spot_img
Friday, June 14, 2024
Homeነፃ አስተያየትየሸኔ እና የብልጽግና የአምስት ዓመታት ጉዞ፤  ለፋኖ መነሳት ገፊ ምክንያት 

የሸኔ እና የብልጽግና የአምስት ዓመታት ጉዞ፤  ለፋኖ መነሳት ገፊ ምክንያት 

1። የሸኔ እና የብልጽግና የአምስት ዓመታት ጉዞ፤  ለፋኖ መነሳት ገፊ ምክንያት 

በእያደር ባሰ ( ከታዘብኩት) 

ሀ፡ መንግስትነት ምንድን ነው? ሽፍታስነትስ ወይም ነጻ አውጪነት? 

በሌላው ዓለም መንግስት የህዝብ ሰላምን ሊጠብቅ፤ ሊያስጠብቅ በህዝብ አደራ የሚቀበል ሀይል ነው፡፡ መንግስት የማህበረሰብ ጉልበት እና አሌንታ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ ሊሟላ የማይችሉ ፍላጎቶች ( የሰላም እና የደንነትን የጨምራል) በመንግስት ጉልብት መሟላት አለባቸው፡፡ ሰላም የማስከበር ጉዳይ ወይም የፖሊስነት ጉዳይ መንግስት ከሚያስፈልግበት ዋነኛ ምክንያቶች ግንባር ቀደም ነው፡፡ የሆነው ሆኖ በአሁኒቱ ኢትዮጵያ የሰላም ጉዳይ ከመንግስት ሀላፊንተ አንጻር እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ባንድ በኩል የለየለት ጦርነት ከትህነግ ጋር  ተደርጎ በሰላም ደርድር ትቋጨ ተብሎ ሳይረጋ ኡሁን ደግሞ ከፋኖ ጋር ግብግብ ተይዧል፡፡ በሌላ  በኩል በኦሮሚያ ‘ሸኔ’ በሚል የዳቦ ስም የሚጠራ ‘የጠራ የፖለቲካ ግብ የሌላው’ ቡድን መጠነ ሰፊ የግደያ እና የዘረፋ ዘመቻ ላይ ነው፡፡ ዘመቻው በዋነኝነት አማራ በማለት የሚጠሩት፤  ተዋልዶ እና ተቀላቅሎ በሚኖረው ግለሰብ እና ማህበረሰብ ላይ ነው፡፡ ዝምድና የማይገባው ከሀዲ ሰቆቃውን ይመራል እንዲሁም የፖለቲካ ግብ ሊሰጠው ይማስናል፡፡ 

ይህ የፕለቲካ እና የዘረፋ ቡድን መንግስታዊ ሥሥ ልብ እንዲሁም የጥቅም ሸርክና አግዞት እንደፈለገ ይናኛል፡፡ በአንድ በኩል በመንግስት ውስጥ ያሉ ቆራጦች እና የህዝብ አደራ እና ውክልና ሸክም የሚግባቸው የሚያረጉትን ትግል መና በማስቀረት ብሎም የሚላኩ የጸጥታ አካላትን የጭዳ በግ በማስደርግ በመንግስት የሚያሴሩብትን የመንግስት አካላትን መሪ ተብዬዎቹ መለየት አልቻሉም ወይም አልፈለጉም፡፡ ውጤቱ ኦሮሚያ ውስጥ ታማኝ የህዝብ አገልጋዮችን ተስፋ እያስቆሪጠ ነው፡፡ ወይም  ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ በሎም የአማራ ከልል ፋኖ መንግስትን እንዲታግል በር ከፍቷል በሎም ዋና  ገፊ ምክያት ሆኗል፤ ትግሉም ተጀምሯል፡፡

ሆኖም የግድያ እና የዘረፋ ተጠቂዎች በዋነኝነት አማራ ይባሉ እንጂ ሁሉም ጥረው ግረው ትንሽ ጥሪት ያላቸው ፣የሚሰሩ እጆች እና የሚያስቡ አዕምሮ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በዘራፊዎች ኦሮሞ የሚባሉትም ጭምር ጥቃቱ አይቅርላቸውም፡፡ ንብረት ካለው ኦሮሞም ቢሆን፤ በነሱ መስፍርት ማለቴ ነው አያምልጥም፡፡ ማምለጥ የሚችለው በመፈርጠጥ ነው፡፡ አሸዋ ሜዳ የተከማቸው ማህበረሰብ ከወለጋ እና ም/ ሸዋ የተሰደደ ነው፡፡ ቀማኛውም ወደ ሸገር ይሸሻል፤ ከተማዋ መደበቂያ ዋሻ ሆናለች፡፡ የመጨረሻው የጦር ሜዳ እንደምትሆን ግን እሙን፡፡ የጀመረም ይመሰላል፡፡ 

ለ፡ ታዲያ መንግስት ምን ያርግ ወይም ምን ሊያረግ ይችላል? 

1ለ፡ መንግስት እንደ ተጠቂ?

 መንግስት እንደ ተጠቂ ሲተውን እንደማየት የሚያም ነገር የለም፡፡ መንግስት ወይ ስራውን መስራት ወይም አልችልም ብሎ ካቢኔውን አፍርሶ መሰናበት አለበት፡፡ እንደ ተጠቂ እና ምን ላርግ? በሎ ሲብስም በዜጎች ዳተኝነት ላይ ማሳበብ መንግስታው ሀላፊነትን መሸሽ ወይም ድርብ እና የሚጋጩ ግብ ይዞ መዳከርን የሚያመልክት ነው፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ ጀገና ሆኖ ለመታየትበአማራ ክልል ሲዳክር ይታያል፡፡

2ለ፡ ኦሮሚያ?

ኦሮሚያ የሚሰሩ እጆች እና የሚወጥን ልቦና የሚኮላሽብት ምድር ሆናልች፡፡ ባለንብረት ሁሉ ከተሰደደ ወይም ከተገደል የቀረው ማህብረስብ እጣፈንታው ምን ሊሆን ይችላል? ጥቃቅን ነጋዴዎች፣ መምህራን፣ ገበሬዎች፣ የመንግስት ሰራተኛ ሳይቀሩ እየታፈኑ ገንዘብ በመቶ ሺዎች ይጠየቃል፤ ከተከፈለ በኋል መርዶ ወይም ፈጣሪ ከረዳ በዱላ የላቆጦ እና ቅስሙ የተሰበረ ግለሰብ ይመላሳል፡፡ በአንዳንድ አከባቢ ደሞ መሉ ወረራ ይካሄድና ጅምላ ግድያ ይፈጸማል፤ ቀሪው ማህበረሰብ ስደት ይሆናል፡፡ 

3ለ፡ የኦሮሚያ መንግስት ምርጫ?

በገዳይ አስገዳይ ቡድን “ኦሮሞ አይደሉም” የተባሉትን አቶ መልስ ዜናዊ ‘ኤርትራዊያን” ላሏቸውን የወቅቱ ዜጎች የሰጧችውን “ክብር እና ምርጫ” መስጥት እንዲችል ፈጣሪን መለመን ብቻ ነው የሚቻለው፡፡ ወይም የፋኖን ትግል ዳር ማድረስ? በፌደራል መንግስት በኩል ምንም ተስፋ ያለ አይመስልም፡፡ ሊኖርም አይችልም፡፡ ድንበሩም ግልጽ አይደለም፡፡ በዚህ እሳቤ  አንድ ግለሰብ ኦሮሞ ለመሆን ምን ያህል የደም ‘ጥራት’ እንደሚያስፍልግ የአሜሪካን ልምድ ቢጠቀሙ መልካም ይመስለኛል፡፡ አሜሪካ በነጭ አክራርሪ ዘረኞ መዳፍ በነበረች ጊዜ፤ 95% ነጭ መሆን ጥቁር ከመባል አያስጥልም ነበር፡፡ ባሪያነት ንግድ ስለነበረ የጥቁሩ ቁጥር መብዛት ይፈለግም ነበር፡፡ በኦሮሚያ አማራን፣ ሌሎች ጎሳዎችን፣ በተለይ “ቅይጥ እና የደም ጥራት”  ( በሽመልስ አብዲሳ ትርጉም ሰጪነት) ችግር ያለበትን በአፋጣኝ መዝግቦ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡  የፌደራል መንግስት ደሞ አማራ ክልልን እና ሌሎች “ደጋግ” ክልሎችን በማሳማን የአዲስ ሰፋራ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ የዓለም መንግስታትን እርዳታም በመጠየቅ፤ ሰው የሚፈልጉ አገራት ከተገኙ መስጠትም ጥሩ አማራጭ ነው፡፡  ውጤቱ የደም ጥራቱ የተጥበቀ የኦሮሚያ ምድር ለሸመልስ እና አብይ ( በሎም ለኦኔጋዊያን) ኦሮሞዎች ይኖራል፡፡ እንዲሁም  የራሱ የኦሮሞም መዘረፍ ሰበብ ያጣል፡፡ ሰላም ይወለድ ይሆናል፡፡ ምን ትላላችሁ ጎበዝ? 

የሆነው ሆኖ፤ የአማራ ሀዝብ የቆረጠ የምስላል፡፡ ጀገና ልጆች የባት፤ ያአያቶቻቸውን መንገድ ጀምረዋል፡፡ ፋኖ ተነስቷል፤ መነሻዬ አማራ መዳረሻዬ ኢትዮጲያ ብሎ ግብ አስቀምጧል፡፤ ብሶት የወለደው ወጣት ዱር ቤቴ ካለ ሰነባብቷል፡፡ ድልም እየቀናው፤ ማህበረሰባዊ መሰረቱን እያሰፋ ነው፡፡ በተለይ የመንግስት ተበዬው ውንብድና እስከቀጠለ ድረስ ይፍጠንም ያዝግምም ፋኖ ማሸነፉ አይቀሬ ነው፤ ታሪክም የግፏንን የመጨረሻ አሸናፊነት ሲዘክር ነው የሆኖረው፡፡ 

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here