spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትየክርስቲያኖችን መታረድ እንዴት እናስቁም? (ክፍል አንድ )

የክርስቲያኖችን መታረድ እንዴት እናስቁም? (ክፍል አንድ )

ክፍል አንድ 
ከሰይፈስላሴ 

በዝቋላ መዕመናን ታረዱ፡ በየቀኑ ክርስቲያኖች ሲታረዱ እኛ ፊስ ቡክ ላይ ሻማ እያበራን ማስቆም የሚገባንን ግድያ አብረን እየፈጸምን ነው። አንተ ግዴለም ግደል እኛ ደግሞ ሻማ በፊስ ቡክ እናበራለን ብለን ከሰይጣን ጋር ውለታ የገባን እስኪመስል ተባባሪ እየሆንን ነው። እንደ ክርስቲያን ይህንን የማስቆም ግዴታ የለብንምን? 

ይህ ለኛ ለኦርቶዶክስ አማኞች የቀረበ ፈተናስ ቢሆን? ፈተናውን እናልፋለን ወይንም እንወድቃለን? በመጨረሻስ እኛም “እናንተ ርጉማን፥  ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ  አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና” (ማቲ 25፡ 41_43) ከመባል አናመልጥ ይሆን? በመጨረሻው ስንጠየቅ እኔ በፌስ ቡኬ ሻማ አብርቻለሁ ወይንም አቡኑ እንትና አድርግ ቢሉኝ ኖሮ አበላ፤ አጠጣ፤ አጠይቅ ነበር ብለን እናመልጥ ይሆን? ወይስ እንደ ቃዬል እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን ብለን ለማምታታት እንሞክራለን? 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አናሳ ወይስ ትልቅ ቁጥር አለው ህዝብ? 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባላት በቁጥራቸው ከ60 እስከ 70 ሚሊዬን ይደርሳል ይባላል። የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በፈርንጆቹ 2014, 99.7 ሚሊዮን ከነበርና ህዝቡ 2.52% ካደገ የኢትጵያ ህዝብ ቁጥር በ2024 የሚገመተው 129,719,719 ነው የሚል መረጃ ኦንላይን አለ። የህወሐትን ህዝብ ቆጠራ ከተቀበልን 45% ኦርቶዶክስ ነው ይባላል። ይህ ማለት 60 ሚሊዮን ነው። 

ይህን ያህል ክርስቲያን ቁጥር ያለባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ሩሲያ የህዝብ ቁጥሩ ከኢትዮጵያ ይበልጣል። ይሁን እንጂ የ70 አመቱ የኮሚኒዝም አስተምህሮ በርካታው ኢ_አማኒ እንዲሆን አድርጎታል። የሩሲያ ህዝብ ኦርቶዶክስ ነኝ ቢልም ቤተክርቲያን የሚሄደው ግን ከ4.4 እስከ 7.4 ሚሊዮን ቢሆን ነው። (The number of practicing Orthodox Christians, meaning those who regularly attend  church services, is estimated to be between 4.4 million and 7.4 million in Russia). ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ ቁጥር በአንድ ንግስ ቀን ግልብጥ ብሎ የሚወጣው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ አማኝ ነው የሚባልበት ምክንያት ከ28 እስከ 38 ሚሊዮን ህዝብ እሁድ ቤተ ክርቲያን ይሳለማል፤ ያስቀድሳል። (The number of regular churchgoers in Ethiopia would be between 28.1 million and 38.8  million)። 

ይህ ማለት አለም ላይ ካሉ 190 ሀገራት ውስጥ 150ዎቹ የህዝብ ቁጥራቸው 38 ሚሊዮን በታች ነው። ማለትም እሁድ ከሚያስቀድሰው 38 ሚሊዮን ህዝብ ያነሰ ነው። እንግዲህ 60 ሚሊዮን እዝብ ለምን የአናሳ ስነ ልቦና ተላበስ ብሎ መጠየቅ ያሻል። የማንም ዱርዬ አሰልፎ የሚያርደው ሆነ። ለምንስ በራሱም በፈጣሪውም እምነት አጣ ብለን መጠየቅ አለብን?  

ኦርቶዶክሱን ምን ሰለበው? 

ታድያ ለምን ይሄንን ያህል ቁጥር ያለው ህዝብ ለዘርና ለሀይማኖት ጥፋት ተጋለጠ ብለን ስንጠይቅ ለሀምሳ አመት የተሰበከው ርዕዮት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች “ነፍስን የሚገልውን ሳይሆን ስጋን የሚገለውን እንዲፈሩ” የስነ ልቦና እጥበት ስለተደረገባቸውና እነሱም አምነው ስለተቀበሉት ነው።  

ከአንገትህ ላይ መስቀሉን ንቁረት ከነጠላህ ላይ ሰንደቅ አላማውን ልቅደድ ሲባል ተሰልፎ የሚያስቀድድ በክፋ የፍርሀት መንፈስ የተያዘ ሆነ። 

“ሞትኩ” ብለው የቁም ተስካር ያወጡጽ መነኩዎች ሳይቀር ሞትን ይፈራል። የቁም ተስካርና መገነዙ ለትያትር ይሆን ወይስ በፈጣሪው ላይ እምነት ማጣት?

መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነነዌ ም1፡9 “በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?” ይላል። ታድያ መፍራት፤ መደንገጥ፤ ጽናት ማጣት ከየት መጣ። 

ዛሬ በብሄር በተሳከረበት አገር አንድ የትንሹን ብሄር ለምሳሌ የአደሬን ወይንም የወራቤን መሀበረሰብ አባል አንድ ሰው በጥፊ መታ ቢባል ሀገር ይታመሳል። በገዳም ያሉና ማንንም ያልነኩ፤ በማንም የማይደርሱ ንጹሀን ሲታረዱ ግን 60 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኦርቶዶክስ አማኝ አንድ ነገር አያደርግም። አትግደሉን ብሎ ለመጠየቅ እንኳን ይፈራል። አሁን 60 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ ሌላው ይቅር ከሀጥያት ጋር አልተባበርም ቢል መፍትሄ ማምጣት ያቅተዋል? 

የህሊናና የተግባር ጥሪ 

ኦሪት ዘፍጥራት 4፡9 “እግዚአብሔርም ቃየንን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ  ነኝን?”  

ስለዚህ “እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን” ካላልን በስተቀር ይሄንን ግድያ ማስቆም የሚጠበቀው ከብርሀኑ ጁላ፤ ከሽመልስ አብዲሳ ወይንም ከአብይ አይደለም። አነሱማ ክርስቲያንን ለማጥፋት ቆርጠው የተነስተው አደራጅተው የለቀቁብህ ናቸውና በሚጣራው በአቤል ደም ይጠየቃሉ። 

አሁን ችግሩ ያለው የኦርቶዶልስ እምነት ተከታዮ ላይ ነው። እንደ ትልቁ ቁጥር ድምጽ እንዳለው ህዝብ፤ በመከላከያም፣ በፖሊስም፤ በፍርድ ስርአቱምና በመንግስት ቢሮክራሲውም ውስጥ ያለ ሀይል ወንድምህን ለመጠበቅ ምን አደረግክ ተብሎእ ይጠየቃል። በእጅህ ላይ ያለው የንጹሀን ለማስቆም ምን አድርግሀል ይባለል። መንግስትን እየታዘዘና የወንጀል ተባባሪ እየሆነ ሁሉ ጳጳሱ ቢያዙ ኖሮ በጎ እሰራ ነበር በማለት ከፍርድ አያድንም። 

አዎ የወንድሞችህ ጠባቂ ነን። ከዚህ ሀላፊነት ማንም አያመልጥም። በሰው ፊት ብልጥ መስለንና መታየት ይቻላል በፈጣሪ ፊት ግን አይቻልም። 

የሚገርመው ደግሞ አንዳንዱ ክርስቲያን ከሀጥያት ጋር አትተባበር ሲባል አቡነ ጴጥሮስንን ሁንና መትረየስ ፊት ቁም የተባለ ያህል ይሸበራል። ማንም መትረየስ ፊት ቁም የተባለ የለም፤ ከሀጥያተኞች ጋር እያበርክ ሀጥያትን አትስራ ነው።  

ጥሪው ከነፍሰገዳዮች ጋር አትተባበር፤ የንጹሀን ደም ሲፈስ ነግ በኔ ብለህ አውግዝ፤ ለተራበው አብላ፤ የተሰደደውን አጽናና፤ ለታረዙት አልንስ። ለሀጥያን ነፍስን ለሚያጠፉ አትታዘዝ። ደሙ ባንተም እጅ ላይ ይሆናልና። ይህ ደግሞ በሲኖዶስ የሚታወጅ ሳይሆን አንተ ከፈጣሪግ ጋር የምትገባው ነው። 

ስለዚህ ከዛሬቷ ቀን ጀመሮ ከሀጥያት ጋር አልተባበርም፤ እጄን በንጹሀን ደም ከሚታጠበው ጋር አላነካካም፤ የስራውም ተባባሪ አልሆንም። እኔም የወንድሜ ጠባቂ ነኝ እንጂ አሳራጅ አይደለሁም በል።

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News English page

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here