spot_img
Monday, June 24, 2024
Homeነፃ አስተያየትዘርፈ ብዙ የገቢ ምንጮችን ለፋኖዎች/ለነጻነት ሀይላት/ እንዴት መፍጠር ይቻላል?

ዘርፈ ብዙ የገቢ ምንጮችን ለፋኖዎች/ለነጻነት ሀይላት/ እንዴት መፍጠር ይቻላል?

ለፋኖዎች

ሸንቁጥ አየለ

ጦርነቱ በዐጭሩ ቢጠናቀቅም ወይም ረዥም ጊዜ ቢፈጅም ህዝባችን በምድሪቱ ይኖር ዘንድ ፋኖዎች/የነጻነት ሀይላት የግድ ማሸነፍ አለባቸዉ::

በመሆኑ ከልዩ ልዩ ሁኔታዎች: ታሪካዊ መሰል ጭብጦች እና አለም አቀፍ ልምዶች ጋር በማዛመድ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮችን ፋኖዎች/የነጻነት ሀይላት ተግባራዊዕንዲያደርጉ ማገዝ ይቻላል::

የተወሰኑ የገቢ ምንጮችን ለመትቀስ:-

1. ከደጋፊዎች ገንዘብ ማሰባሰብ/Donations and Support from Sympathizers/ :- ይሄ አሁን የተለመደዉ እና ዋና አካሂያድ ይመስላል

2. ከዉጭ ሀይላት/መንግስታት/ቡድኖች ድጋፍ ማሰባሰብ(Foreign Sponsorship);- ይሄ በደንብ አልተሰራበትም::ልዩ ልዩ የፋኖ/የነሳነት ሀይላት የድጋፍ ቡድኖች በትብብር በዚህ ጉዳይ ላይ መክረዉ እና ጊዜ ወስደዉ መስራት ያስፈልጋል::

3. በቁጥጥር ስር ከገቡ ዐካባቢዎች ታክስ አና ቀረጥ መሰብሰብ (Taxes and Levies in Controlled Areas):- ይሄ በጣም ወሳኝ የገቢ ምንጭ ነዉ::በፍጥነት ስርዓት ተበጅቶለት ወደ ስራ ሊገባ ያስፈልጋል::ልዩ ልዩ የፋብኖ ደጋፊ ቡድኖች እና ማህበራት በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ወስደዉ አፋጣኝ የስር ዓት ዝርጋታ : የሰነድ ዝግጅት ብሎም በልዩ ልዩ አካባቢ ያሉ ፋኖዎች/የነጻነት ሀይሎች በጋራ እንዲተገብሩት የጋራ ስልተናዎች ማዘጋጀት ወሳኝ ነዉ::

4. በፋኖዎች/በነጻነት ሀይላት/ ቁጥጥር ስር የሚሰሩ ልዩ ልዩ ለትርፍ ያልሆኑ ወይም ትርፋማ የሆኑ ተቋማትን መመስረት

5.የማ እድናት ቁፋሮ ላይ እና የከበሩ ድንጋዮች ላይ መሰማራት

6.የዉጭ እና የሀገር ዉስጥ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረኮችን በስፋት መተግበር (External and Internal Fundraising)

7.ከጠላት ሀብት አሰባሰብ ስልትና ስትራቴጅ መዘርጋት

ከላይ ከተጠቀሱት ዉጭ ሌሎች ከእስከ 20 የሚደርሱ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጭ ዘርፎች አሉ::ለምሳሌነት እነዚህ በቂ ናቸዉ::

—————————–

ተግባር መር የትብብር ስትራቴጂ እና ስልት ለፋኖች ደጋፊዎች ሁሉ::

በዉጭ ሀገር ያሉ የፋኖ/የነጻነት ሀይላት ደጋፊዎች/ቡድኖች/ማህበራት/ግለሰቦች ነገሮችን ሰፋ አድርጎ በማንሰላሰል እና ጥናት በማድረግ የተሻለ የመተባበሪያ ስትራቴጂዎችን በመተግበር እና ለፋኖዉ በማመቻቸት ብዙ ስራዎችን መከወን ይቻላል::

ይሄን በማድረግም ተግባር ተኮር ትብብርን መፍጠር ይቻላል::የድጋፍ ሀይላት ለየብቻ ቆመዉ ከመቆጨት እና ከመንገብገብ በመዉጣት ልዩነታቸዉን ትተዉ በትልልቅ ተግባር መር ስራዎች/ፕሮጀችቶች/ ላይ ቢተባበሩ የፋኖ አመራሮች እና ተዋጊዉን ሀይል እንዲሁም በአጠቃልይ የነጻነት ሀይሉን ከፖለቲካ ፓርቲ እስከ ሲቪል ማህበራት ብሎም እስከ ጦረኛዉ ሀይል ማስተባበር ይቻላል::

ይሄም የህዝባችንን ነጻነት እዉን ለማድረግ ቁልፍ ነዉ::ሞት የተፈረደበት ህዝብ ተላቶቹን በመደምሰስ ነጻነቱን ከማወጅ ዉጭ ምርጫ የለዉም::
_

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here