spot_img
Tuesday, November 28, 2023
Homeነፃ አስተያየትቀይ ባህር አዲሱ ቁማር! (በላይነህ አባተ)

ቀይ ባህር አዲሱ ቁማር! (በላይነህ አባተ)

advertisement

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

በመላእክትነት ተመርጦ የነበረው ሳጥናኤል እግዚአብሔርን ከድቶና ክርስቶስን ወደ ተራራ ወስዶ ከተማ እያሳዬ በንብረት ሊደልለው ሞከረ፡፡ የሳጥናኤል ተከታዮች ደግሞ ከዓለም በፊት እግዚአብሔርን እያመለከ የኖረውን አማራ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ ወዘተርፈ በሚሉ የቁማር ካርታዎች ሲያታልሉ ኖሩ፡፡  አማራ ክርስቶስን ስላለሆነ  ተታለለ፡፡

በቁማር መጫዋቻ ካርታ መደለሉ የሰለቸው አማራ ራሱን ለማዳን እንደ ቅድመ አያቶቹ ቆርጦ ሲፋለም  ደሞ እንደተለመደው ቀይ ባህር የሚል የቁማር ካርታ ይዘው ብቅ አሉ፡፡

ሳጥናኤል አዙሮ የሚያይበት አንገትና ይሉኝታ እንደሌለው ሁሉ ተከታዮዎቹ ጭራቆችም ትናንት የሰሩትን ዞር ብለው የሚያዩበት አንገት፣ እንደ አቡጀዲ የሸረከኩትን ውሽት የሚያፍሩበት ህሊናና ይሉኝታ የሳጥናኤል ያህል እንኳ የላቸውም፡፡

አማራ የኢትዮጵያ ግዛት ከራስ ካሳ እስከ ሞያሌ፤ የባህረ ነጋሽ ሰዎችም ወንድምና እህቶታችችን ናቸው ሲል እነዚህ የሳጥናኤል ተከታዮች ኢትዮጵያ የባህረ ነጋሽ ቅኝ ገዥ፣ ሰዎቹም የተለዩ ስለሆኑ ይገንጠሉ ብለው ያሳደገቻቸውን ኢትዮጵያን ከአርባ አምስት  ዓመታት በላይ ወጉ፣ ሕዝቡን በድድ አናከሱ፡፡ አማራ ሕዝባችንን አትከፋፍሉ አገሪቱንም ወደብ አልባ አታድርጉ ሲል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን በከንቱ በማስጨርገድ ወደብ አልባ አድርገውና ከዓለም በፊትም ኢትዮጵያ ወደብ አልባ እንድትሆን ድምጥ ሰጥተው የሚያሳፍር ወራዳ ሥራ በታሪክ ማህደር ጣፉ፡፡ ትንሽ ቆይተው በዘረፉት የኢትዮጵያ እንጀራ ሲጣሉ ደሞ የባህረ ነጋሽን ሰዎች በላንባ ዲና እየፈለጉ በወረንጦ ነቅለውና ንብረታቸውን ገፈው አባረሩ፡፡ በለማተቡ አማራ በአደራ ንብረታቸውን የጠበቀላቸው የባህረ ነጋሽ ሰዎች በኋላ ንብረታቸውን ተረከቡ፡፡

ቁማርተኛ ጭራቆች ዛሬም እንደ ወትሮው አዙሮ የሚያዩበት አንገትና ሊያፍሩ የሚችሉበት ህሊና ወይም ይሉኝታ ስለሌላቸው ቀይ ባህር የምትል ማታለያ ቁማር ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ዳሩ ዛሬም በዚህ የሳጥናኤል ተከታዮች  ቁማር እንደገና ተጠልፎ የሚወደቅ  የእንግዴህ ልጅ የሆነ የአማራ ምሁር  ያጣሉ አይባልም፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ በሚሉ ይሁዳዊ ሰባኪያን የተንዘላዘሉና የተከንከረፈፉ ጁላጅል ምሁራን በወደብ ስብከትም እንደ ገለባ ተጠርገው የአማራን ሕዝብ ማሳሳቱን አይቀጥሉም አይባልም፡፡ 

የወቅቱ የአማራ ጥያቄ ቀይ ባህር፣ ወደብ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ልማት፣ ጅኒጃንካ የሚል ድስኩር ሳይሆን የህልውናና የአገሩ ባለቤትነትን የማረጋጋጥ  ጥያቄ ብቻ ነው፡፡ አማራ ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ንብረቱንም ሆነ መንፈሱን ማዋል ያለበት ለራሱ ህልውና ብቻ ነው፡፡ አማራ እንደ ማርያም ጠላት በሚዋከብበት በዚህ ክፉ ዘመን የራሱ ልጅ እየተራበ ሌላውን አጎርሳለሁ የሚል፣ የራሱ እያረረበት የሌላውን የሚያማስል የእንግዴህ ልጅ ነው፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ እያሉ የአማራ ምሁራንን ሲያጃጅሉ የኖሩት ቁማርተኞች ዛሬ ደሞ ቀይ ባህርና ወደብ የሚባል የካርታ ጨዋታ የጀመሩት አንድም እንደዚህ ዓይነቱን የእንግዴህ ልጅ ሙልጭ አድርገው ቁማር ለመብላትና የአማራን ዘር የማጥፋቱን ሴራ ለማጧጧፍ ሁለትም በምዕራባውያን ጌቶቻቸው ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው  ነው፡፡

ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/06/Abay.pdf

ፈንድ ፈንዳጅ ዲያስጶራ እባክህ ስማ! ለዘራፊዎች የማይነጥፍ ጥገት መሆንህ ይብቃ!   ቦንድ ቦንዳጅና ፈንድ ፈንዳጅ.docx (ethiopatriots.com)

ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here