spot_img
Wednesday, May 29, 2024
Homeነፃ አስተያየትየፋኖ ምዕራፍ ሁለት የትግል አላማዎች (ራሴላስ ወልደማርያም)

የፋኖ ምዕራፍ ሁለት የትግል አላማዎች (ራሴላስ ወልደማርያም)

የፋኖ ትዋጊዎች

ራሴላስ ወልደማርያም

ፋኖ በምዕራፍ አንድ የተነሳበትን አላማ ከመቶ ፐርሰንት በላይ አሳክቷል። የዛሬ ስምንት ወር ገደማ በወሎ በተካሄደው ሚስጥራዊ የፋኖ የፓለቲካና የወታደራዊ አመራሮች ውይይት ዋነኛ ፈተና ይሆናሉ ተብለው የተገመቱ

፩ኛ የትጥቅና የተኳሽ እጥረት
፪ኛ ብዙ የፋኖ ታጋዬች በየቦታው መታሰራቸው
፫ኛ አላንቀሳቅስ ያለው የብአዴን መዋቅር የሚሉት ነበር።

እነዚህ ሶስቱ በምዕራፍ አንድ ትግል ተፈትተዋል።  የፋኖ ሀይል በ54 ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች ጥቃት በማድረግ በርካታ መሳሪያና ተተኳሽ ታጥቋል። ይህ የትጥቅ ችግሩን በከፊል ፈትቷል። የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በአማራ ክልል እስከ ቆየ ድረስ ብርሀኑ ተተኳሽ ማስገባት አያቆምም ፋኖም ማርኮ መታጠቁ ይቀጥላል።

ሁለተኛው የታሰሩ ጓደችን ማስፈታትና ታጣቂ ማብዛት ነበር። ይህም ተሳክቷል። በርካታ እስር ቤቶች ታሰብረው የነበሩ፣ ሀገር ሰላም ነው ብለው በየቤታቸው እየኖሩ የነበሩና እየታፈኑ የተወሰዱ ፋኖዎችን በማስፈታና የፋኖ ሀይል ማጠናከር ነበር። ይህም ተሳክታል

ሶስተኛውና ዋናው ይልቃል ከፍያለን መዋቀር ማፍረስና ህዝቡን ከጥርነፋና ከአሳባቂ ማጽዳት ነበር። ይህም ተሳክቷል። ፋኖ ክልሉን ሲቆጣጠር በቪላ ቤትና በv8 መኪና ሸንግሎ ይጋልባቸው የነበሩትን መሀይማን ከፋኖና ከህዝብ ሊያድኑት እንደማይችል ስለገባው እነ ሽመልስ ተልከው እነ ይልቃልን  አባረው አዳዲስ ቀንዳውጣ አሽከሮች ሾመዋል። ይሁን እንጂ ህወሓት ለ27 የተበተበውን መዋቅር አፍርሶ አዲስ መዋቅር በጦርነት መሀል ማዋቀር እንዲህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ አካባቢውን ማደራጀት እና ማስተዳደር በፋኖ እጅ ገብቷል። ትላልቅ ከተሞችን ደግሞ በሺመልስ አብዲሳ የሚዘወረው የኮማንድ ፓስት የሚባለው ነው። እንኳን ህዝብ ሊያሳምን ልፕራሱም ኑሮ የቆቅ ሆኖብፕታል። ሚስቱን ልጁን ወደ አዲስ አበባ ሲያሸሽ እንኳን የሽመልስ አብዲሳ ልዩ ሀይል አዲስ አበባ የአማራ መታወቂያ ይዘህ እትገባም እያለ እየመለስባቸው ነው። ስለዚህ ለራሳቸው ለልጆቻቸው ደህንነት ፋኖ በቅርብ ይሆናሉ።

ዛሬ ታጣቂ አስከትሎ በአማራ ክልል የሚንጎማለል ወይ ስብሰባ የሚመራ ብአዴን የለም።  እነዚህ የምዕራግ እንድ ዘመቻ ግቦች ከተጠበቀው በላይ ተሳክቷል።

የምዕራፍ ሁለት አላማ የስርአቱን አቅም ማዳከም፣ የመንግስት ሰራዊትን የመዋጋት አቅም ማዳከም ማሰላቸት፣ ሰራዊቱ የሚሞትበትን አላማ እንዲጠይቅ ማድረግ፣ የሰራዊቱን ስነልቦና መሸርሸርና የስርአቱን መሰረት መነቅነቅ ነው። ከዚህ በላይ ህዝባዊ ድጋፍን ማበራከት፣ የተዋጊ ኃይልን ማብዛት፣ ጠንካራ የኮማንዶና የከተማ ተዋጊዎችን ማሰልጠን፣ ከወንድም ክልሎች ጋር ግንኙነት መፍጠር፣ የደቡብ የኦሮምያ የአፋር የጉራጌ ወዘተ ፋኖን ማደራጀት ማሰልጠንና ትግሉን እንዲቀላቀሉ ማገዝ ነው።

ፋኖ እስካሁን የፕሮፓጋንዳ ስራውን ትኩረት ስጥቶ አልስራም። አሁን ዝግጅቱን ጨርሷል በየቀኑ በየ ሰአት ሰራዊቱ እራሱን ነጻ እንደሚያወጣ፣ ተበትኖ ያለው ኢትዮጵያዊ እንዴት ከእርድ እራሱን ለማዳን ምን ማድረግ እንዳለበት፣ የአዲስ አበባ፣ የሻሸመኔ፣ የናዝሬት የደብረ ዘይት የአንቦ የፍቼ የአሰላ የጅማ ወዘተ ሰው እንዴት እራሱን ማደራጅትና እራሱን ከመታረድ መከላከል እንደሚችል ስልጠናና ትምህርት ይስጣል።  

ፋኖ ወታደራዊ ድል በህዝባዊ ንቅናቄ ካልታገዘ የተራዘመና ብዙ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ያስከፍላል።ስለዚህ በህዝባዊ አደረጃጀት ላይ አተኩሮ ይሰራል፣ ያደራጃል።

ፋኖ የኢትዮጵያ ሰራዊት እንደ ማገዶ እየተማገደ ማለቁ ልቡን ያደማዋል።  ባንዲራ አዋርዶ ልጆችን እያረደ ህዝብ እየከፋፈለ እናትህ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ አትገባም፣ ልጅህ በአባቷ ባንዲራ አታጌጥም ብሎ በጥጋብ ለሚደነፋ የኦፒዲኦ መንግስት መሞት እንደሌለበትና ጠመንጃውን በ2000 ሺ ካሪ ሜትር መሬት የተገዙት መሪዎቹን በማዞር ከህዝብ ጋር እንዲቆም ፋኖ ድጋፍ ይሰጣል በሰራዊቱ ውስጥም ገብቶ ያደራጃል።

ፋኖ ከትግራይ ህዝብ ከአፋር፣ ከቱለማ፣ ከጉራጌ፣ ከጋሞ፣ ከሱማሌ ጋር ግንኙነት መስመር ዘርግቷል። ውስጥ ካሉ ንቅናቄዌችና አመራሮች ጋር ውይይት በቅርብ ጊዜ ይከፍታል። የነሱን ስጋት ፍህራት በትግሉ ውስጥ አካቶ ለእነሱም አጀንዳ ይታገላል።

ፋኖ ተባብሮ እንዴት የኦፒዲኦን አንባ ገነናዊ ስርአት ማስወገድ እንዳለበት ያወያያል፣ የሽግግር ስርአቱንም አጀንዳዎችና ግቦች በውይይት ያጽድቃል። ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አንባገነንነት ከኢትዮጵያ ተወግዶ፣ ሰላም ሰፍኖ፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት በነጻነት ያለ ካድሬ ረገጣና ጉቡ በሀገሩ ላይ ስርዓት የሚከብርበት። ተፎካክሮ መንግስት የሚሆንበት በነጻነት ሀሳቡን የሚገልጽበት፣ መስጊድ በዶዘር የማይናድበት ቁራኑ የማይዋረድበት፣ ቤተክርስቲያኑ እስከነ አማኙ የማይቃጠልበት ሁሉም የኔ የሚላት ኢትዮጵያን መፍጠር ነው። ይህንን የማይመኝ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ ጋሞ፣ አኝዋክ፣ ቅማንት፣ ሳሆ፣ ኢሮብ፣ አዲስ አበቤ ወዘተ የለም። ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያ ደግሞ ነጻ አወጣሁህ በሚል ቡድን ሳይሆን እራሱን ነጻ ባወጣ ህዝብ ነው። የኦፒዲኦ አገዛዝ ያልረገጠው ያልቀማው በሀገሩ ላይ ባይተዋር ያላደረገው መሀበረሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ የለም። ሁሉም ቄስሎ መስጊድ ሱፈርስ ፈርቶ ዝም አለ እንጂ አንጀቱ ያልቆሰለ የለም። ቤተ ክርስቲያኑ ከነ መእመኑ ሲቃጠል ልቡ ያልደማ የለም። በሰላም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ተከልክሎ አባቱ በሞተላትና ሀገር ሁለተኛ ዜጋ ያልሆነ የለም። ቀበሌ ሄዶ፣ ገቢዎች ሄዶ ጉቦ ካልሰጠሀኝ ድርጅትህን እዘጋብሀለሁ ያልተባለ ዜጋ የለም።

ስለዚህ በምእራፍ ሁለቱ ትግል ወታደራዊ ድሎች ብቻ ሳይሆን ፓለቲካዊ ሌሎችም የሚበሰሩበት፣ በርካታ ብሄረሰቦችና የኢትዮጵያውያን ነጻ አውጪ መጠበቁን ትተው ወደ ትግሉ የሚቀላቀሉበት ምዕራፍ ነው። ፋኖ ለሁሉም የኢትዮጵያውያን በሩ ክፍት ነው። እጃቸውን የሰጡ የደቡብ የመሀል አገር ልጆች ፋኖን ለመውጋት ተልከው እጃቸውን ሰጥተው ከፋኖ ጋር ተቀላቅለው ትግሉን ጀምረዋል። በሚሊዮን ወደ ትግሉ እንደሚገቡም ፋኖ ጥርጥር የለውም። ሁሉም እንደግፋኖ እናቴ አትደፈርም ልጆቼ አይታረዱም ብሎ እንደሚነሳ ጥርጥር የለውም።

ኦፒዲኦ ጠጉራም ውሻ ነው። ጥርስም አቅምም የለውም። በቅርብ ጊዜ ሰንሰለት እናስገባለታለን።

የፋኖ ወታደራዊ ትግል በህዝብ አለት ላይ በጽኑ ስለተገነባ ወደ ፓለቲካዊው ትግል መግባት ግድ ይላል

ዛሬ በቄሌም ወለጋ የምትኖር እናት ብቻ ሳትሆን በደብረ ማርቆስ፣ በወልድያ፣ በባክህር ዳር፣ በጎንደር፣ በደራ፣ በደብረብርሀን የምትኖር እናት የመንግስት ስራዊት መጥቶ በልጄ ላይ ቀይ ሽብር! ነጻ እርምጃ! ይወስድብኝ ይሆን ብላ ትሰጋለች።

ህዝብ ለትግል የተነሳሳ መሆኑ በተግባር የታየ ቢሆንም እነ ጄኔራል ማርዬና እና እነ በአበባው ታደሰ በአማራ ወጣት ላይ ቀይ ሽብር ያውጃሉ ብሎ የጠረጠረ ህዝብ አልነበረም። አሁን ወጣቶችን ሴቶችን ከየቤታቸው እያወጣ ሲረሽኑ። ቁስለኞችን ከሆስፒታል አልጋ እያወጡ በጭንቅላታቸው ላይ መኪና ሲነዱ ያየው እናት አባት ልጄ ከቤት ተጎትተህ ሲኖ ትራክ ከሚነዳብህ እንደዉንድሞችህ ወጥተህ እየታገልክ ሙት እያለ ልጁን ወደ ፋኖ መርቆ እየሸኘ ነው።

ስለዚህ ምዕራፍ ሁለት እውነተኛው የነ ጄ/ል ምርዬ እና አበባው ለአማራ ህዝብ ያላቸው እቅድ ለህዝብ ግልጽ ተብሎ የታየበትና እነሱ በ2000 ካሬ ሜትር መሬት እናታቸውን የሚደፍሩ ሞራል ቢሶች መሆናቸውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሰራዊቱም ተገንዝቧል።

ሰራዊቱ በአንድ በኩል ለሀገርህ ለባንዲራህ ሙት እየተባለ እየተማገደ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሚስቱን ልጁ የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለው ልብስ ለጥምቀትና ለመውሊድ ለብሰሻል እየተባሉ በፌዴራል ፓሊስና በኦሮምያ ልዩ ሀይል ሲጠፈጠፏ ተመልክቷል።

እራሱ የሰራዊቱ አባል እና የብአዴን አባል የሆነ ሰው ወደ አዲስ አበባ ለህክምናም ሆነ ለዘመድ ጥዬቃ አትገባም እየተብለ እየተመለሰ ነው። ታድያ ይህ ሰራዊት ለኦነግ ባንዲራ ነው የሚሞተው ብሎ ራሱን መጠየቅ ይጀምራል? ባንዲራዬን ኦፒዲኦ መሬት ላይ እየረገጠ እንዴት ለሀገርህ ሙት ይለኛል እያለ እየጠየቀና እየተወያየ ነው። እንዲህ በኢትዮጵያ ጥላቻ ያበደን አይን ብርሀኑ ጁላን መታዘዝ ለዘመናት በዚህ ባንዱራ ተጠቅለው የሞቱ ጀግኖችን መክፈት ነው የሚለው ጥያቄ ተነስቷል። ከመቶ የማይበልጡ ጀኔራሎችንና ካድሬዎችን ረሽኖ ከህዝብ ጋር የሚያብርበት ቀን ደርሳል።

የሰራዊቱ ህይወት በካሪ ሜትር ስንት ቢገመት ነው ለአዋጊዎቹ 800 ካሪ ሜትር የተሸለሙት የሚለው ጥያቄ ተጭራል። በአጭር ቀን በአፈሙስ ምላሹን እናያለን።

ስለዚህ ይህ ግንዛቤ በሁሉም መሀበረሰብ መሀል ግንዛቤ ተፈጥሯል። ስለዚህ ይህ ሰራዊት በአለቆቹ ላይ ጠመንጃውን አንስቶ ከህዝብ ጋር ቆሞ ስርአቱን እንደሚያስወግድ ጊዜ ሩቅ አይደለንም። ይህ ሲጀመር በምዕራፍ ሶስት መጀመሩ ይታወቃል።

የፋኖ ትልቁ ስጋት

አብይ አህመድ ለፓርላማ ባደረገው ንግግር በአሁን ሰአት “መነፈንቅለ መንግስት ማሰብ እብደት ነው።  በአንድ ሰአት ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚታረዱበት tragedy/ ትራጄዲ/ እንፈጥር ይሆናል እንጂ መንግስት አይኮንም” ብሏል።

ይህንን አብይ ለማስፈራት ብቻ ሳይሆን ለመተግበርም እቅድ ይዞ ሪፓብሊካን ጋርድ፣ የኦሮምያ ልዩ ሀይል፣ ኦነግ ሸኔ፣ የአዳነች አቤቤ የአብዬት ጠባቂ ስልጠና እየስጠ ለእርድ እየተዘጋጀ ነው። የዚህን ማምከኛ ዝግጅት ማድረግ አዲስ አበባን ከመቆጣጠር በፊት መቅደም አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። ስለዚህ አብይን ማባረር ብቻ ሳይሆን ይሄንን አብይ ያቀደውን የመቶ ሺዎች ግድያ እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል እቅድና ስራ ይጠይቃል። ይህንን ማስቀረት የሚችለው ህዝቡ ራሱን በማዘጋጀት ብቻ እንደሆነ ስምምነት አለ።

በአጭሩ ህዝብ እራሱን አደራጅቶ እራሱን የመከላከያ አቅም ፈጥሮ ልጆቹን ሚስቱን በመከላከል እንጂ ፋኖ ወይንም የመንግስት ሐይል ያድነኛል በማለት የለበትም። የሩዋንዳ (Rwanda Patriotic Front) የፓል ካጋሜ ጦር እያጠቃ ኪጋሌን ጋራ ላይ ሆኖ እየተመለከተ ነው የሁቱ ሚሊሻዎች 900 ሺህ ሰው ያረዱት። የአብይና፣ የሽመልስንና የአዳነች አቤቤን ዝግጅት ማጣጣል ጅልነት ነው። ስለዚህ ፋኖ ወደ አዲስ አበባ ከመቅረቡ በፊት ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ማስገንዘብና ህዝብን ማዘጋጀት ግድ ይላል።

ስለዚህ ይህ ሊታረድ ያዘጋጁት ህዝብ ዛሬውኑ ይህ ሀይል ግልብጥ ብሎ ቢመጣ እንዴት እድናለሁ ብሎ ልጄን አድናለሁ ብሎ ማሰብ አለበት፣ ለዚህም የስነልቦና ብቻ ሳይሆን አካላዊ ዝግጅት ይጠይቃል። ጎረቤት ከጎረቤቱ ይህ ቢመጣ ብሎ ጠይቆ የየራሱን እቅድ ማውጣትና መተግበር አለበት። “ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ፣ አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ፣ ያልጠረጠረ ተመነጠረ፣ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የሚባሉት ተረቶች ዳተኞችን ለምንቃት ነውና። የአብይንና የሽመልስን እቅድ መክሸፍ የሚቻለው “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” በሚለው አስተምህሮ ብቻ ነው። የአዲስ አበባ ስድስት ሚሊዮን ድር በቀላሉ ያራት ኪሎዋን የጥንቆላ ፒኮክ ማሰር ይችላል።

ስለዚህ የአዲስ አበባ፣ የናዝሬት፣ ቢሾፍቱ፣ የሻሸመኔ፣ የአሰላ ወዘተ እንደ ድር አንድ ሆኖ የኦፒዲዮን ገዳይ እጅና እግር ማሰር ይችላልና ተዘጋጁ፣ ተማከሩ፣ ከቻላችሁ እራሳችሁን ልትከላከሉበት ዱላም ሆነ መጥረቢያ አዘጋጁ። በአንድ ፏጨት በአንድ ጩሀት ግልብጥ ብላችሁ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ እንደ አጥር ሆናችሁ ልጆቻችሁን ከመታረድ ሚስታችሁ ከመድፈር ታድናላችሁ።

ለዚህ ነው ነው ፋኖ “የነጻ አውጪና የነጻ ወጪን”ትርክት እንተው የሚለው። ፋኖ ራሱን ነጻ አውጥታል፣ የአማራ ክልል ሰው ነጻ አውጪ አልጠበቀም እራሱን ነጻ አውድትቷል። ስለዚህ የስነልቦናህን ዝግዝጅት ጀምር ፣ተዘጋጅ፣ ታጠቅ ሰልጥን። ያለበለዚያ ከመቶ ሺዎች ከሚታረዱት ቀን እሩቅ አይደለም። እነ አዳነችና ሽመልስ ሊያርዱህ ተዘጋጅተዋል፣ አብይ ስልጣንን ከነካችሁ በሰአታት ውስጥ በመቶ ሺዎች ለማረድ ተዘጋጅተናል ብሏል።  ስለዚህ ያልሰማህ ካለህ አብይን ከዩቲዮብ ፈልገህ አድምጥ። እንቅጩን ነግሮሀል። በመቶ ሺዎች እናርዳለን ብሏል። እኛ ደግሞ አንድ ሰው ሳይታረድ የኦፒዲኦን ባለስልጣኖች በቁጥጥር ስር ለማድረግ እንሰራለን። እናንተም ተዘጋጁ። አግዙ። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር የሚለውን ጽንሰ አሳብ በድንብ አጥኑት። ድር ቢያብር ነው። ካበረ ብቻ ነው። ካበራችሁ ትድናላችሁ ካላበራችሁ ትታረዳላችሁ። አርዳችሀለሁ ብሏል።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here