spot_img
Friday, June 21, 2024
Homeአበይት ዜናየብዙዎች ትዝታ ፥ የሜክሲኮ አድባር ሎምባርዲያ ፈረሰ 

የብዙዎች ትዝታ ፥ የሜክሲኮ አድባር ሎምባርዲያ ፈረሰ 

ሎምባርዲያ

👉ከ10 ዓመት በፊት ምን ተወስኖ ነበር?

(ዳዊት ዓለሙ)

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሜክሲኮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው እና የከተማይቱ ቅርስ የሆነው እድሜ ጠገቡ ሎምባርዲያ ካፌ የሚገኝበት ህንጻ ፈረሰ።

የብዙዎችን ትዝታ የያዘው፥ ቀደምት ከሆኑ ካፌዎች መካከል የሚመደበው፥ የሜክሲኮው አድባር – ሎምባርዲያ ካፌ መፍረሱ ብዙዎች አስቆጥቷል። 

የሼክ አህመድ ሳለህ አልዛህሪ ህንፃ እንደሆነ የሚነገርለት፥ ሎምባርዲያን ጨምሮ በርካታ አግልግሎት መስጫ ተቋማትን የያዘው ይህ ቅርስ፥ በባለሞያዎች ተጠንቶ በቅርስነት እንዲመዘገብ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለቅርስ ጥበቃና ክብካቤ ጥበቃ እንዲደረግለት በ2016 ዓ.ም ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቦ ነበር።

የቱሪዝም ቢሮው ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ለአዲስ አበባና ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ፣ ሕንፃው ቅርስ መሆኑን ገልጾ በማስተር ፕላኑ በቅርስነት እንዲያዝ አስታውቆም ነበር፡፡

በወቅቱ ይሄን ጉዳዩ የተከታተሉት ከፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ከቅርስ ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ደረጃ ማውጣት ዳይሬክቶሬትና ከቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት፣ እንዲሁም ከራሱ ከቢሮ የተውጣጡት ባለሙያዎች የቅርስ መሥፈርት ያሟላል በማለት ወስነው ነበር። የማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃውን በቅርስነት እንዲያዘውም ተጠይቆ ነበር፡፡

ሆኖም ከወራት በኋላ የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ውሳኔውን በመሻር፣ ‘ይህ ጥንታዊ ሕንፃ ቅርስ አይደለም’ በማለት አስደንጋጭ መረጃን አውጥቷል። እንደምክንያት የጠቀሰውም “በከተማችን እየተካሄደ ያለው ልማት መደናቀፍ የሌለበት በመሆኑ በመግለጽ ሕንፃው የቅርስነት መስፈርት አያሟላም” ሲል ውሳኔውን በውሳኔ ሽሯል። በቅርስነትም እንዳይመዘገብ መወሰኑ ታውቆ፥ “እየተዘጋጀ ባለው ማስተር ፕላን ላይ በቅርስነት እንዳይመዘገብ” በማለትም ግልጽ ደብዳቤ ጽፎ ነበር።

ውሳኔው ይፋ ከሆነ 10 ዓመታት ተዳፍኖ የነበረው እድሜ ጠገቡ ህንፃ የማፍረስ ተግባር ዘንድሮ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል። ሎምባርዲያ የሚገኝበትየሼክ አህመድ ሳለህ አልዛህሪ ህንጻ እጣ ፈንታ፡ ልክ ሰሞኑ ከአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪ.ሜ ሙዚየም ግንባታ ጋር ተያይዞ ከፈረሱት የኢየሩሳሌም እና የቴሌ ጥንታዊ ህንፃዎች ተርታ ሆኗል።

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚነቀሳቀሱ ፖለቲከኞች ጋር ባደረጉት ውይይት፡ መንግስታቸው ምንም ቅርስ እንዳላፈረሰ ሲነገሩ ተሰምተዋል። መረጃ ጠቅሶ ‘ይሄን ቅርስ አፍርሳችኋል ብሎ የሚጠይቀን የለም’ ማለታቸውም ይታወሳል።

የከንቲባዋን ንግግር ተከትሎ፡ ከዚህ ቀደም የፈረሱትን እንኳ ብንተው የዛሬው የሎምባርዲያው ህንፃ መፍረስ ማስረጃ አይሆንም ወይ? የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ።

በስልጣን ላይ ያለው የብልጽግና መንግስት የተለያዩ ቅርሶችን ፥ ታሪካዊ ይዘት ያላቸውን በዓላትን እና ዕድሜ ጠገብ ህንፃዎችን በማፍረሱ ምክንያት ፀረ ቅርስ የሚል ስያሜ በብዙዎች ዘንድ ተሰጥቶታል።

___የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ 
t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here