
ክፍል አንድ፡
በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ – በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ
E-mail –→Debesso@gmail.com – አምስተርዳም (ሆላንድ) ሃምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም.
“ብሄረተኛነት እንደ እስስት በአካባቢው ያለውን ቀለም ይወስዳል” “Chameleon-like nationalism takes its color from its context1”
ይህንን ከላይ የገለጽኩትን አክራሪ ብሄረተኞች ሁልጊዜ እንደ እስስት ቀለማቸውን እየቀያየሩ ጠላቶቻቸውን በማታለል ባህሪ እንዳላቸው የገለጸው አንቶኒ እስሚዝ የሚባለውና ስለብሄረተኛነትና ብሄረተኞች በጻፋቸው በርካታ መጽሃፍቶቹ የሚታወቀው እንግሊዛዊ የአንትሮፓሎጂ ፕሮፌሰር ነው። ይህ ሰው አብዛኛውን ህይወቱን ስለብሄረትኛነት ጥናት በማድረግ በርካታ መጽሃፎችን ከጻፉት ጥቂት በዓለም ውስጥ እውቅ የተባሉ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሰው ነው። “ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞትም ኢትዮጵያዊ” እያለ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በተደጋጋሚ ያታለለው ዓቢይ አህመድም ሆነ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ” ነው በማለት ዓባይን ተሻግሮ የብአዴንን ካድሬዎች ቀልብ የሳበው፤ በመቀጠልም የኢትዮጵያን ህዝብ ይሁንታ ያገኘው ለማ መገርሳ ድርጊቶች የዚህ ከላይ የጠቀስኩትን የአክራሪ ብሄረተኞችን ከፍተኛ የሆነ የአስመሳይነትና የአጭበርባሪነት ባህርይዎች የሚመሰክሩ ናቸው።
ባለፉት 32 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስታዊ ሥርዓትነት የተቋቋመው ትግራዋይነትን (የትግራይን የበላይነት፤ የትግሬዎችን ልዩ ባለመብትነት፤ ልዩ የታሪክ፤ የባህል፤ የእውቀት፤ የጀግንነት፤ወዘተ ባለቤትነት ይሰብክ የነበረ የአፓርታይድ አገዛዝ)፤ ባለፉት 5 ዓመታት ትግራዋይነትን ተክቶ ሥልጣን የተቆናጠጠው ኦሮሙማ የተባለው አቻው (የኦሮሞን ነገድ ተወላጆች የበላይነት የሚሰብክ የአፓርታይድ ሥርዓት) ፋሽስታዊ የሆነ መንግስታዊ ሥርዓት ነው ብዬ ስሟገት ቆይቻለሁኝ። በዚህ ጽሁፌ የፋሽዝም መሰረት ስለሆነው የሶሻል ዳርዊኒስት አስተሳሰብና በዚህ አስተሳሰብ የሚመሩ ፋሽስቶች በምንም ዓይነት በድርድር እንደማያምኑ አሳያለሁኝ። እንዲያውም ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አታለውና አጃጅለው የሚያጠፉበት ዓይነተኛ መሳሪያቸው እንደሆነ ለማሳየትና ለማመልከት እሞክራለሁኝ።
ሙሉውን ከፒዲኤፍ ፍይል ያንብቡ አዚህ አለ። ከኦሮሙማው የፋሽስት መንግሥት ጋር ድርድር አይሞከር፤ ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አዘናግቶ ማጥፊያ መሳሪያ ነውና!!!!!!
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ