spot_img
Friday, June 14, 2024
Homeነፃ አስተያየትበሕብረት ካልቆምን በየተራ እናልቃለን (ከአሰፋ ታረቀኝ)

በሕብረት ካልቆምን በየተራ እናልቃለን (ከአሰፋ ታረቀኝ)

War in the Amhara region

ከአሰፋ ታረቀኝ

በደርግ ዘመን ሰው በዘሩ ወይም በጎሳው ተመንዝሮ አልተገደለም ወይም አይገደልም ነበር፡፡ ኢሀፓና መሰሎቹ ግን መሪዎቹን ፋሽስቶች፣ ሥርአቱን ፋሽዝም ብለው ሰየሙት፣ የተራዘመ ፕሮፓጋንዳም ሠሩበት፤ ሰውን በጎሳው፣ በነገዱ፣ በቋንቋውና በሀይማኖቱ እየለየ የሚረሽን መንግሥት መጥቶ አገር ሲያጠፋ፣ በህይወት የተረፉት ኢህፓያዊያንም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው ድምጻቸው ጠፋ፡፡

ኦሮሙኛ ተናጋሪ የሆኑ ግልገል ፋሽስቶች የኢትዮጵያን በትረ-መንግሥት ከተቆጣጠሩበት ጊዜ አንስቶ፣ የሰው ልጅ በጎሳው በቋንቋና በዕምነቱ እየተለየ ይገላል፣ይባረራል፣ በቤት ውስጥ ተዘግቶ ይቃጠላል፣ በዛፍ ላይ ተዘቅዝቆ ይሰቀላል፡፡ የትህነግ ቅብጠት ሰበብ ተደርጎ ትግርኛ ተናጋሪው ተመታ፤ ባለፉት አምስት አመታት በሥልጣን ላይ ያሉ የኦሮሞ ግልግል ፋሽስቶች የፈጁትን አማራ ያክል፣ ባህር ተሻግሮ የመጣው ፋሽስቱ ጣሊያን አልፈጸመውም፡፡ ናዚ ጀርመን ፍጅቱን የጀመረው በጥቂት አይሁዳዊያን ላይ ነበር፡፡ ጥቂት በጥቂት እያለ ፍጅቱን ካለማመደ በኋላ፣ ወደ አጠቃላይ የአይሁዳዊያን ፍጅትና የአውሮጳ ውድመት አሸጋገርው፡፡ ለአብይ አህመድ ንግሥናና ከኢትዮጵያ ሞት በኋላ ለምትወለደው “ኦሮሚያ” ተገዳዳሪ ይሆናሉ ተብለው የሚፈሩት አማራና ትግሬ፣ አርቆ ለማየት ባልታደሉት ስግብግብ የትህነግ መሪዎች በለኮሱት ጦርነት፣ ሁሉቱ ህዝቦች ተቋስለዋል፣ በአብይ አህመድ የሚመራው የፋሽስት መንግሥትም በኢኮኖሚም በማህበራዊ ቀውስም አዳክሟቸዋል፡፡ 

“ኦሮሚያ” ተብሎ በተከለለው የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖረውን አማራ በማረድ፣ በመግደል፣ ከነንፍሱ በስለት ሰንጥቆ እስከመጣል የደረስ ስቃይ አወረዱበት፡፡ ለዚህ የተሰጠው ምላሽ ምንም እንዳልሆነ ሲረዱ፣ በአድስ አበባ ዙሪያ ያሉትን ከኦሮሞ ጎሳ ውጭ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን አፈረሱ፣ ህዝቡን እሜዳ ላይ አፈሰሱት፡፡ ይህም ድርጊት ጎሳን ቋንቁንና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ሆን ብሎ ህብረተስብን ማስቆጣት( provocation) ሌላኛው የፋሽዝም መታወቂያ ነው፡፡ ከፋፋይና ትውልድ አውዳሚ የሆነው የኦሮሚያ መዝሙር ይዘመር፣ የኦሮሞም ባንድራ አድስ አበባ ይሰቅል አሉ፡፡ አዲስ አበቤ ተቆጣ፡፡ተመጣጣኝ ከተማ ዙሪያውን እንገነባለን ብለው ተነሱ፡፡ ክርስትናና እስልምና ኦሮማዊ አይደሉም(  foreign) ናቸው አሉን፡፡ ይህም ከፋሽዝም ዋና ባህሪያት አንዱ ነው፡፡ ትናን እንድህ ነበርን፣ እኛ ዛሬ እንድህ መሆን አልነበረብንም እያሉ ህብረተሰብን ቁጭት ውስጥ መቆስቆስና ለጠባብ አላማቸው መጠቀሚያ ማድረግ ሌላኛው የፋሽዝም መገለጫ ነው፡፡ለዚያም ነው የ16ኛ ክፍለ ዘመን የገዳ ሥርአት መተዳደሪያችን፣ የኢሬቻ ባህል ባህላችን እንድሆን የምንሰበከው፡፡

ከላይ እንደተገለጸው ሆን ብሎ ማስቆጣትና ጠብ ጫሪነት(provocation)፣ ከፋሽዝም ዋና ባህርያት አንዱ ነው፡፡ ለዚህም ነው በሁሉም አቅጣጫ በጠላት ተከቦ የሚገኘውን አማራ ፋኖ የአብይ መንግሥት ከሁሉ ቀድሞ ትጥቅህን ፍታ ያለው፡፡ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንድሉ፣ በትጥቅ ማስፈታት ሰበብ አማራውን ለማንበርከክ የታቀደ ዘመቻ ነው፡፡ በአብይ አህመድ መሪነት እየገነፈለ ያለ ፋሽስዝም ለማንም ምህረት የለውም፡፡ የጀርመን ናዚዝምና የጣሊያን ፋሽስዝም መጨረሻ ላይ ከባድ ዋጋ ያስከፈሉት የራሳቸውን ህዝብ ነው፡፡ ኦሮሞን እወክላለሁ የሚለው የፋሽስት ስብስብ፣የመጨረሻውን አስከፊ እዳ የሚያመጣበት በኦሮሞ ሕዝብላይ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚሠራውን ልብ ብሎ የሚያይ ሰው “ የት ነው እየኖረ ያለው?” ያሰኛል፡፡ ቤት የፈረስባቸውን፣ የተሳደዱትን፣ ከአድስ አበባ 130 ኪሜ ርቀት ላይ ሰፍረው ያሉትን 800000(ስምንት መቶ ሽህ) ከወለጋ የተፈናቀሉ አማራወች ዘወር ብሎ አይቷቸው አያወቅም፡፡ ማየት የሚፈልገው ክርስቶስ የሞተለትን፣ የተጎዳውን፣ በሀዘን የተጎሳቆለን የሰውን ልጅ ሳይሆን፣ ፓርኮችን፣ የሙዝና የብርቱካን ዛፎችን፣ ፓፓያና አቦካዶ ዛፎችን ነው፡፡ ለፋሽስቶች ምን ጊዜም ሰው እቃ ነው፡፡ ለዶ/ር አብይ አህመድ ባለቤቱ የምትዘምርለት ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቀው ክርስቶስ መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ የባሏ የጭካኔ ጥግ ያንን አያሳይምና፡፡ 

 የሀገር፣ የትውልድና የታሪክ ባላደራነት የሚሰማችሁ፣ 

  • በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ የትግራይ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የከንባታ፣ የሀድያ፣ የጋሞ፣ የሶማሌ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ ከኦሮሞ “ምሁራን” አጠቃላይ እብደት የተረፋችሁ እውነተኛ የኦሮሞ ምሁራን፣ አክራሪነትን ከትህነግና ከኦነግ ተውሶ ከሚጮኸው አማራ ውጭ ያላችሁ የአማራ ምሁራን፣ የአገው፣ የሽናሻና ጎሳችሁን ያልጠቀስኳችሁ ምሁራን ሁሉ፣ ኢትዮጵያ በዘመኗ ሁሉ ገጥሟት የማያውቅ አደጋ የተደቀነባት መሆኑን አምናችሁ በጋራ በመቆም ሀገር አድኑ፡፡ በኦሮሞ ብሄረተኞች እየተተገበረ ያለው ፋሽዝም፣ አማራና ትግሬን ደብድቦ በማስገበር የሚያቆም አይደለም፡፡ ባንድ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ኦሮሞ በአፍሪካ ውስጥ ታላቁ ብሄር ነው ማለታቸውን አንርሳ፡፡ ኦሮሞኛ ከቀርሳ እስክ ሞምባሳ ድረስ ይነገራልም ተብለናል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያን ብሄረሰቦች፣ ኦሮሞን ጭምር ከአደጋ ለማትረፍ ተባባሩ፤ የቂም እስረኛና የበቀል ምርኮኛ አትሁኑ፡፡

በጠራራ ጸሀይ ፍጡራንን ጨፍጭፎ አለመጠየቅ የተለመደው በቡራዩ የንጹሃን ጋሞዎች ፍጅት ነው፡፡

አማራው ከ “ኦሮሞ መሬት” የሞተው ሞቶ የተረፈው ተሰዷል፤ የሰሜን ወሎው ጳጳስ አቡነ ኤርሚያስ “ ከወለጋ የተሰደዱ 40 ሽህ ስደተኛ በኔ ሰበካ ጉባኤ ክልል ውስጥ አሉ” በማለት በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ እኒሁ ጳጳስ፣ በኦርቶዶክስ ዙሪያ ተንስቶ በነበረው ውዝግብ፣ ስም ሳይጠቅሱ፣ “በኦሮሚያ አካባቢ  የሚሾሙት ጳጳሳት፣ ኦሮሙኛ መቻላቸው ብቻ ሳይሆን፣ በእናትም በአባትም ንጹህ ኦሮሞ መሆናቸው መረጋገጥ አለበት ተብለናል” ነበር ያሉት፤ ንጹህ የአርያን ዘር አልነበር ያለው ሂትለር? አደጋው አፍጥጦ መጥቷል፤ ሀገር በሞት አደጋ ላይ ናት፡፡ በኦሮሞ አክራሪዎች ተሸካሚነት እየገንፈለ ያለው ፋሽዝም ቶሎ ካልተገታ መዘዙ ማንንም አይምርም፡፡  ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ የትኛውንም ጎሳ ወይም ነገድ አይወክልም፡፡ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ትመሠረት ዘንድ ድግሡ እየተዘጋጀላት የምትገኘው “ኦሮሚያ” ከተፈጠረች በኋላ፣ አገር አለኝ ብሎ ሊያወራና ሊኮራ የሚችል ማነው? ትዋጣለህ ወይ አገር ለቀህ ትሄዳለህ፡፡ ከየጎሳው ጠብጠብ ብልው የሥልጣን ፍርፋሪ የተጣለላቸው አሉ፤ ፋሽዝም የቂሎች ስብስህ አይደለም፡፡ ማታለል ይችላል፡፡ በአብይ አህመድ አፋኝ ቡድን ውስጥ አማካሪው ረድዋን ሁሴን ጉራጌ ነው፤ የአፈናው ብርጌድ ሥራ አስፈጻሚ ተመስገን ጥሩነህ አማራ ነው፡፡ ማን ብቻውን ይሞታል? መቸም ጊዜ እንድህ እንደሆነ አይቀር! ፈገግተኛው ፋሽስት አየሩንም ምድሩንም እንደተቆጣጠረ ተማምኗል፤ ለሱ ያልገበረ ሁሉ መወገድ አለበት ብሎ አምኗል፡፡

“አሉኝ በለው በለው፣ አሉኝ ጣለው ጣለው አውሬ መስያቸው፣

የሰው ዘር መሆኔን ማን በነገራቸው” 

አለ ግፉ የጠናበት ያገሬ ልጅ፤

ፋኖ መሳሪያውን አንስቶ አውሬ አይደለሁም እያባረርክ አታጠፋኝም ብሎ ራሱን መከላክል ጀምሯል፡፡ ለጊዜው ዝም ያሉን ቢመስልም፣ ለኦሮሞ ፋሽስቶች ሁላችንም አውሬዎች ነን፡፡ በየተራ እየታደንን መጥፋታችን የማይቀር ነው፡፡ ይህንን እኩይ አካሄድ በህብረት መቋቋም ግድ ይላል፡፡ “ግልገል አማራ” የሚል ስም ተስጥቶት ጉራጌ እየተፈጀ አይደል?

 በሕብረት ቆመን ካላስቆምነው በየተራ እናልቃለን፤ 

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. Dear Aseffa, Thank you so much for your eye opening article. Yes, we have to stand together against the mad Abiy. His dream of being a king will not come easily.

    • I agree. Why do you choose the nick name I was using in this site and one other related for years. If it is not on purpose I wish you change your nick name.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here