spot_img
Sunday, May 26, 2024
Homeነፃ አስተያየትየኦሮሞና ትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች ያልተቋረጠ ሃፍረተቢስነት- “አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ባህል?”

የኦሮሞና ትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች ያልተቋረጠ ሃፍረተቢስነት- “አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ባህል?”

ጻድቃን ገብረትንሳይ መቀሌ የ አሸንዳ በዓል ለመታደም መቀሌ ከመጡ የኦሮሚያ ተወካዮች ጋር (ፎቶ ከድምጺ ወያኔ የተገኘ)

ሰሎሞን ገ/ስላሴ
ነሐሴ 2015


በቅርቡ በመቀለ የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲን ወክለዉ በአሼንዳ በአል ላይ ንግግር ያደረጉት የሽመልስ አብዲሳ ወኪል የአማራን ህዝብ በስም ሳይጠሩ ከተለመዱት የዳቦ ስሞቹና በነሱ አንደበት መገለጫዎቹ “አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ባህል” ከሚሉ ሃይሎች ጋር የትግራይና የኦሮሞ ሕዝብ በጋራ ጥምረት እንዲዋጋ የዘር ማጥፋት ጥሪ በይፋና በአደባባይ ጥሪ አድርገዋል፡፡

አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ አገዛዝና ቀደም ብሎ በስልጣን ላይ የነበረዉ ህወሃት፤ ዉሸትን በየደቂቃዉ እንደሚፈበርኩ ርሰበርሳቸዉ የተባባሉትን ወደ ሆዋላ ተመልሶ በዩቱብ ማየት በቂ ነዉ፡፡ ሆኖም የዛሬዉንና የእለቱን ብቻ ሳይሆን ያለፈዉን በተለይም በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ከ 50 አመት ወዲህ የኢትዮጵያ በተለይም የኣማራዉ ፖለቲከኞች በተማሪ እንቅስቃሴም ሆነ ተከትለዉ በተመሰረቱ የመጀመሪያዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች “አንድ ህዝብ፤ አንድ ሃይማኖትና አንድ ባህል” በሚለዉ አደናጋሪ ቀመር ላይ የነበራቸዉ አመለካከት ምንድን ነበር? የሚለዉን ማየት ቁልፍ ጥያቄ ነዉ፡፡

ከተማሪዉ እንቅስቃሴ ብንጀምር በእንቅስቃሴዉ ጉልህ ሚና ከተጫወቱት ማህበረሰቦች መካከል የአማራ ተራማጆች ግምባር ቀደም ነበሩ፡፡ ይህም ማህበረሰቡ በኢትዮጵያ ካለዉ ቁጥር አንፃር የሚገርም አይደለም፡፡ ከነዚህ ተማሪዎች መካከል ግለሰቦችን ብናወሳ ከአማራዉ ማህበረሰብ የተገኘዉ ዋለልኝ መኮነን በዋነኛነት ይጠቀሳል፡፡ የዋለልኝን ርእዮተአለም የምንጋራዉ ሰዎች ከጊዜዉ ቀድሞ ተራማጅ የነበረዉን ዋለልኝን የምንተቸዉ ተናጋሪዉ ከፈበረኩት በተለየ አካሄድ ነዉ፡፡ መለስ ዜናዊ ራሱ የተከለዉ የጎሳ ፌዴራሊዝም የፈጠራቸዉን እንደ መቀሌዉ ተናጋሪ ያሉትን ሰዎች ethnic entrepreneurs (የጎሳ ነጋዴዎች) ብሎ ይጠራቸዉ ነበር፡፡ ይህም ማለት የያዙትን ስልጣን ያገኙት በአቅማቸዉና በትምህርታቸዉ ሳይሆን በዘር ፖለቲካ ዝምድና መሳሳብ እንደሆነ ለማሳየት ነዉ፡፡ ዋለልኝ ወደ ሌላ ፅንፍ በመሄድ አንድ አገር የጋራ መግባቢያ ቋንቋና የጋራ ስነ አእምሮአዊ ተግባቦት ሊኖረዉ እንደሚያስፈልገዉ በሚገባ አለማጤኑ እንጂ እኒህ ተናጋሪ ከመወለዳቸዉ በፊት ማህበረሰቦች ባህላቸዉን የመንከባከብ መብታቸዉን አስረግጦ ተናግሯል፡፡

ወደ ተማሪዉ እንቅስቃሴ ስናልፍ ደግሞ እኒህ መሃይምና እሳቸዉን ወደ መቀለ የላኳቸዉ ሰዎች የማይገባቸዉ ተማሪዎች ለብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች መብቶች በመታገላቸዉ ታስረዋል፤ ተሰደዋል፤ ሞተዋል፡፡ “መሬት ላራሹ” በሚለዉ መፈክር ከ1958 የፓርላማ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ጀምሮ እስከ 1967-68 እድገት በህብረት ድረስ የአማራ ተማሪዎችና መምህራን ከሌሎች ወንድሞቻቸዉና እህቶቻቸዉ ጋር ሆነዉ ታግለዉ መስዋእትነትን ከፍለዋል፡፡ ከዘመቻዉም በፊት የየካቲት 1966 አብዮት እንደፈነዳ በታላቅነቱ በሚታወቀዉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የሃይማኖት እኩልነት ጥያቄ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአማራ ተወላጆች ሰልፉን ከማዘጋጀት እስከ ሰልፉን ማድመቅ አኩሪ የትግል ታሪክ አሳይተዋል፡፡

የተማሪዉን እንቅስቃሴ ተከትለዉ የተመሰረቱት ኢህኣፓና መኢሶንም በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት ብሄረሰቦች የቋንቋ፤ ሃይማኖትና ባህል መብቶች የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በመሆናቸዉ እንዲከበሩ አበክረዉ ታግለዉላቸዋል፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ መሃይማን ድንገት እነሱ የተገለጠላቸዉ የመብት ጥያቄዎች ትግል አድርገዉ ሲያዉገረግሩ ማየት በእጅጉ ያማል፡፡ ከምራቸዉ ሳይሆን ስልጣናቸዉን ማስጠበቂያ ታክቲክ መሆኑ ደግሞ ወደዉ አይስቁ ያሰኛል፡፡ የተማሪዉ ጥያቄና ፓርቲዎቹ ግራ ዘመም ስለሆኑ ነዉ ተራማጅ ጥያቄዎችን ያነሱት ሊባል ይቻል ይሆናል፡፡ አዎ እዉነት ነዉ፡፡ ግን ከዚያም በሆዋላ የተፈጠሩ ግራ ዘመም ያልሆኑ ፓርቲዎችና እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ቅንጅትና ህብረት እነዚህን መብቶች ሙሉ በሙሉ ደግፈዋል፡፡ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ ለኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርአት ተስማሚ የፖለቲካ ስርአት እንደሆነ የማይቀበል የፖለቲካ ፓርቲ የለም፡፡ ይህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ 25 ኣመት ያለፈዉ የፖለቲካ ክስተት ነዉ፡፡ በዘር ሳይሆን በመልካአ ምድርና ታሪካዊ አሰፋፈር የተዋቀረ ፌዴራሊዝም ደግሞ የክፍለ አገሮችን ያካባቢ መብቶች የሚቀበል፤ ስልጣን በፌዴራል መንግስቱና በክፍለ አገሮች የሚከፋፈልበት ስርአት እንደሆነ የሚቀበል ነዉ፡፡

ዛሬ እነዚህ የወያኔና የኦሮሞ ብልፅግና የጎሳ ነጋዴዎች ከኛ ወዲህ ለብሄረሰቦች መብቶች ታጋይ የለም በሚል ሽፋን የሚያደርጉት የያዙኝ ልቀቁኝ አጉራ ዘለል ጩሀትና የአማራዉ ፍጅት፤ አገሪቱን በጦርነት አዙሪት ከማሽከርከር ሌላ ፋይዳ የለዉም፡፡

ወደ ዛሬዉ ያገሪቱ ሁኔታ ስንመጣ፤ ሲጀመር ባገሪቱ ካሉት ክልሎች ዉስጥ ለሌሎች ብሄረሰቦች የዉስጥ አስተዳደርን የፈቀደና ተቻችሎ የሚኖር ከአማራ ብሄረሰብ ሌላ የለም፡፡ሲቀጥልም የኣማራ ሃዝባዊ ሃይልና የኣማራ ግምባር ፋኖ ሃይሎች አለምን ባስደመመ ሁኔታ ያሳዩት የዲስፕሊን ጎዳና በኣማራ ክልል የሚገኙና ከክልሉ ዉጭ ያሉ ማህበረሰቦችንና ንብረታቸዉን በከፍተኛ ጥንቃቄ ማክበራቸዉና መያዛችዉ፤ የጦር ምርኮኞችን በከፍተኛ ጥንቃቄና ህክምና የያዙበት ሁኔታ “አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ባህል” ከሚል ማህበረሰብ የሚመነጭ አይደለም፡፡

የኦሮሞና የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች እነዚህን ዉሸቶች የሚደረድሩበት ምክንያት ራሳቸዉ የሰሯቸዉን ወንጀሎች ለመሸፈን ነዉ፡፡ ወያኔ በ27 አመት አገዛዙ በኣማራዉ ላይ ያሰራጨዉ የሃሰት የጨቋኝ ትርክትና የማይካድራና የጪና የዘር ማጥፋት ወንጀል፤ ዛሬ ደግሞ የኦሮሙማዉ ብልፅግና የፈፀመዉ በወለጋና በቤኒሻንጉል የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በሚፈበረኳቸዉ ዉሸቶች ሊታጠቡ አይችሉም፡፡ እስካሁን ለፈፀሟቸዉ ወንጀሎች ሆኑም ላቀዷቸዉ ወንጀሎች ወደፊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለዉም፡፡

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here