው ስልጣን የስሙ ቢሆንም የህወሀት መሪዎችና ደጋፊዎች አንደኛ ጠላት አድርገው የጥላቻ ዘመቻ የከፈቱት በአማራ ህዝብ ላይ ነውና። 

አማራን ፎጣ ለባሽ፣ ሂሳብ እናወራርዳለን ብሎ ሰራዊት ጸረ አማራ የሆነ የፌዴራሊስት ሀይል ፈጥሮ አማራውን የማዋረድና የማጥፋት ዘመቻውን ቀጠለ። ከዛም አማራን ወሮ ንብረት እየዘረፈ እናቶችን እየደፈረ ረግጦ ለመግዛት ሞክረ። ይህ ጥዋው ሞልቶ እንዲፈርስ አደረገ። 

አሁን በአማራ ላይ እንደድሮ ከበሮ እየደለቁ ተረማምዶ የሸዋን ስልጣን መቆጣጠር ቀርቶ መንቀሳቀስም የማያስችል ግንብ ተፈጠረ። እኛ አንድ ነን ወንድማማች ነን የሚለው ስነቦና ከአማራው ውፕጣት ልብ ሸርሽሮ እነሱ ተፈጠረ። ይህ ለ50 አመት የተነዛው አማራን የመጥላት ዘመቻ መነሻው ምንድነው? የትግራይ ህዝብ ከአማራ መጥፋት ምን ይጠቀማል የሚለውን እንወያያለን። 

ለመሆኑ የአማራ ህዝብ የትግራን ህዝብ የበደለው ነገር ይኖር ይሆን? 

ከአንድ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከሆነ ወዳጄ ደውሎ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል፣ ለማዳከም ከዛም ለማጥፋት የሚደረገው ሴራ እየከረረ መምጣቱን አጫወተኝ። ይህ ሰው በትውዱ የቱለማ/ሸዋ/ ኦርቶዶክስ መምህር ነው። ይሁንና በደብረጽዬን እና በሽመልስ የሚመራው ጵጵስና የኢትዮጵያን ክርስቲኖች በመፋፈል የብሄር ፓለቲካ አገልጋይ ሊያደርጉት ወስነዋል። ይሁንና የትግራይ  ፓለቲከኞች በጥላቻ ከመነዳት ይልቅ ለትግራይ ህዝብ ምን ይጠቅመዋል ብለው መጠየቅ ለምን ተሳናቸው አለኝ? የዚህ ጽሁፍ መነሻ ይህ ነው። 

እነ ሽመልስ የትግራይና የአማራ ዲያቆን፣ ቄስና ጳጳስ ከክልላችን ይባረር፣ ወደ ክልል ሁላችንም ሁለተኛ እንዳይመጣ ብለው ነው ዘመቻ የጀመሩት። ሁለተኛም እንዳይመደብብን የሚሉትን አዎ ትክክል ነው የትግራይ ቄስ ከትግራይ መውጣት የለበትም የሚሉ ጳጳሶች የኦፒዲኦ አጫፋሪ ሆነው ብቅ አሉ። ይህ ለትግራይ መከራ እና ችግር ውጪ እንደሚያመጣ ጥቅም ይኖር ይሆን? 

ይህ ስህተት ተደጋገመ። ህወሀቶች ድግስ ያለ ይመስል የትግራይን ሚኒስትሮች፣ የፓርላማ አባሎች፣ ወታደሮች፣ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ጡረተኞች ሳይቀሩ ጦርነቱን ከመጀመራችው በፊት ወትውተው አስፈራርተው ከመላው ሀገሪቷ ጥለው እንዲወጣ አደረጉ። ፓርላማ ውስጥ እንኳን ይጮሁ የነበሩ ጥለው ሲሄዱ ብልጽግና መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ ብሎ የብሄረሰቡን ስም ሳይቀር ቀይሮ፣ ጁንታ ብሎ በሙሉ ድምጽ ሽብርተኛ ብሎ ፈርጆ አወደመው?_

“አኩራፊ ልጅ ምሳው እራቱ ሆነ”። በዚህ ፓሊሲ ምክንያትሽ የትግራይ ወጣት አለቀ፣ እግሩን እጁ ተቆረጠ አይኑ ጠፋ፣ በችጋርና በመድሀኒት እጦት ረገፈ። ይህ ሁሉ ካደረጉ ቦሀላ ዛሬ እነ ጌታቸው እንደ ሳሎን ቡችላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየምርቃቱ ይዟቸው የሚሄድና የነበራቸውን ቦታና ንብረት ለማስመለስ ደጅ የሚጠኑ ተለማማጮች ሆኑ። 

የደብረጽዮንና የሽመልስ ሴራ ከተሳካ የትግራይ ድህነትህ ምንጭ ተዋህዶ እምነትህ ነውና የብልጽግና መጽሀፍ ቅዱስ ተቀበል መባሉ አይቀርም። የብልጽና ጎስፔል በምንም መመዘኛ ሀዋርያቱ ያስተማሩት ክርስትና አይደለም። በ1950ዎ አንድ Granville Oral Roberts  በተባለ አሜሪካዊ ሰባኪ የተፈጠረ ሀይማኖት ነው። 

የእምነቱ መሰረት አንድ ሰው እንዴት ገነትን ይወርሳል ሳይሆን እንዴት ሀብታም እንደሚሆን የሚያስተምር ነው። የጤናና የሀብት ሀይማኖት (Wealth & Health Gospel) ይሉታል። ይህ ሀይማኖት ለመስራቹ 117 ሚሊዮን በላይ እንዲያከማች ያደረገ ሲሆን እንደ ጠንቋይ ቤት ለኔ አንድ እጅ ከሰጠህ 7 እጥፍ እግዚአብሔር ይሰጥሀል የሚል አስተምህሮ ነው። ካፒታሊዝም ሁሉን ገንዘብ አፍቃሪ ስላደረገው የብልጽግና መጽሀፍ ቅዱስ ዛሬ በአሜሪካ ውስጥ ትልቁ ተከታይ ያለው የአምልኮ ስርአት ነው። 

ወደኛ ጉዳይ ስንመለስ የፓለቲከኞቹ እና የስልጣን ፈላጊዎች ጥምረት ደግሞ “ሃይማኖትን የተቆጣጠረ ህዝብን መቆጣጠር ይችላል ብለው ዶ/ር አብይ ጽፎታል። ስለዚህ ሃይማኖትን መቆጣጠር የሚፈልጉት እኛን ለማጽደቅ ሳይሆን ታዛዥ እንድንሆን ነው። በፋና ቴሌቭዥን አልገባ ያለውን አርብ አርብ በጁማ፣ እሁድ እሁድ ደግሞ በቤተክርስትያን ጉባኤ ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ ተገዙ እንዲሉን ነው። 

ታድያ ይህ ግልጽ የሆነ ፈተና እያለ የትግራይ ጳጳሳት ምን ጠብ ሊልላቸው ይሆን ለዚህ ተባባሪ የሆኑት ብዬ እራሴን ጠየቅኩ። ይህ መልስ ሳይሆን ሌላ ጥያቄ ጫረብኝ። ይሄም 

፩ኛ ምን ጠብ ሊልላቸው ነው ኤርትራን የኢትዮጵያ/ ትግራይ ቅኝ ግዛት ነች ብለው መስዋዕትነት ከፍለው አስገነጠሉ?  ፪ኛ የብሄር ፓለቲካው በማምጣታቸው ለትግራይ ህዝብ መከራ እንጂ ምን ጠብ አለለት የሚሉ ጥያቄዎች መጣብኝ። 

ይሄንን ሳሰላስል ምናልባት አማራ የሰራውን ነገር ሁሉ ማፍረስ ለትግራይ ይጠቅማል የሚል ትርክት ለ50 አመት ስለተረጨ መሰለኝ። ምናልባት ይህም ወደ ጭፍን ጥላቻ አድጎ ይሆን?  

እስቲ እንፈትሸው 

ኦርቶዶክስ በመከፋፈል የብልጽግናን እምነትን በመቀበል ደሀው ህዝብ ብልጽግናንም ሳያይ ገነትም ሳይገባ ሁለት ሞት ይሞታል። ምክንያቱም በማቲዮስ 4:8-10 እንደተጻፈው “8 ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ። 9ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።10 ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው። ይህ ጥቅስ የሚያስተምረን ለሰይጣን ከሰገድንለት የአለምን ሀብና ሞገስ ሊሰጠን እንደሚችል ነው። ይሁንና ይህ ቃብድ ነፍሳችንን ወደ ገሀነም ይዞ ለመውረድ ነው። አብይ አህመድ መጀመሪያ ቤተ መንግስት ሲገባ በሩ ላይ ያቆመው መስቀል ሳይሆን የጠንቋዬች ወፍ ፒኮክን ነው። ፒኮክ የሰይጣን አይን መከላከያ ነች ተብሎ ይታመናል። peacock and evil eye ብሎ ማንም ጉግል ቢያደርግ ስለ ፒኮክ የጥንቆላ አገልግሎት መረዳት ይችላል። አብይ የክርስቶስ ተከታይ አይደለም ይልቁንም በማቲዎስ 4:8-10  እንደተገለጸው ሀብትና ኃይልን በምድር መስጠት የሚችለው ሰይጣን ተከታይ ነው። 

ታድያ የዚህ የሰይጣን አምልኮ አስፈጻሚ ሆነው ጥቁር የሚለብሱት መስቀል የሚይዙት የሚጦሙትና ሰአታት የሚቆሙት ጳጳሳት ለምን የራሳቸውን እምነት የሚያጠፋና የወንጌልን ቃል በኦሬምያና በሌሎች ክልሎች መስበክ የሚያግደውን የሽመልስን እና የሳሪዎስን እቅድ ለማስፈጸም ፈለጉ ካልን ያው የተቀበረው የአማራ ጥላቻ ነው። በርካታ የህወሀት ደቀ መዝሙር አማራን ከመቶ 10 እጅ የሚጎዳና ትግራይን 90 በመቶ የሚጎዳ ከሆነ መርዙን ይጠጡታል። ይህ ነው ኤርትራን ለማስገንጠል ኢትዬጵያን በመከፋፈል የገፋፋቸው። 

ወደ ስልክ ጭውውቴ ስመለስ ይህ መምህር የልቡን ቅንነትና ለክርስቶስ ያለውን ፍቅር ስለማውቅ በርታ ወንድሜ ብዬ ስልኩን ዘጋሁ። ይህ ትልቅ የሀይማኖት መምህር ክርስቶስን ትቶ በሽመልስ አብዲሳን ቢከተል ባለ ሀብትና ዝና በቀላላሉ ይሆን ነበር። ሰይጣን ክርስቶስ ብትሰግድልኝ ይህንን ሁሉ ሀብት እሰጥሀለሁ እንዳለው እነ ሽመልስና አብይ ጳጳስ አድርገው፣ ቪላ፣ ፎቅ፣ መኪና ሰጥተው አጃቢ መድበው ጳጳስ ሊያድርጉት የሚያስችል እውቀትና መከበር ያለው አስተማሪን ነው። በአማርኛ፣ በግዕዝ፣ በኦሮምኛ፣ በእንግሊዘኛ የሚጽፍ የሚያስተምር የዘመናዊውንም የሀይማኖታዊ ትምህርቱንም ያጠናቀቀ ነው። ይሄንን የሀይማኖት እንጂ ለብሄሩብ አልገዛም ስላለ ተሳዳጅ ሆንዋል። ታድያ የትግራዮቹ ጳጳሶች የክርስቶስ አንድነት ሳይሆን የነ ደብረጽዮንና የሽመልስን ልዩነት አራማጅ ለመሆን መረጡ? ከዚህ ተግባራቸው የትግራይ ህዝብና ቄስ ምን ይጠቀማል?

የዚህ ጽሁፍ አላማ የትግራይ ምሁራን ጳጳሶች ካድሬዎችና ወጣቶች ቆም ብለው እርሳቸውን እንዲመረምሩ ለመኮርኮር ነው። እውነት አንዳንዴ መራር ነውና ብዙ ሰዎችን ሊያስቆጣ ይችላል። አለባብሼ በዙሪያ ጥምጥም ከማስረዳት ቀጥተኛውን መርጫለሁ። ይቅርታ ካስቀየምኩ። 

ጥያቄ አንድ ለምንድነው የትግራይ ሊህቃን የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ነገር እየፈለፈሉ የሚተገብሩት? ምንድነው የስነቦና ቀውሱ መሰረት ብለን ከጠየቅን አማራ የሚባል ጭራህ ህወሓት ፈጥሯል። ስለዚህ 10 በመቶ አማራን የሚጎዳ ከሆነ የትግራይ እሊቶች 90 በመቶ የሚሆነውን መርዝ ለመጠጣት አይፈሩም። ለዚህ ምሳሌ ኤርትራን የኢትዮጵያ ቅኝ ናት ብለው የራሳቸውን አዱሊስ፣ ዶጋሊ፣ ሰቲት አስመራ ምጽዋ ኢትዮጵያ በቅኝ የያዘችው ምድር ነው ብለው አስር ሺህ ህይወት ከፍለው ለተባበሩት መንግስታት መማጸኛ ደብዳ ድፈው ቀይ ክብርን ከትግራይ አሰጡ። እነ ፕሮፌሰር ገላውዲዎስ አርአያ፣ እነ ፕሮፌሰር ክንፈ፣ እነ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፣ ዶ/ር አለምሰገድ አባይ ይሄንን አዱሊስ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነው የሚለውን ባረኩ። ፣ 

ኢትዮጵያ 10% ቢያማትም ትግራይ ግን እ አመት 90% ስቃይ በደስታ ትቀበላለች። ከኤርትራ መገንጠል ወላይታ ኮንሶሶ አማራ ኦሮሞ ሳይሆን ትግራይ ነች 90 _በመቶውን መርዙን የጠጣችው። በአስመራ ሰርቶ ከብሮ ኢኮኖሚውን ተቆጣሮ የነበረው ባለሀብት ተባሮ በጃልሜዳ የላስቲክ ድንኳን ውስጥ ተኝቶ በርካታ እሬሳውን በየቀኑ መዘጋጃ ቤት ነው የቀበረው። ከአሰብ ምጽዋ የተባረረው የትግራይ ወዛደር ነው። ድንበሩን የተገፋው እስካሁንም በቦንብ የተወቀረው ራሱ የትግራይ ህዝብ ነው። አማራን እጎዳለሁ ብለው የጠጡት መርዝ እስካሁን እስካሁን ደም እያስቀመጣቸው ነው። 

ማሰብ የሚችል ትውልድ ከተፈጠረ ድግሞ ስህተቱ ሲገባው ለአንድ ሺ አመታት ያለቅሳል። የራስን መሬት የራስን ባህር በር ቅኝ ግዛት ነው ብሎ መስጠት ምን አይነት የሚያሳውር ጥላቻ እነ እሰዬ አብረን: ደብረጽዮንን፣ አስመራ ያደገውን ቴዎድሮስ አድሀኖምን: እነ ጻድቃንንና ይወቅሳል። ከዚህ ውስጥ መለስ ከኤርትራ በመወለዱ ለናቱ ሀገር ትግራይን መርዙን በማጠጣቱ ታሪክ እንደ ብልጥ መሪና ሰላይ ታሪክ ያከብረዋል። ሌሎቹ አማራን እጎዳለሁ ብለው መርዙን በመጋታቸው ታሪክ ደደቦች ብሎ ያቆያቸዋል። 

የትግራይ የእምዬ ምኒሊክን ጥላቻ 

ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ምኒሊክ ቅኝ ገዢን ተዋግት አስቁሙው የትግራይ ሰው ከመቀሌ እስከ ቶጎ ጫሌ፣ ከአክሱም እስከ ሞያሎ፣ ከዛላ አንበሳ እስከ ጋንቤላ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ ከብሮ እንዲኖር እድል በመክፈታቸው የትግራይ ህዝብ ምን ተጎዳ? ምስጋናው ይቅር ይሄንን ያህል የከረረ ጥላቻን ምን አመጣው? ኢትዮጵያ ያነሰች የጠበበች ብትሆን ኖሮ ትግራይ ምን ይጠቀማል? በጅቡቱ የሰፈረው ፈረንሳይ፣ በሀርጌሳና በኬንያና በደቡብ ሱዳን የከበበው እንግሊዝ፣ በመቃድሾ የነበረው የጣልያን ጦር ገፍቶ መጥቶ እዚህ ሸዋ ድረስ ቢያጠበው ኖሮ ትግራይ ትጠቀም ነበር? መጠቀሙ ይቅር ትግራይ ምን ተጎዳች? 

በእርግጥ ምኒሊክ እጁን አጣጥፎ ቢቀመጥ ኖሮ ዛሬ ደቡብ ክልል፣ ጋንቤላ፣ ሱማሌ፣ ሲዳማ፣ ኦሮምያ የሚባሉት ክልሎች ይኖሩ ነበር?  እንዴት ነው የትግራይ ፓለቲከኞች፣ ምሁራን እንዲህ ከድንጋይ የከበደ ድንቁርና የሰፈነባቸው? ምኒሊክ ፈጥኖ ባያስቆማቸው ኖሮ ዛሬ ነጻ ኬንያ፣ ነጻ ሱማሊያ ነጻ ደቡብ ሲዳንና ሰፊ ጅቡቲ እንጂ ሰፊ ኦሮምያ ይኖር ነበር? ፈረንሳይ፣ እንግሊዘኛና ጣልያንኛ የሚናገር ኦሮሞ፣ ደቡብ እንጂ አንድ የሆነ ኦሮሞ ይኖር ነበር። ምንሊክ ከቅኝ ገዥዎች ጋር ተናንቆ ሀገር ስላሰፋ የትግራይ ህዝብ ምን ተጎዳ? ይሄንን ሀገር በመከፋፈል በመበተን የትግራይ ህዝብ ምን ይጠቀማል? ፈረንጆቹ “ፍቅር አይን ስውር ነው” ይላሉ። የትግራይ ምሁራን ግን በጥላቻ ታውረው አማራን የግድ መስሏቸው ጸረ-የትግራይ ህዝብ የሆነ ፓሊሲ መተርጎም ብቻ ሳይሆን ህይወትም እየሰጡ ነው። ስለዚህ አማራን እጎዳለሁ ብለው ኢትዮጵያን በብሄር ከፋፍለው፣ የትግራይን ግዕዝ ፊደል እንዳይጠቀም አድርገው አደራጅተው አማራ እንዲገደል እንዲፈናቀል ካደረጉ ብሀላ በመጨረሻው የዘሩትን መርዝ አጨዱ። ያደራጁት ሀይል የብሄር ስማቸውን ቀይሮ ጁንታ ብሎ ሰብስቦ አሰራቸው፣ ንብረታቸውን ዘረፈ፣ ንግዳቸውን አከሰረ። ያ በጥጋብ ይኮፈስ የነበረ ባለሀብትና ካድሬ አፈር መስሎ በነጠላ ጫማ ሆኖ እጁን ወደ ሃላ እድርጎ አዲሶቹን ገዢዎቹን የሚለማመጥ፣ በራሱ ሀገር ላይ ይቅርታ ጠያቂ፣ መጤ፣ ተለማማጭ ሆነ። ለአማራ የተቀመመውን መርዝ እራሱ የትግራይ ህዝብ ተጋተው። 

ሶስተኛው ደግሞ የባህል ጭቆና በትግራይ ላይ ተጭኖ ይኖር የሚለው ጥያቄ ነው? 

ስታሊንናዊ አስተምህሮ እንዳለው የባህል ጭቆና ይሆን እንዴ ትግራይን ያስከፋው የሚለውን አሰላሰልኩ። በእርግጥ የትግራይ ሀይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ አልባሳት፣ ጽሁፍ፣ ቤተ እምነት ተደምስሶ በአማራ ታሪክ ተተክቶ ይሆን ብዬ አሰብኩኝ። ሁሉም ጨቋኞችና ቅኝ ገዢዎች ይሄንን ነው ያደረጉት። ይህ በመሆኑ አፍሪካውያን፣ የላቲን አአሜሪካ፣የኤዥያ ሰዎች በላቲን ነው የሚጽፏት በእንግሊዘንኛ፣ በፈረንሳ፣ በስፔንሽ ወይንም በፖርቹጋል ነው የሚግባቡት። ታድያ አማራ ያጠፋው የትግራይ ጽሁፍ፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖት፣ ልብስ፣ ምግብ፣ ከበሮ፣ ሹሩባ ይኖር ይሁን ብዬ አሰብኩ። አንድም አጣሁ። እንደውም ዳዊት የደገመ ዲያቆን ሁሉ የፍርድ ጸሀፊ እየተባለ ከትግራይ እየመጣ ጋሙ ጎፋ፣ ኢሊባቡር፣ ባሌ፣ ወለጋ እየተላከ ጠቦቱን እያረደ ብርዙን እየጠጣ ተከብሮ ተወዶ እንዲኖር ነው በር የከፈተለት። እነ ስብሀት ነጋ ሲዳሞ የትምህርት ቤት ዳይሬክተር ተደርጎ በመላክ ተጎዳ? አዲስ አበባ መጥቶ መለስ ጄኔራል ውንጌት ገብቶ አዳሪ ትምህርት ቤት በእንግሊዝ ማግኘት በመማሩ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ በመመደቡ ተጎዳ? 

የአክሱም ጥልፏንም፣ የእንደርታ ጭፈራውንም የተንቤን ሽለላውንም አክብሮ ገበያ ፈጥሮ ከትግራይ ተወላጅ ውጪ ያለው ሁሉ እንዲወደው እንዲጨፍርበት እንዲገለገልበት አማራ ማድረጉ ትግራይ ምን ተጎዳ? ደብተራውም ግዕዙንና ዳዊትን ይዞ በመላው ኢትዮጵያ አባቴ ይፍቱኝ የነፍስ አባት ይሁኑኝ እየተባለ እንዲከበር፣ እንዲወደው አማራ ማድረጉ ትግሬ ምን ተጎዳ? ታድያ የአማራ ገዢ መደብ የትግራይን ባህል ሁሉ አሻሽሎ አሳድጎ ዘመናዊ አድርጎ አስከበረው እንጂ ያጠፋው ነገር አለ? በቢሮክራሲው በፍርድ ስርአቱ በትምህርት ቤቱ በየቤተ እምነቱ አገልጋይ፣ አዛዥ አናዛዥ አደረገው እንጂ የጎዳው ነገር አለ? ባሌን እጎዳለሁ ብላሷን ራሷን በንጨት ወጋች እንደሚባለው ነገር ሆነ። 

የትግራይ ህዝብ አማራን እጎዳለሁ ብሎ እየጠጣ ያለው የትግራይ ፊደል የቆጠረ ለአጭር ግዜ ተጠቃሚ የሆነ፣ አማራን በማስጠላት እሱ የሚወስድ መስሎት መርዝ በጥብጦ በጥብጦ በመጨረሻው ጁንታ ተብሎ ራሱ ተጋታት። ጥላቻ እንደ ኤድስ ቫይረስ ተሸካሚውን ነው የሚችለው የሚባለው ለዚህ ነው። 

አማራን እጎዳለሁ ብሎ የአክሱም ስልጣኔ በር የሆነበረውን አዱሊስ፣ አሉላ አባነጋ የቆረቆረው አስመራ፣ የተዋጋበት ዶጋሊና ሰቲት ወደ ኢትዮጵያ በነ ጸሀፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ጥረት በመመለሱና ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤት በማድረጋቸው የትግራይ ህዝብ ምን ተጎዳ? አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በመላው ኢትዮጵያ በመስፋፋቱ የትግራይ ህዝብ የሚጎዳው ነገር ምን ይሆን? ሰፊ መሬት ሰፊ ሀገር በመኖሩ የትግራይ ሰው ሄዶ ሰርቶ ቅድስት እየኖረበት አይደለምን? 

በሌላ መንገድ ስናየው ደግሞ ማንም ትግራይ ሄዶ ሱቅ ከፍቶ እንኳን አልኖረም። ከገብሩ አስራት አባት በስተቀር በፈቃዱ ትግራይ ገብቶ ኑሮን ለማሸነፍ የገባ አማራ አላውቅም። በተቃራኒው የትግራይ ሰው የሌለበት የአማራ መንደር ከተማ ቀበሌ ያለ አይመስለኝም። ቡና ቤት፣ ጋራዥ፣ ወፍጮቤት፣ ትራንስፓርት፣ አስተማሪ፣ የፍርድ ቤት ጸሀፊ፣ በፍርድ ሸንጎ፣ አብዮት ጠባቂ፣ የቀበሌ ሊቀመንበር፣ ፓሊስ ወይንም ገበሬ የሌለበት ቦታ ያለ አይመስለኝም። ካለ አረ በኛ መንደር ትግሪኛ ተናጋሪ ሰው አይተን አናውቅም በሉኝ። ታድያ ይህ እውነታው ከሆነ የትግራይ ሊህቃን የአማራ ጥላቻ በማርክሲስታዊው ትንታኔ መደባዊ ጭቆና ብዝበዛ ምክንያት አይደለም። የአማራ ህዝብ ትግራይ እየሄደ ሀብት ንብረት ይዞ ቀጣሪ አዛዥ ሆኖ ቢሆን ኖሮ የመደብ ጥያቄ ይመስል ነበር። ይልቁንም ሀገር አስፍቶ ኑ ስሩ ክበሩ በማለቱ ምንድነው ሀጥያቱ? 

እንደውም የትግራይ ገዢ መደብ ከሸዋ ነገስታትና መኳንንት ጋር ተጋብቶ ተዋልዶ አብሮ ሲፈተፍት ነበር። ዳግማዊ ምኒልክም አጼ ኃይለስላሴም ሴት ልጆቻቸውን የሰጡት ለትግራይ ልኡሎች እንጂ ለመንዝ ገበሬ አልነበረም። ታድያ አብሮ ሲፈተፍት የነበረው የትግራይ ገዢ መደብ እንዴት ጸረ አማራ ሆኖ ተገኘ? ስለዚህ ጥላቻው መደባዊ ጭቆናና ብዝበዛ አይደለም ብለን እንደምድም። 

እነ መለስ ዜናዊ፣ እነ ደብረ ጽዮን፣ እነ ጻድቃን፣ እነ ፕሮፌሰር ገላውዲዎስ፣ እነ ሰዬ፣ እነ ስብሀት ነጋ፣ እነ አረጋሽ፣ እነ ገብሩ አስራት ሸዋ ሲገቡ ቱለማ፣ ኦሮሞ፣ አፋር ሱማሌ ሲዳማ ለምን በግዕዝ ትጽፋለህ ለምን የራስህን አትፈለስምም ብለው በአለም ቅኝ ገዢዌቹ እንግሊዝ ፊደል ጻፍ ብለው ቀስቅሰው ይሄው የትግራይ ልጅ ከአማራ ክልልና አዲስ አበባ ውጪ ተላላኪ እንኳን ሆኖ ለመቀጠር መስፈርቱን አያሟላም። ይህ ነው እንግዲህ ምክናታዊ ያልሆነ ጥላቻ። ይህ ፓሊሲ አማራ የሚባለውን ለመጉዳትና ለማግለል ነበር ይሁንና የትግራይ ሰው ላለፏት 27 እንደነበረው ጠመንጃ ደግኖ እያስፈራራ መሬት ወስዷል፣ የጨው ሀይቅ፣ የእርሻ ቦታ ወስዶ ነበር ይሁንና እራሱ ብዘራው ጥላቻ የጁንታ ሀብት ተብሎ ተዘርፎ ተከፋፈለ። 

ዛሬ አንድ የትግራይ ወጣት ሀዋሳ፣ ጅማ ወይንም አዳማ ላይ የፊዚክስ አስተማሪ ሆኖ መስጠት አይችልም። አሁንም ያለው እድል ጎንደር፣ ባህርዳር ወይንም ደብረ ብርሀን ነው የፊዚክስ አስተማሪ አድርጎ የሚቀጥረው። 

ህወሓት አማራን እጎዳለሁ ብሎ የትግራይን ህዝብ በህገመንግቱ ከትግራይ ውጪ እኩል ሰው ሆኖ እንዳይታይ እንዳይሰራ እንዳይንቀሳቀስ አደረገው። ትግራይ የግላችን ኢትዮጵያ የጋራችን ተብሎ የተጀመረው ብልጠት ጠልፎ ጣለ። 

ይሄው ስልጣን በተቀማ እለት በጅምላ ታሰረ። ንብረቱ ተቀማ። በራሱ ህገመንግስት ትግራይ አትበሉኝ ትግራዋይ ነኝ እያለ እንዳልተሞላቀቀና በየመሸታ ቤቱ ሽጉጥ እንዳልመዘዘ ቀን ሲጎልበት ህወሓት ያሳደጋቸው እነ አብይ፣ ሽመልስ አዳነች አቤቤ ጁንታ ብሎው እራሱ በመሰረተው ፓርላማ፣ እራሱ ባወጣው ህገመንግስ፣ እራሱ ባቋቋመው ዋልታ እና ፋና ቴሌቭዥን ተወግዞ ንብረቱ ተገፎ፣ ልብሱን በፌስታል አንጠልጥሎ በየቀበሌው እስር ቤት ታጎረ። የብሄር ጭቆና አለብኝ ብሎ የሸፈተው ያሽቃበጠው ህይወት የብሄር

ጭቆና ምን እንደሆነ አየ። ዛሬ እንደ ጌታቸው ረዳ የሳሎን ድንክ ቡችላ ሆኖ ይዘውት የሚዞሩት እሱም የጌታውን እግር እግር እየታከከ ወደላይ ወደላይ ጌታውን ፈቃድ የሚጠይቅ ሆነ። 

በተከበረባት አባቴ ይፍቱኝ፣ አባት ይሁኑብኝ ይባልባት የነበረችውን ኢትዮጵያን አፍርሶ እንደ ቡችላ እግር የሚታከክባት ፈቃድ የሚጠይቅ እስከ ዘላለሙ ህዳጣን የሆነባት ኢትዮጵያን ለመለስ፣ ለጌታቸው፣ ለጻድቃን፣ ለስብሀት፣ ለሰዬ፣ ለገላውዲዎስ፣ ለስታሊን፣ ለአሉላና ለትዎድሮስ ጸጋዬ ልጅች እና የልጅ ልጅ ባርነት አወረሰ። 

አሁን ደግሞ በአብይ ድጋፍ ጎንደሬንና ወሎዬ በቅኝ ይሰጠኛል ከዛ እያፈናቀሉ እያሰርኩ እየገረፍኩ እገዛለሁ ብሎ ይመኛል። አማራ እንደ ትግራይ ማንም አይምጣብኝ ብሎ አያውቅም ለዚህ ነው ዛሬም በሚሊዮን የሚቆጠር የትግራይ ሰው በአማራ ክልል በቢሮክራሱው፣ ብል ትምህርት ቤቱ፣ በንግዱ፣ ብፕትራንስፓርቱ በፍትህ ስርአቱ በኢንቨስትመንት እኩል ተሳታፊ ሆኖ ክብር የሚኖረው። አሁን ኦርቶዶስ ከትግሬ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ሲኖዶስ ገንጥዬ ጎንደርን በቅኝ ተሰጥቶኝ አፈናቅላለሁ የሚለው ቅዠት አማራን አስር በመቶ ይጎዳ ይሆናል ይሁንና መርዙን ዘጠና በመቶ የሚሆነውን የሚጠጣው የትግራይ ህዝብ ነው። 

ለዚህ ነው እባካችሁ ከአማራ ጥላቻ አልከበራችሁም አልተጠቀማችሁም። ።አሁን ያለው የአማራ ወጣት እናንተ የፈጠራችሁት ነው። የኔ ዘመን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለው ቁጥሩ መንምኖ መጥፊያው ላይ ነውና ከአማራው ጋር ስላም ፍጠሩ። ቢያንስ ቢያንስ አማራን እንጎዳለን ብላችሁ መርዝ አትጠጡ። 

ለትግራይ ህዝብ ያለው አማራው ነው። ስለዚህ እባካችሁ አስቡበት። አማራው ነቅቷል፣ ተደራጅቷል ታጥቋል። ለራሱ አያንስም። ስለዚህ ራሳችሁን መርምራችሁ ከአማራን ጥላቻ ተላቀቁ። 

የነ መለስ የነ ስብሀት የልጅ ልጆች ሲዳሞ ባሌ አያቶቻቸው ከየት ናችሁ ሳይባሉ ሀብት አፍርተው በግዕዝ እየጻፏ እንዳልተንቀባረሩ ዛሬ ጁንታ ተብለው ሀብታቸው የሚዘረፍ መብታቸው የሚገፈፍ ሆነ። ኢትዮጵያን ጥሎ ወይ አሜሪካ ተሰዶ ሬስቶራንት ውስጥ መታዘዝ ያለበለዚያም መኪና ነው የተከፈተላቸው እድል። ነገ ጅማ አጋሮ ጅጅጋ ጋንቤላ ሀገሬ ነው ስፕርቼ አርሼ እኖራለሁ የሚለው በር ተዘግቷል። የስብሀት ነጋ፣ የመለስ ዜናዊ፣ የአረጋዊ በርሄ፣ የስኡል፣ የስዩም መስፍን፣ የሙሴ፣ የጃማይካ እና የነጻ አውጪነት ትግል ቱሩፋቶች። 

አንዳንድ እንደነ ቴዎድሮስ ጸጋዬ የርዕዮት ሬዲዎ አዘጋጅ ገብቷቸው የህዋት ትግል ውጤት የትግራይን ህዝብ ለዘላለማዊ ህዳጣንነት ያጋለጠ ነው ይላሉ። የሚቀጥለው ትውልድ በ38 ወንበሩ ታዛዥ ሆኖ ይኖራል ያበለዚያም እነ ስብሀት ነጋ የጻፏትን ህገ ታግሎ በደሙ ይቀዳል እንጂ ሌላ ምርጫ የለውም። 

በክፍል ሁለት ለምን የትግራይ ሰዎች በተለይ ደግሞ ባለፏት 50 አመታት የተነሱ የትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ታጋዬች፣ መሪዎች፣ ምሁራን፣ ፓለቲከኞች፣ ካድሬዎች ባለሀብቶች ደግመው ደጋግመው የትግራይን ህዝብ የሚጎዳ ውሳኔንና ተግባርን ይፈጽማሉ ብዬንአሰብኩ። 

፩ኛ ለምን የትግራይ ሰዎች በተለይ ደግሞ ባለፏት 50 አመታት የተነሱ የትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ታጋዬች፣ መሪዎች፣ ምሁራን፣ ፓለቲከኞች፣ ካድሬዎች ባለሀብቶች ደግመው ደጋግመው የትግራይን ህዝብ የሚጎዳ ውሳኔንና ተግባርን ይፈጽማሉ ብዬንአሰብኩ። ከዛም የሀሳቤን መነሻ ርምርና የደረስኩበትን መደምደሚያ በእንግሊዘኛ ጻፍኩት። ልለጥፈው ስል ስንቱ እንግሊዘኛ ያነባል ብዬ እንደገና በአማርኛ ጻፍኩት። 

በዚህ ጽሁፍ አማራ የሚባለው መሀበረሰብም ሆነ ንጉሳዊ ስርአት በእርግጥ ትግራይን የሚጎዳ ነገር አድርጎ ይሆን የከረረ ጥላቻ በአማራ ላይ የተፈጠረው ብዬ ጠየቅኩ። ስንት የአማራ ባላባት አድዋ ገብቶ የትግራይን ቤተሰብ ጭሰኛ አድርጎት ይህንን መሬቱን ወስዶበት ይህንን ሱቅ ፋብሪካ በየ ከተማው ገብቶ በዝብዞ ከብሮበት ይሆን ብዬንአሰብኩኝ።

አድዋን፣ መቀሌን፣ አክሱምን በአይነ ህሊናዬ ቃኘሁ። አንድ የአማራ ነጋዴ ወይንም ገበሬ በትግራይ የለም። ከዛ የገብሩ አስራት አባት ትዝ አሉኝ። ገብሩ አስራት መለስን ሲቃወም የመለስ ካድሬዎች ይህ የሸማኔ ልጅም አባቱ ከጎጃም መጥተው በሽመና ይተዳደሩ እንደነበርያነገሩንር። የጉዳዩ መንስኤ የአባቱ ሸማኔነት ሳይሆን ንጹህ ትግሬ አይደለም የምትለውን መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር። 

ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በየጠቅላይ ግዛቱ ትምህርት ቤት ክፍተት የደሀ ልጅ የሀብታም፣ ብሄር፣ ሀይማኖት ሳይለዩ የጎበዘውን ሁሉ ሰአት እየሸለሙ አዳሪ ትምህርት ቤት አቋቁመው ፈረንጅ ለምነው በማስመጣት በዘመኑ ከአለም ተፎካካሪ የሆነ ዘመናዊ ትምህርት ሰጥተው ነበር ። ተማሪ ጎበዝና ሰንፍ እንጂ በብሄር በሀይማኖት በኢኮኖሚ አቅሙ በመሀበራዊ የኢኮኖሚ ደረጃ ተለይቶ ተገሎ አያውቅም። ከአድዋ ከመንግስት ሳባ ትምህርት ቤት ይሁን ከደንቢዶሎ ይሁን ማትሪኩን ያለፈ ጀነራል ውንጌት መጥቶ አልጋ ተሰጥቶት በፈረንጅ ሞግዚት ጤናው እየተጠበቀ የፈረንጅ ያበሻ በልቶ ስርአት እየሰራ ሲኒማ እያየ እፕስተምረዋል። 

በርትቶ ኮሌጅ የበጠስውንም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨስቲ ሙሉ ወጪው ተሸፍኖን እንደ እንግሊዝ የገዢ መደብ ልጆች ኮት፣ሸሚዝ ፣ ከረባት ተሰፍቶለት መክበር፣ መደነቅ፣ የተማረ ይግደለኝ እስከ ባል ይደርስ ነበር። ሲመረቅ አለቃ ሆኖ ተምድቦ በኖሩትና ለዘመን ባገለገሉ ባለስልጣኖች ላይ ተሾሞ አባቶቹ የሚሆኑት ብድግ እያሉ እንዲቀበሉት፣ እንዲታዘዙት መሀበራዊ ተቀባይነት እንዲ 

ከዛ ስታሊንናዊ አስተምህሮ እንዳለው የባህል ጭቆና ይሆን የሚለውን አሰላሰልኩ። በእርግጥ የትግራይ ሀይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ አልባሳት፣ ጽሁፍ፣ ቤተ እምነት ተደምስሶ በአማራ ታሪክ ተተክቶ ይሆን ብዬ አሰብኩኝ። ሁሉም ጨቋኞችና ቅኝ ገዢዎች ይሄንን ነው ያደረጉት። ይህ በመሆኑ አፍሪካውያን፣ የላቲን አአሜሪካ፣የኤዥያ ሰዎች ዛሬ በእንግሊዘንኛ ወይ በፈረንሳ ካልሆነም በስፔንሽና በፖርቹጋል ጽሁፍ ነው የሚጽፈው። ታድያ አማራ ያጠፋው የትግራይ ጽሁፍ፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖት፣ ልብስ፣ ምግብ፣ ከበሮ፣ ሹሩባ ይኖር ይሁን ብዬ አሰብኩ። አንድም አጣሁ። እንደውም ዳዊት የደገመ ዲያቆን ሁሉ የፍርድ ጸሀፊ እየተባለ ጋሙ ጎፋ ኢሊባቡር እየተላከ ጠቦቱን እያረደ ብርዝ እየጠጣ ተከብሮ ተወዶ እንዲኖር ነው ያደረገው። የአክሱም ጥልፏንም፣ የእንደርታ ጭፈራውንም የተንቤን ሽለላውንም አክብሮ ገበያ ፈጥሮ ከትግራይ ተወላጅ ውጪ ያለው ሁሉ እንዲወደው እንዲጨፍርበት እንዲገለገልበት ነው ያደረገው። ደብተራውም ግዕዙንና ዳዊትን ይዞ በመላው ኢትዮጵያ አባቴ ይፍቱኝ የነፍስ አባት ይሁኑኝ እየተባለ እንዲከበር፣ እንዲወደው ነው ያደረገው። ታድያ የአማራ ገዢ መደብ የትግራይን ባህል ሁሉ አሻሽሎ አሳድጎ ዘመናዊ አድርጎ አስከበረው እንጂ ያጠፋው ነገር አለ?  በቢሮክራሲው በፍርድ ስርአቱ በትምህርት ቤቱ በየቤተ እምነቱ አገልጋይ፣ አዛዥ አናዛዥ አደረገው እንጂ የጎዳው ነገር አለ? ባሌን እጎዳለሁ ብላሷን በንጨት ወጋች እንደሚባለው ነገር ሆነ።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here