spot_img
Tuesday, November 28, 2023
Homeነፃ አስተያየትፖለቲከኞቻችን አሴ ጆሊ ጃክን እየመሰሉኝ መጡ !!!

ፖለቲከኞቻችን አሴ ጆሊ ጃክን እየመሰሉኝ መጡ !!!

advertisement

ተፃፈ በ ጓንጉል ተሻገር

በንጉሱ ጊዜ አሰፋ ጆሊው አምስት ኪሎ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ሆኖ እኔ ሀይ ስኩል ተማሪ ሆኜ ፓርት ታይም መምህርነት ተቀጥሮ ኬሚስትሪ አስተምሮኛል። የኬሚስትሪ ተማሪ ለምን እንዳልቀጠሩ አልገባንም። ሆኖም ጎበዝ መምህር ነበር። አሴ ጆሊውን ከዚያ በፊትም በሩቁ በአንገት ሰላምታ ብቻ አምስት ኪሎ አካባቢ የጓደኞቼን ወላጆች ቤት ተከራይቶ ሴቶች ሲያሳድድ ስለማውቀው ከእኔ ጋር በጣም ሽርክ ሆነን የትምህርት ዓመቱ አለቀ። አሴ ጆሊው መዘነጥ፣ መሽቀርቀር ይወድ ነበር። ሽቶ ስለሚያበዛ ተማሪዎች በርሻኮ ይሉት ነበር። በመካከሉ አሴ ጠፋብኝ። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ አንድ ቀን ፒያሳ ብጭቅጭቅ ያለ ልብስ የለበሰ፣ የጠቋቆረ፣ እጅግ በጣም  የተጎሳቆለ ሰው  ጥቂት ሰው ከቦት ሁለት እጁን በቁጣ ወደሰማይ እያወናጨፈ በእንግሊዝኛ ረጅም ንግግር ሲያደርግ አይቼ ጠጋ አልኩኝ። መጀመርያ አላወኩትም ነበር። እኔን ሲያይ አንተ ደህና ነህ ብሎ ፈገግ ሲል አሴ ጆሊው መሆኑን አስታወስኩት። እንባ ተናነቀኝ፣ እጅግ በጣም አዘንኩ። ድምፄ ቾክድ ሆነ። እንደምንም ቀልቤን ገዝቼ ሻይ ልጋብዝህ ብዬ ይዤው እኔ እና እርሱ ብቻ ወክ ማድረግ ጀመርን። አንድ ቡና ቤት ይዤው ስገባ ዘበኛውም አስተናጋጆቹም ሲያንገራግሩ፣ ሲጠየፉት ገላምጫቸው ሂድ እዚያ ዘብ ቁም አንተም ዝምብለህ ታዘዝ በማለት አስደንግጫቸው በሆዴ አይ የአበሻ ነገር አሞት ወድቆ አይታችሁት እንጂ በእንጨት አይነካችሁም ነበር ብዬ ለአሴ እና ለእኔ ሻይ አዘዝኩ። አሁን ዝም ብሏል፣ እርግት ብሏል። እንደው በእግዜር ኃይል መለስ ያለለት ሁሉ መሰለኝና ወሬ ጀመርኩ፣–

እኔ:- አሴ ምን ሆንክ?

አሴ:- ምን እሆናለሁ? ምንም አልሆንኩም

እኔ:- አይ አሴ የማየውንማ አታስክደኝም። አሞህ ነበርን?

አሴ:- ዘመዶቼ ተሰባስበው አብዷል ብለው አማኑኤል ሆስፒታል አስገብተውኝ ነበር። ሳይኪያትሪስቱ አንድ ወር አስተኝቶን  የታመማችሁ እናንተ ናችሁ፣ ይሄ ሳይንቲስት ነው፣ ሊቅ ነው አላቸውና እኔን ዘወር ብሎ አሴ አንበሳው ይቺን ክኒን በቀን ጠዋት ከቁርስ በፊት  ወይም በኋላ ሳትረሳ ሁሌ አንዳንድ ብቻ ዋጥ ብሎ አሰናበተኝ። አብዷል ያሉትን ዘመዶቼን ኩም አደረገልኝና አስደሰተኝ።

እኔ:- አሴ ያቺን ክኒን ዛሬ ወስደሀል?

አሴ:- አይ ተውኩት

እኔ :- ለምን?

አሴ:- ክኒኑን ስውስድ ድብት ያደርገኛል፣ እንቅልፍ አበዛለሁ። 

እኔ:- ክኒኗን አሁን እንግዛት። ስሟን ታስታውሳለህ?

አሴ:- ፋርማሲ ስንሄድ ትዝ ይለኛል ። 

ተያይዘን ፋርማሲ ሄድን ፣ እንዳለውም “በክሮ….” የሚጀምር የመድኃኒት ስም ጠራና ፋርማሲስቱ መድኃኒቱ አለን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ አይሸጥም አለን ።

ከፋርማሲ ወጥተን ወክ እያደረግን ወሬ ስንጀምር አንድ ልዩ ፎርሙላ፣ የጦር መሳርያ ማምረቻ ኬሚካል ከኬሚስትሪ የታወቁት ኢለመንቶች ውጭ ባለ እርሱ ዲስከቨር ባደረገው ኢለመንት የተሰራ ልዩ የውድመት ጦር መሳርያ መፈልሰፉን እና ሲአይኤ ሰምቶ ፣ በረቀቀ የስለላ ዘዴ ደርሶበት እንደሚያባርረውና እየትሹለከለከ እንደሚኖር ነገረኝ፣ ውድያውኑ ወደ ሰማይ አይቶ አንድ አውሮፕላን እያሳየኝ  ይሄ አውሮፕላን እኔን ለመግደል የተላከ ነው አለ። ትንሽ ሪዚስት ማድረግ ስሞክር በከፍተኛ ደረጃ ተበሳጭቶ ከዓይኑ ላይ እሳት ነገር ብልጭ ሲል አይቼ ደነገጥኩና አብሬ ምን እናድርግልህ ስለው አሁን አንተንም ይከተሉሀል ። እኔም ቤቴ ልግባና ማታ ሌላ ቦታ አድራለሁ ብሎኝ ተለያየን።   

አሁን በኛ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ ብዙ አሴ ጆሊዎች ይታዩኛል። የባለሙያ የወዳጅ  ዘመድ ምክር የማይሰሙ በምናባቸው በፈጠሩት የቅዠት ዓለም የሚኖሩ ፖለቲከኞቻችን እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።

እግዜር ይጠብቀን!

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com  

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here