spot_img
Friday, June 14, 2024
Homeነፃ አስተያየትበዉጭ ሆናችሁ ፍኖዎችን ለምትረዱ ልዩ ልዩ ሀይሎች የተሰጠች አጭር ምክር እና የሀሳብ...

በዉጭ ሆናችሁ ፍኖዎችን ለምትረዱ ልዩ ልዩ ሀይሎች የተሰጠች አጭር ምክር እና የሀሳብ አቅጣጫ

ሆናችሁ ፍኖዎችን ለምትረዱ
ከኢትዮጵያ ኢንሳይት የተገኘ

ሸንቁጥ አየለ

———–

1. የምትፈልጉትን አድርጉ ግን እኔ የምፈልገዉ ብቻ ይሁን ከሚል የመደብ ትግል ቅኝታዊ ፖለቲካ ዉጡ:-

——–

የምትፈልጉትን ፋኖ በተናጠል ወይም ደግሞ ፋኖዎች ተባብረዉ እንዲቆሙ ለማድረግ በምትችሉት መንገድ ሁሉ ድጋፍ አድርጉ::ሆኖም አንዱን የፋኖ ቡድን ደግፋችሁ አንዱን ፋኖ መንቀፍ ወይም ሌላዉ ፋኖ እንዲከስም አትስሩ::ፋኖዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች አይደሉም::ፋኖ የሀገር እና የህዝብ ተፈጥሮአዊ የመከላከያ ሀይል ነዉና አፈጣጠሩ እና በተነሳሽነት ወደ ትግል የገባበትም መንገድ የተለዬ ነዉ::ፋኖዎቹ የሚተባበሩት የጋራ የትብብር ተግባራዊ ስልት እና ስትራቴጂ ሲኖራቸዉ ስለሆነ ከፖለቲካዊ አመለካከት እና የተለመደዉ ፓርቲያዊ አካሂያድ አጥብቃችሁ ትርቁ ዘንድ በግዚአብሄር ህዝብ ስም ትለመናላችሁ::

2. ተግባር ተኮር ትብብሮች ላይ አተኩሩ:-

——–

በትልልቅ ስትራቴጂያዉ ጉዳዮች ላይ ትብብር እንዲኖር በተለይም ተግባር ተኮር ትብብሮች እንዲኖሩ በትህትና ስሩ::ለምሳሌ ፋኖዎች የራሳቸዉን የገቢ ምንጭ (ለምሳሌ ንግድ:ቀሬጥ እና ልዩ ልዩ ሌሎች ተጓዳኝ የገቢ ምንጮች) በሀገር ቤት እንዴት አድርገዉ ሊያዳብሩ ይችላሉ የሚል ሰነድ በማዘጋጀት ስትራቴጂዎችን በመንደፍ በጋራ እና በተናጠል ወደ ተግባር እንዲገቡ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ቁልፍ ስራዎች ናቸዉ::ሌላዉ ነጻ የወጡ አካባቢዎችን ፋኖዎች በምን መልክ ያስተዳድሯቸዉ የሚሉ ሰነዶችን በዉጭ ሆናችሁ የተለያዩ ፍኖዎችን የምትረዱ ሀይላት በትብብር መስራት ትችላላችሁ::

3. እኔ ብቻ ከሚል እብጠት ዉጡ:-

——

አሁን የተፈጠረዉን የፋኖዉን መታጠቅ ብሎም የነጻነት ቀንዲል ሆኖ እንዲነሳ ያስተባበረዉም የመራዉም እግዚአብሄር ብቻ ነዉ::ስራዉም የእግዚአብሄር እንጂ የማንኛችሁም ሚዲያዎች:የድጋፍ ድርጅቶች ወይም የማንኛዉም አክቲቪስት የተለዬ እና የተናጠል ስራ አይደለም:: እግዚአብሄር በፈቀደላችሁ መጠን ግን በሂደቱ ላይ የየራሳችሁን አሻራ አሳርፋችኋል::አሁንም እግዚአብሄር የህዝብን ጠላቶችን እያደናበረ ስራዉን እየሰራ ነዉ:: በመሆኑም አንዳንዶቻችሁ አሁን ከምታሳዩት እኔ ብቻ ከሚል እብጠት በፍጥነት ትወጡ እና በትህትና ትተባበሩ ዘንድ በእግዚአብሄር ህዝብ ስም ትጠየቃላችሁ::ለእብጠት ለእብጠት ኢህአፓም:ድርግም:መኤሶንም :ቅንጅትም: ግም7ም ብዙ እብጠት እና እርስ በርስ መበላላት አድርገዋል::ዉጤቱን ታዉቁታላችሁ::ክፋት ሸር እና እና እብጠት ለእግዚአብሄር ህዝብ ጥፋት እንጂ ድህነትን አያመጣም::መሸነፍን እንጂ አሸናፊነትን አያመጣም:: እናም ወደ ቀና መንፈስ ተመለሱ:: አሁን የትህትና የእዉነት እና የወንድማማችነት መንፈስ ብቻ የፋኖዉን ሀይል አሸናፊ ያደርገዋል::ወንድሜ ወንድሜ የምትለዋ የፍቅር ሚስጢር ላይ አተኩራችሁ ተባበሩ::ያኔም የድሉ ፍጥነት ከድምጽ ፍጥነት ገስግሶ ይመጣል::

4. አንዱን እያወደሳችሁ ሌላዉን የምትከሱ አክቲቪስቶች እረፉ :-

———–

በእብር ስም ተደብቃችሁ አንዱን የአማራ ስብስብ እያወደሳችሁ ሌላዉን የምትከሱ አክቲቪስቶች እረፉ::ባልተጨበጠ እና በበሬ ወለደ መረጃ ወይም በሚመስል መረጃ ስም ማጠልሸታችሁን አቁሙ:: ጥርት ያለ መረጃ ከተገኘባቸዉ የአማራ ጠላቶች ማለትም ከብአዴናዉያን:አብን: ኦነጋዉያን/ኦነጋዉያን:ህዉሃታዉያን:የግም7/ኢዜማ ሀይላት ዉጭ ያሉ ሀይሎች ላይ መረጃ እስኪገኝ ለገሮችን በቅርበት ከመከታተል የዘለለ አሉታዊ ክስ አይኑር:: ጥርት ያለ መረጃ ሳይኖር በይሆናል ክሱ ኪሳራ ነዉ::የማትስማሙበት ሀሳብ ሲኖር በሀሳብ በገሃድ ሞግቱ::ሙግቱም ያለክስ እና ያለነቀፋ መሆን ይችላል::

5. ፋኖ የሀገር መከላከያ በፍጥነት እንዲመሰርት ተግባራዊ ትብብር የሚያደርግበት ሁኔታ በፍትነት ይመቻች::እንዲሁም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሄን ሀሳብ እንዲደግፍ የሽግግር መንግስት ሁሉም ጸረ ህዝብ ያልሆነ ሀይል በጋራ የሚተማመንበት ሂደት ይነደፍ:-

————-

ከሁሉም ከሁሉም በላይ ግን በአንድነት እና በጋራ ተባብረዉ ፋኖዎች እና የታጠቁ ልዩ ልዩ ሀይላት እራሳቸዉን በተግባራዊ ስራ በማስተባበር ወደ ሀገር መከላከያ ሀይነት እንዲያድጉ የሚያስችላቸዉን ታላቅ የስትራቴጂ ሰነድ በጋራ ሆናችሁ ለማዘጋጀት በተግባራዊ ትብብር ተነሳሱ:: ይሄንንም እዉን ለማድረግ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት እና በዚህም የሽግግር መንግስት ዉስጥ የሚሳተፉ ጸረ ህዝብ ያልሆኑ ሀይሎች ሁሉ የፋኖዉ ሀይል መከላከያ ሀይልን በፍጥነት እንዲመሰርት ከዚያም ዘሎ ልዩ ልዩ ኢትዮጵያዊ ነገዶችን በማስተባበር ከልዩ ልዩ ነገዶች የሚጣዉጣጣ ሀገራዊ የመከላከያ ሰራዊት እንዲመለምል እንዲያሰለጥን ብሎም እንዲያቋቁም የሚያስችል ስትራቴጂክ ግብ ላይ ስራ ስሩ::ይሄንንም የፋኖ መሪዎች ተቀብለዉ እንዲያጸድቁትና ይሁንታ እንዲሰጡበት አድርጉ::

6. የህልዉና ፈተና የተጋረጠበት ህዝብ ከፊታችሁ አለና ጉዳዩ ከፖለቲካ በላይ መሆኑን ግንዛቤ ያዙ:-

————-

በጥቂቱ ርካታ ተዉ::ጥቁር ልባችሁን አዉልቃችሁ ጣሉ::ብዙ ከፊታችሁ አለ::ከሁሉም በላይ የህልዉና ፈተና የተጋረጠበት እና የሚድን ህዝብ ከፊታችሁ አለ::የህልዉና ፈተና የተጋረጠበት ህዝብ ከፊታችሁ አለና ጉዳዩ ከፖለቲካ በላይ መሆኑን ግንዛቤ ያዙ::

7. ስራዉን እግዚአብሄር ሰርቶታል

ስራዉን እግዚአብሄር ሰርቶታል::ይሄን በፍጥነት ወደ እዉነት ለመለወጥ እና ኢትዮጵያንም ለመቆጣጠር ቀዳሚዉ መርህ እዉነት ቅንነት እና የጋራ መከባበር ነዉ ቅንነት ወሳኝ ነዉ::

—————-

ይህችን አጭር ምክር እየደወልኩ ለማቃችሁ ለማስረዳት ሞክሬአለሁ ወይም በኢሜይል እንዲደርሳችሁ ሞክሬአለሁ::በአደባባይም እንዲህ አካፈልኳችሁ::በቅንነት ደግማችሁ አንብቧት::የማሸነፊያዉ ቁልፍ እላይዋ ላይ ተንጠልጥሏል:: ወንድሜ ወንድሜ ወደሚል መንፈስ ተመልሳችሁ በቅን ልብ ተባብሮ መስራት ቁልፍ የመዳኛዉ ስልትና ስትራቴጂ መሆኑን እንረዳ::

————-

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

  1. መቼ ነው ከዚህ ጠባብ የዘር ፖለቲካ የምንላቀቀው?
    ለኔ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here