spot_img
Sunday, May 26, 2024
Homeነፃ አስተያየትሞት ላይቀር ፋኖ ሆነህ ኑር! ፋኖ ሆነህ ተቀበር! (በላይነህ አባተ)

ሞት ላይቀር ፋኖ ሆነህ ኑር! ፋኖ ሆነህ ተቀበር! (በላይነህ አባተ)

Fano _ Ethiopia _ combatant

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

በዚህም ሆነ በዚያ ተገላብጦ ሲታይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ታሪክ የፋኖ ተጋድሎ ታሪክ ነው፡፡ ታሪክ ፍንትው አድርጎ እንደሚያሳየው ፋኖ በሰላም ጊዜ አራሽና ቀዳሽ በወረራ ጊዜ ደግሞ ወታደርና ተኳሽ ነው፡፡ በአድዋው ዘመቻም ሆነ በሁለተኛው የጣልያን ወረራ የኢትዮጵያ ሕዝብ በፋኖና ባንዳ የተከፈለ  እንደነበር ትውልድ የሚያውቀው ነው፡፡ 

በእነዚህ ወረራዎች ዘመን እንኳን የሕዝብ የአህያና የፈረስም ፋኖና ባንዳ ነበር፡፡ አርበኛው ፋኖ ግንባር በመፋለምና በመዋደቅ፣ በሽለላና በፉከራ ወኔን በመቀስቀስ፣ የጀግንነት ትያትር፣ ጽሑፍና ግጥም በማዘጋጀት፣ ስንቅ በመሰነቅ፣ ታቦት በመሸከም፣ አቅሙ የደከመ ወይም ዓይኑ የታወረም ወራሪ ብን ብሎ እንዲጠፋ በልባዊ ፀሎት ይፋለም ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በእነዚህ ወረራዎች ወቅት በመንገድ መሪነት ወይም በሎሌነት ያገለገለ ብቻ ሳይሆን ዝምብሎ እንደ አሳማና ጉንዳን በልቶ ለመሞት የቆረጠ ሁሉ እንደ ባንዳ ይቆጠር ነበር፡፡ ከድል በኋላም እነዚህ ባንዳዎች ክርስቶስ አሳልፎ ከሰጠው ከይሁዳ በላይ እየተጠሉና እየተነቀፉ አካባቢያቸውን ለቀው ጅራታቸውን እንደ ቡችላ ወትፈው እየተንጦለጦሉ ወደ እማይታወቁበት አካባቢ እየተሰደዱ አንገታቸውን አቀርቅረው እንደ ከርከሮ በልተውና የከረፋ ታሪክ ትተው ወደ መቃብርና ሲኦል ይሄዱ ነበር፡፡

በዚህ ዘመን ያለው ወረራ የአማራ ሕዝብ በታሪኩ ከደረሰበት ወረራ ሁሉ የከፋ ነው፡፡ ቱርክም፣ ጣሊያንም፣ ደርቡሽም ሆነ ሌሎች ወራሪዎች ዘርን ሙልጭ አድርጎ ለማጥፋት የእርጉዝ ሆድ እየቀደዱ የአማራ ሽል አላረዱም፡፡ የአሁኖችን ያህል ከተማ መሐል መድፍና ባሩድ እየረጩ ልጆችና ሴቶችን አልፈጁም፡፡ በግፍ በተያዘ እስረኛ ላይ የከረፋ ሽንታቸውን እንደ ውሻ አልሸኑም፡፡ ለፍቶ አዳሪውን አማራን ብቻ አየመረጡ ከምዕራብ፣ ከደበቡብ ምዕራብ፣ ከምስራቅና ከመካከለኛው ኢትዮጵያ አላረዱም፤ የተረፉትን እናቶችም በርሃብ የጠወለጉ ልጆቻቸውን በጀርባቸው አዝለው የሚንከራተቱ ስደተኞች አላደረጉም፡፡ የአማራ ቤተክርስቲያኖችንና መስጊዶችን እየመረጡ አላጋዩም፡፡ በችጋርና በበሽታ ለማጥፋት አማራን እየመረጡ ማዳበርያ አልከለከሉም፤ የሕክምና መስጫ ጣቢያዎችን አላወደሙም፡፡

በዚህ ዘርን ከምድረ ገጥ ለማጥፋት በመጣ ወረራ ወቅት የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም አማራውን አፋጦት ያለው ሁለት ምርጫ ፋኖ የመሆን ወይም የከረፋ የባንዳ ኮቴን መከተል ብቻ ነው፡፡ ፋኖ ያልሆነ ወይም ፋኖን በሚችለው መንገድ ያልረዳ ሁሉ ባንዳ ነው፡፡ ባንዳዎች ለወራሪዎች ሎሌ ሆነው ወገናቸውን የሚፈጁትና መንገድ ጠቋሚ እርጉሞች ብቻ እንዳልሆኑ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ በአድርባይነት፣ በሆዳምነትና በግድየለሽነት ድምጡን አጥፍቶ አለዚያም “ተዋልደን ተካብደን” የሚል አማራን ያዘናጋ ድስኩር እንደ ባዘቶ እየተረተረ እንደ አሳማ በልቶ ነገ አፈር ለመሆን የቆረጠ ሁሉ ቀንዳም ባንዳ ነው፡፡ እንደ ኤፍሬም ይስሀቅ “በሽምግልና” ስም የሳጥናኤልን መንፈስ በሚተገብሩ ጭራቆች እየተላከ ዘሩ እንዳይጠፋ የሚፋለመውን ፋኖን የሚያስበላ”ሽማግሌ ነኝ” ባይ ጭራ አወናዋኝ ሆዳም ሁሉ ጥፍሩ ያዘረዘረ ባንዳ ነው፡፡ “ካህን ነኝ!” እያለ ቆቡን ወይም ጥምጣሙን እንደ አውሎ ነፋስ ቦጅሮና የእንጀራ መብያ መስቀሉን ጭብጦ በውሽታም አስታሪቂነት የሚያዘጠዝጥ “ካህን ነኝ” ባይ ሁሉ እነ ፋኖ በላይ ዘለቀ ወንፊት የሚሉት ዓይነት ጅራታም ባንዳ ነው፡፡

ይህ ወቅት እንኳን አማራ የሆነ አማራ ሰው ነኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚፈተንበት ጊዜ ነው፡፡ አማራ በዚህ ዘር አጥፊ ወረራ ወቅት ሁለት ረድፍ ብቻ አለው፡፡ አማራ አገር አልባ እንዳይሆንና ከምድረገጥ እንዳይጠፋ የተቻለውን ሁሉ የሚያደርግ ፋኖ አለዚያም የዘር አጥፊዎች ሎሌ ሆኖ የራሱን ዘር የሚያጠፋ እርጉም ባንዳ ወይም ደሞ ድምጡን አጥፍቶ እንደ ቅንቡርስ ሲጎሰጉስ ኖሮ ለማለፍ የወሰነ ከርሳም ባንዳ፡፡

ቆሞ ሲሄድ ፋኖና ባንዳ እንደሚባለው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሲሞትም አስከሬኑ ስም ሊሰጠው ይገባል፡፡ ፋኖ ተዚች ዓለም ሲለይ አስከሬኑ የተከበረው የፋኖ አስከሬን፤ ባንዳ በቁንጣን ወይም በእርጅና ሲው ሲል ደሞ ጥንብ የባንዳ እሬሳ ተብሎ መለየት ይኖርበታል፡፡ የፋኖን የክብር አስከሬን ለመሸከም ሕዝብ መሽቀዳደም፤ የባንዳ የጠነባ እርኩስ እሬሳ እንዳይነካውና እንዳይሸተው ደግሞ መራቅና መጠንቀቅ ይኖርበታል፡፡ እንደ ደብረ ሊባኖሱ አባ ገብረ እየሱስ ወራሪን ተፋልሞ ላለፈ ፋኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት መገኘት በምድርም በሰማይም ያስከብራል፡፡ ተይሁዳ ተባሰ ባንዳ የእሬሳ ቀበር መገኘት በምድር አሸማቆ ያዋርዳል፤ በታሪክ ያስረግማል፤ በሰማይ ቤትም ያስኮንናል፡፡

በአጠቃላይ ከአድዋውና ከአምስቱ ዘመን ወረራም በከፋው በዚህ ዘመን ወረራ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የዘር ፍጅቱ ተቀዳሚ ሰለባ የሆነው አማራ ፋኖ ወይም ባንዳ ተብሎ በመካከል ምንም ሳይኖር በሁለት ብቻ ይከፈላል፡፡ ፋኖ ሲያልፍ አስከሬኑ የተከበረው የፋኖ አስከሬን፤ ባንዳው ሲው ሲልም የጠነባው የባንዳ እሬሳ ተብሎ ይጠራል፡፡ ታሪክም ፋኖና ባንዳን ክቡርና ጥንብ እያለ እንደ ሥራቸው እስከ ዳግም ምጣት ሲዘግባቸው ይኖራል፡፡ የፋኖ ልጅናን የልጅ ልጅ ደረቱን ነፍቶ ሲጎማለል የባንዳዎች ደሞ በዝቅተኝነት መንፈስ ሲያፍርና ሲንቀዠቀዥ ይኖራል።
ሕዝብ ሆይ! ባንዳን እግዚአብሔርም እንደማይወድ ከመላእክት መሐል እግዚአብሔርን የከዳው ሳጥናኤልና ከሐዋርያትም መካከል ክርስቶስን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ምስክሮች መሆናቸውን ያጤኗል፡፡ እንደ ሳጥናኤልና ይሁዳ የከዳ ሁሉ ከአጥናፍ አጥናፍና ከዘመን ዘመን በምድርም በሰማይም ሲረገም ይኖራል፡፡ ሰልቅጦና ውጦ ድፍጥጥ እንደሚል ቅንቡርስ በአደጋ፣ በበሽታ ወይም በእርጅና አንድ ቀን ክንችር ማለታችን ላይቀር እንደ ይሁዳ በዲናር የተገዛን አለዚያም የስግብግብነት፣ የአድርባይነት፣ የመሐል ሰፋሪት፣ የግድየለሽነት ትል የወጋን ባንዳዎች መሆን ይብቃን፡፡

ጎበዝ! ባንዳነት እንክርዳድ ለመቃም ያለ ድብዳብ ቅርቀብ ተጭኖ በዱላ ከሚደለዝ ገጣባ አህያ በታችም ያደርጋል፡፡ ፋኖ ሆኖ መኖርና ማለፍ ግን በምድርም በሰማይም ያስከብራል፡፡ ስለዚህ ሞት ላይቀር ፋኖ ሆነህ ኑር፤ ፋኖ ሆነህ ተቀበር፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here