
አሰፋ ታረቀኝ
ሰሞኑን የኦነጉ መሥራች አቶ ሌንጮ ለታ፣ አንደበት ከተባለ ሜዲያ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ ለምን ወደ “ትግል” እንደገቡ ለቀርበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ቀልቤን ሳበውና ማዳመጥ ጀመርሁ፡፡ ትግል የጀመሩት ኦሮሞን “ነጻ” ለማውጣትና ‘ኦሮሚያ’ የምትባል ሀገር ለመመሥረት ንደነበር፣ አብራሩና የአጀንዳም የትግልም ለውጥ ያስፈልጋል ስላሉ የመሠረቱት ድርጅት እንዳሰናብታቸውና ሌላ ድርጅት መሥርተው እየታገሉ እንደሆነ ለጋዜጠኛው መለሱለት፡፡ “ቅኝ ተገዝተናል” የምትለውን ተረተረት አልፈው “የአንድ ብሄር የበላይነት እንደነበረ” አሥረግጠው አብራሩ፡፡አንድ እግራቸው መቃብር አፋፍ ላይ ያለው አዛውንት፣ ከፈጠራ ታሪክ ጋር እንደተፋጠጡ ወደማይቀርው ጉዞ እያዘገሙ መሆናቸው ገረመኝ፡፡
ለባህላዊ በአል አከባበር በአቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሞ ፕሬዚዳንት ተወክየ ነው ያለ ዱልዱም፣ የአማራው አካባቢ ሸህ ሁሴን ጂብሪልና መምህር አካለወልድ የተወለዱበት ቦታ እንደሆነ መረጃ የለውም፡፡ ስለ ሐይቅ እስጢፋኖስና ስለ ግሼን ማርያም፣ ስለ መርሳ አባገትየና የእስልምና እምነት ምሁራን ስለሚፈልቁበት አንጾኪያ አልተነገረውም፡፡“ አንድ ኅይማኖት፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድት ሀገር የሚል ተንስቶብናልና ተባብረን እንውጋ” የሚል መልእት አስተላለፈ፡፡ ይህ የታላቁ የኦሮሞ ህዝብ መልዕት ሳይሆን፣ የዶ/ር አብይና የሽመልስ አብዲሳ መልዕክት ነው፤ ምክንያቱም፣ ከጠቅላይ ሚንስትሩም ሆነ ከኦሮሞው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስተባበያ አልተሰጠምና፡፡ጠቅላይ ሚንስትሩን የአዕምሮ መታወክ ይግጠማቸው፣ ወይ መጥፎ አማካሪዎች ይክበቧቸው፣ ወይ አሜሪካኖች ወጥመድ ውስጥ ያስገቧቸው ቁርጡ ባይታወቅም፣ እየሄዱበት ያለው መንገድና የችግር መፍቻ ብለው የያዙት ዜደ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ከታወቀችበት ዘመን አንስቶ ገጥሟት ወደ ማያውቅ አዘቅት እየገፏት ነው፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ ትናንት የተናገሩትን ዛሬ ሽምጥጥ አድርገው ሲክዱ፣ “የተናገሩት ከሚጠፋ፣ የወለዱት ይጥፋ” ብሎ የሚያምንና ቃለ አባይነትን የሚጠየፍ ሕብረተሰብ እየመሩ መሆኑን የረሱት ይመስላል፡፡ አማራን የሚያሳርደው፣ በአዋሳኝ ክልል የሚኖሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያስጨፈጭፈውና በአድስ አበባ ዙፊያ የሚኖረውን ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ ቤት አልባ እያድረገ ያለው የኦሮሞው ፕሬዚዳንት ቁንጥጫ ሳይነካው፣ የአማራው አካባቢ ከአምስት ጊዜ በላይ አመራር እንድቀይር ተገደደ፡፡ አማራ ወርዶ ወርዶ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የተጻፈ መግለጫ የሚያነብ ፕሬዚዳት ተሹሞለታል፡፡
“ ጌታው ለጌታ አድሮ ሳያውቀው ብልሀቱን፣
ሲለምን ያመሻል እንደውሻ እራቱ” ነበር ያለችው የሀገሬ አቀንቃኝ?
የግፍ ጽዋው ሞልቶ ስለፈሰሰ፣ ነፍሴን ማትረፍ አለብኝ ብሎ የተነሳን አማራ፣ የጥቂት ወሮበሎች ስብስብና አላማ የለሽ ግርግር አስመስሎ ለመሳል የሚደረግው ጥረት የዱልዱም ፖለቲክኞች ጫጫታ ከመሆን አያልፍም፤ ዱልዱም በወሎየዎች ቋንቋ፣ ለመቁረጥም ለመብሳትም የማይችል የደነዘ ቢለዋ ማለት ነው፡፡ በጠበብቶች የተገነባችው ሀገር እዱልዱሞች እጅ ገብታ ከልክ በላይ እየተሰቃአየች ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድን የፖሊሲ ውዥንበ ብቻ ሳይሆን የተአማኒነት ቀውስ/integrity crisis/ አንገታቸው ድረስ አስምጧቸዋል፤ ተአማኒነት፣ ለተናገሩት ቃል ወይም ለገቡት ውለታ ሳያወላዱ ጸንቶ መገኘትና በመርህ መመራት ማለት ነው፡፡ Integrity is the quality of being honest and having strong moral principles.
ስንት ጊዜ ቃላቸውን አጠፉ? እነ ክርስቲያን ታደለንና ዮሐነስ ቧያለውን አሥረዋል፣ የስድስት መቶ ሽህ ሕዝብ እልቂት አመራር ሰጭ የነበሩትን የወያኔ መሪዎች ሸልመው ወደ አሜሪካ ልከዋል፡፡ ስለ ጭካኔው በትህነግና በአሳዳጊዎቹ ብዙ የተባለለት ደርግም ሆነ በትህነግ ዘመን ያልተሠራ ድርጊት፣ እየተፈጸመ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች የአማራ መታጎሪያዎች ሆነዋል፡፡ ሦሥቱ የጥፋት ኅይሎች ማለትም፣ ትህነግ፣ ኦነግና ኦሆድድ፣ አማራው የጋራ ጠላታችን ነው እሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሱ ቆይተዋል፡፡ ለሕዝቡ ካላቸው ንቀት የተነሳ፣ እሱ በሌለበትና በታንክ በታጀበ ስብሰባ “መንግሥት መሥርተውለታል” የአቅጣጫ ለውጥ ካልተደረገ፣ እንኳን ለአማራው፣ ለአድስ አበባውም መንግሥት አስጊ ነው፤ ተቃውሞው ደቡቡንም እያካተተ ነው፡፡ በፍጥነት ምክክር ካልተጀመረ፣ በኢህአደግ ቁጥር 2ና በኦነግ ጥምረት የተዋቀረው ብልጽግና፣
“በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት
ብትትን ይላል ጅብ የጮኸ ዕለት”
እንደተባለው እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ አማራው በኢትዮጵያዊነት ላይ ጥያቄ ስለሌው፣ ከትህነግ፣ ከኦነግና ኦሆድድ በስተቀር ሁሉም ይደግፈዋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የሚከበረው በኢትዮጵያዊነቱ ነውና፡፡
“ባንዲራችን ወድቆ ከመሬቱ ላይ፣
ታግሎ ታግሎ አነሳው አበበ አረጋይ”
የተባሉት የአምስቱ አመት አርበኛ የሸዋው ኦሮሞ ራስ አበበ አረጋይ በቸሬ ነበሩ፡፡ ኦሮሞ በነዚህ ወሮበሎች አይመዘንምና እሱንም እንድረሰው፣ ድርሻውን እንድወጣ እናስተባብረው፡፡ ትንንሽ ጭንቅላቶች የታላቁ የኦሮሞ ህዝብ መመዘኛ መሆን ፈጽሞ አይችሉም፡፡
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ