
በሊጋባው
የጽሁፉ አላማ
የዚህ ፅሁፍ አላማ በአማራ ህዝብ ላይ ከዛሬ አራት አስርት አመታት ጀመሮ እየተካሄደ ያለውን የአማራን ዘር ከምድረ ገጽ የማጥፋት መንግስት መራሽ እና ሕጋዊ የሚመስል ሁሉን አቀፍ ዘመቻ እንዲሁም ከ 16ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩትን አማራን የማጥፋት እና መሬቱን የመውረር እንቅስቃሴ እንድሚረዳ አማራ ለአዲሱ ትውልድ የትግል አቅጣጭን ለማሳየት ነው። አሁን ባለው ነባራዊ የአማራ ብሔርተኝት እንቅስቃሴ ተሳታፊ እየሆነ
ያለው አዲሱ የአማራ ትውልድ የሚሄድበትን መንገድ ለማዛባት እና ብሔርተኝነቱን ለማደብዘዝ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለሆነ ወጣቱ ትግሉ እንዳይጠለፍ እንዲሰራ እና ትግሉ በህልም አለም በሚኖሩ ሰዎች እንዳይጠለፍ ለማሳሰብም ጭምር ነው።
በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ስማቸውን ልጠራቸው የምችላቸው ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ወይም ተቋማት አሉ። እነዚህን ተቋማት ወይም ግለሰቦች የማነሳበት እና ገንቢ ሂስ የምሰጠው በሚከተሉት 6 ምክንያቶች ነው።
● እንደ አንድ አማራ በአማራ ስም የሚካሄድ ትግል እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ስለሚመለከተኝ።
● የአማራ ህዝብ የሚመራው እና የሚያታግለው ድርጅት በሚሻበት ሰአት፣ የአማራን ሞትና መፈናቀል
ለማስቆም ዘለቄታዊ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ሞታችንን እና በደላችንን እንደመቆስቆሻ በመጠቀም
በምእናባችው ዉስጥ ብቻ የሚኖርን ቅዠት እንዲያድን የአማራን ወጣት ለመጠቀም የሚታይ ትግል
የመጥለፍ እንቅስቃሴ ስላለ።
● የአማራ ህዝብ በመዋጮ ያቋቋማቸው ድርጅቶች ለአማራ ህዝብ ዘላቂ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ጠላት
ማፍራት በተካኑ አካላት እጅ ስለተጠመዘዙ።
● የአማራ ህዝብ መደራጃ ምሰሶ የሆነን አማራዊ ጎሰኝነት የሚጸየፉ ሰዎች ትግሉን ሊመሩ ስለመጡ።
● የአማራን መሞት እና መፈናቀል እንዲሁም የዘር ፍጅት በቻሉት አቅም ማሳወቅ ወይም (advocate)
በማድረግ የተሳካልቸው አካላት፣ ይህንን ስኬታቸውን የአማራን ፖለቲካ ለማቡካት እንደ ፍቃድ
መጠቀማቸው እና የአማራን ፖለቲካ በተሳሳተ መንገድ እየቀረፁ ስለሆነ።
● በደርግ ጊዜ ያልተሳካላቸውን “ኢትዮጵያን ማዳን” ያልቻሉ አካላት የአዲሱን የአማራ ትውልድ ደም
ለማይሳካ ትግል ለመማገድ ስላሰፈሰፉ።
ማህበራዊ መስተጋብር ( Social fabric )
ሙሉውን በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ