spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትይድረስ ለክልል ባለሥልጣናት (ከእስጢፋኖስ መኰንን)

ይድረስ ለክልል ባለሥልጣናት (ከእስጢፋኖስ መኰንን)

 ለክልል ባለሥልጣናት

ነጻ ምልከታ

ከእስጢፋኖስ መኰንን

ብልጽግና በኦሮሞ ጽንፈኞች የበላይነት የሚመራ አደገኛ ሃይማኖታዊ ፓርቲ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥትን ከፍተኛ ሥልጣን በአብዛኛው የተቆጣጠሩት የብልጽግና ወንጌል ተከታይ ኦሮሞች  መሆናቸውን ለመገንዘብ ከጠቅላይ ሚንስትሩ እስከ ከንቲባዋ፡ ከኢታማጆር ሹሙ እስከ ማረሚያ ቤት አዛዦች ያሉትን ዋና ዋና ባለሥልጣናትን መመልከት ይበቃል።  መከላከያን፡ ፖሊስንና ድህንነቱ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ የተቆጣጠሩት እኒህ አማራ ጠል ኦሮሞች ሲሆኑ የኦሮሞ ልዩ ኃይልን አሰልጥነው መጠነ ሰፌ ዘር ትኮር ጭፍጨፋ ለማስጀመር ሁነኛ ቀን እየጠበቁ ነው። 

ጠቅላይ ሚንስትሩ “በአንድ ጀንበር መቶ ሺ ሰው ማሳረድ . . . “

“ቀይ ሽብርን አሥር ግዜ የሚያጥፍ እርምጃ እንወስዳለን” ያሉት ያስታውሷል።

የብልጽግና አባል የሆናችሁ የክልል ባለሥልጣናት ፡

በኦሆዴድ የበላይነት  ከሚመራውን  ብልጽግና በአስቸኳል ለቅቃችሁ ካልወጣችሁ፡ በዚህ ፓርቲ ባለሥልጣናት፡ ካድሬዎችና የታጠቁ ኃይላት ለተፈጸሙ እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ግድያዎች ሁሉ ተጠያቂ እንደምትሆኑ፥ ለግለ-ሰባዊ በቀልም የምትጋለጡ እንደሆነ ልታውቁ ይገባል።

የብልጽግና ግፍ ተዘርዝሮ አያልቅም። በፖለቲካ ሻጥር ምክንያት የተለኮስውን የሰሜኑን ጦርነትና ያስከተለውን ሰብኣዊና ቁሳዊ ውድመት ትተን፡ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ብቻ የተፈጸመውን ግፍ በጥቂቱ እንዳሥስ፥ ኦሆዴድ ብልጽግና በኦነግ ሸኔ አያማኻኘነት በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናት አሳርዷል፡ የእናት ሆድ ቀዶ ሽል ወርውሯል። በሻሸመኔ ሰው በቁሙ ቆዳው ሲገፈፍ፥ ካህን በካራ ሲታረድ፥ ቤቶች በእሳት ሲጋዩ እያየ ለማስቆም ምንም ሙከራ አላደረገም።  ወለጋ ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ንጹህ አማሮች በዘግናኝ ሁኔታ ሲጨፈጨፉ እንደ መንግሥት አልደረሰም፥ ጥፋተኞችንም ለሕግ አላቀረበም። 

ኦሆዴድ ብልጽግና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማሮችን በማንነታቸው ከኦሮሚያ አፋናቅሎ ለረሃብና እርዛት፡ ለበሽታና ሞት ዳርጓቸዋል። ሸገር በሚለው ከተማ መስጂድ አፍርሷል፥ አብያተ ክርስቲያን አጋይቷል፡ ካህናት አስደብድቧል፡ አስገድሏል። በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮችን በማንነታቸው ብቻ ከሥራ አባርሮ ለመከራና ለችግር  ዳርጓቸዋል። የድሆች ጎጆ አፍርሶ በአስራ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ጎዳና ላይ በትኗል፡ መድረሻ ያጡ ህጻናትን በጅብ አስበልቷል። 

ብልጽግና ዜጎችን በሃሰት ከስሶ በእስር ያማቅቃል፡ በማጎሪያ ያሰቃያል፣ አሥሮ ምግብና ሕክምና ይነፍጋል፥ ከእስር ቤት አውጥቶ ይረሽናል። በአማራ ክልል ጦርነት ከፍቶ ከተሞችን በድሮንና በከባድ መሳሪያ ይደበድባል። ቤት ለቤት እየዞረ ያልታጠቁ ሰዎችን ይደበድባል፡ ወጣቶችን ደጃፋቸው ላይ ይረሽናል።

እናንት የክልል ብልጽግና ፓርቲ አባላት፡

የፓርቲው አባላት እንደመሆናችሁ መጠን ኦሆዴድ ብልጽግና ለሚፈጸማቸው አሰቃቂ ግፎች ሁሉ፡ እጃችሁ በቀጥታ ባይኖርበትም፡ በፓርቲ አባልነት ብቻ ተጠያቂ ከመሆን ፈጽሞ አታመልጡም። ከተጠያቂነት የምታመልጡበት መንገድ ቢኖር ከወዲሁ ራሳችሁን ከፓርቲው በማግለል ብቻ ነው። በአንዳንድ ክልሎች በሺዎች የሚቆጠሩ የብልጽግና አባላት ፓርቲውን ተሰናብተዋል። የቀራችሁትም በግዜ ለቅቃችሁ ካልወጣችሁ በቀር ለፈሰሰው ንጹህ ደምና በወገን ላይ ለደረሰው ግፍና መከራ ተጠያቂ ከመሆን አትድኑም። 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here