
ከኦሮሙማው የፋሽስት መንግሥት ጋር ድርድር አይሞከር፤ ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አዘናግቶ ማጥፊያ መሳሪያ ነውና!!!!!!
ክፍል ሁለት።
በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ – በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ
E-mail –àDebesso@gmail.com – አምስተርዳም (ሆላንድ) ሃምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም.
ፋሽስቶች ያሉትን ሁሉ በጭፍንነት የሚያደርጉ ናቸው – የዶ/ር ዲማ ነገዎ ንግግርና የእሱ ትንቢትና ምኞት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ መሆኑ።
ዓቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ እንደወጣ በህገወጥ መንገድ አቶ ታከለ ኡማ የተባለ አንድ በዘረኝነት አስተሳሰብ የሰከረ የኦሮሙማን ፓለቲካ በቅጡ ሊያስፈጽም የሚችል የኦሮሞ ካድሬ በከንቲባነት ሾመ። ታከለ ኡማ ከተነሳ በኋላ ደግሞ የኦሮሙማው መንግሥት ወ/ሮ አዳነች አበቤ የተባለችውን የኦህዴድ ካድሬ ከንቲባ በማድረግ የአዲስ አበባን ከተማ የህዝብ ስብጥር ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የመቀየር እቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ። እነዚህ ሁለት ከንቲባዎችና በስራቸው ያሰለፏቸው የኦሮሙማ ፋሽስታዊ ፓለቲካ አራማጆች ባለፉት አምስት ዓመታት የፈጸሟቸው ድርጊቶች፤ የተገበሯቸው ዘረኛ ፓሊሲዎች በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባሉ ከተሞችና ክፍለ ከተማዎች ዛሬም የቀጠለው የዘር የማጽዳት ድርጊት (በሱሉልታ፤ ሰበታ፤ አቃቂ፤ ቦሌ ቡልቡላ፤ ለገጣፎ፤ አሁን ደግሞ ሸገር ብለው በሰየሙት የአዲስ አበባ ክፍል ወዘተ) ከዚሁ የፋሽስታዊ አገዛዝ መሰረት ከሆነው የሶሻል ዳርዊኒስት አስተሳሰብ የሚነሳ ነው። እነ ሀጂ ጀዋር መሃመድ ዓቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ በወጣ ማግስት ሃሮምሳ ኦሮሚያ[1] (Resurgence of a Dominant Oromo Nationalism and Consciousness) በሚል ሥም በአዲስ አበባ ያሉትን የኦሮሞ ተወላጆች በዜግነት ሳይሆን በአዲስ የኦሮሞን የበላይነት፤ የኦሮሞን ልዕለ-ሰብዕና የሚሰብክ ፋሽስታዊ አስተሳሰብና አመለካከት በመቅረጽ (super-man status of Oromos) ያከናወኑት ሰፊ የሆነ የፓለቲካ
[1] – ይህ ሃሮምሳ ኦሮሚያ[1] (Resurgence of a Dominant Oromo Nationalism and Consciousness) የሚለው ፕሮጄክት ፋሽስቶች ተከታዮቻቸውን አዲስና አንድ ወጥ በሆነ አመለካከት ቀድሞ አንድ ህዝብ ከሚታወቅበት እሴቶች የተፋታ፤ አዲስ ፋሽስታዊ ሥነምግባር ያለው ከራሱ ነገድ ውጭ ያሉ ህዝቦችን በጠላትነት፤ በአጥፊነት፤ በመጤነት፤ በጥገኛነት(parasitic) እንዲያይና እንዲጠላ፤ እንዲያጠፋ የሚያደርግ ሂትለራዊ እንቅስቃሴ ነው። የዚህ አዲስ ፋሽስታዊና አክራሪ የኦሮሞ ብሄረተኛነት እንቅስቃሴ ውጤት የሆኑት የአዲሱ የኦሮሞ ትውልድ ተወላጆች በወለጋ በአማሮች ላይ፤ በሸገር በአማራ፤ በጉራጌና ሌሎች የደቡብ ተወላጆች ላይ የሚፈጽሟቸው ኢ-ግብረገባዊ ድርጊቶች ሃሮምሳ ኦሮሚያ የሚባለው ፋሽስታዊ የአይምሮ-አጠባ (brainwashing project) ለፈጸማቸው የፕሮፓጋንዳ ስራዎች ምሥክር ናቸው።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ፋሽስቶች ያሉትን ሁሉ በጭፍንነት የሚያደርጉ ናቸው ፤ የዶክተር ዲማ ነገዎ ንግግርና የእሱ ትንቢትና ምኞት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ መሆኑ። (1)
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ