spot_img
Wednesday, June 12, 2024
Homeነፃ አስተያየትአማራነት እና የብሔርተኝነቱ ልክ (በደሳለኝ ቢራራ)

አማራነት እና የብሔርተኝነቱ ልክ (በደሳለኝ ቢራራ)

በደሳለኝ ቢራራ

በደሳለኝ ቢራራ
ጥር 20 2016 ዓ .ም.

መግቢያ

ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ጃንዋሪ 22/2024 ቦርከና ላይ በታተመ ሁለት ገጽ ጽሑፍ፡ የጋብቻ ፖሊሲ ስለማርቀቅ ባቀረብኩት ሀሳብ ላይ የደረሰኝ ትችት ነው። ብዙ ትችቶች ደርሰውኛል፡ አንዱ ግን መልስ እንድጽፍበት አስገደደኝ። ያቀረብኩትን የፖሊሲ ሀሳብ “የኢትዮጵያኒስት ሀሳብ ነው” የሚል ነበር። ማለትም ሀሳቡ የአማራ ብሔርተኝነትን የሚያግዝ ስላልሆነ አንቀበለውም በሚል የተቃውሞ ድምጸት ነው ግብረ-መልሱ። እና የአማራ ብሔርተኝነት ላይ ያለውን የአረዳድ ብዝሀነትና መጣረስ ስለታዘብኩ ያለኝን የአማራ ብሔርተኝነት አተያይ ለማስረዳት ፈለግሁ። 

በፖሊሲው ምክረ-ሀሳብ ላይ ስልክ ደውላችሁ የሞገታችሁኝ፤ መልእክት የጻፋችሁልኝና መልስም የላኩላችሁ፤ በሀሳብ መመካከሪያ ቡድኖች ውስጥ የተከራከራችሁኝ እና በኢሜይል ማብራሪያ እንድሰጥ ወይም ጽሑፌን እንድሰርዝ የጠየቃችሁኝ በሙሉ አከብራችኋለሁ። ትችቶቻችሁን ሁሉ ስቀበል ገንቢ ናቸው ብየ በማመንና ስጋቶቻችሁን ሁሉ ከልብ በመረዳት ነው። 

በእርግጥ ሁሉም ትችቶች በሚባል ደረጃ በጽሁፉ ውስጥ ተግዳሮቶች ተብለው በተዘረዘሩት አራት ነጥቦች የተጠቀሱት ናቸው። በስድብና ማንጓጠጥ መልክ የቀረቡ ደግሞ በርካታ ግብረመልሶች ትዊተር ላይ አይቻለሁ። ለእነርሱ ብዙም ትኩረት አልሰጠኋቸውም። ምክንያቱም የትዊተር አጸፋዎች እንደ አየሩ ጠባይ የሚግሉና የሚቀዘቅዙ ስሜቶች መሆናቸውን ደጋግሜ ታዝቤያለሁ። ስሜቶችን ደግሞ ትችት አድርጌ መውሰድ አልፈልግም። አጠቃላይ የፖለቲካ ሀሳብ ክርክርን በተመለከተ ያለን ባህልና ስነምግባር ግን የሚያሳስበኝን ነገር ሳላሳውቅ ማለፍ አልፈልግም። 

በተለይ በአማራ ፖለቲካ ውስጥ እንኳን የልዩነት ሀሳቦች ይቅርና የድጋፍ ድምጾችን የምንመለከትበት አተያይ እጅግ አስፈሪ እየሆነ ነው። ይህ የህልውና ትግሉን ይጎዳዋል። ጭፍን ውግዘት በርካታ ተቆርቋሪዎችንና አጋዦችን ገፍቶብናል። በአንድ ወቅት ኦስማኖቪች የሚባል በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ተከታይ ያለው አንቂ “የአማራን ብሔርተኝነት አምንበታለሁ፡ መደገፍም እፈልጋለሁ። ነገር ግን እጅግ አስፈሪና የማያስቀርብ አድርገውታል። ምን አገባችሁ ነው የሚሉን” ብሎ ነበር። 

ባሳለፍነው ሳምንትም ፕሮፌሰር ሀብታሙ ተገኘ እና አቻምየለህ ታምሩ ያቀረቡትን መሰረታዊ አካሄዶችን የማጠየቅ ጥያቄዎች እንደ ሀሳብ ተቀብሎ ከመወያየት ይልቅ ሰዎቹን የሚያወግዝና የሚደግፍ ቡድን ወደመለየት ነው የተገባው። በምን ጉዳይ ሲሆን ነው ተቀራርበን መወያየት የምንችለው? የፕሮፌሰር ሀብታሙን ጉዳይ እዚህ ላይ ያነሳሁት ደጋፊም ነቃፊም ሁኜ አይደለም፤ ነገር ግን መወያየት የማንችል መሆናችን ስለሚከነክነኝ ነው። ስለአማራ የህልውና ትግል እና የብሔርተኝነቱን ልክ በተመለከተ ግን ከሁለቱም አካላት ማለትም ከነፕሮፌሰር ሀብታሙና ከእነሻለቃ ዳዊት የተለየና የባሰ አተያይ አለኝ። እነአቻምየለህን “ለምን ጥያቄ ታነሳላችሁ?” ብሎ የሚረግም ወይም ሻለቃ ዳዊትን “ከትግላችን አጠገብ ድርሽ እንዳይል!” የሚል አእምሮ እኔንም በዚህ ጽሁፍ ይህን አተያይ ሳቀርብ የሚያወርድብኝን ማንኛውንም ውግዘትና ስድብ ለመቀበል በቂ የስነልቦና ዝግጅት አድርጌ እንጅ “ጎሽ! አበጀህ የኛ ልጅ!” እባላለሁ ብየ አይደለም። ይህን አተያይ ከማንኛውም ቡድን ጋር ከማጋጨት ወይም ከማዳበል ይልቅ በራሱ አድማስ ለመረዳትና የሚኖሩትን አሉታዊና አወንታዊ ገጽታዎች ገንቢ በሆነ መልኩ ቢሞገት ደስ ይለኛል። 

የአማራ ብሔርተኝነት

ከወቅታዊው ነባራዊ ሁኔታ ለመጀመር ያህል የአማራ ብሔርተኝነት እየተቀነቀነ ያለው አማራ-ጠል ስርአቶች ሰፍተው በሰጡት ልክ ነው። ብሔርነቱንም ወርድና ቁመት ለክተው የሰጡት ህወሓትና ኦነግ ናቸው። ይህን ተቀብለው ከታሪካዊ የማህበረሰቡ እርስት ጋር የተገናኘ ማንነትን የማነጽ ብሔርተኝነት (ኢሪደንቲዝም) አስመስለው የሚያቀነቅኑት አሉ። ነገር ግን ይህ ከትክክለኛው አማራነት ያነሰ እና የኮሰሰ ጎጠኝነት  መሆኑን ማስገንዘብ እፈልጋለሁ። የአማራ ዘውግ ማንነት አሁን የአማራ ተብሎ በተካለለ ቦታና በእርስትነት ጥያቄ በተነሳባቸው ቦታዎችም እንኳ የተወሰነ አይደለም። አማራነት ከዚያ ይሰፋል። በሚገርም ሁኔታ በጠላት ጥብቆ ልክ ለመሆን እና ላለመሆን በሚደረግ ፍርግጫ አማራነትን  ለንዑሳን ማንነቶች መነሻ እየተደረገ ነው። ምክንያቱም አማራነትና ብሔርተኝነቱ በዋናነት በአራት ክፍለ-ሀገሮች (አማራ ክልል ተብለው በሚታወቁ) ቦታዎች የተገደበ እንዲሆን ሌትም ቀንም የሚሰሩ አሉ። እነዚህ ኃይሎች የአማራ ብሔርተኝነት ትክክለኛ አቀንቃኝ እኛ ነን የሚሉና ሌላውን ሁሉ አተያይ ለማጠልሸት የትኛውንም ያህል ርቀት ለመሄድ የሚዳፈሩ ናቸው። ከዚሁ ፋንዳሜንታሊስት ስብስብም “አባት ሀገር አማራ” የሚሉ ሰምቻለሁ። 

በዚህ አሰላለፍ የከረረ መካሰስና መወጋገዝ ይበረታል። ከፍተኛ መጠራጠርና መፈራረጅም አለ።  ሞገደኝነትና ከፍተኛ የስሜት ማእበልም ይንጠዋል። ገዥው ስርአትም ይህንን ስሜታዊነት ተረድቶ በየዕለቱ መነጋገሪያ የሚሆኑ ጉዳዮችን የሚፈጥረው ይህንን ቡድን ኢላማ አድርጎ ነው። ስሜታዊነቱ የአጀንዳ ተቀላቢ አድርጎታል። አጀንዳ ተቀላቢ መሆኑን ግን አያምንም። ይህንንም መወዘጋገብ በመሀሉ እየገባ የሚያምሰው ብአዴንነትን እየረገመና እያወገዘ ብሔርተኝነቱን ባለበት እንዲረግጥ የማድረግ ተልእኮ የወሰደው ዳያስፖራው የብአዴን ክንፍ ነው። ብአዴንን በመስደብ ከዚህ የብአዴን ክንፍ ማንም አይበልጥም። ትክክለኞቹን ተቆርቋሪ አማሮች “እናንተ ብአዴን ናችሁ” ብሎ ቁምነገር ካለው ዲስኮርስና ከማህበራዊ ሚዲያው እንዲጠፉ የሚያደርጋቸው እራሱ ብአዴን ነው። 

ሁለተኛው የአማራ ብሔርተኝነት ደግሞ ከመጀመሪያው ሰፋ ያለ፡ አቃፊ የሚመስልና የሌሎች ብሔረሰቦችንም ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው። ይህ ብሔርተኝነት “አባት ሀገር አማራ” ከሚለው ኃይል ጋር ተደጋጋፊ የሚመስል፡ ነገር ግን ተፎካካሪ አስተሳሰብ ሁኖ “ኢትዮጵያዊነት” የሚባለውን ከዘውግ ውጭ የሆነ ብሔራዊ ማንነትን የሚያቀነቅነው አሰላለፍ ነው። መጀመሪያ የተብራራውን የአማራ ብሔርተኝነት፡ “መዳረሻውን ኢትዮጵያዊነት እናደርጋለን” የሚል ስለሆነ አሁን በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተፎካካሪ አስተሳሰቦች እንጅ የአንድ አስተሳሰብ ሁለት ደረጃዎች እንዳልሆኑ ማስመር እፈልጋለሁ። 

የመጀመሪያው አስተሳሰብ አማራነትን በራሱ አጽንቶ እንደማንኛውም ብሔርተኝነት ሀገር እስከመሆንም የሚያዘልቅ አቋም ሊኖረው ይችላል። የየትኛውም ብሔርተኝነት ግብ ሀገር መሆን ነው። ሁለተኛው ግን የሀገር ስልጣን ለመያዝ ብሔርተኝነቱን መንገድ ወይም ስልት አድርጎ የሚጠቀም ነው። “ስልጣን ከያዘ በኋላ ብሔርተኝነቱን ያፈርሰዋል ወይስ ያስቀጥለዋል?” የሚለውን ጥያቄ በሂደቱ ላይ ማንሳት ሊያስቆጣው ይችላል። ከስልጣን መያዝ በኋላ የሚወሰዱትን እርምጃዎች የሚወስነው የወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ስለሚሆን አሁን ላይ መልስ መስጠት ወይም ቃል መግባት አይችልም። 

በአማራ ብሔርተኝነት ውስጥ “መዳረሻየ ኢትዮጵያዊነት ነው” የሚለውን አስተሳሰብ ዶ/ር ምስጋናው አንዷለም “ታክቲካል የአማራ ብሔርተኝነት” ሲል ኢሪደንቲስት ነኝ ከሚለው ይለየዋል።  

በእኔ አተያይ ታክቲካል ብሔርተኛውም ሆነ ፋንዳሜንታል ብሔርተኛው ኃይል አማራነትን በወርድና ቁመቱ ልክ ተረድተውታል ብየ አላምንም። የአማራን መሰረታዊ አንድነትና ክብርም በተናጠል ያመጣሉ ብየ አላምንም። ሁለቱም የአውድ ጥበትና አድማሳዊ ብዥታ አለባቸው። ግልጽ በሆኑ ስልቶችና መሳሪያዎች እናሳካዋለን የሚሉት ግብ አልተገለጸም። “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” እንዲሉ ሁለቱም አካሄዶች ከስልጣን ቢያደርሱ እንኳ ተቀምጦ የሚጠብቃቸው ውዝፍ ስራ ይኖራል። የአማራ ብሔርተኝነት ሲቀነቀን “አማራነት ምንድን ነው? አማራስ ማነው? የትስ ይኖራል? ስንት ነው? ምንስ አለው?” ተብሎ መጤን አለበት። የአማራ ብሔርተኝነት በዚህ መሰረት መቃኘት አለበት። ሁሉንም የኢትዮጵያ ወረዳዎች ተዘዋውሮ እንዳጠና የስነማህበረሰብ ባለሙያ ባለኝ እይታ፡ አማራ ከኢትዮጵያ አያንስም አማራነትም ከኢትዮጵያዊነት አያንስም። ይህን አተያይ ጭፍን ሪቫንሽዝም ብለው የሚፈርጁ አካላት ቢኖሩ አያስጨንቀኝም። ካየሁት ካጠናሁትና ከማውቀው ተነስቸ ነው ይህን እይታ የማቀርበው። 

አማራነት 

በአማራ ማንነት ላይ ከተደረጉት ጥልቅ ጥናቶች መካከል “On the origins of Amhara” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ በ1993 ዓ/ም በሴንት ፒትርስበርግ የአፍሪካ ጥናት ጆርናል ላይ የታተመው የቸርነት እና ሰቪር ጽሑፍ ይገኝበታል። የጽሑፉ አጠቃላይ ጭብጥ የአማራን ማንነት መልክአምድራዊ አሰፋፈር እንጅ በዘር ግንድ ትስስር እንዳልሆነ ሲያስረግጥ “Amhara is toponym, not an ethnonym.” ይለዋል (https://books.google.be/books?hl=nl&id=jJhxAAAAMAAJ&focus=searchwithinvolume&q=on+the+origins+of+Amhara) ። ብሔረሰቦችን የመሬት ባለቤት ከሚያደርገው የክልል አስተሳሰብ ጋር ዝምድና ያለው አረዳድ ይመስለኛል። በአንጻሩ በአማራ መሬት ላይ ስለሚኖረው የሌላ ማንነት ያለው ህዝብ አለማንሳቱ የሚተነትነው ርዕስ ማህበራዊ ጉዳይ መሆኑን የዘነጋው ያስመስላል። አማራ መሬት ከሆነ ባለቤቱ አማራ ነኝ የሚል ሰው መሆኑ ገሀድ ነው። 

አማራነት እንደ ከተሜነት

ሲግፍሪድ ፓውዘዋንግ የሚባሉ ተመራማሪ “The two-faced Amhara identity” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ በ2005 ዓ/ም ባሳተሙት የምርምር ጽሑፍ “Amhara is the Amharic speaking urban population using the elite culture in Ethiopia. … it is a collection of diverse ethnicities who assimilated to exercise Ethiopianism & adopt elite lifestyles’ (https://brill.com/view/journals/scri/1/1/article-p273_17.xml?language=en) የሚል ማጠቃለያ አስፍረዋል።

በግርድፉ ሲተረጎምም ‘አማራ ማለት አማርኛ ቋንቋ የሚናገረውን የአብዛኞቹ ከተሞች ህዝብ እና እራሱን በኢትዮጵያዊነት የሚገልጸውን ከተሜ ያጠቃልላል’ ይላል።  ፓውዘዋንግ ይህንን የአማራ ማንነት ሲጠቅስ ከዘር፥ ሐይማኖትና ባህል ያለፈ የአንድነት ስሜትን በመስፈርትነት ወስዶ ነው። ማሳሰቢያም አስቀምጧል። “Ethnicity is identity, not race or belief or culture. A nation consists of those who feel to be, who identify themselves as one… nationalism becomes dangerous when it is used to engage offers for a suggested common ground, hiding differences of interest for the sake of creating unity for an undefined & obscure agenda… the ethnic group of the Amhara, mostly a peasant population, is different from a mixed group of urban people coming from different ethnic backgrounds, who have adopted Amharic as a common language & identify themselves as Ethiopians.”  

በመሆኑም በፓውዘዋንግ አተያይ ሁለት አይነት የአማራነት ማንነት አለ። የአማራነት ሁለት ገጽታ (two faced identity) በሚል ርዕስ ያቀረበውም ይህንን ነው። አንደኛው ከተለያዩ ብሔረሰቦች ተውጣጥቶ በከተሞች ተደባልቆ የሚኖረው ህዝብ ከየግሉ ዘር፥ ሐይማኖትና ባህል አልፎ እንደ አንድ የከተማ ማህበረሰብ የሚያስተሳስረውን እሴት አዳብሮ በኢትዮጵያዊነት እራሱን የሚገልጸውን አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በስፋት በግብርና የሚተዳደረውን በባህል፥ በዘር እና በሌሎቹም መገለጫዎቹ አማራ ነኝ የሚለውን ማህበረሰብ ነው።  

አማራነት እንደ ክርስትያንነት

“የሰው ልጅ ትውልድ እንጅ ዘር የለውም”!

በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመንግስት ሐይማኖት የተደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአማራን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ህዝቦች ማንነት በእምነቱ አስተምህሮ መሰረት በመተርጎም ለማስረጽ እና ተቀባይነት እንዲኖረውም ለማድረግ ሞክሯል። አማራው ቀድሞ የነበረውንና ለእልፍ አእላፍ ዘመናት ተደራጅቶ በርካታ ስልጣኔዎችን የሰራበትን የማንነት መሰረት ንዶ ከሌሎች ህዝቦች በተለየና በፈጠነ መልኩ ክርስትናን አዲስ ማንነቱ እንዲሆን የተዳረገው እራሱ የሰራው ስርአተመንግስት አምኖ የተቀበለው ስለሆነ ነበር። በክርስትና አስተምህሮ የሰው ልጆች ሁሉ የአዳምና የሄዋን ልጆች ስለሆኑ አሁን በምድር ላይ ያሉት ሰዎች በሙሉ ትውልዳቸው ይለያያል እንጅ ዘራቸው አንድ አዳምና ሄዋን ብቻ ነው። በመሆኑም ሰው ከሰው የተለየ ዘር የለውም የሚለው አስተሳሰብ ሰርጾ በመጀመሪያ የዘር ማንነቱን ያፈረሰው የራሱን የአማራውን ህዝብ ነበር። በአንጻሩ ሌሎች ማህበረሰቦች ክርስትናንም አይሁድነትንም ወይንም በወቅቱ ይተገብሩት የነበረውን ልዩ ልዩ የእምነት ስርአት ከነባሩ የማህበረሰብ ማንነታቸው በላይ መገለጫቸው አድርገው አላሰረጹትም ነበር። በመሆኑም አማራው በወቅቱ ሌሎች ህዝቦች ሊረዱት ከሚችሉት የማንነት አድማስ እጅግ የሰፋ ክርስቲያንነት የሚባል ማንነትን ሲቀበል ዘርና ቋንቋን የተሻገረ አካታች አድማስ ነበረው። 

በአንጻሩ ሌሎቹ ነባሩን የቋንቋ እና የዘር ማንነታቸውን እንደጠበቁ እና በዛም መሰረት የነበራቸው ማህበራዊ ስሪት ሳይፈርስ ነበር በመንግስት አዋጅ የተጣለባቸውን አዲስ ማንነት የተቀበሉት። በዚህ የተነሳ የአማራው ነባር ማንነት እና ዘርን መሰረት ያደረገው ማህበረሰባዊ ስሪት እየፈረሰ መንግስት በሰራው ሐይማኖታዊ ስሪት ሲካተት የራሱ የዘር ማንነት አካል ያልነበሩትንም ከራሱ እኩል ወገን አድርጎ ተቀብሏል። ሌሎቹ ግን ሰፊውን መንግስት-ሰጥ ክርስቲያናዊ ማንነት እንደ ዋና ማንነት ተጠቅመው በውስጡ በዘራቸው ማንነት እና በቋንቋ ደግሞ የተሰናሰሉ: ከዘውጋዊ ትስስሮቻቸው ነባሩን አማራ ያገለሉ ህዝቦች ነበሩበት። የአማራው ቀደምት ማንነት ፈርሶ ክርስቲያንነት ሲሆን የሌሎቹ ሁለቱንም ይዞ መቀጠል ችሏል። እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ነገር እስልምና እንደ ሐይማኖት ከመጀመሩ ከ300 አመታት በፊት የተፈጠረ የማንነት ስሪት መቀያየርን ነው የተነሳው። አማራነትን ከክርስቲያንነት ጋር አቻ አድርገው የሚተረጉሙ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ጸሐፊዎች፡ እስላሙን ማህበረሰብ ደግሞ አማራ ያልሆነ ወደሚል ፈጽሞ መሰረት የሌለው አመዳደብ ወስደውታል። በዘርም በሐይማኖትም አማራ የነበረው ህዝብ ነው ከጊዜ በኋላ እስልምናን የተቀበለው። ስለዚህ እስላሙም አማራ ነው። 

ሐይማኖትን ማእከል ያደረገው ይህ የማህበራዊ ፖለቲካ ስሪት በተለይ በ15ኛው እና 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተነሱ ነገስታትና ልሂቃን አንቂዎች አድማሱን በማስፋት የተጠናከረ መሰረት ይዟል። በአጼ ዘረያዕቆብ ዘመን ከፍተኛ የሆነ ክርስትናን የማስፋፋት እንቅስቃሴና ተጋድሎ ተደርጓል። እንደሚታወቀው በግራኝ አህመድ ጦርነት የደረሰው የክርስትና ቅርሶችን የማጥፋትና ክርስትያኖችን የመግደል ዘመቻ አማራውን ከዘር ማንነቱ ይልቅ በሐይማኖቱ እንዲጠነክርና በአንድነት ተነስቶ ህልውናውን እንዲያስቀጥል አስገድዶታል። በሐይማኖት የሚመሳሰሉት ህዝቦች የፈጠሩት ትብብርም ህልውናውን እንዳስቀጠለለት የተረዳው ህዝብ ክርስቲያንነቱን ዋና ማንነቱ አድርጓል። ጥቃት ሲደርስበት እና ጥቃቱን ለመመከት ሲነሳም የሚጠቀምበት ማንነቱ ክርስቲያንነቱ ሁኖ ነበር። በመሆኑም አማራ ነኝ ሲል ክርስቲያን ነኝ ከማለት ጋር እኩል ትርጉም ሊሰጠው ይችላል። በሐይማኖቱ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ጥቃትም በማንነቱ ላይ የተደረገ የህልውና አደጋ አድርጎ ስለተረዳው “ቢስማር ሲመታ ይጠብቃል” እንዲሉ ከዘር አማራነቱ ይልቅ ክርስቲያንነቱን ሙሉ በሙሉ ማንነቱ ወደ ማድረግ አድጓል። 

አማራነት እንደ ርዕዮተ ዓለም

የዳማትና የአክሱም ስርአተ መንግስታትን የመሰረተና ህያው ሁኖ የሚኖር የታሪክ አሻራ ያለው፡ ለብዙ ሽህ ዘመናት ለዓለም ስልጣኔ ፋናወጊ ሁኖ የዘለቀውን የአማራ ህዝብ አሰራርና ስሪቱን ከሌሎች ማህበረሰቦች ስነልቦናና ስሪት አንጻር በመቃኘት ሊወዳደርላቸው አልችል ሲል፡ ህዝብነቱን ትተው “አማራነት ርዕዮተዓለም ነው” የሚሉ ብዙ ምሁራን አሉ። ምክንያቱም አማራ ፍጹም ርትዕ-ገዝ ህዝብ ነው። በለስ ቀናኝ ብሎ ደካማውን አይደፈጥጥም። አቅም አጣሁ ብሎም ለጉልበተኞች እጅ አይሰጥም። እስከ ህልፈተ ህይወቱ የሚከተለው የህይወት ፍልስፍና እና መርህ አለው። እጅግ ፍትህ ወዳድና ስለፍትህ ማንኛውንም መስዋእትነት የሚከፍል ከፍተኛ ሞራል ያለው ህዝብ ነው። እኩልነትን የሚሻውና ለፍትህ የሚሰዋው እውነተኛ ሰላም መኖር የሚችለው በዚህ መንገድ እንደሆነ ተረድቶ በማህበራዊ ስሪቱና አሰራሩ አስርጾታል። የህዝቦች አንድነትና ወንድማማችነት የእኩልነትን እሴት የማይጋፋ መሆኑን በተግባር ለማሳየት ከዘሩ በተጨማሪ የቋንቋን እና የሐይማኖትን አጥር አልፎ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተዋህዶ በመስራትና በመኖር ታላላቅ ስልጣኔዎችን ለዓለም አበቃ። በእርግጥም “አማራነት ጽንሰ-ሀሳብ ነው” የሚያስብል በርካታ ረቂቅ እሳቤዎች፥ እሴቶች፥ ስሪቶችና አሰራሮችን አበርክቷል። 

ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን አማራነት የማህበራዊ ፖለቲካ አይዲዮሎጂ ነው ብለው ያምናሉ። በርካታ የኦሮሞ ተወላጆችም በአይዲዮሎጅው በማመን የነበረውን ስርአተመንግስት የተቀላቀሉና አማራዎች የሆኑ እንደነበር ይከራከራሉ። ለአብነትም የሚያነሱት የአጼ ምኒልክ ጦር ዋና አዛዥ የነበሩትን ደጃች ጎበና ዳጨ እና መሰል የሸዋ ቱለማዎችን ነው። በእርሳቸው አተያይ አማራነት ከነገስታቱ፥ ከወታደሮቹ እንዲሁም ከህዝቡ ነባር የጎሳና የዘር ማንነት የተለየ ሁሉም በጋራ የሚፈልጉት እና ጸንቶም እንዲኖር የሚጠብቁት አስተዳደራዊ ስሪትና ርዕዮተ ዓለም ነው። ይህም በመሰረታዊነት እንደ ነገድ አማራ የሚባለውን ህዝብ በአንድ ዘር፥ ቋንቋ፥ ታሪክ እና መልክአምድር ተጋሪ ማህበረሰብ መገለጫነት የሌለ የሚያደርግና “የመንግስት ስርአት” መሆንን ብቻ የሚተነትን ነው። 

አማራነት እንደ ደገኛ

ከክርስቲያንነት ጎን ለጎን የሚነሳው የአማራ ማንነት በደጋ አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ መሆኑ ነው። ከኢትዮጵያ መልክአምድርና ከአማራው ስርጭት አኳያ “በደጋ የሚኖር ህዝብ” መባሉ ትክክል ነው። ነገር ግን እንደ አንድ ማህበረሰብ ትርጉም ሲሰጥ በዚህ የተቀነጨበ ወይም የተለጠጠ መስፈርት ሊሆን እንደማይችል በድፍረት ለመናገር ምሁርነት አይጠይቅም። ምክንያቱም በደጋ የሚኖር ህዝብ ሁሉ አማራ ብቻ ላይሆን ይችላል፤ በቆላ የሚኖር አማራም እነዳለ የዘነጋ አተያይ ነው። ደጋማ አካባቢዎች አስቀድሞ በብዛት አማራ የሰፈረባቸው ቢሆኑም ከአማራው ውጭ የሆኑ ህዝቦችም ሰፍረው የኖሩባቸው ደጋ አካባቢዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ። የትርጉም ማጠቃለያ አሰጣጡ ላይ ስህተት ቢኖርበትም ግን አማራን ከደገኛነት ጋር የሚያቆራኘው እውነታ ከታሪክ የሰነድ ማስረጃዎች በተጨማሪ በሳይንሳዊ የዘረመል ጥናቶችም ማረጋገጫ ያለው ሀቅ ነው። አማራ በደጋማዎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰፍሮ የኖረ ቅድመቀደምት ህዝብ ነው። 

ደገኛነት እና ቅድመ-ቀደምት ኢትዮጵያዊነት

በደጋማዎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሚኖሩ ሰዎች ናሙና እየተወሰደ ከአርባ አመታት በላይ በተደረገ የዘረመል ጥናት አማራዎች ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ ያስመዘገቡት ውጤት አለ (https://journals.plos.org/plosone/article?id=10.1371/journal.pone.0002342) ። ሌሎቹ ናሙናዎች ባስገኙት ውጤት ሲታይ የደጋማውን አካባቢ ተላምዶ ለመኖር የሰውነት አካላቸው በቂ የዝግመተ ለውጥ እድገት የሚያገኝበትን ጊዜ ያህል በቦታው እንዳልቆዩና በዚህም የተነሳ በአየር ንብረቱ ምከንያት የሰውነት ስርአታቸው መረበሽ እንደተስተዋለ ተረጋግጧል (https://www.ncbi.nlm.nih.gov/pmc/articles/PMC3516565/) ። በኢትዮጵያ ወይና ደጋማ እና ደጋ አካባቢዎች ለመኖር የሚያስችለውን የሰውነት ጀነቲክ ለውጥና ልምምድ ለማዳበር ቢያንስ ሰባ ሽህ አመት በነዚህ አካባቢዎች መኖር እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል። 

“Ethiopian Native Highlander’s Adaptation to Chronic High-Altitude Hypoxia” በሚል ርዕስ ከታተመ የምርምር ጽሑፍ ላይ በጥልቀት እንደተብራራው በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች ለረጅም ዘመናት ያልኖሩ ማህበረሰቦች፡ በተለይም እንደ ኦሮሞ አይነት ዘላን ህዝቦች ከቆላማ አካባቢዎች በተለያየ መንገድ ወደ ደጋማው ዘልቀው ሰፍረው የሚኖሩ ሰዎች (https://journals.physiology.org/doi/full/10.1152/ajplung.00451.2016) በደም ዝውውራቸው ውስጥ በቂ የኦክስጊጅን መጠን ማስተላለፍ ስለሚቸገሩ ሰውነታቸው የሚፈልገውን ተፈላጊ የኦክስጅን መጠን ለማግኘት ሲል ሲስተማቸው የሄሞግሎቢን መጨመር አጸፋ ይሰጣል (https://www.hindawi.com/journals/bmri/2022/5749382/) ። በአማራ እና በኦሮሞ ናሙናዎች ላይ የተደረገ የጀነቲክ ጥናት እንዳረጋገጠው አማሮች በኢትዮጵያ ከሰባ ሽህ (70,000) ዓመታት በላይ ስለኖሩ ለአካባቢው ተስማሚ የሰውነት አካላት ልምምድና በቂ የዝግመተ ለውጥ ሂደት ማድረግ ችለዋል። በአንጻሩ በኦሮሞ ናሙናዎች የተገኘው ውጤት የተለየ ነበር። የጀነቲክ ምርመራው እንዳረጋገጠው በኢትዮጵያ ከፍተኛው መልክአምድር ውስጥ የኖሩት አጠቃላይ ጊዜ ከአራት መቶ አመት ያልበለጠ በመሆኑ ለአካባቢው ተስማሚ የሰውነት ስርአት ለመገንባት የሚፈጀውን ዝግመተ ለውጥ እንዳላደረጉና አእምሮአቸው ላይም ጉዳት እንደሚያሳይ ተመላክቷል (https://doi.org/10.1152/ajplung.00451.2016) ። ይህ የአእምሮ ጉዳትም ሊሆን ይችላል ለበርካታ ማህበራዊ ቀውሶች አስተዋጽኦ ሲያደርግ የቆየው። በርካቶቹ የሰው ሳይሆን የዱር እንስሳት እንኳን ያደርጉታል ተብሎ የማይጠበቅን ነውር በድፍረትና በአረመኔነት ሲፈጽሙ ታይቷል። የጋብቻ ፖሊሲው በሀሳብነት ከተሰነዘረባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ይህንን ችግር በቋሚነት ለመቅረፍም ጄነቲክ ልምምዱን በበቂ ሁኔታ ካደረጉ ማህበረሰቦች ጋር እንዲዋሃዱ በማሰብ ነበር። አሁንም ሌላ ሰላማዊ መፍትሔ የለውም። 

በቲቤት እና አንዲያን ከፍተኛ ደጋማ ቦታዎች ነባር ነዋሪ ከሆኑ ህዝቦች ላይ በተደረገ ጥናት ለብዙ መቶ ሽህ አመታት ዘሮቻቸው በደጋ የኖሩ በመሆኑ ሰውነታቸው በዝግመተ ለውጥ ያዳበረው በደም ዝውውር ውስጥ ከፍተኛ የኦክስጅን ማመቅ አቅም ተስተውሏል። በአማራዎች ላይ ለበርካታ አስርት አመታት የተደረገው ጥናት በሚገርም ሁኔታ ያሳየው ውጤት በዓለም ሁሉ ካሉት የሚልቅና ድንቅ ነው። 

አማራዎች በኢትዮጵያ ከፍተኛ አካባቢዎች ለረጅም ጊዜ በመኖራቸው በዝግመተ ለውጥ ሰውተነታቸው ያዳበረው ለደጋ አየርንብረት ተስማሚ ስርአተ እንሽርሽሪትና ስርአተ ትንፈሳ አላቸው። በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የተስተዋለው የሄሞግሎቢን መጨመርም አልታየባቸውም። ይልቁንም በቲቤትና በአንዲያን የደጋ አካባቢ ነዋሪ ሰዎች ከታየውም የኦክስጅን እመቃ አቅም በበለጠ ውጤት አስመዝግበዋል። ለዚህ ከፍተኛ የአየር ንብረት መላመድ ውጤት አስተዋጾ ያደረገው በዋናነት ዘር እና ዘር አውራሾቻቸው በቦታው በመቶ ሽዎች አመታት በመኖር ያዳበሩት የዝግመተ ለውጥ እድገት እና የጀነቲክስ ለውጥ ሲሆን የጋብቻ ስርአታቸውም ለትውልዶች ጤናማ እድገትና ተስማሚነት አስተዋጽዖ አድርጓል። በተጨማሪም በአመጋገብ ስርአት የሚኖሩበትን የአየር ንብረትና መልክአምድር በማጤን ሰውነታቸው የሚፈልገውን ንጥረምግብ ቀምመው በመጠቀም የላቀ አሰራርና የኑሮ ዘይቤ ፈጥረው ለሌሎች ማህበረሰቦችም አበርክቶ ያደረጉት ቱባ ባህል አለ። በእነዚህ ስልቶችና ጥበቦች አማራው እራሱን ከሚኖርበት ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ከባቢ ጋር አስማምቶ በመኖር የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደቻለ ተረጋግጧል። 

ጋብቻ

አማራ ዘመደ-በድ አይደለም። ይህም ከሐይማኖት በፊት የነበረ ሳይንሳዊ ምክንያትን መሰረት ያደረገ ባህል ነው። አማራ በሚኖርበት ፈታኝ መልክአምድርና አየር ጠባይ ውስጥ የትውልዶች የማሰብ አቅም፥ ጥበብ፥ ፈጠራ እና የአካል ጥንካሬ ካላዳበረ በስተቀር በዝግመተለውጥ ወደ ዘር መጥፋት ሊወስድ የሚችል አደጋ እንደሚኖር ቀድሞ የተረዳ ህዝብ ነው። በዚህም ምክንያት የሚተኩ ትውልዶች በአካልም ሆነ በአእምሮ የተሻሉ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲታሰብ የጋብቻ ስርአትን ወጥ በሆነ ስሪት ውስጥ ማስገባት አንዱ ዘዴ ነበር። የተለያየ የጂን ስሪት ያላቸውን ሰዎች እንዲጋቡ በማድረግ ከሁለቱ ተጋቢዎች የሚወለደው ልጅ ከሁለቱም የተሻለ አእምሮና አካል ያለው እንዲሆን ታቅዶ የተሰራ የጋብቻ ደንብ ነው። ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸውም በሳይንሳዊ ምርምር ያገኙት ውጤት በሚገርም ሁኔታ ስኬታማ ስለነበር ነው። እንደሚታወቀው አማራ በደጋ እንደመኖሩ ለአካባቢው ለማዳ የነበረው እንስሳ እና ከጭነትና መጓጓዣነት አልፎ ለእርሻም ያገለግል የነበረው የቤት እንስሳ ፈረስ ነበር። የፈረስ አቅም በቂ እንዳልሆነ ያስተዋሉት አማሮች ታዲያ ከአህያ ጋር አዳቅለው በቅሎን እንደፈጠሩ ይታወቃል። በቅሎ ከአህያም ከፈረስም የጠነከረ እንስሳ መሆኑን በተግባር ፈትነው ያረጋገጡትና ለዘመናትም እያስቀጠሉትና እየተገለገሉበት ያለ ጥበብ ነው። በመሆኑም ሰውን ከሩቅ ሰው ጋር እንዲጋባ በማድረግ፡ ቢያንስ ደግሞ የቅርብ ዘመዱ ከሆነ ሰው ጋር እንዳይጋባ ለማድረግ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ዝምድና ተቆጥሮ ጋብቻ ይፈጸማል። ይህን ደንብ ጥሶ፥ ዝምድና አፍርሶ የሚጋባም ሰው ይወገዛል። እንብዳዴ እስከመባልም ድረስ ከፍተኛ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል። በዝምድና ጋብቻ የሚወለደው ሰው የሚኖረው የጅን ወይም ዘረመል ባህሪ በሽታ የማይቋቋምና ደካማ እንደሚሆን ስለሚታወቅ ነው ጠንካራ ዘረመል ያለው ህብረተሰብ እንዲፈጠር ታልሞ ጋብቻ ከባዳ ጋር እንዲፈጠር የተደነገገው። 

በአንጻሩ በሌሎች ማህበረሰቦች እስከ አሁንም ድረስ ዘመደበድነትና ጋብቻ እንደቀጠለ ነው። የአክስትና የአጎት ልጆች የሚጋቡበት በርካታ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ። ይህ ጋብቻ የሚፈቀድበት መሰረታዊ ምክንያት የቤተሰቡን ሀብት በጋብቻ ስም ወደ ባዳ እንዳይወሰድ ለመጠበቅ እንደሆነ ይነገራል። ንብረት ለባእድ ውርስ እንዳይደረግ ወንድምና እህቶች ልጆቻቸውን አጋብተው ገንዘባቸውንና ትውልዳቸውን ያስቀጥላሉ። በአማራ ባህል ግን በገንዘብ ስስት ስብእና ላይ ዋጋ የሚያስከፍል ነገር አይደረግም። ይወገዛል እንጅ!

አማራ ትውልድ ቆጥሮ ዝምድናው ከሰባት ትውልዶች ካለፈ በኋላ ጋብቻን ሲፈጽም አንድም ዝምድናውን ያድሳል፤ አንድም ይሰፋበታል። ማለትም ዘመድን ማግባት አዲስ ዘመድ አይፈጥርም፤ ባእድ ጋር መጋባት ግን ወገንን በእጥፍ ያባዛዋል። ማህበራዊ መስተጋብሩ ለሚፈልገው ከፍተኛ የሰው ኃይል ማሟያ ስልትም ይሆናል። ባዳን ዘመድ የሚደረግበት፥ የራቀውን ቅርብ የሚደረግበት መተሳሰሪያ አጋጣሚ ነው ጋብቻ። የጠላትነት ስር መንቀያ፥ ቋሚ ጠብ በቋሚ ወዳጅነት የሚተካበት መንገድ ሁኖም ያገለግላል። የአማራ ጋብቻ ከገንዘብ ያለፉ እና የገዘፉ ማህበራዊ ችግሮችን መፍቻ ተቋም እና መዋቅር ነው። የአማራ ጋብቻ የሰላም ስር የፍቅር አውድ ነው። ደም የተቃባ (የተገዳደለ ሰው) ከመገዳደል አዙሪቱ ወጥቶ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖረው የሚያደርግበት ብቸኛ መንገድ ጋብቻ ነው። የአማራ ጋብቻ እጅግ ብዙ ግለቶችን ያበርዳል፤ ውጥረቶችን ያረግባል። በገንዘብ የማይፈቱ የማህበራዊ ፖለቲካ ጉዳዮችን በጋብቻ ይፈታል። አማራ በዚህ ረገድ የላቀና የዳበረ ልምድና ታሪክ አለው።   

ማጠቃለያ

አማራነት ከተዘረዘሩት ማንነቶቹ ውስጥ የትኛውንም ቢሆን ብቻውን አይደለም። የተዘረዘሩትን ሁሉንም የአማራነት ማንነቶች ያካተተ ነው። አማራነት ደገኛነት ነው፤ ቆለኛነት ነው፤ ክርስቲያንነት ነው፤ እስላምነት ነው፤ ገጠሬነት ነው፤ ከተሜነት ነው፤ ርዕዮተዓለምነት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ነው፤ ቀደምትነት ነው። ከነዚህ ማንነቶች ላይ የትያውም ቢቀነስ አማራነት ምሉእ አይደለም። እነዚህ ማንነቶች ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ባሉ መንደሮች፥ ቀበሌዎች፥ ወረዳዎች፥ ዞኖችና ክልሎች እንዲሁም ከተሞች ሁሉ የነበሩ ያሉና የሚኖሩ ናቸው። 

የአማራ ብሔርተኝነትም  የትኛይቱንም የኢትዮጵያ መንደር ወይንም ግለሰብ የቀነሰ ቢሆን ምሉእ አይሆንም። ኢትዮጵያ የአማራ ነች፤ አማራም ነች። ይህንን እውነት በይሉኝታና ጠላት በሰጠኝ ጥብቆ ልክ እሆናለሁ ብሎ የሚሸማቀቅ የአማራ ፖለቲከኛ ባይጽፍ ባይናገር ይሻለዋል። አማራ አሁን በሚጠራባቸው አራት ክፍላተ ሀገሮች የሚኖረው ህዝብ ብቻ አይደለም። በነዚህ ክፍለሀገሮች ከሚኖረው የበለጠ በሌሎቹ የሀገራችን አካባቢዎች ተሰራጭቶ ይኖራል። በተጨማሪም ሁሉም በሚባል ደረጃ የሀገራችን ማህበረሰቦች አማራነትን መገለጫቸው እንዳደሩና ማንነታቸውም መሆኑን በርካታ ምሁራን ያጠኑትን ተመልክተናል። አማራ እስከ የመንና ኦማን ያስቀጣቸውን አሻራዎች በዚህ የብሔርተኝነት አውድ ውስጥ የማንነት አስረጅ አድርገን ባናነሳቸውም፡ ቢያንስ ግን ቋንቋውን የሚናገሩትን፥ ወደውና ፈቅደው የማህበራዊ ህይወትና አስተዳደር ፍልስፍናውን የሚከተሉትን፥ ምግቡን የሚበሉና ልብሱን የሚለብሱትን፥ በልዩ ፍቅርና አንድነትም የሚደግፉትን ማህበረሰቦች ነጥሎ የተወ መሆን አይችልም። “ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?” ተብለው ሲጠየቁ “አማራ መሆን” የሚሉ ልጆች በየመንደሩ ያሉበት ተፈላጊና አካታች ማንነት ነው። ባእድ ማንነታቸውን በግድ ጭነው የሌሎቹን ማንነት በማጥፋት የእነርሱን ማግነን የሚፈልጉ ባላንጣዎች በነገሱበት ዘመን የማንነት ልክን ከሆነውና ከሚገባው ደረጃ አሳንሶና አኮስምኖ ማቀንቀን ተራማጅነት አይደለም። ከሆነም ወደ ገደል ነው። 

ስለሆነም አማራነት ከኢትዮጵያ አያንስም። ይህም አዲስ የሚፈጠር ማንነት አይደለም። ያለ የነበረና ወደፊትም የሚኖር ነው። የአማራ ብሔርተኝነት ይህንን መጠበቅ እንጅ አዲስ ነገር መፍጠር አይጠበቅበትም። የአማራ ብሔርተኛ የኢትዮጵያን ምልክቶች ያስከብር፥ ተቋማቱን ያጠናክር፥ ለሁሉም ዜጋ እኩልነትና ፍትህ ይታገል። ሁሉም  ኢትዮጵያዊ አማራ ነው። ይሆናልም።

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here