spot_img
Friday, June 21, 2024
Homeአበይት ዜናብጹዕ አቡነ ሉቃስ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው 

ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው 

ብጹዕ አቡነ ሉቃስ
ብጹዕ አቡነ ሉቃስ

ዳዊት ዓለሙ 

ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ላይ ባስተላለፉት መለልእክት መንግስትን ክፉኛ ተችተዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ በመንግስት ሃላፊዎች ዘንድ ንዴት እና የግድያ ማስፈራሪያ እየደረሳቸው መሆኑን ተስምቷል፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ሁኔታ አስመልክተው “እኛ [ኢትዮጵያያን] ከሞቱት በላይ በህይወት ካሉት በታች ነን” ሲሉ መረር ያለ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባልደረባ የሆኑት ንጋቱ ቶሎሳ ጎንፋ፣ አቡነ ሉቃስንም ሆነ ደጋፊዎቻቸውን ‘የማጽዳት ዘመቻ ግድ ይላል’ ሲሉ ጽፈዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና የውጪ ግንኙነቶች ክፍል ሃላፊው የአቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ንጋቱ ቶሎሳ፣ 22 ሲህ ተከታይ ባለው የፌስ ቡክ ገጻቸው በብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ላይ እንዲሁም በሃሳብና በእምነት የሚመስሏቸው ላይ የግድያ ዛቻ ሰንዝረዋል፡፡ አስተያየቱ የክልሉ መንግስት በቀጣይ 10 ዓመት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ከክልሉ የማጽዳት ዘመቻ አካል ነው የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡

የአቡነ ሉቃስን ጠንካራ ትችት ተከትሎ ከቤተ መንግስቱ አካባቢ ከፍተኛ ቁጣዎች እየተሰሙ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ እና በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጩ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዋነኝዐው ናቸው፡፡

በኦፊሴላዊው የቲዊትር ገጻቸው ላይ “ክብረ ነክ ነው” የተባለውን ሃሳብ የሰነዘሩት ዲያቆን ዳንኤል፣ “በአስኬማ ስር ተደብቆ የነበረው ጃውሳ እንደ ይሁዳ አለሁ ብሎ እየወጣ ነው” በማለት ጽፈዋል፡፡ መልእክቱ ላይ ስም ጠቅሰው ባይናገሩም የንግግሩ ቀጥተኛ ኢላማ አቡነ ሉቃስ ስለመሆናቸው ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ 

የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ጨምረውም ጵጵስና አገልግሎት ከመንፈሳዊነት ይልቅ ለገንዘብ መሰብሰቢያ እየዋለ እንደሆነ ሲገልጹ “ ‘አባ’ መከላከያን መግጠም ያዋጣኛል ካሉም ሜዳው ክፍት ነው፡፡ መጀመሪያ ግን ቆቡን ያውልቁት፡፡ ዕሩቅ ብእሲ ሆነው አይምጡ፡፡” በማለት አብዛኛውን አማኝ ያስቆጣ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ 

ከመንግስት ሃላፊዎች መካከል በተመሳሳይ ቁጣ አዘል አስተያየት የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባልደረባ የሆኑት ንጋቱ ቶሎሳ ጎንፋ ናቸው፡፡ ንጋቱ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት “አቡነ ሉቃስ ለኦሮሞ ተወላጆች ያላቸውን ጥላቻ በታቦት ፊት ቆመው ተናግረዋል” ያሉ ሲሆን አክለውም፣ “ለደገሱልን ክፉ ድግስና ለጠሩብን ዘመቻ ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት ስየአቡነ ሉቃስ ዘመዶች እና መሰል ደጋፊዎች ከኦሮሚያ ምድር የማጽዳት ዘመቻ ግድ ይላል” በማለት በብጹዕ አቡነ ሉቃስ እና በመላው ክርስቲያን ላይ የታሰበውን የሞት ድግስ ይፋ አድርገዋል፡፡

ከሰሞኑ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ዘንድ፣ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት እያሰጠበቀ አይደለም በማለት ከወትሮ ጠንከር ያለ እና ግልጽ ትችት እያሰሙ ነወ፡፡ ከነዚህም አባቶች መካከል ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ለምእመና በሰጡት ትምህርት፣ “ኢትዮጵያ ገላግሉኝ እባካችሁ በህይወት እና በሞት መሃከል ነኝ የምተል ሃገር ሆናች” ብለዋል፡፡ ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩም “መሪዎቿ [ይሄን] ችግሯን ያልፈቱላት ሃገር ናት” በማለት ተናግረዋል፡፡

የእነዚህ አባቶች መልእክት “መራራ ሃቅ” ነው የሚሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሃሳቡን  ይጋራሉ፡፡ ይሁን እንጂ እንደዚህ ሃሳባቸውን በአዳባባይ የሚገልጹ አባቶች በመንግስት በኩል ጥርስ እየተነከሰባቸው ለመሆኑ በአቡነ ሉቃስ ላይ የተደገሰውን የግድያ ዛቻ በማንሳት አስተያየታቸውን የሚሰጡ አሉ፡፡     

___የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ 
t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here