spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትየክርስቲያኖችን መታረድ እንዴት እናስቁም? (ክፍል ሁለት )

የክርስቲያኖችን መታረድ እንዴት እናስቁም? (ክፍል ሁለት )

የክርስቲያኖችን መታረድ እንዴት እናስቁም

ከሰይፈስላሴ

ፈተናው አዲስ አይደለም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ብዘ ግዜ ተፈትና ጠፋች እስከሚባልበት የደረሰችበት ጊዜ ነበር።  ይሁንና በፈጣሪ ድጋፍ የጠነከሩና መከራውን ለመቀበል የተዘጋጁት አንገታቸውን ለሰይፍ እየሰጡ ክርስትናን በዚህ ሀገር አስቀጥለዋል።  ይህንን ባማድረጋቸው ደግሞ እንደነ  ሊቢያ፤ ግብጽ፤ ሱዳን፤ የመን፤ ኢራን ያሉ ክርስትያኖች አልጠፈም።  የዮዲት ክርስትናን አጥፍታ ይሁዳዊ ለማድረግ፤ የግራን መሀመድ ክርስትናን አጥፍቶ እስላም ለማድረግ፤ የካቶሊክ ጀስዊቶችና ግራዚያኒም ኦርቶዶክስን አጥፍቶ ካቶሊክ ለማድረግ፤ ደርግና ሀወሓትም ክርስትናን አጥፍተው ኢአማኒ ለማድረግ፤ አሁን ደግሞ አብይ አህመድ ክርስትናን አጥፍቶ የቁስ አምላኪ (የብልጽና መጽሐፍ ቅዱስ)  አምላኪ ለማድረግ ጦር አውጆ ሰይፉን ስሎ ዘምቶ እያረደ ነው።  

ዮዲት ይሁዳዊ ማድረግ ዘመቻ

ዮዲት ጉዲት ለ40 አመትታት ክርስትናን ከዚህ ሀገር ለማጥፋት አሳዳ አቃጥላ ጨፍጭፋ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ሞክራለች። በዛን ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር  በመቶ ሺዎች የሚቆጠር እንጂ ሚሊዮንም አይደርስም። (ወደ ሃላ ሄደን የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በ2% ያድጋል ብለን ብናስብ የኢትዮጵያ ህዝብ በመቶ ሺዎች እንጂ በሚሊዮን የሚቆጠርም ነበር)።   ከዚህም መሀከል አሳዳጅ የይሁዳ እምነት ተከታዮችና ተሳዳጆች ደግሞ ክርስቶስኖች ነበሩ።

ክርስትና ገና ጀማሪ ሲሆን የይሁዳ እምነት ደግሞ ስር የሰደደና ጠንካራ ነበር።  ይሁንና ክርስቲያኖች በየ ጋራውና ዋሻው እየተደበቁ ክፉውን ግዜ በማሳለፍ የክርስትናን እምነት ለልጆቻቸው አውርሰው አልፈዋል። 

ግራኝና ኦቶማን

ግራኝ መሀመድም ለ17 አመት ካገር አገር እየዞረ ቤተ ክርሲያኑን አቃጥላል፤ አስገድዶ እያሰለመ፤ እንቢ ያለውን ደግሞ አንገቱን በሰይፍ እየቀጠፈ ሌላውን ደግሞ በሰሰለት እያሰረ ወደ የባርያ ገበያ እያቀረበ (export) አደርጎታል። ዛሬ አንዳንድ የጃማይካ ታሪክ ጸሀፊዎች እኛ በግራኝ መሀመድ ግዜ ከሸዋ ከጀማ ወንዝ አካባቢ ተይዘን የተሸጥን ነን ይላሉ። መልካቸውም ከምስራቅ አፍሪካ መሆኑን ይጠቁማል።

ይሁንና ግራኝ አህመድ ለ17 ዓመት (በደረንጆቹ 1527 እስከ 1543) ቀጥቅጧል ይሁንና ክርስትን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት አልቻለም።  ከዚህ ቅጥቀጣ ክርስቲያኑ ሳያገግም ካቶሊኮቹ ደግሞ በግድ ካቶሊክ ካልሆናችሁ ብለው ብዙ ክርስቲያኖች እንዲያልቁ ምክንያት ሆኑ። 

ከዛ የተረፈው ደግሞ ከደቡብ ወደ ሰሜን የፈለሰው በርካታ የደቡብ ክርስቲያኖችን አጥፍቶ ወይም በሞጋሳ ባርያ አድርጎ ለሶስት መቶ አመታት በላይ ያለ ክርስትና እንዲኖሩ አድርጓል። የወላይታ ህዝብ ታሪክ ማንበብ ይበቃል። ከዛ በድጋሜ ክርስቶስ የተሰበከለት ከሚኒሊክ ግዜ ቦሀላ ነው። 

ጣልያንና ግራዚያኒ

ጣልያን ሲመጣምም እንዲሁ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ከካቶሊኩ ጳጳስ (ፓፕ) ጋር አብረው በርካታ ቤተ ክርስቲያንን አቃጥለዋል። የ Ian Campbell, The Holy War የሚለውን ላነበበ 750 ሺ ሰው ተጨፍጭፋል። መናንያንንና ገዳማትን አቃጥሏል፤ ከየገዳሙ ቄስና ዲያቆንን እያፈስ ከመቋድሾ ወጣ ብሎ ባቋቋሙት ዲናኔ በምትባል ኮንሰትንትሬሽን ካንፕ ውስጥ በማጎር ብዙዎችን በሙቀት፡ በረሀብ፤ በጥማትና በኮሌራ ጨርሰዋል።  በዚን መሀከል እንደነ አቡነ ጴጥሮስ በፒያሳ አቡነ ሚካኤል ደግሞ በጎሬ አደባባይ ተረሽነው ነው ሀይማኖታችንን ያቆዮልን። 

ደርግና ኮሚኒስቶች

ባለፉት 50 አመታት ውስጥ ደግሞ ማርክስ ሀይማኖት “የጭቁን ህዝብ ማደንዘዣ ሀሺሽ ነው” ብለው ፈረንጆቹ ለተማሪዎቹ አስጠንተው ላኩዋቸው። ተማሪዎቹ ደግሞ ያጠኑትን ይዘም መጥተው ክርስትናን ከዚህ ምድር ለማጥፋት በጣም ደከሙ።  ካሪኩለም ተዘጋጅቶ፤ መጽሐፉ ከሩሲያ ተተርጉሞ፤ የዮኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች ተመርጠው ተማሪው በፊሎዞፊ 101 እና 102 እግዚአብሄር የለም የሚለውም የአይምሮ አጠባ ተሰጥቶት ብዙ ሰው አምኖ ተቀብሎ እግዚአብሄር የለም ብሎእ እርስ በእርሱ ተጨራርሶ አለቀ።

በየ ቀበሌ ማህበሩ (ከነማ)፤ ወጣቶች ማህበር (መኢወማ)፤ በሴቶች (መኢሴማ)፤ ታዳጊዎች ማህበር፤ የገበሬ ማህበር (መኢገማ)፤ የሰራተኛ ማህበር (መኢሰማ)፤ የመምህራን ማህበር እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የማርክሲዝምና የሌኒንዝም ትምህርትና ንቃት ተብሎ ሁሉም አርብ ከሰአት ቦሀላ ስራ እያቆመ “ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው፤ ሀይማኖት የጭቁኑ ህዝብ ማደንዘዣ ሀሺሽ ነው ተብሎ ንቃት እየተሰጠ ሀይማኖትን ለመጨረሻ ግዜ ለማጥፋት ሰርተዋል።  ህወሓትም ኮሚኒስት ስለነበረ በትግራይ ህዝብን አሳምኖ ከፈጣሪው ለይቶ እያዋጋ አዲስ አበባ ገባ። ይሄንንም የኮሚኒስት አስተምሮ በመላው ኢትዮጵያ ያስቀጠለው። አሁንም በትግራይ የሚደመጠውና የሚከበረው ህወሓት እንጂ ክርስቶስ አይደለም። ክርስቶስ አስተምህሮ ለህወሓት አምልኮ አጋር ድርጅት ሆንዋል። አቦይ ጸሀይ የሚመራው ቡድን መናንያንን ከገዳም እያወጣ፤ በሰንሰለት እያሰረ፤ እየገረፈ ከገዳም በማስወጣት ያንኑን የኮሚኒስቶች ፈጣሪንና ሀይማኖትን በተግባር አሳየ። ይሁንና እደሁሉም ኮሚኒስቶች ተቀጠፈ። እንደውም አቶ ስብሀት ነጋ አማራውንና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብሎ በድፍረት አውጀው ነበር።  

አብይ ከላይ ያለው ሁሉ

አብይ የህወሓት ልጅ ነው። ይሁንና የሱ ደግሞ ከግራኝ መሀመድንም፤ የግራዚያኒም፤ የኮሚኒስቱን ዘመቻ አቀላቅሎ ነው የመጣው። በአንድ እጁ በደቡብ አሜሪካ የተጻፈውን የብልጽግና መጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ይዞ ሀይማኖት ቀይሩ፤ ደሀ የሆናችቡት ከርስቶስ ለደቀመዝሙሮቹ ያስተማራቸውን ስላከበራችሁ ነው።  በሉቃስ ወንጌል ም 8 ቁ3 ላይ “3 እንዲህም አላቸው። በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ፥ ሁለት እጀ ጠባብም አይሁንላችሁ።”  አብይ ይሄንን የክርስቶስ ቃል አይቀበልም። እንደውም ስህተር ነው ብሎ ያምናል። ብር ከተመኘህ ብር በሞባይል ገንዘብ ይገባሀል ብሎ የሚያምን ነው። ይህ እንግዲስ ክርስትና ሳይሆን መሰረቱ የሜሪካኖቹ ታዋዊ አነቃቂዎች አስተምህሮ ነው። 

ከዛ ደግሞ እንደ ግራኝ መሀመድ ሰይፍ  የታጠቀ ሰው በየገዳሙና ቤተ ክርስቲያኑ እየላከ የሚያርድ ነው። እንደ ግራዚያኒ ደግሞ በድሮንስ ከሰማይ ልኮ ገዳምንና ቤተ ክርስቲያንን ይደበድባል፤ እንደ ኮሚኒስቶቹ ደግሞ ገነት ማለት አበባ ያለባት ቦታ ማለት ናት፤ እዚህ ፈጥሬያለሁና እዙሁ ገነት ግቡ የሰማይ አባታችሁን አትጠብቁ ይላል። አሁን አብይ ላይ የደፈረው የክፋት መንፈስ ካለፉት ሁሉ ስህተቶቹ ተምሮና ተደረጅቶ የመጣ ይመስላል።  ዮዲት፤ ካቶሊክና ግራኝ መሀመድ ሀይማኖቴን ቀይሪያለሁ የናንተን ተቀብያለሁ ካለ አይገሉም ነበር። ግራዚያኒ የሞሶሎኒን ንጉስነት ተቀብያለሁ ካለ እንደውም ባንዳ አድርጎ ሾሞ ፓስታና ቪኖ ጠጣ ይል ነበር።  ኮሚኒስቶችም በሰይ ላይ ገነት የለም እዚሁ ነው ያለውን አላጠፋም። አብይ ግን የሱን የሳይኮሎእጂ መጽሐፍም ተቀብለናል ብንል አይምረንም። 

በዝቋላ የታረዱት መነኩሴዎች አልደረሱበት፤ አልመጡበት፤ ለስልጣንና ለጥቅም ተፎካካሪ አይደሉም። ቆሎ ቆርጥመው ጫካ ውስጥ ተኝተው አምላካቸውን ቀንም ሌሊትም ሲያወድሱ በመኖራቸው ምን አደረጉት። እነዚህን ምንም ያላደረጉ መናንያንን ያረደ እ አቡነ ማትያስን፤ እነ አቡነ ኤርሚያስን እነ ዳናኤል ክብረትን አያርድም ብለን ማሰብ የዋህነት ነው። እንደ ዳናኤል ክብረት ያለው ሌላው ሲታረድ እኔ ጋ አይደስም ብሎ ሲቀመጥ ገበሬው በጉን ጨው ሲያልሰው እንዲሰባለትና ሊያርደው መሆኑን አይገባውም። የወደደው መስሎት ይተሻሸዋል። በየ ስጋ ቤቱ ቁርጥ እየበላ ክሽን የሚጠጣው እንደ ኖህ ዘመን አሸሸ ገዳሜ መቼነሽ ቅዳሜ የሚለው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መታረዱ አይቀርም። የመናያኑ ወንጀል ከድራፍት ቤቶቹ ሰዎች አይበረታም።

ለምን ይህ ሁሉ ክርስቲያንን ላማጥፋት ተጋ?

ሀይማኖት የስጋዊ ብቻ ሳይሆን የሀይማኖታዊ ጦርነትም ነው። ይንን ለመን በኛ ላይ መጣ ካልን ሁሌም ሀይማኖቱን ለማጥፋት የሚሰራ ሰይጣን አለ። ሰይጣን ደግሞ ከሩቅም ከቅርብም የክርስቶስን ተከታዮች የሚያሳድድ ሀይል ያስነሳል።   ለምሳሌ ጣልያን ሲወር እነ አቡነ ጴጥሮስ በፒያሳ፤ እነ አቡነ ሚካኤል በጎሬ ወስዶ ረሽኖ ነበር።  በሌላ በኩል “ስጋን የሚገለውን የፈሩ” እንደ አቡነ አብረሐም ከግራዚያኒ ጳጳስና ተቀብለው ጣልያንን ለማገልገል የፋሺስት ሲኖድ ሾመው ነበር። 

“On 27 November 1937, Marshal Rodolfo Graziani convened an assembly of Ethiopian clergymen to elect a new archbishop. Abune Abraham, bishop of Gojjam, was elected. However, the Holy Synod of the Coptic Orthodox Church of Alexandria under Pope John XIX declared the election illegitimate and excommunicated the new archbishop. Ignoring the interdiction of the Holy Synod and the Pope, Abune Abraham and his successor Abuna Yohannes XV (r. 1939–1945) designated eleven bishops in order to constitute a full ecclesiastical hierarchy before the Italian occupation ended in 1941”

ስለዚህ እነ አቡነ አብረሀምና እነ አቡነ ዮሀንስ የተነሳሳውን የክርስቲያን አመጽ ለማብረድ ሊያነዱት ሞክረው ያቃታቸውን የአራዳውን ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያ  እዮ ጣልያን እያደሰው ነው። ያወደመውም የደብረ ሊባኖስን ገዳም እገነባለሁ ብሏል እያሉ ለግራዚያኒ አማላጅ ሆነው ነበር። ዛሬም እንዲሁ አይነት ለሰይጣን ቅኔ የሚቀኙ ዝማሬ የሚያወጡ ቄሶችም አሉ። እነ አቡነ አብረሐም መእመኑ በባርነቱን ተቀብሎእ በሰላም እንዲኖር እንዲያስተምሩ ተደርገው ነበር። አቡነ ዮሀንስ ተተኩክተው ግራዚያንን አገልግለዋል።  

የግራዚያኒ ከልክ ያለፈ ጭካኔ የኦርቶዶክ ክርስቲያኑን አነሳሳብው። አለቀ የተባለው ጦርነት ተፋፋመ። ይህ በመሆኑ ሞሶሎኒ እራሱ ግራዚያኒን ክአዲስ አበባ አንስቶ ወደታች ወደ አስመራ አሽቀነጠረው። አብረው የመጡትንም የካቶሊክ ቄሶች አባሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መቃጠል እንዲቆም የተቃጠሉትም ትላልቆቹ እንዲገነቡ አዞ ነበር። ይሁንና አርበኛው ጊዜ ሳይሰጠው ከመሰረቱም እዛው ሮም ላይ መሸነፍ መጀመሩ ኮተቱን ትሎ ወጣ። 

 ክፋትን ያወገዙት እነ አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ሀውልት ቆሞላቸው ታሪካቸው ለሺ ዘመናት ሲተረክ  የሚኖረው “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።”ማቲዎስ ወንጌል 16_25

ፈርተው ስጋቸውን ለማዳን የሞከሩት ስጋቸው እንደማንኛውም ሰው ተቀበረ። ሰለነሳቸውን ግን ማንም አያስውቅም።  750ሺ ኢትዮጵያውያንን ጨርሶ፤ መናንያን፤ ቄሶች፤ ዲያቆኖችና መዕመናኖች ፈጅቶ ሞሶሎኒ እስከነ ውሽማው በሚላን አደባባይ እግሩ ወደላይ ተደርጎ ተሰቀለ።  የኛም በግራዚያኒ 9 ጳጳሳትም ስማቸውም ታሪካቸውም ከነሱ ጋር ተቀበረ።  

የዚህ ጽሁፍ አላማ

የዚህ ትምህርት ዋነኛ አላልማ አንድ መምዕን ሀይማኖቱን ለማስጠበቅ የጳጳስ ትዕዛዝ አይፈልግም።  ጳጳስ ኖረም አልኖረም  ሀይማታችንን መጠበቅ የእያንዳንዱ ግዴታ ነው። በሌላ ማመካኘት ከፍርድ አይድንም። አዳም ፍሬውን በልቶ ለምን በላህ ሲባል ይቅርታን አልጠየቀም። ይልቁንም ማመካኘት ነው የመረጠው። ሶሪት ዘፍጥረት 3፡ 12_13 “ አዳምም አለ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።1እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን። ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች። እባብ አሳተኝና በላሁ።” ማመካኘታቸው ግን በገነት አላቆያቸውም። እኛም ክርስቲያኖች ሲታረዱ ዝም ካልን እንደ ቃዬል “ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን” እንደማለት ነው። ወንድማችንን መጠበቅ ግዴታችን ነው። 

ስለዚህ የወንድማችን እረኞች እኛ እንጂ ጥቁር የለበሰ ቆብ የደፋ የጳጳስና የመኖክሴ ሀላፊነት ብቻ አይደለም።  ለዚህ ሀጥያትን ማውገዝ ከሀጥያት ጋር አለመተባበር የእያንዳንዱ ክርስቲያን ሸክም እንጂ የሲኖዶስ አይደለም።

ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ 6: 4_5 ላይ “ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና።”

የወንድማችን ጠባቂነት ለጳጳስና ለመነኩሴ ብቻ የተባለ አይደለምና። የሁላችንም ሀላፊነት ነው። በእርግጥ ሁላችንም እንፈራለን። ስለዚህ እነሱ ቢያደርጉልን ደስ ይለናል ነበር። ግን ክርስቲያን ያለ ፈተናና ችግር አልፎ መንግስተ ሰማያትን አይወርስም።  

እንደኛውን እንደ አንዳንዶቹ እኔ አልጾምም እኔ ክርስቶስ ጾሞልኛል፤ ዋጋ ከፍሎልኛል እንደሚሉት እንዳንሆን።  አንድ አባት ሲያስተምሩ ክርስቶስ ጦሞልኛል ካልን ለምን ክርስቶስም በልቶልኛል ብለን ምግቡን አልተውነውም ብለው ይጠይቃሉ። 

ፍርሀታችንን ማሸነፍ ግድ ይላል።

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡7_8 “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።  እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል”

ሌላው ነገር ፈርተን ከሀጥያት ጋር አለመተባበር ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡14_17 “በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ። ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም፤ ፈቀቅ በል ተዋትም።  ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና።  የኃጢአትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና”

የሄንን ሳንዳደርግ በመጨረው ፍርድ ጳጳስ ሆንን መዕመን ብንሆን መጠየቃችን አይቀርም።  አዳም በሄዋን፤ ሄዋን ደግሞ በእባብ አመካኝታቸው ከፍርድ ማምለጥ አልቻሉምና ዛሬ በልባችን የያዝነውን ፈጣሪ ያውቃል። ሰውን ማታለል ይቻላል ፈጣሪን ግን አይቻልም። 

ከግል ሀላፊነት ለማምለጥ “እነሱ እንዲህ ቢያደርጉ እነሱ በጠሩ፤ እነሱ ቢያውግዙ፤ እነሱ ቢጾሙ፤ ቢጸልዩ ምህላ ቢገቡ’ የሚለው ከተጠያቂነት አያድነንም። 

ምንም ያልሰሩ ገዳማውያንን የሚያርዱ የኛል ልጆች ይምራሉ ብሎ ማሰብ እራስን ማታለልና በፍርድ ደግሞ ማቲዎስ ወንጌል 25፡ 41_43 ላይ እንደተጻፈ “በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና”

አሁን የሚጠየቀው በልባችንን ያለውን ፈጣሪ ያያል። ሀጥያት ስሩ ግደሉ፤ ስደቡ አልተባለም። ለሚሞቱት ጸልዩ፤ ሀጥያትን አውግዙ፤ ከሀጥያት ጋር አትተባበሩ፤ ክፋውን ክፋ በሉ፤ የተራቡትን አብሉ፤ የተጠሙትን አጠጡ፤ የታረዙትን አልብሱ ነው።  ይሄንን ብናደርግ   ግድያንና ስደትን ለማስቆም ከሚያስችል አቅምና ቁጥር አለን ለማለት ነው  

ኦርቶዶክሱን ምን ሰለበው?

ታድያ ለምን ይሄንን ያህል ቁጥር ያለው ህዝብ ለዘርና ለሀይማኖት ጥፋት ተጋለጠ ብለን ስንጠይቅ ለሀምሳ አመት የተሰበከው ርዕዮት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነፍስን የሚገልውን ሳይሆን ስጋን የሚገለውን እንዲፈሩ የስነ ልቦና እጥበት ስለተደረገባቸውና እነሱም አምነው ስለተቀበሉት ነው።  ከአንገቱ ላይ ማተቡን ከልብሱ ላይ ሰንደቅ አላማውን ልቅደድ ሲባል ተሰልፎ የሚያስቀድድ የፍርሀት ክፋ መንፈስ የያዘው ይመስላል።

“ሞትኩ” ብሎ የቆም ተስካሩን ያወጣው መነኩሴ ሳይቀር ሞትን ይፈራል። ይህ ደግሞ በፈጣሪው ላይ እምነት  ማጣት ይመስላል። 

መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነነዌ ም1፡9 “በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”  አሁን አትፍራ ቢባል ሞኝህን ፈልግ የሚል ክርስቲያን በዝቷል።

ዛሬ በብሄር በተሳከረበት አገር ውስጥ አንድ የትንሹን ብሄር ለምሳሌ የአደሬን ወይንም የወራቤን መሀበረሰብ አባል አንድ ሰው በጥፊ መታ ቢባል ሀገር ይታመሳል።  በገዳም ያሉና ማንንም ያልነኩ፤ በማንም የማይደርሱ ንጹሀን ሲታረዱ ግን 60 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኦርቶዶክስ አማኝ አንድ ነገር አያደርግም።  አትግደሉኝ ብሎ ለመጸለይና ለመጠየቅ እንኳን ይፈራል። አሁን 60 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ ሌላው ይቅር ከሀጥያት ጋር አልተባበርም ቢል መፍትሄ ማምጣት ያቅተዋል?

የህሊናና የተግባር ጥሪ

ስለዚህ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን ካላለ በምድርም በየተራችን እንታረዳል በሰማይም ደግሞ እንጠየቃለን። አንዳንዱ ከሀጥያት ጋር አትተባበር ሲባል  አቡነ ጴጥሮስን ሁን የተባለ ያህል ይሸበራል። መትረየስ ፊት ቁም የተባለ የለም፤ ከሀጥያተኞች ጋር እያበርክ ሀጥያትን አትስራ ነው።  አንተ በሰው ፊት ብልጥ የሆንክ ቢመስልህም  ፈጣሪ ግን የልብን እያየ ነው።  

ጥሪው ከነፍሰገዳዮች ጋር አትተባበር፤ አትግደል፤ ንጹሀን ሲገደሉ በተግባር አውግዝ ፤ ለተራበው አብላ፤ የተደሰደውን አጽናና፤ ለታረዙት አልብስ። ነፍስን ለሚያጠፉ አትታዘዝ። ደሙ ባንተም እጅ ላይ ይሆናልና። ይህ ደግሞ በሲኖዶስ የሚታወጅ ሳይሆን አንተ ከፈጣሪህ የተጣለብክ ግዴታ ነው። 

ስለዚህ ከዛሬቷ ቀን ጀመሮ ከሀጥያት ጋር አልተባበርም፤ እጄን በንጹሀን ደም ከሚታጠበው ጋር አላነካካም፤ የስራውም ተባባሪ አልሆንም። እኔም የወንድሜ ጠባቂ ነኝ እንጂ አሳራጅ አይደለሁም ይበል።

የመጨረሻው መልዕክት ብትወድስ ተከተለኝ ነው

እኛ ፈተናውን አለፍንም ወድቀንም፤ ገሀነም ገባን ገነትም ለራሳችን ነው። ለሌላው ብለን የምናደርገው አንድም ነገር የለም። ብትወድ ተከተለኝ ነው።  

አንድ የሕግ አዋቂ ክርስቶስን ሊፈትነው ፈልጎ  ባልምጀራዮ ማን ነው ብሎ ጠየቀው። ክርስቶስም በሉቃስ ወንጌል ም10፡29_37 ይህን ምሳሌ ሰጠው”  “እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን። ባልንጀራዬስ ማን ነው? አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ። አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ። እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም። በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና። ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው። እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?  እርሱም። ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም። ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው።

ክርስቶስ ምን አለ? ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው። እኛም እንደ ካህኑና፡ እንደ ሌዋዊ መንገድ እየቀየርን እየሄስን ፈጣሪን የምናታልል ይመስልለናል። ለኛ የተሰጠን ምክር እንደ ሳምራዊው ማድረግ ነበር ግን እያደረግን አይደለም። ፈተናውንም እየወደቅን ነው።

አንድ የምንዘንጋው ነገር ለጻድቃንም ለሀጥያተኞችም ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል። ሰው ፊት እንደ አብይ ቅዱስ፤ አዋቂ፤ ገነትን በምድር ላይ ከሸራተን ሆቴል አጠገብ እየገነባሁ ነው የሚል የክፉ መንፈስ ያለበት መሆን ያለበለዚያም ልብን የሚያየውን ፈርቶ እንደ ሳምራዊው በጎ መስራት ነው። 

እነ አብይ አህመድ፤ ሽመስ አብዲሳ፤ እነ አዳነች አቤቤ፤ እነ ዳናኤል ክብረት፤ እነ አበባው በአደባባይ ክርስቲያን መስለው ለመታየት ይጣጣራሉ።  እንደ ሌዋዊው ዞር ብለው ያልፋሉ። እኛን ያታልላሉ ይሁንና ፈጣሪያቸውንም ማታለል አይችሉም። እንደነ አባይ ጸሀዬ ፍርድ ይሰጣቸው ይሆናል። እነሱ በሚታረዱት ደም በልባቸው ደስ ይፈነድቃሉ። እኛ የልባቸውን አናየውም።  ፈጣሪ ግን የልብን ያያል።

በርካታውም ኦርቶዶክስ ነጠላ ለብሶ እንደ ካህኑና ሌዋዊው መንገድ ቀይሮ የሚሄደው ብዙ ነው። ጥሪው እንደሳምራዊው ሁላችንም እንድንሆን ነው።

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here