spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትትዝታ ወ-ጳውሎስ (Tizita we Paulos)

ትዝታ ወ-ጳውሎስ (Tizita we Paulos)

ጳውሎስ ሚልክያስ (ፒ ኤች ዲ)

ዐባይ ቡሬ ዳሞት፡ ቢሾፍቱ ሆሎታ፣
ሚዛን አማን ገነት: አንኮበር ኤፍራታ
ትግራይ አክሱም አድዋ ተምቤንና አንደርታ
ጂማ ኢሉባቦር ሊሙ ወላይታ
ቄለም የጆቴ ወርቅ: በኒሻንጉል በርታ
ሐረር ድሬ ደዋ ከረመራ ኤርታ
ወለል ብሎ ታየኝ ከፋ ዬም ሱሉልታ
መረብ ተሻግሬም በሕልም ዓይን ስቃኝ
ሰራዬ አኩለጉዛይ ሐማሴን ናፈቁኝ
አረ ወገን ያለህ እንዳልንገላታ
ወሮኛል ሰመመን: ቀስቅሱኝ በሆታ
በቄሶቹ ወረብ በሴቶች እልልታ
በሶዶ አቦላላ በጎንደሬ እስክስታ
በቄልም ኩምኩሜ ባክሱም ሽሉክሉክታ
እንጀራን ዱለቱን ክትፎም በገበታ
አምጡልኝ ልከስክስ በልደታ በዓታ
ልቋደስ ወጣሁኝ ከጾመ ፍልሰታ
በረዶው በቅቶኛል ከቆፈን ልገታ
አላስችል ብሎኛል ያበሻ ትዝታ
ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሞንትርያል፣ ካናዳ
ኮብልዬ ልሔድ ነው ከያንኪ አገር ጓዳ

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News – English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

3 COMMENTS

 1. የአገራችን ሰላም ማጣት፣ የመሪዎች ግራ ማጋባት ብዙዎች ወደ አገራቸው እንዳይመለሱ ዋነኛው ምክንያት ነው። ጥቂቶች ጨክነው የተመለሱ አሉ። ደርሰው ሞክረው የተመለሱ አሉ። እየተመላለሱ ኢንቬስት ማድረግ የፈለጉ የመንግሥት ሹማምንት ቢሮክራሲ እና ዘረፋ አላሠራ ብሎ እርግፍ አድርገው ትተውታል። ጠ/ሚ ዐቢይ የሚናገሩት ቅዠት የመሰለ ቃል እና ምግባራቸው እየተጋጨ ነገሮችን አባብሰዋል። ፕሮፌሰር ጳውሎስ፣ ቅኔዎ የብዙዎችን ስሜት ይገልፃል እላለሁ። አመሰግናለሁ።

 2. “Time is the great author. Always writes the perfect ending.” Charlie Chaplin. ግጥሙ ከልብ ነው። ያንባቢንም ልብ ይነካል። ግን እንዲህ በርቀትም ሆነው ወይም በሃገር ውስጥ የቀን ተቀን ሃበሳ እየቆጠሩ የሃገርና የወገን ናፍቆት እየገረፋቸው ሰላምንና ደስታን ሽተው በግፈኞች እጅ ሃበሳን ተቀብለው አፈር የተመለሰባቸው እልፍ ናቸው። ከዚያም የተረፉት የሥጋና የጭንቅላት ጠባሳን እያስታመሙ በየስርቻው ይገኛሉ። እውነት በሃበሻ ምድር ኑሯ አታውቅም። ከዘመን ዘመን ግፈኞች የሚናጠቋት፤ ካለፈው የመጣው ወይም ሊመጣ ያለው ይሻላል ስንል የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት እየሆነ ይኸው ያለነው ዛሬም እናላዝናለን። መልስ ግን ከሰማይም ይሁን ከምድር የለም። ያኔ ያለቀሱ አይኖች ጠፍተዋል ከመከራ ብዛት። አሁን የሚያለቅሱት ቀልተዋል። ሰው በሰላም ውሎ መግባቱ ቀርቷል። የቋንቋና የክልል ፓለቲካ ጢቢራው ላይ ከወጣ የዘር አምላኪ መንጋ ምንም አይነት ስብዕና አይጠበቅም። የተለከፈበት ያዙሪት ፓለቲካ ለጥቁር ህዝቦች የሚያስብ ሳይሆን ለጎሳና ለነገድ ብቻ ነው።
  ጊዜ ግን ሁሉን በሰአቱ ግልጽ ያረጋል። ያኔ አሁን እንዘጥ እንዘጥ የሚባልለት የፓለቲካ ሽኩቻና አዙሪት ሁሉ መና ይቀራል። ያለፈው ታሪክም ያሳዬን ይህን ነው። ለ 70 ዓመታት ሙሉ የተለፋበት የሶቪየት ህብረት ቁስ አካላዊ ርዪተ ዓለም ፍልስፍና ንፋስ እንደ መታው ደመና ላይመልስ ተበትኗል። Secondhand Time: The Last of the Soviets – Svetlana Alexievich ላነበበ ምን ያህል ፍራሹ ዓለም በፊት ጀግና እያለ ያቆለጳጰሰውን እንደ አሮጌ ቁና ሜዳ ላይ አውጥቶ እንደሚጥል ያሳያል። በእኛም ሃገር በወያኔ የተበተኑት የሃገሪቱ የሰራዊት አባላትና ሌሎችም የሚያስብ ጭንቅላት ያላቸው ሁሉ የደረሰባቸው ገመና ሰማይ ጠቀስ ነው። አሁን እንሆ ነገር ሊሻል ነው ሲባል ዶ/ር አብይና የኦሮሞ ብሄርተኞች ሌላ ገመናና መከራ በህዝባችን በማዝነብ ላይ ይገኛሉ። ግን ለዚህ ተጠያቂው መንግስት ብቻ አይደለም። በብሄር ስም ያኔም አሁንም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችና በጥቅሉ የደነዘዘው ህዝቡ ነው። ግን በውጭ ሃይሎች የሚሾፈር ታጣቂ ሃይልም ሆነ መንግስት በራሱ አስቦ ለራሱ መኖር አይችልም። አሁን እንሆ ሰላሳ ጊዜ ወደ ግብጽ የሚመላለሰው የሻቢያ መሪ ለኤርትራ ህዝብ አስቦ ሳይሆን እንዴት ባለ ሁኔታ ራሱን ለሌላ ፍትጊያና ውጊያ ለማዘጋጀት እንዲችል ለመምከር ነው። ይመቸው። ሞት የሰለቸው ህዝብ ይዞ ጦርነት!
  በሌላ መልኩ የቱርክና የሱማሊያ ወታደራዊ ስምምነት፤ የግብጽ ከሱማሊያ ጎን ቆመናል የአረብ ሊግ ዝንተ ዓለም ኢትዮጵያ ጠል የሆነ አቋም ሁሉ የሃበሻዋ ምድር ቆርቁዟ እንድትኖር ሆን ተብሎ የተተለመ የፓለቲካ ስሌት ነው። የእድሜ ልኩን የኤርትራ መሪም አጋፋሪ ያደረጉት ለዚህ ጉዳይ ነው። በጥባጭ እያለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንዲሉ ነውና። ያኔ በጠ/ሚ አብይና በሻቢያው መሪ የነበረው አፍላ መውረግረግ ዛሬ የለም። ያኔም በተለያዪ ድህረ ገጾች እንደጻፍኩት ሁሉ ሻቢያ ፍቅሩ የመነጨው የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ከሚል ወያኔን ከልብ ከመጥላት የመነጨ እንጂ የ 100 ዓመት ሥራ የሰጣት ኢትዮጵያን ከማመስ ወደኋላ አላለም። ወደፊትም አያቆምም። ኤርትራ ዛሬ የትግራይ ልጆች ከጎን ሆነው ባይዋጉ ኖሮ ሃገር አትሆንም ነበር። በየዓመቱ ክራርና ከበሮ የሚደለቅለት የፈንቅል ውጊያም በሊቢያ አጥቂ ትናንሽ መርከቦች፤ በግብጽ፤ በሱዳን፤ በኢራን በቅንጅት የተፈጸመ ጥቃት ነው። ያን ግን ይፋ ማድረግ ለሻቢያ ውርደት ነው። እውነቱ ግን እሱ ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ ሁሉም በጊዜው የሮም አወዳደቅን እየወደቀ እያየን ነው። ሊቢያ የለችም፤ ኢራቅ የለችም፤ ሶሪያ የለችም፤ ሱዳን እሳት ላይ ተጥዳለች እነዚህ ሃገሮች ሁሉ በቀጥታና በሰውር ለወያኔና ለሻቢያ ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያ እንድትዳከም ያደረጉ ሃይሎች ናቸው። ግን አፍራሽ ራሱ ሲናድ ከማየት የበለጠ ደስታ የለምና ገና ይቀጥላል።
  በመዝጊያው ከላይ ፕ/ሩ የቀመሩት ግጥም እነ ዳኛቸው ወርቁን፤ ደበበ ሰይፉን፤ ብርሃኑ ዘሪሁንን፤ በዓሉ ግርማን፤ ሰዓሊና ገጣሚውን ገብረ ክርስቶስ ደስታን፤ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን፤ ከቅርቦቹ ሙሉጌታ ተስፍዬ (አያ ሙሌ) እና ሥፍራ የማይበቃኝ ገጣሚዎችና ሃያሲያን ግፍና መከራን፤ የሃገር ናፍቆትና የሰላም እጦትን ረሃብና ጠኔን ጦርነትና የፍትህ መጥፋትን ተመልከተው አንብተው አልፈዋል። ግን መቼ ነው የሃበሻ ምድር የሰላም አየር የምተነፍሰው? መቼ ነው ወንድምና እህቶቻችን ገድለን ከበሮ ይዘን መዝለል የምናቆመው? ግን ይህን ሁሉ የሚያይ የሰማይ አምላክ አለ? አይመስለኝም። ቢኖር ለ 3ሺ ዘመን ዝም አይልም። የአያ ሙሌን ግጥም ” እውነት ከመንበርህ የለህማ” የሚለው የበለጠ ከእውነት ጋር ይቃረባል። በቃኝ!

 3. ዶ/ር ጳውሎስ ግጥም መሆኑ ይሆን?

  ጥረትዎን አደንቃለሁ በእንግሊዘኛ መጣፍ እንጅ በአማርኛ የፍቅር ደብዳቤ እንኳ ፍጡም መጣፍ የማይችሉ ብዙ ፒ ኤች ዲዎች ስላሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here