spot_img
Saturday, July 13, 2024
Homeነፃ አስተያየትኢትዮ ሶማሊ ላንድ መግባቢያ ስምምነት (MoU) : ተስፋ እና ስጋቶች 

ኢትዮ ሶማሊ ላንድ መግባቢያ ስምምነት (MoU) : ተስፋ እና ስጋቶች 

ኢትዮ ሶማሊ ላንድ መግባቢያ ስምምነት

ሀብታሙ ብርሃኑ 

ሰሞኑን በኢትዮጵያ መንግስት እና ሶማሊላንድ መካከል የተደረገው መግባቢያ ስምምነት አሜሪካ እና አፍሪቃ  ህብረትን ጨምሮ  ብዙዎችን ስያነጋግር እያየንም እየሰማን ነው።  ከዚህ ጋር ተያይዞ  አፍሪካ ህብረት;  አሜሪካ እና IGDን ጨምሮ የተለያዪ አጋራትና አለም አቀፉ ተቋማት መግለጫ ሲያወጡ ተስተውሏል።  ፕሮፌሰር ብሩክ ሃይሌ ከኢቲቪ ጋር በደረጉት ቃለ ምልልስ  እንዳነሱት እነዚህን መግለጫ የሚያወጡ ተቋማት እና አካላት መግለጫውን የሚያወጡት ለሶስት ምክንያት ነው። የመጀመሪያው ዝም ተብሏል እንዳይባሉ ነው። ይህ ማለት IGD እንዳስተቀው ጉዳዮን በቅርብ ርቀት እየተከተልኩ ነው እንዳለው ማለት ነው። ሁለተኛው በህብረተሰቡ ዘንድ ብዥታ ለመፍጠር።  ይህ ደግሞ እውነታውን እያወቁ ነገር ግን ህዝቡ ትክክለኛውን ሀቅ እንዳይረደ ለማወናበድ ተስቦ የሚደረግ ስሆን ሶስተኛው ደግሞ ከለማወቅ የተነሳ ነው።  ምክንያቱ ምንም ልሆን ይችላል ጉዳዩ መሆን የለበት ይህ ስምምነት ጠቀሜታው እና ሰጋቶቹ ምንድናቸው የሚሉ እና መፍትሄውስ ምን መሆን አለበት የሚሉ ጉዳዮች ናቸው። 

ጉዳዪ ከአከባቢው geopolitics አንጻር ስታይ በተለይም ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል።  ስምምነቱ በዋናነት ከኤኮኖሚ;ከጸጥታ እና ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ አኳያ የለው ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል።

1)ከኢኮኖሚ አንጻር:-ከኤኮኖሚ ጠቀሜታ አንጻር ስታይ ሌላው እንኳን ብቀር ኢትዮጵያ የወደብ ተጠቃሚ በነበረችበት ወቅት ምን አይነት ገናና አገር እንደነበረች እና የነበራት የንግድ እንቅስቃሴዎቿ  እንዴት እንደነበር  በዘርፉ የተጻፉት የተሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።  ይሁንና ከአለም አቀፍ ስርዓት (world order) መቀያየር በተለይም ቀዝቃዛ ጦርነት (cold war) እና የኤርትራን መገንጠልን ተከትሎ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ እንትሆን ከተደረገች ግዜ ጀምሮ በወደብ በኩል የሚደረገው የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴዎቻችን ምንያህል ደካማ እንደነበር ብቻም ሰይሆን በከፍተኛ ወጪ የጅቡቲን ወደብ ብቻ ስንጠቀም መቆየታችን ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው። ስለዚሀ ይህ ስምምነት መደረጉ በጥንቃቄ ከተመራና ወደ ፍጻሜው ከደረሳ አጋራችን በወደብ በኩል የምታደርገው የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ አንድ እርምጃ ከፍ የማድረግ አቅም የለው መሆኑ እውን ነው። 

2)ከዲፕሎማሲ አንጻርም ከታየ ስምምነቱ በጥንቃቄ ከተመራና ወደ ፍጻሜው ከደረሳ የአገራችንን ዲፕሎማሳዊ ግንኝነት ከፍ ልያደርግ እንደምችል የአደባባይ ምስጥር ነው። እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት በዚህ ቀጠና ላይ ስደረጉ የነበሩ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ኢትዮጵያን የገለሉ እንደነበሩ ለጉዳዩ ቅርበት የላቸው እና በዘርፉም ሰፊ ጥናት እና ምርምር ያደረጉ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ይነገራሉ። ነገር ግን ይህ ስምምነት ፍጻሜ ካገኛ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሳዊ ተሳትፎዋን ከፍ መደረግ ይችላል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ እንደ ባድርሻ አካል ብቻ ሳትሆን እንደ ዋና/መሪ ተዋና main actor) የመሳተፍ እድል ይከፍትለታል ማለት ነው።

3)ሶስተኛው እና በጣም መሰረታዊው ነገር የጸጥታ ጉዳይ ነው። ከዚህ አንጻርም ስታይ  ስምምነቱ የንግድ ጉዳይ ብቻ ሰይሆን ወደቡ ለባህር ሀይል ጦር መሰረትም (military base) ልያገለግል እንደሆነ ነው። ይህ ማለት ኢትዮጵያ የባህር ሀይል ጦር መሰረት (military base) ይኖራታል ማለት ነው። ይህ ደግሞ በቀጠናው ለይ የሚደረገው የትኛውንም የጸጥታ እንቅስቃሴን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከነበራት ተሳትፎ  በተሻለ የመሳተፍ እድል ከመሰጠቱም በተላይ እንደ ዲፕሎማሲው ተሳትፎ እንደ ባድርሻ አካል ብቻ ሳትሆን እንደ ዋና/መሪ ተዋና main actor) የመሳተፍ እድል ይከፍትለታል ማለት ነው።

በአጠቃላይ ስምምነቱ  በጥንቃቄ ከተመራና ወደ ፍጻሜው ከደረሳ አገራች ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው  ከለችው ፕሮጀክቶች ጋር ተዳምሮ  በቀጠናው ላይ የላትን እኮኖሚያዊ;ዲፕሎማሲያዊ እና ጸጥታ ተሳትፏን;ተደማጭነቷን ብሎም ተጽዕኖ ፈጠርነቷን ከፍ የማድረግ አቅሙ ግልፅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያን የላትን ተሳትፎ; ተደማጭነቷን እንድሁም ተጽዕኖ ፈጠርነቷን እና ከፍታ የማይፈልጉ አካላት ጋና ከጅምሩ የመግለጫ ጋጋታ እየወጡ ያገኛሉ። ይህ ደግሞ ጉዳዪ በጥንቃቄ እና አለም አቀፍ  መርሆዎችን  ተከትሎ በብስለት መመረት የለበት መሆኑን ያስረዳናል። እንዴት መመረት አለበትስጋቶቹስ ምንድናቸው ለሚለዉ ሀሳብ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። ለጊዜው የግሌን ሀሳብ በዚህ ልክ ከገለጽኩ ይበቃኛል። 

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here