spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeነፃ አስተያየትለምን እና እንዴት የፋኖ ንቅናቄ በአጭር ቀን ውስጥ 54 ከተሞች መቆጣጠር ቻለ? 

ለምን እና እንዴት የፋኖ ንቅናቄ በአጭር ቀን ውስጥ 54 ከተሞች መቆጣጠር ቻለ? 

የፋኖ ተዋጊዎች ( ማህበራዊ ሚዲያ)

ከEthio2023a

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፈረንጆቹ እንደሚሉት በሳሎን ዝሆኑ ቆሞ ሳለ ማንም አያይታየውም ይላሉ። በአለፈው ሳምንት ይህንን ያህል ታጣቂ ያሳተፈ እንደ ባህርዳር፤ ጎንደር፤ ደብረማርቆስ ፣ላሊበላና ደብረ ብርሀን ያሉ ከተሞች እና 54 መካከለኛ ከተሞችን በፍጥነት ወሮ ተቆጣጥሮ እስርቤት ሰብሮ መሳሪያ ማርኮ የሚወጣ ሀይል በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ተብለው ቢነገራቸው የብልጽና ሰዋች ሆዳቸውን ይዘው ይስቁ ነበር።

አዲሱ ትውልድ እነደቀደመው ማውራት ሳይሆን መስራት በማስቀደሙ ሁሉንም ያስገረመ ውጤት አሳይቷል።  

የፋኖ አላማው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት፤ ማፈናቀል፤ ግድያ፤ዝርፍያና አፈና ለማስቆም ነው።  እነዚህ ጥያቄዋች በህዝብ ድምጽ፤ እንባ፤ ሰልፍና በጽሁፍ ተጠይቀው ነበር ይሁንና ስልጣን ላይ ያሉ ህዝብ ሲያለቅሱ ሶፍት ስጡዋቸው፤ ተገደልን ሲሉ ችግር የለም ችግኝ ይተከልባችሁል፤ ሰላም አጣን ተጠቃን ሲሉ የቀበሌ ሮንድ አይደለሁም የሚል የንቀት ምላሽ ነበር የሚሰጠው። 

ስለዚህ ይህንን ማስቆም የሚቻለው ሶፍት በመግዛት ወይንም በፌስ ቡክ ሻማ በማብራት ሳልሆን ልገልህ እየመጣሁ ነው የሚለውን ናና ሞክረኝ በማለት ብቻ ነው።  ስለዚህ ሁሉም በየመንደሩ እየተደራጀ እራሱን፤ ቤቱን ሚስቱን ቀበሌውን አካባቢውን ለመጠበቅ ተሰባሰበ፤ ተደራጀ ታጠቀ ስምምነት ፈጠረ። 

የፋኖን ህዝባዊ ሀይል ልዩ የሚያደርገው እንደ ቀድሞ ፖለቲከኞች በማስፈራራት ሳይሆን ድምጽን አጥፍቶ በመስራት እንደሆነ በመረዳቱ ነው። ሁለተኛ በማርክሲስት ጥርነፋ የሚታዘዝ የሚማገድ ሳይሆን በራሱ ጠመንጃ፤ በራሁ ግዜ እና እምነት የሚወስን ስለተደረገ ነው።  በአጭር ሰአታቶች ውስጥ 54 ከተማ በማጥቃት መቆጣጠርና እስረኞችን ማስፈታት፤ ትጥቅ ማስፈታትና የቻለው። ይህንን ማንም ባለ 5 ኮኮብ ጀኔራል ሊያቅደው ሊመራው የማይችል ሚስጥራዊ ግዳጅ አፈጻም ነበር።  እያንዳንዱ የየራሱን አቅም ወስኖ የመንቀሳቀስ ስልጣን ስላለው ይሄው የሚያስደምም ውጤት አስመዘገበ።  

የፋኖ የፓለቲካና የወታደራዊ አመራሮች በወሎ ውስጥ ለሶስት ሳምንት ተሰባስበው ባለ ብዙ ምዕራፍ እቅድ አውጥተው ነበር።  የመጀመሪያው በእርግጥ ህዝብ ከሰፈረበት ድብርት ተላቆ ህዝባዊ ተቃውሞ ለማድረግ የሚያስችል ስነ ልቦና ዝግጅት አለወይ የሚል ነበር። ብዙ ህዝብ ይደግፈናል ጫፋችን ቢነካ አገር ይሄዳል ያሉ እንደነ ጃዋር ያሉ ሳይቀር ሲወድቁ ስለ ታየ የህዝብ ዝግጅት እንዳለ መፈተሽ ግድ ነበር።

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ያለው አማራጭ ህዝባዊ ተቃው መጥራት ነበር።  መጋቢት 20 ዶ/ር አብይ አሻግራለሁ ብሎ ስልጣን የያዘበትን ቀን ተመረጠ። ብዙ ዝግጅት ተደረገ፤ ከበርካታ መሀበራዊ ስብስቦች ጋር በሚስጥር ውይይት ተደረገ ከዛም ዝርዝር መፈክር አጀንዳ አስተናባሪ ተዋቅሮ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ።  ከተጠበቀው በላይ 25 ትላልቅ ከተሞች ህዝብ ግልብጥ ብለው ወጣ። ወጣቱ ሰራተኛው ህዝብ ከዛም አልፎ ህዝብን ለመጨቆኛና ለማስፈራሪያ የተመሰረተው ልዮ ሀይል ሳይቀር ተሳታፊ ሆነ። በስሜት የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ መልዕክቱን አስተላልፎ የስራአቱን መሪዎች አስደንብሮ ተጠናቀቀ።   

በዚህ የተደናገጠው አብይ አህመድ ልዩ ሁይሉ ይፍረስ ብሎ በእሳቱ ላይ ቤንዚል ጨመረበት። ለአንድ ቀን የታቀደው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ መንገድ መዝጋትና ስርአቱን ማባረር ከፍ አለ። ህዝብ በድርጅት ሲያምን አደራጅ ጠርናፊ እንደማይፈልግና በራሱ ፈቃድ መስዋዕት እንደሚከፍል ከልብ ተረጋግፕጠ። ይሁንና ፋኖ የህዝብ አካለ ስለሆነ ለፋሲካ በአል መንገድ ከፈተ ህይወት ወደ ነበረበት ተመለሰ። 

ቀደም ብሎ እንደታቀደው የህዝብ ድጋፍ ካለ ፋኖ በአንድ እዝ ያሰባሰበውን 55ሺ ታጣቂ ወደ ጫካ እንዲወጣ ማሳመን ነበር።  ይህ ትልቁ ፈተና ነበር። እርጉዝ ሚስቱን ህጻን ልጁን የሚጦራት እናቱን እርሻውን እቁበን ጥሎ ጫካ መግባት ቀላል ውሳኔ አልነበረም። ይሁንና የአላማ ጽናትና ቁጭት ሁሉን የሚያስጥል ነበርና ሰራዊቱ ከከተማ ወጥቶ ጭቃ፣ ጫካ፣ ዝናብ ውስጥ ማደር መረጠ።

ደግነቱ ስርአቱ የመሀይማን ስብስብ ነውና ጦር ሲያውጅ ብዙው ቤቱን ለቆ “ዱር ቤቴ ድንጋይ ትራሴ” እንዲል አስገደደ።

ከዛም ቦታ መረጠ፤ ብርዱን፤ ዝናቡን፤ ረሁቡን የእግር መንገዱን ተለማመደው።

በምዕራፍ ሁለት አላማ የአማራን ህዝን ትጥቁንና ቀበቶውን አስፈትቼ ረግጬ አዋርጄ እያሳደድኩ፤ እያረድሁ፤ እያፈናቀልኩ እየሰደብኩ እገዛዋለው ብሎ የተንሳስውም የኦፒዲኦ እብሪት ማስተንፈስ ነበር። ምንም አማራጭ የለም ናና ሞክረኝ ማለት ነበር።  ሰራዊት አዝምቶ ከጎጃም ጎንደር ከወሎ ሸዋ ሰራዊት ቢያሰማራም ብክጽግና 20 ክላሽንኮቭ ማስፈታት አልቻለም።  ይልቁንም በየቦታው እየተመታ ፋኖን ማስታጠቅ ቀጠለ።    ገዳይ ሲያረፋፍድ ምች ይገሰግሳል ሆነ።

በዚህ ላይ በተሰማራበት ሁሉ ገዳምንና ቤተ እምነትን ማውደም መደብደብ ስራው ስላደረገ ከተማ ቀርቶ ልጅ ሊያሳድግ እቁቡን ሊጨርስ ያሰበው ፋኖ ሁሉ ሞት ቤቱና ገዳሙ ድረስ ተላከበት። በየ ቤቱ የነበረው የከፋው ሀይል ሞት ገዳምም ቤተ ክርስቲያንም መስጊድም እንደማያድነው ሲረዳ ጠመንጃውን እየወለወለ ወደ ፋኖ ሀይል ተቀላቀለ። 

የቆጡን አወርዳለሁ ብሎ የተነሳው ብልጽና የብብቱን የያዘውን ድሽቃ እየጣለ ፋኖን አስታጠቀ።  የፋኖ ሀይል ብርዱን ዝናቡን ጭቃውን መልካ ምድሩን ህዝቡን ተላመደ።  ወታደራዊ ስልጠና፤ የፖለቲካ እምነትን ማጥራት፤ የአጭር ግዜ ግብንና የረጅም ግዜ ግብን ማስረጽ ተሰራ። ትልቁ ፈተና የነበረው የኢንሳና የስለላው ድርጅት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ስልክ ስለሚያዳምጥና ስለሚቀዳ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንደማይቻል ግልጽ ሆነ።  ስለዚህ ቴክኖሎጂን ትቶ አዲስ መንገድና ግንኙነት መፍጠር ግድ አለ።  

ይህ ተከትሎ ወደ 54 ከተሞች መሳሪያና ሀይል ፋኖ ሲያስጠጋ የኦፒዲኦ ጥርብ መሀይሞች ተሰብስበው “የአብይን ስልጣን የተመኘውን  እጁን እንደሚቆርጣለን”እያሉ ያስጨበጭቡ ነበር። ሀገር ሰላም ነው ብለው እንዴት የጎበና-የኦርቶዶክስ ልጆች ብለው የሚከሱትን የቱለማን የእርሻ መሬት እየነጠቁ ከሀረር፤ ከአርሲ ከወለጋ ለሚያመጡት ሰፋሪዎች እንዴት አንደሚሰጡና እንዴት አዲስ አበባን እንደሚከቡ ይዶልቱ ነበር።

የቱለማን መሬት ሸጠው እንዴት አሜሪካ ለልጆቻቸው ቤትና ሀብት እንደሚያከማቹ ይወያዩ ነበር። የቱለማን መሬት በመሸጥ እንዴት እንደሚከብሩ ሲያሰሉ ትልቁ ዝሆን ሳሎን ውስጥ ቆሞ ነበር።    

ምዕራፍ ሶስት ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገር። ያለውን የትጥቅና የተተኳሽ እጥረት መንግስትን በማስፈታት መታጠቅ፤ በየ እስር ቤት የሚማቅቁትን የፋኖ ታጋዮች ነጻ ማውጣን፤ ብአዴን ሆዱ እንጂ ልቡ ከብልጽና ጋር እንዳልሆነ ሁሉም ያውቃል።  ይሁንና ሆዱን የወደደ ልክስክስ ነውና እሱን ማስደንገጥና V8፤ መኪና፤ ቪላ ቤትና መሬት ሸጬ እከብራለሁ ብሎ ማሰብ ብቻ ሳይሆን መልአከ ሞትም በሩን ሊያንኻኻ እንደሚችል ማሳየት ነበር። 

ከሁሉ በላይ ደግሞ ልክ በምዕራፍ አንድ እንደተፈተሸው ህዝን ትጥቅ ትግሉን በተግባር ይደግፋል ወይ የሚለውን መፈተሽ ነበር።  ከኦነግ የ50 አመት ስህተት የተወሰደ ልምድ ነው።

በምዕራፍ ሶስት ከመከላከል ወደ ማጥቃት ሲጀጋገር ምንም ኮሽ ሳልይል ሚስጥሩ እንደተበቀ በአንድ ግዜ መላው የአማራን ክልል መቆጣጠር ተሻለ።  ኢንሳ ቁጭ ብሎ ወሬ ሲያዳምጥ ትልቁ ዝሆን ሳሎን ውስጥ ቆሞ ነበር። የዚህ ኦፕሬሽን ትልቁ ድል ሚስጥር መጠበቅ መቻሉ ነው።

በዚህ ዘመቻ የቀበሌና የወረዳ፤ የዞን መዋቅርብ ማፍረስ ተብሎ የተጀመርረው ትላልቅ ከተሞችን ወደ መቆጣጠርና ክምር መሳሪያ መማረክ፤ እስረኞችን ማስፈታት፤ ጠመንጃ ያልተኮሱ የብአዴን ካድሬዎች ማንም እንደማይነካቸው ማሳየት ነበር ።  

የህዝብ ንብረት ባንክ መገልገያና በህዝብ ላብና ደም የተገነበቱን ሀብቶች መጠበቅ ነው።   ፋኖ አመራር ባደረገው ኮንፍረንስ የሶስት መቶ ሺህ ብር ተተኻሽ በጀት ጠይቆ ነበር’ ይህም ለእያንዳንዱ ታጣቂ መቶ ሀምሳ ጥይት ለመስጠት ነበር።  ይሄንን አንድ ባንክን በመዝረፍ ሊያገኝ ይችል ነበር ይሁንና የአላማ ያለው ድርጅት ስለሆነ እየተዋጋም ባንክ እንዳይዘረፍ እየጠበቀ ተልዕኮንውን አሳክታል።  በዚህን የህዝብን የአለማቀፍ አድንቆት አተረፈ ።

ከሁሉ በላይ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለትጥቅ ትግል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው የሚለውን ጥያቄ መፈተሽ ነበር።  ይህ ጥያቄ በህዝብ ሙሉ በሙሉ ተመልሷል።  ፋኖ ዛሬ 55 ሺ ተዋጊ ሳይሆን 120 ሚሊዮን ህዝብ ከጀርባው እንደሆነ ተረዳ። ፋኖ በየደረሰበት ከተማ መንቀሳቀስ እስከሚቸግር ድረስ ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ እያቀፈ በመሶቡ ያለውን እንከነ መሶቡ ወጥ እየገለበጠ ወጥቶ ተቀበለ።  ከተማ ከመያዝና የብአዴንን ምርጫ አንዲት ብቻ መሆንዋን እሷም ከህዝብ ጋር ቆሞ መታገል ወይም መውደም መሆኑን እንዲረዱ ከማድረግ በላይ የህዝቡ ዝግጁነት በደንብ ታይታል።  ገበሬው ጅራፍ ሳይሆን ጭስ የጠጣውን መውዜሩን ቤልጅጉን ይዞ መንገድ እየዘጋ ምሽግ ይዞ ፋኖን እንዲወጋ የታዘዘው ሀይል እንዳንቀሳቀስ አድርጎ ወጥሮ የዞ ከረመ።  

የህዝብ ድጋፍና እንደው በደቡብ በአዲስ በሰናሌ በኦሮንያም ሳይቀር አድናቆትን ድጋፍ ተቸረ። ፋኖ የሁሉ ኢትዮጵያዊ ባህልና እርስዎ ነበር።  እነ አበበ አረጋይ እነ ሀይለማርያም ማሞ በላይ ዘለቀ መስፍን ስለሺ ብቻ ሳይሆኑ ፋኖዎች እነ ገረሱ ዱኪ፣ እነ አብዲሳ አጋ፣ እነ ባልቻ አባነፍሶ እነ ኡመር ሰመተር እነ ባልቻ አባነፍሶ የነ ገብርዬ ታርክና ባህል ነበር ። ቀደም ተብለው የተጀመሩ የአፋር የደቡብ የመላው ሸዋ ፋኖ ንቅናቄዎች እኔም እንደ ወንድሜ ብለው ወደ ትግል እንደሚገቡና አካባቢያቸውን ከጨቋኞች እንደሚያጹዱ ጥርጥር የለም።

ተጀመሩ የአፋር የደቡብ ፋኖ ዝግጅቶች ውጤት እንደሚያመጡ በምእራፍ አራት ይፈተሻል።

ፋኖ በርካታ ታጋዮችን አስፈትቶ አዳዲስ መሳሪያ ማርኮ በርካታ ወጣቶች ፋኖን አስከትሎ ወጣ። የዛሬ ሶስት ወር 55 ሺ እንሆናለን ተብሌ የተገመተው ተዋጊ በምዕፍ ሶስት ትግል ከመቶ ሺ በላይ ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል። ቀለብና ትጥቅ እንጂ የሚታገለው ወጣት ከቁጥር በላይ እየሆነ ነው። 

ለምን ፋኖ ትላልቅ ከተሞችን ለቀቀ?

ፋኖ ትላልቅ ከተሞችን ተረክቦ ማስተዳድር በርካታ ሀይሉን እንቅሰቃሴ እንደሚገታበው በወታደራዊ ኮንፍረንስ ላይ በደንብ የተወሰነ ነውና የምዕራፍ ሶስትን እቅድ ከመቶ ፐርሰትን በላይ አሳክታል።  ህወሀትን ሻቢያም በትግሉ ግዜ ትላልቅ ከተሞችን አጥቅቶ መውጣት እንጂ ይዘው አስተዳድረው አታውቁምን

ለፋኖ መሪዎች፤ ደጋፊዎችና ህዝቡም ፋኖ ይህንን ያህል እምቅ ሀይል ይኖረዋል ብሎ የገመተ የለም።  

በእርግጥ 55 ሺ ተዋጊ ይዞ መላው ኢትዮጵያን መቆጣጠር አይቻልም።  አሁን የሰው ሀይልና የመሳሪያን አቅርቦት በከፊል ተሳክቷል።  ወጣቶች ጀሌ ሆነው መጥተው ድሽቃ ታጥቀው ተመልሰዋል፤ ወታድራዊ ልምድም አግኝተዋል።  አሁን ምዕራፍ አራት ላይ ነን። በቅርቡ ደግሞ ምዕራፍ አራት ምን እንደሆነ በተግባር እናያለን።  ለጊዜው ቦታ ይዞ ጥንካሬና ድክመትን መገምገም። ሥስ ቦታዎችን መሸፈን፤ የመንግስትን ወታደራዊ እቅዶች በሰራዊቱ ውስጥ ካሉ ደጋፊዎች ማፈላለግና የአጻፋ እቅድ ማጽደቅ፣  በተያዙ የወረዳ ከተሞች ሁሉ ወታደራዊ ስልጠና መስጠትና ለምዕራፍ አራት በደንብ ማቁሰል ከዛ በምዕራፍ አምሰት መደምደም ቡጢ መሰንዘር ይሆናል።    

ህዝብ በመላው ኢትዮጵያ ኦሮምያንም ጨምሮ ፋኖን ተስፋ አድርጓል። ስለዚህ ኢንሳ ወሬ ሲቀዳ ትልቁ ዝሆን ለሰይጣንና ለቡዳ  መከላከያ ተብሎ በአረብ ጠንቋዮች ምክር አብይ አህመድ ያቆማትን ፒኮክ አልፎ ቆሞ ይገኛል። 

እንዴት የሚለውን በምዕራፍ አራት እናውፕጋለን።

ለብአዴን መልዕክት  

ከምዕራፍ ሶስት በፊት የህዝብ ቁጣ ገና ሩቅ ነው ብላችሁ እስከዛው እንብላ ብላችሁ  የተሰለፋችሀ ብአዴኖች ከመበላታችሁ በፊት ከህዝብ ጋር ቆማችሁ ታገሉ። የህዝብን ጥያቄዎች መልሱ። 

ጉድጋዳችሁ የተማሰ ልጣችሁ የተራሰ ደረጃ ላይ ናችሁ ያላችሁን ቢያንስ ቢያንስ ከነ አብይና ለማ መማር እንዴት ያቅታችሀል።  ኦፒዲኦ በ10 ሺ የሚቆጠር የኦሮሞን ወጣት አፍሶ ግማሹን ገሎ አንዳንዱን ገርፎ አንዳንዱን ደዴሳ ካምፕ አስገብቶ ቀጥቅጦ (ስዩም ተሾመን ጨምሮ) ማስቆም እንደማይችል ሲገባው ማልያውን ቀይሮ ቄሮ ላይ ቁጭ ብሎ ጋልቦ አራት ኪሎ ገባ። ስለዚህ የብአዴን ካድሬዋች ራሳቸውን ለማዳን ከህዝብ ጋር ለመታረቅ የሚከተሉትን በአፋጣኝ አድርጉ። ህዝብ ተነስቷል ወለጋም አይደብቃችሁም አዳነች አቤቤም አዲስ አበባ አታስገባችሁም።   እስቲ አስቡት 54 ከተማ ለመቆጣጠርና መሳርያ ለመታጠቅ የሚስጥር ስራዊት የብአዴን መሪዎችን ማደንና ማጥፋት ቢሆን ኖሮ አንዳችሁ ትተርፏ ነበር። እናንተ የሆዳችሁ እንጂ የብልጽግና ደጋፊዎች ህዝቡም ፋኖም ስለሚያውቅ ነው ያላጠፋችሁ። ይህ እድል ግን ሁሌም አይኖርም  የአማራን ልጅ እያስገደልኩ፣ እያሰርኩ፣ እየሰደብኩ አብይ ይሾመኛል አዳነች ቢላ ትሰጠኛለች ብላችሁ የምትቋምጡ እንጂ የብልጽግና እምነት ተከታዮች እንዳልሆናችሁ እናውቃለን። ወበባው በስልክ ያማል እልፍ ኤርፓርት ቦታ ሲሰጠው ደግሞ ወጥቶ ይደነፏል። ስለዚህ ከሆዳችሁ ጋር ሳይሆን ከህሊናችሁ ጋር ለመቆም የሚከተሉትን በአስቸኳይ ፈጽሙ።

1ኛ በክልሉ የገባው ሰራዊት እንዲወጣ በምክርቤት ውሳኔ ማስተላለፍ። 

2ኛ የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የዘር መጥፋት አደጋ ለመከላከል እንዲችል የመሰልጠን የመደራጀትና የመታጠቅ መብቱን እንዲያከብር በምክርቤቱ አቅርቦ እንዲያስወሰን።  

3ኛ በወለጋ በቤንሻንጎል ለአደጋ የተጋለጡትን ወገኖች ብአዴን ሰራዊት ልኮ እንዲታደግ።  

4ኛ የራያን፤ የጠለምትን፤ የሁመራን ህዝን እጅ እግር አስሮ ለድጋሜ ለዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደሚጋልጥ በምክር ቤቱ አስወስኖ እንዲያሳውቅ  

5ኛ በእጁ ያሉና በፌዴራል እስር ቤት የሚሰቃዩትን የፖለቲከኛ እስረኞችን እንድትፈቱ። እስረኞች መፈታታቸው ላይቀር ለምን ብአዴን በህይወት ይከፍላል።  ላታመልጪኝ አታራሩጪን ለምን ይሆናል። ዘመነ ካሴን ባይፈታ ኖሮ ትላንት ይፈታ ነበር።  በመፍታታችሁ ተመስግናችሀል። 

6ኛ፡ በመላው ኢትዮጵያ በአማራነታቸው ብቻ ታስረው የሚሰቅዩትን በአስቸካይ ኦፒዲኦ እንዲፈታ መጠየቅና እንቢ ካለም ህዝባዊ ጥሪ አድርጎ ተጸኖ እንዲፈጥር።  

7ና በአማራ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ የሚያካሂዱ የብአዴን ካድሬዎችን ከስራቸው እንዲያግድ ወንጀለኞቹምን ብዙ እስር ቤት ባዶ ስለሆነ ወደ ማረፊያ ቤት እንዲያቆይ ማድረግ ነው።  

ይህንን በማድረግ የተነሳበትን እሳት ማብረድ ይችላል።  ልጆቻችሁም አሳዳጊ እናቶቻችሁም ጧሪ አታሳጡ። ከለማና አብይ ተማሩ። ከህዝብ ጋር ቁሙ። 

ለኢትዮጵያ ሰራዊት  

ፋኖ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ የመትኮስ እቅድ አልነበርውም። አብሮ በልቷል አብሮ ሞቶ ተቀብሯል።  ለሞቱትም ለተማረኩትም ልቡ ይደማል ይሁንና በክልሉ በቀዮው በክልሉ መንግስት ሳይጠራ፣ አስቸኳይ ጊዜ እንኳን ሳይታወጅ ህግ ጥሶ በአንባገነን ወንጀል እንዲፈስም ትዝብት ተቀብሎ በሰፈሩ  መጥቶ በሚተኩስበት ላይ አልሞት ባይ ተጋዳይ መሆን ግድ ነውና የኢትዮጵያ ሰራዊት በስልጣን ላይ ያለው የብልጽግና ስርአት አሽከር ሳይሆን የህዝብ ጠባቂ መሆን አለበት። 

የኦፒዲኦ መሪዎች የሰራዊቱ ጠላቶች ናቸው።  እነሱ ኦሮምያን ለመመስረት ነው  አላማቸው ። ኢትዮጵያ የለችም ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ የሚባል ሰራዊት አይኖርም። ስለዚህ ሰራዊቱ ሊበትኑት ለሚፈልጉት ህይወት መገበር የለበትም።  ከቻለ ወደ አዛዦቹ አፈሙዙን ያዙር፤ ይህንን ካልደፈረም ወንድምንና ህዝብን ጨፍጭፍ ሲባል እንቢ ማለት የህሊናው ውሳኔ ነው። ማንም አልመህ ተኩሰህ ግደል ብሎ የሚያስገድድ ሀይል የለም። አልሞ መግደልም አልሞ መሳትም የህሊና ፍርድ ነው። እግዚአብሄርና ህሊና ያያልና።  

የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ዘረኛና ጨቃኝ ስርአት ነጻ መውጣቱ አይቀሬ ነውና ከገዢዎችና ጨቇኞች እራሱን ነጻ አውጡ። በብሄር ተደራጅቶ የኢትዮጵያን ባንዲራ በልብስህ ላይ ጥልፍ አለ ብሎ የሚገድል ስርአት ለሞት ሲሆን ደግሞ የኢትዮጵያን ባንዲራ አልብሶ ያዘምታችሃል። ስለዚህ ለገዢዋች ሳይሆን ለህዝብ ወገንተኝነታችሁን አሳዩ።  

በምዕራፍ አራት ትግል ህይወታችሁን እንዳታጡ ለአንባገነን ሳይሆን ለህዝብ ቁሙ።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here