spot_img
Tuesday, June 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትፋኖ ያለጥርጥር የሚያሸንፍባቸዉ 7 ምክንያቶች

ፋኖ ያለጥርጥር የሚያሸንፍባቸዉ 7 ምክንያቶች

ፋኖ
ፎቶው ከቢቢሲ የእማርኛ አገልግሎት ድረ፟፟፟፟-ገጽ የተገኘ ነው

ሸንቁጥ አየለ

1) የአማራ ህዝብ በመላ ሀገሪቱ የተከፈተበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በስፋትና በጥልቀት ይቀጥላል። ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን የመጨረሻ ጥይታቸዉን እንኳን አንድ ህጻን አማራ በመግደል ይሆናል እስትንፋሻቸዉን ከመላዉ ኢትዮጵያ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆረጥ የሚያደርጉት።

የአማራም ህዝብ ሞቱና ስደቱን በዘረኞቹ ጭካኔ በበረታበት ሰኣት አሁን ካለዉ ሁኔታ በባሰ እና በመረረ መልክ በመላ ኢትዮጵያ ሆ ብሎ ይዋጋል። ለመኖር ኦነግ/ኦህዴድን መደምሰስ ብቸኛዉ አማራጩ መሆኑን እጅግ በጣም አልምጥ የሆኑ የአማራ ልሂቃን ፥ የሀይማኖት አባቶች፥ ሰባኪያን እና ሀብታሞች ሳይቀሩ የመከራ እሳት ዉስጥ በገቡ ጊዜ አሁን የተነሳዉን የፋኖ ትግል ሆ ብለዉ ይቀላቀላሉ። ኦነግ/ኦህዴድ እንደሆነ እላዉ ላይ የሰፈረበት ሰይጣን የሰዉ ደም በጅምላ ከማፍሰስ እና ህዝብ ከማፈናቀል ለቅጽበት አያሳርፈዉም።ይሄም የአማራን ህዝብ ለቁርጠኛ ትግል ያጸናዋል።

2) አሁን ያሉ የፋኖ ሀይላት የወታደራዊ ክህሎት እየጨመረ እና እየደደረ ይመጣል። ፋኖዎቹም ህልቆ መሳፍርት የሌላቸዉ መሪዎችን ያወጣሉ። እንደሚታወቀዉ የአማራ ባህል የጦር ገበሬ በማፍራት ድንቀኛ ነዉ።ጦረኞቹም ፍጹም መረመረ እና የማይታጠፉ ጦር ገጥመዉ ሳያሸንፉ የማይቆሙ ናቸዉ። ይሄን አለም በተለያዬ የታሪክ አጋጣሚ መስክሯል። ሆኖም ላለፉት 50 አመታት የአማራ ህዝብ ድንቀኛ የጦር መሪዎች እንዳያወጣ ከፈሪ ደናቁርት የደርግ ጀነራሎች እስክ ምናምንቴ ወያኔዎች ብዙ የዘረኝነት ስራ ሰርተዉበታል። አሁን ያ ዘመን ተቆርጧል።

እግዚአብሄር የአማራን ነገድ የእስራት ዘመን ቆርጦለታል። ከ እስር ቤቱ የአማራ ህዝብ ሰብሮ ወጥቷል። ከእንግዲህ የአማራ ሰዉ ፍጹም መራራ ጦረኛ መሪዎችን ያወጣል። አረብ ቢንቀጠቀጥ ምእራባዊ ተንኮል ቢጎነጉን ፍጹም የሆነዉ የጦር ሀይል በኢትዮጵያ ምድር እየተሰራ ነዉ።

ነገደ አማራን ከምድሪቱ ለማጥፋት ተንኮል እና ግፍ በዝቷል እና ህዝቡን ለማዳን ያቀደዉ መድሃኒአለም ነገሩ ዉስጥ አለበትና ይሄን የተነሳ ሀይል ምንም አይነት ምድራዊ ተንኮል ወይም የስለላ ደህንነት ወይም ትብብር አያቆመዉም።አለም ካሁን ብሁዋላ በነገድ አማራ ላይ በክፋት ቢተባበር ፈጽሞ አይሳካለትም። የእግዚአብሄር የማዳን ስራ አለበትና።

3)አሁን ኢትዮጵያዉያን ነገዶች መከራ ዉስጥ እና የመኖር ፈተና ዉስጥ ገብተዋል። መከራዉ ለ50 አመታት ነገደ አማራ ላይ እንዲሁ፡ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ላይ የጠጠረ እና የገዘፈ ቢሆንም የመከራዉ ዳፋ ተግፎ ተግፎ ይሄዉ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነገድ እሳቱ ወላፈን መሃል እየሳበዉ ነዉ።

በርካታ ነገዶች ኦነግ/ኦህዴድ የአማራን ነገድ ጨርሶ ይቆማል የሚል የሞተ ሀሳብ ይዘዉ ቢቆዩም አሁን ኦነግ/ኦህዴድ ሁሉንም ነገዶች መጨፍጨፉን በተግባር እያሳዬ ነዉ። ይሄም ሌሎች ነገዶች እጃቸዉን ለትብብር ወደ ፋኖ እንዲዘረጉ ያስገድዳቸዋል። ወደዉ ሳይሆን ለራሳቸዉ ህልዉና ሲሉ አንድ በታላቅ ሀገራዊ እሴት የተሸከመ ሀገራዊ ሀይልን ማማተር ይጀምራሉ። ይተባበራሉም።

4) ሀገራዊ የኢኮኖሚ ቀዉስ ፥ የፍትህ መጥፋት እና የዜጎች ከሰዉነት በታች መቆጠር ኦነግ/ኦህዴድ እስካለ እየከፋ የሚሄድ ይሆናል። ኦነግ/ኦህዴድ እንደሆነ የኢኮኖሚ ፡ የፍትህ የፖለቲካ እና የዜጎች እኩልነት የሚሉት ጽንሰ ሀሳቦች ፈጽሞ የ ማይገቡት በ14ኛ ክፍለ ዘመን የገዳ ስርዓት ተቸክሎ የ21ኛዉ ክፍለዘመንን የፖለቲካ ዉስብስብ ስሌት ሊፈታ የሚባዝን ነዉ።

ይሄም ኋላቀር ህሳቤዉ ለሁሉም ፖለቲካዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ ፡ፍትሃዊ፡ ሰበአዊ ጥያቄዎች ሌሎች ነገዶችን ጨፍጭፎ ማጥፋት ብቸኛዉ መፍትሄ ነዉ ብሎ የሚያስብ የድንጋይ ዳቦ ዘመን ተረት ተረት አራማጅ ሀይል ነዉ።ምድሪቱን በሙሉ ለመዉረስም ሌሎች ነገዶችን ማጥፋት አለብኝ ብሎ በተግባር ሌሎች ነገዶችን እየጨፈጨፈ ስለሆነ ሌሎች ነገዶች ፋኖ ፈጥነህ ድረስ የሚል ጩሆታቸዉ እየበረታ ይመጣል።

5) የራሱ የኦነግ/ኦህዴድ የዉስጣዊ የንኡሳዊ የጎሳ እና የሀይማኖት ትርምስ እየጎላ እና እየጎመራ መምጣት። በኦነግ/ኦህዴድ ዉስጥ ሶስት ዋና ዋና የሀይማኖት ተጻጻሪዎች እና እርስ በርስ ለመበላላት ያደፈጡ ተንኮሎች አሉ።

የወለጋዉ አክራሪ የፕሮቴስታንት ቡድን፡ የምስራቁ አክራሪ እስላማዊ ሀይል ፡ በመሃል ኢትዮጵያ የሚገኘዉ አክራሪዉ የዋቄፌታ ሀይል ናቸዉ። እንደገናም ይሄዉ ሀይል በጎጥና በንኡስ የጉሳ ሽኩቻ ዉስጥ ያለ ነዉ።

አንድ የሚያያይዘን የሚሉት ነገር ቢኖር ” ሴሜትክ አማራና ትግሬ ስልጣኑን እንዳይነጥቁን እንተባበር የሚለዉ ” ብሂላቸዉ ቢሆንም ይሄ ስሌት የትም የሚያደርስ አይሆንም። በቅርቡም እንደተስተዋለዉ አክራሪዉ የምስራቅ ሀይል ክርስቲያን ነኝ የሚሉ እና ዋቄፌታ ነን የሚሉት ላይ ዘመቻ ጀምሯል።ይሄም የአጸፌታ ምላሽ የሚኖረዉ እንቅስቃሴ ነዉ። በዚህም ዋና ጦርነት እርስብ በእርሳቸዉ ያደርጋሉ።

6) የአማራ ባንዳዎችና የብአዴን ልምሻዎች በሀገር ቤትም ሆነ በዉጭ ሀገር እየኮሰመኑ ይሄዳሉ። ፋኖ በወታደራዊ፡ አስተዳደራዊ እንዲሁም የደህንነት አደረጃጀት እየፈረጠመ እና እየደደረ ሲመጣ እነዚህ ጠላቶችን የመመንጠር ጉልበቱ እየሰፋ እና አስፈሪ እየሆነ ይመጣል። ይሄም የባንዳና የብአዴን ልምሻዎች ከእነ አስተሳሰባቸዉ ሲነቀሉ ድሉ በፋኖ እጅ ይገባል። ፋኖ ነጻ የሚያወጣቸዉን ወረዳዎች በዲሞክራሲያዊ መንገድ ህዝብ ምርጫ እንዲያደርግ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ለህዝብ የሚመች አስተዳደር እየፈጠረ ስለሚመጣ ህዝብ የፋኖን አስተዳደር እየናፈቀ ይመጣል።

7) የፋኖ ዉስጣዊ አንድነት እየጎመራ መምጣት እና በመላ ሀገሪቱ አዳዲስ ፋኖዎች የመቋቋም ሂደት ይፈጠራል። የፋኖ አንድነት በሂደት እየጎመራ ይመጣል።

በኢትዮጵያዊነት እና በአማራነት ተሰልፎ ፋኖን የሚያግዘዉ ሀይል ይበልጥ እየተናበበና ድጋፉን በተሻለ መልክ የሚያሳልጥበት ስርኣት ይፈጥራል። ይሄም መናበብና የተሳለጠ ድጋፍ ፋኖዉን ወደ ታላቅ ማማ ላይ አስፈንጥሮ ያወጣዋል። በመላ ሀገሪቱም ፋኖ ይመሰረታል።

እያንዳንዱ ከተማ በፋኖ ይናጣልል፡በኦነግ/ኦህዴድ ዘረኝነት የተማረረዉ የመላዉ ኢትዮጵያ ወጣትም ፋኖ ሆኖ የወጣል። በተለይም ከተሞች ለኦነግ/ኦህዴድ ረመጥ ይሆናሉ። ፋኖም ማንም እፊቱ የማይቆም አስፈሪ ሀይል ይሆናል።

ያኔም ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ነገድ ወጣቶች ሀያሉን የፋኖ የነጻነት አርማ እንስተዉ ፋኖን ይቀላቀላሉ።

ፋኖም በርግጠኝነት ያሸንፋል !

ይሄ እዉነት ነዉ። ኢትዮጵያም ትድናለች። ኢትዮጵያዉያንም ሀገር ይኖራቸዋል።

===≈=====

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !

__በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here