
ነዓምን ዘለቀ
ጥቅምት 3 , 2016 ዓ.ም.
የመጀሪያው ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ Mr. Convince and confuse, የሸራተን አዲስ ንግግር በርካታ ሚዲያዎች ከዘገቡት የተወሰደ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አለቃው አብይ አህመድ የዛሬ አራት አመት ተኩል የተናገረው ነው። “የምስራቅ አፍሪካ የኦሮሞ ኤምፓየር፣ ኤርትራን፣ ጂቡቲን ፣ ሶማሊያን በመቆጣጠር በኤርትራ 2 ሚሊዮን፣ በጂቡቲ 1 ሚሊዮን፣ በሶማሌያ 2 ሚሊዮን ኦሮሞዎች እናሰፍራለን”። ከአራት አመት ተኩል በፊት አብይ አህመድ የመደመር መጽሐፉን የአፋን ኦሮሞ እትም ባስመረቀበትና ከ 200 በላይ የኦሮሞ ልሂቃን በተጋበዙበት መድረክ ላይ ሕልሙን/ ወይንም የቀን ቅዠቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን ፍላጎት ያረጋገጠበት ንግግር ነው።
ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የዛሬ 4 አመት ተከብሮ በነበረው የእሬቻ በአል ላይ “ነፍጠኞቹን ሰበርናቸው” በማለት ከተናገረበት እለት እስካሁን ድረስ በየመድረኩ የሚናገራቸውን ነውረኛ፣ ዘረኛ ንግግሮቹና ድርጊቶቹ ሁሉ አለቃው ዐቢይ አህመድ ይህን ተናገር፣ ይህን አድርግ የሚለውን ብቻ መሆኑን አረጋግጠናል። ሁለቱ ነውረኛ የኦሄድድ/የኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎች የዛሬ አመት ተኩል ግድም ለኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ”አማራ አሰብና ቀይ ባሕርን እናስመልሳልን የሚል አጀንዳ አላቸው፣ አትመኗቸው” ሌላ ሌላም እንደተናገሩ ለኤርትራ መንግስት ቅርበት ያላቸው ኤርትራውያን የሰሙትን በአግራሞት አድርሰውን ነበር። የሽመልስ አብዲሳና የኦሮሚያ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች ተዋናይ በሆኑባቸው ጸረ አማራ ትርክቶችና፣ ዘረኛ ድንፋታዎች ሁሉ ዋናው ደራሲና አቅጣጫ ሰጪ ዐቢይ አህመድ መሆኑን ዘግይተንም ቢሆን ተረድተናል፣ አውቀናል። ይህ የቀን ቅዠታቸውና ነውረኛ ክህደታቸው ወደ “አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል”ነት እንደሚለወጥ ምንም ጥርጥር የለውም።
የአብይና የሽመልስ የኦሮሚያ ብልጽግና በቅርቡ አውራ ጎዳና በሚባል ቦታ 3500 የአማራ አባወራዎችን ማፈናቀል፣ መግደልና፣ መዝረፍ ጨምሮ ከደቡብ ፣ ከሶማሌ፣ ከሲዳማ፣ ከጋምቤላ፣ ከቤኑሻንጉል፣ ከአዲስ አበባ መሬት በመውረር ልዩ ልዩ ማህበረሰቦችን በማፈናቀል፣ በመጨፍጨፍ፣ በማስጨፍጨፍ፣ አንድን ማንነት፣ ባህልና ቋንቋን መጫን ፣ “እኛን የምትመስል ኢትዮጵያ እንመሰርታለን” የሚል እኩይና የእብሪት አጀንዳ እንዳላቸው ከበቂ በላይ መገለጫዎችና ማሳያዎች አይተናል። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖርበትም የሲኦል ህይወት ከዚሁ በእኩልነት ስም፣ የአልጠግብ ባይነት የእብሪት ጥግ አካል ነው። እዚህ ላይ ሁሉም ልብ ሊለው የሚገባው ግባቸው ሁላችንንም የምትመስል ኢትዮጵያ ሳይሆን “እኛኝ የምትምሰል ኢትዮጵያ” “ኬኛ” እውን እናደርጋለን መሆኑን ይሰመርበት። በሰፊው ኦሮሞ ህዝብ ስም እየነገደ ለመዘርዘር በሚያታክት ደረጃ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ገጸ ብዙ ወንጀሎች እየፈጸመ የሚገኘው ይህ ነውረኛ ቡድን “የኛ” “ኬኛ” ከሚሉት ውጭ የሚገኙ ማህበረስቦች ላይ ወረራ መፈጸም፣ መሰልቀጥ ዋና መገለጫው አድርጎታል። ኢትዮጵያን አፍርሰው “እኛን የምትመሰል ኢትዮጵያ” እውን የማድረግ የቀን ቅዠታቸው፣ የበላይነትና ፈላጭ ቆራጭነት ለመጫን እቅፋት ነው ያሉትን የአማራ ህዝብ ለማንበርከክ፣ ለማድቀቅ፣ ለመጨፍጨፍ ፣ የዘር ፍጅት ለማድረግ ምንም ለከት የሌላቸው መሆኑ ትላንትም ዛሬውም በበርክታ መገለጫዎች እያየን ነው።
በአማራ ህዝብ ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ብቻ የሚወሰን አይድለም፡ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያነጣጠረው ይሄው የኦሮሚያ ብልጽግና የወረራ፣ የተስፋፊነት፣ የጦረኝነት፣ የፋሽስታዊነት አጀንዳ በፍጥነትና ለከት አጥቶ ባፈጠጠና ባገጠጠ ሁኔታ ለመተግበር የማይፈነቅሉት ድንጋይ እይኖርም።ከሰሞኑም ዳር ዳሩን የሚሽከረከሩት የዚሁ እቅዳቸው አካል ነው። ለአመታት በቅርበት የምናውቃቸውን ሚኒስትሮችን ጨምሮ በየመድረኩ የሚያራግቡት “የቀይ ባሕር፣ አሰብን ” በሕግ ወይንም በግድ ማግኘት አለብን” ቅስቀሳ ከቅርብ ወራት ጀምሮ ዐቢይ አህመድ በሰበሰባቸው መድረኮች የሰጣቸውን እቅጣጫ ተከትሎ የሚደረግ የዚሁ የቀን ቅዠት አካል ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት በአብይ አህመድ ባለሟሎችና ካድሬዎች ፣ አምባሳደሮችና ሚንስትሮች እየተቀነቀነ፣ እየጦዘ የሚገኘው “የአሰብ የቀይ ባሕር በህግ ወይንም በግድ” አጀንዳ የኢትዮጵያ ሕዝብን ትኩረት ማስቀያሻ ያገለግለናል የሚል ስሌትም የተጨመረበት ነው። የአብይ እህድመድ የጭቆና፣ የአፈና አገዛዝ ከሁሉም አቅጣጫ ያጣውን ቅቡልነት መልሶ ለማግኘት ይጠቅመናል የሚል መሆኑ ነው። እንደጧት ጤዛ የረገፈውን የሕዝብ ድጋፍ ዳግም ለመመለስ፣ ብሎም ራሱ አብይ አህመድ በክህደት ድርጊቶቹ የአማራን ሕዝብ ፣ እንዲሁም ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጣውን ድጋፍ መልሶ ለማግኘት ቀልብ ለመሳብ ጭምር መሆኑን ለመገመት ነብይ መሆን እይጠይቅም።
አብይ አህመድ በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከከፈተ በኋላ ባለፉት ጥቂት ወራት “አሰብን በሕግም ሆነ በግድ” ማግኘት አለብን የሚለው ቅስቀሳ ለብልጽግና ስራ አስፈጻሚ፣ ለሚኒስትሮች ካቢኔ፣በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ለሰበሰባቸው የመከላከያ ጀኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ በጠ/ሚ ጽ/ቤት አንቂዎችና የተለያዩ የሚዲያ አካላት በተገኙበት በተደረጉ ስብሰባዎችም ዋና መወያያ አጀንዳ ነበር። አብይ አህመድ ይንኑ አጀንዳ በማድረግ ሲቀሰቅስ “አሰብን በሕግም ሆነ በሃይል ማግኘት እለብን” በማለት አቅጣጫ ሲሰጥ እንደነበር በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃን ተሰራጭቷል።
አብይ አህመድ አቅጣጫ የሰጠባቸውን እነዚህን ስብሰባዎች ተከትሎም፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ ጋዜጠኖች በተለያዩ መድረኮች እድርጉ የተባሉትን ፣ የተሰጣቸውን አቅጣጫ ሲያስተጋቡ ተደምጠዋል። እንድ የካቤኔ ሚኒስትር በቅርቡ ባደረገው ንግግር ሃገሪቱ የምትገኝበትን ዘርፈ ብዙና ተደራራቢ ቀውሶች ወደ ጎን በመተው ጉም ዘገን ዲስኩር ባደረገበት መድረክ ላይ ይህንኑ “የወደብ” አጀንዳ በመሸንቆር የአብይ አህመድን የቀን ቅዠት ሲያስተጋባ ተደምጧል። ያን ተከትሎ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደጻፈው በእርግጥም “ክህደት በሕብረት”
ኤርትራ የኢትዮጵያ ህልውና ከባድ አደጋ ላይ በወደቀበት ጨለማ ሰዓት ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረገች፣ ብዙ የህይወት መስዋእትነት እንደተከፍለም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ከሁለት ወራት በፊት አብይ አህመድ ጀኔራሎቹን በአፍሪካ ልህቀት ማእከል ይህን አጀንዳ ሲያቀብርላቸው “አብረን መስዋእትነት ከፍለን፣ እንዴት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ይታሰባል” የሚሉ የተቃውሞ አስተያየቶች የሰነዘሩ ጀነራሎች እንደነበሩም መረጃዎች ደርሰዋል። የኢትዮጵያ ወደብና ሌሎችም ፍላጎቶች በሚመለከት አዎንታዊ አቋም ኤርትራ እንዳላት፣ ከጦርነቱ በፊት ከአስብ እስከ ኢትዮጵያ ድንበረ መንገዶች እየተጠገኑ እነደነበር፣ ሌሎች ከወደብ አጠቃቀም ጋር ተያያዥነት የነበራቸው፣ የኢትዮጵያን ወደብ የመጠቀም ፍላጎቶች ተግባራዊ ለማድረግ ጅማሮዎች እንደነበሩ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ዐቢይ አህመድ ከህወሃት ጋር በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተፈራረመ ማግስት ጀምሮ በኤርትራ ላይ ሲሸርብ እንደነበረ፣ የሃሰት ክሶችንም ሲደረድር እንደነበር ተሰምቶአል። የአማራ ልዩ ሃይልም ሆነ ፋኖ በህልውና ዘመቻው ወቅት በአማራ ብልጽግና ከፍተኛ መሪዎች፣ እንዲሁም በራሱ አብይ አህመድና በአማራ ብልጽግና መሪዎች እውቅና በኤርትራ አሰልጣኞች ሰፊ ስልጠና ያገኘ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ፣ ከሃዲው አብይ አህመድ “ሊያስገድሉኝ ነው፣ ፋኖን ፣ ኦነግን እያሰለጠኑ ነው” የሚሉ የሃስት ክሶችን ለልዩ ልዩ ግለሰቦችና ቡድኖች ሲያማና ለእኩይ አላማው ተበዳይ ሆኖ ለመታየት የክስ ዶሴዎች ሲያዘጋጅ እንደቆየ ከተለያዩ አቅጣጫዎች መረጃዎች ወጥተዋል።
የህወሃት መሪዎች ጋር በሃላላ ኬላ ባደረገው ስብሰባ ግዜ ኤርትራ፣በአሰብና ቀይ ባሕር ጉዳይ እንዳናገራቸው ተአማኒ ምንጮች ጉዳዩን ተናግረዋል። አብይ አህመድ በአማራ ክልል ሕዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት ውስጥ እንዲተባበሩ፣ እንዲገቡ ሕወሃቶችን እንደጠየቃቸውም መረጃዎች ወጥተዋል። አልተሳካለትም እንጂ ለምእራባዊያን ሀገሮች “ኢሳያስን ማስወገድ እችላለሁ” የሚል ማማለያ በማቅረብ የእነሱን ድጋፍ ለማግኘት መሞከሩን እንዳንድ ወገንኖች ጠቁመዋል። ይሁንና ግብዣው እምብዛም የማረካቸው እንዳልሆነ ፣ ለአብይ አህመድ አመኔታም ሆነ እምብዛም ክብር እንደሌላቸው ጉዳዩን የሚከታተሉ እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።እንደሚታወቀው ሕወሃቶች በ1998 ከኤርትራ ጋር ሲጣሉ፣ ረግጠውት የነበረውን ኢትዮጵያዊነትና ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ ፣ በኤርትራ ላይ ላወጁት ጦርነት የኢትዮጵያን ሕዝብን ለመቀስቀስ፣ ብሎም ለጦርነቱ ለማሰለፍ ተጠቅመውበት እንደነበር የማይረሳ ታሪክ ነው። ከጦርነቱ በኋላ ኢትዮጵያውያንን ማዋረድ፣ ማሰር፣ መግረፍና መግደል መገለጫቸው እንደነበር ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚዘነጋው እይደለም። ዛሬም እንደትላንቱ የህወሃት የጡት ልጆች የሆኑት አብይና የኦሕዴድ/የኦሮሚያ ብልጽግና ካድሬዎች ይህንኑ ለመድገም እየሞከሩ መሆኑ ከወዲሁ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች ሁሉ ግልጽ መሆን እለበት፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ እንዳልሰጠው፣ ዛሬ ግን ዐይንህ ለአፈር ያለው፣ በክህደት ተግባሮቹና በጭካኔው በሕዝብ የተተፋው ዐቢይ አህመድና የኦሮሚያ ብልጽግና ጋሻ ጃግሬዎቹ ተመሳሳይ ትራጄኮ-ድራማ ሕዝብ ላይ እንዲተውኑ፣ እንዲያጃጅሉን መፍቀድ የለብንም። በእብሪታቸው፣ በጋጠ ወጥነታቸው፣ ኢትዮጵያውያንን በተለይም የአማራን ህዝብን ለማፈን፣ ለማንበርከክ በሄዱበት መንገድ ሳቢያ ከገቡበት መጠነ- ሰፊ ስርአታዊ ቀውስና አገዛዙን እያንገዳገደ የሚገኘውን የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ለመቀልበስ፣ የለውጥ ማህበሉን ለማስቆም የማይፈነቅሉት ድንጋይ እይኖርም። ትላንት የአብይ አህመድን ስልጣን ለማስቀጠልም ሆነ የሀገራችንን ህልውና ለመታደግ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለውን የአማራ ሕዝብ፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ በፋኖ በሰሜኑ ለህልውና በተደረገ ጦርነት ወቅት ከደረሰበት እልቂት፣ መክራና ፣ ውድመት ሳያገግም ሌላ ጦርነት ከፍተውበት ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት በአብይ አህመድ ፈጽሞአል። ባለፉት ስድስት ወራት በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ለማድረግ እንዲመቸው “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” ማወጁን ተከትሎ በድሮን፣ በታንክ፣ በመድፍ፣ በሞርታር አረር በሺ የሚቆጠሩ የአማራ ህዝብ ንጹሐንን፣ ሴቶች፣ አዛውንት፣ ህጻናት ሳይቀሩ በአረሜናዊ ሁኔታ ተጨፈጨፉ። የሞት ድግስ በየአማራው ቤት እንዲገባ አደረጉ። ዛሬ ደግሞ ባለፈው ጦርነት ከፍተኛ እልቂትና ውድመት የደረሰባቸውን የአማራ፣ የአፋር ፣ የትግይን ህዝብ በመጠቀም ፣ የአብይ አህመድ የኦሄድድ/የኦሮሚያ ብልግና ዘረኛ ዘራፊዎች “የምስራቅ አፍሪካ ኦሮሞ ኤምፓየር” የቀን ቅዠት ለማሳካት በመቶ ሺዎች እልቂትና ውድመት ፣ ሀገራዊና ቀጠናዊ የጦርነት፣ የእልቂትና ፣የውድመት አዙሪት እየጠመቁልን ነው።
በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እንዲሁም በአማራ ህዝብ ላይ ያንዣበበውን ከባድ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል የጀመረውን የህልውና ትግል በሁሉም መንገድ ከመደገፍ ውጭ ሌላ መፍትሄም ፣አማራጭም የለም። የአብይ አህመድና የኦሮሚያ ብልጽግናን የጭቆና፣ የዘረፋ፣ የጋጠ ወጥነት አገዛዝ ታግሎ ጥጋባቸውና እብሪታቸውን ከማስተንፈስ ውጭ ሌላ ምርጫ የለንም። የትግሉን አድማስ ማስፋትና በአብይ አህመድ የኦሮሚያ ብልጽግና ተስፋፊ፣ ዘራፊ ፣ጨቋኝ የፓለቲካ ስርአት ማስተንፈስ ብሎም መወገድ አለበት። በስቃይ፣ በአፋና ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች የትግሉ አካል እንዲሆኑ ጥረቶች መደረግ አለባቸው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ሁሉም ዜጎች፣ የሁሉም ማህበረስቦች በእኩልነት፣ በፍትህና በነጻነት የሚኖሩባት ምድር እውን ለማድረግ የተጀመረው የትግል አድማስ እንዲሰፋ በርካታ ስራዎች መሰራት አለባቸው። የቀጣዩ የትግል ምእራፍ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አለም ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የሚያሳትፍ፣ የሚያካትት የተባበረ፣ የተናበበ፣ ዘርፈ ብዙ ትግል እንዲቀጣጠል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት አለበት ። ለሁሉም የአማራ ህዝብም ሆነ የሁሉም የኢትዮጵያ የባህልና የቋንቋ ማህበረስቦች እንዲሁም የእያንዳንዱ ዜጋ ደህንነት፣ እኩልነት የሚረጋገጥበት፣ የህግ የበላይነት የሚከበርበት ፍትሃዊ የፓለቲካ ስርአት መዳረሻ እንዲሆን ሰፊ የፓለቲካ ስራዎች መሰራት አለባቸው። በተለያዩ ደረጃዎች የሚደረጉ የመስክና የፓለቲካ ትብብሮች፣ ቅንጅቶች፣ ህብረቶች ለትግሉ በስኬት መጠናቀቅ ወሳኝ ናቸው። የትብብርና መሬት ላይ የሚከፈለውን መስዋእትነት የሚመጥን የፓለቲካዊ ድርጅት ግንባታ ተግባራት በቅጡ ታስቦባቸው ተግባራዊ መደረግ አለባቸው።
የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎና መስዋእትነት ያልተቆጠበ ድጋፋችንን እንስጥ!
ድል ለፋኖ የአማራ ህዝባዊ ሃይሎች !!
__
በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ