spot_img
Thursday, July 25, 2024
Homeነፃ አስተያየትየብልጽግና ፡ የመጨረሻው መጀመሪያ (ዳዊት ዓለሙ)

የብልጽግና ፡ የመጨረሻው መጀመሪያ (ዳዊት ዓለሙ)

ብልጽግና
የብልጽግና ፖርቲ አመራሮች በፖርቲው ስብሰባ ላይ

ዳዊት ዓለሙ

ከሰሞኑ የሚታዩትና የሚሰሙት ወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች አጃኢብ የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና በውስጡ የተፈጠረው መፍረክረክ አፍጥጦ እየወጣ ነው፡፡ የውድቀቱን ምልክቶች በግልጽ እያየን ይመሰላል፡፡ መቼም ከወደቀ እኮ ቆየ የሚል ሰው አይጠፋም፤ እውነት ነው ከወደቀ ቆይቷል፡፡ ሆኖም የመጨረሻው የውድቀቱ መጀመሪያ ሚስማር ለመመታቷ አሁን ላይ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

አምና በቀናት ውስጥ እቋጨዋለሁ ብሎ የጀመረውን ከፋኖ ጋር ጦርነት አሁን ላይ ወራትን አስቆጠሯል፡፡ በመንግስት በኩል እያስከፈለው ያለው ዋጋ እና የደረሰበት ጫናም በግልጽ መታየት ከጀመረ ሰነባበቷል፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፣ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር በድጋሚ በፈጠረው ጣልቃ ገብነት የኦሮሞው ሲኖዶስ ድጋሚ እንዲያንሰራራ፣ በሊቃነ ጳጳሳት መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር በማድረጉ አብዛኛው ክርስቲያን ፊቱን አዙሮበታል፡፡ በአናቱ ላይ የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ከሃላፊነታቸው ለቀቁ (ተነሱ) መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ የቀድሞው የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በቁም እስር ላይ መሆናቸውም በዚሁ በቦርከና ተዘግቧል፡፡

የአቶ ደመቀን እግር ተከትለው ስልጣናቸውን እንደሚለቁ የMኢጠበቁት የፍትህ ሚንስትሩ ዶ/ረ ጌዲዮን ጢሞቲዎስም የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ መሰንበታቸውም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እየተናገሩ ነው፡፡ እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት ነገር ከፓርቲ አባል ውጪ ሆነ ተቋማትን ይመሩ የነበሩት የፌዴራል ፍ/ቤቶች ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እንዲሁም የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳን የዚህ መንግስት የቁልቁለት ጉዞ ማሳያ ናቸው፡፡

እንግዲህ ዋና ዋናዎቹ ባለስልጣናቱ እየተቀነሱ ከሆነ መደመር ወዴት አለህ አያሰኝም? የዚህ ሁሉ ድምር ውጤቱ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸው የብልጽግና ገደል አፋፍ ላይ ለመሆኑ ሁነኛ ምልክት ነው፡፡

አብዮት ልጆቿን ትበላለች እንደሚባለው፣ ገዢው ፓርቲ ከኦፒዲኦ ወደ ብልጽግና ስያሜውን ከመቀየሩ በማለዳው ነበር ‘የለውጡ ፋና ወጊ’ የሚባሉትን አቶ ለማ መገርሳን በግፋት የጀመረው፡፡ ቀጥሎ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ‘መንግስት ከአማራ ታጣቂዎች ጋር መደራደር አለብት’ የሚልው ንግግራቸው ከለውጥ ቀልባሽነስት አስቆጥሯቸው፤ ከመድረኮች ገልል እንዲሉ አለፍ ሲልም ለቁም እስር ዳርጓቸዋል፡፡

ለእናት ፓርቲያቸው ሳይቀር ጠንካራ ትችት ማቅረብን የማይፈሩት አቶ ዮሃንስ ቧያለውም ቢሆኑ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ተወካዩ ዶ/ር ተሻገር እንዲሁም የሰላም ሚንስትሩ አቶ ታየ ደንደአ ወደ ወህኒ ለመወርወር የፓርቲም ሆነ የምክር ቤት አባልነታቸው አላዳናቸውም፡፡ አገር ጥለው የተሰደዱትን የታችኛው አመራር አባላት ደግሞ መስሪያ ቤታቸው ይቁጠራቸው፡፡

በቁጥር ደርጃ ከታየ የአማራ ባለስልጣናት በእስርና በስንብት ስም አብላጫውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ብልጽግና ያይናቸው ቀለም ያላማረውን የኦዲፒ (ኦሮሚያ) ብልጽግና አባላቱን ለማ መገርሳም ይሑን ታከለ ኡማ ወይም ደግሞ ታየ ደንደአ …. ከገሸሽ ከማድረግ አይመለስም፡፡ በነገራችን ላይ የፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ባገኙት አጋጣሚም የሚያስተላልፉት መልእክት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ያላቸው ስልጣን የተገደበ ቢሆንም ፕሬዝዳንቷ የሚሰማ ካለ ግልጽ መልእክት እያስተላለፉ ነው፡፡

ምናልባት የገዢውን መንግስት እስትንፋስ የተወሰነ መንገድ ሊቀጥል የሚችለው በዙሪያው ያሉት፤ የሆነ ጊዜ ትልቅ ቦታ ተሰጥቷቸው የነበሩ ባለስልጣናት አብረውት ከቀጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደዚያም ሆኖ የህዝቡ በፓርቲው ላይ ያለው እምነት ሊቀየር አይችልም፡፡ የፍጻሜው ፊሽካ የሚሰማው እነዚህ በሰዎች ዘንድ ከበሬታ የነበራቸው ሰዎች የስልጣን መልቀቅ ወይም የመሰናበት እጣ የደረሳቸው ቀን ሊሆን ይችላል፡፡

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here