Homeነፃ አስተያየትእውነት አቡነ ጴጥሮስ ‘ሃገር ጥለው ኮበለሉ’ ?

እውነት አቡነ ጴጥሮስ ‘ሃገር ጥለው ኮበለሉ’ ?

Advertisement
World Wide Travel Group
ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ
ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ

(ዳዊት ዓለሙ)

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ እና የኒዎርክና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ‘ከሃገር ጥለው ሸሹ’ የሚሉ ዜናዎች እየተሰሙ ነው፡፡ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ይሄ ዘመቻ የተከፈተባቸው ደግሞ በመንግስት ደጋፊዎች መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ አየሩን ተቆጣጥሮታል፡፡  

ይሁን እንጂ ብጹእነታቸው ወደ አሜሪካ ያቀኑት ጥር 11 የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በሎስ አንጀለስ ለማክበር እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ለማስመረቅ እንደሆነ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በበላይነት የሚመሩት የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ 

ጽ/ቤቱ በመግለጫው፣ በብጹእነታቸው ላይ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሃገረ ስብከታቸው ያደረጉት ጉዞ ሃዋርያዊ ተልዕኮ እንደሆነ እና “በቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ሥርዓት መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነ” መሆኑን በተጨማሪም በቅዱስ ፓትርያርኩ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፈቃድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አያይዞም አቡነ ጴጥሮስ ሃዋርያዊ ጉዟቸውን ሲያጠናቅቁ ጥር 27/ 2016 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና በጽ/ቤታቸው ስራቸውን እንደሚያከናውኑ ገልጿል፡፡

ከሰሞኑ ብጹአን አባቶች በመንግስት ላይ በሚሰነዘሩት ጠንካራ ትችት የተነሳ በአባቶች ላይ የሚደረገው የጥላቻ እና ሃሰተኛ መረጃ የቀጠለ ሲሆነ፣ በአቡነ ጴጥሮስ ላይም የተሰነዘረው ሃሰተኛ መረጃ የዚህ እንቅስቃሴ አካል እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አባቶችን ‘ህገ ቤተ ክርስቲያንን ያላከበረ ነው’ በማለት ከአቡነ አብርሃም ጋር ፊት ለፊት ሲጋፈጡ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስ ይሄ ቤተክርስቲያንን የታደጉበት ተግባራቸው በመንግስት አካባቢ ቅሬታን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አሁን ላይ የተከፈተባቸው ዘመቻም የዚህ ቤተ ክህነት እውን አለመሆነ ያላስደሰታቸው አካላት ሴራ መሆኑን እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ መንግስትን ክፉኛ የተቹት ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ላይም ቤተ ክርስቲያን ውግዘት እንድታስተላልፍ  ውስጥ ለውስጥ እየተሰራ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ይሄ ውግዘት እውን እንዲሆን የሚንቀሳቀሱ አካላት በተመሳሳይ “አቡነ ጴጥሮስ ወደ ውጪ ኮበለሉ” ብለው የሃሰት መረጃ እየነዙ የሚገኙት ናቸው ተብሏል፡፡ እንቅስቃሴው ቤተ ክርስቲያንን የመከፋፈል ሴራ አካል እንደሆነም በርካቶች ያምናሉ፡፡

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

- Advertisement -
Advertise here _ borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -spot_img

የቅርብ ጊዜ

- Advertisement -spot_img

Related News