spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትይድረስ ለፋኖ ፟ - ስልታዊ ማስታወሻዎች የአማራ ፋኖ፟ ህልውና ትግል ወደ ድርጁ አገር...

ይድረስ ለፋኖ ፟ – ስልታዊ ማስታወሻዎች የአማራ ፋኖ፟ ህልውና ትግል ወደ ድርጁ አገር አቀፍ ፖለቲካ ንቅናቄ ሲሸጋገር – ታሳቢ ጉዳዮች

Tesfaye Demmellash _ Fano

ተስፋዬ ደምመላሽ

ፋኖ፟ በአማራ ጠቅላይ ግዛቶች ወታደራዊ እዞች አቋቁሞ ወደ አንድ የአማራ ጦር ኃይል ምሥረታ እየገሰገሰ ነው። በጦር ሜዳ በተደጋጋሚ የሚቀናጃቸውን አካባባዊና ታክቲካዊ ድሎች በየጊዜው ወደፊት መረማመጃ ለማድረግ ትግሉን እያጠናከራና እያሰፋ ይገኛል። ብዙ ሳይውል ሳያደር ከፍ ወዳለ የፖለቲካ ንቅናቄ ደረጃ ይሸጋገራል ተብሎ ይጠበቃል።

የትግሉን ዘላቂ ስልታዊ ቅኝትና ፖለቲካዊ አመራር አስፈላጊ የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። እዚህ ሁለት የተዛመዱ ነገሮች ጠቅለለ አርጎ መጠቆም ይበቃል። 

አንደኛ፣ አማራው የገጠመው ድርብርብ የህልውና አደጋ (እንደ ፋኖ፟ ታጋይ፣ እንደ ማኅበረሰብና እንደ አስኳል የኢትዮጵያ አካል) ፖለቲካዊ፣ ርዕዮታዊና ተቋማዊ ነው። ሁለተኛ፣ የፋኖ፟ ተጋድሎ የፖለቲካ ኃይል ከመቆጣጠር ባሻገር ነባሩን ዘረኛ አገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ አቅዷል። ይህ ፈታኝ ዕቅድ በስኬት ተፈጻሚ ሊሆን የሚችለው ደግሞ በሚመጥነው ሰፋና ጠለቅ ያለ አገር አቀፍ ስልታዊ ንቅናቄ ነው።

የጥልቅ ስልት/ዘዴ ጠቃሚነት

በመሠረቱ የአማራው የህልውና ትግል ኢላማ ይህ ወይም ያ ተገንጣይ ጎሠኛ ወገን፣ አለያም ኢትዮጵያን በብቸኝነት ልቆጣጠር ባይ ገዢ ቡድን ሳይሆን የጎሣ ማንነት ተሻጋሪ ፀረ አማራና  ፀረ አንድነት የአገዛዝ መዋቅር ነው። መዋቅሩ ከጥሬ ዘረኝነት ባሻገር ብዙ ገጽታዎች አሉት። እነዚህ በዋናነት ፖለቲካዊ ታሪክ አመለካከትን (በተለይ የሃሰት ትርክትን)፣ አስተሳሰብን፣ ምጣኔ ሃብት/ልማት አስተዳደርን፣ ማኅበራዊ ኑሮን፣ ባህልን፣ ትምህርትንና መንፈሳዊ ሕይወትን ያካትታሉ።

ስለዚህ የአማራ ፋኖ፟ የመኖር አለመኖር ትግል በተለያዩ የኅብረተሰብ ዘርፎች የሚገለጸውን ዘረኛ የአገዛዝ አውታር ሰፋና ጠለቅ ብሎ ሊቋቋም የሚችል፣ ብሎም የሚቀለብስና በአዲስ ሥርዓት የሚተካ ሁለገብ ስልት ማዳበር ግድ ይለዋል። መዋቅራዊ (ተቋማዊ) ለውጥ ለማምጣት በተለያዩ ዘርፈ ማኅበራትና አገራዊ ሁኔታዎች እንዳስፈላጊነቱ እየተስተካከለ ተፈጻሚ የሚሆን መሠረታዊ ዘዴ ለለውጡ ዘላቂነት ወሳኝ ነው።

የአማራው/የአገር ጉዳዮች ስልታዊ አቀራረጽ

አማራው ማኅበራዊና አገራዊ ህልውናውን ከዘረኞች ጥቃቶች ለመከላከል ሲንቀሳቀስ ደረጃው ከፍ ወዳለ አገር አቀፍ ትግል የሚሸጋገርበት አንዱ ዋና መንገድ የራሱንና የኢትዮጵያን ብርቱ ጉዳዮች በአዲስ መልክ ወይም መንፈስ አጥርቶና አጠናክሮ መቅረጹ ነው። 

ሁለት የተያያዙ የቀርጻ ደረጃዎች መጠቆም እንችላለን።

አንደኛው እርከን፣ ፋኖ፟ በራስና አገር አድን ትግሉ የአጭር ጊዜ እርምጃዎች ኢንዲወስድ የሚያስገድዱትን ተለዋዋጭ ኩነቶችና ነባራዊ ሁኔታዎች ወይም አካባባዊ ችግሮች (ለምሳሌ የወልቃይትና ራያን) የሚገጥምበት እርከን ነው። 

እነዚህ ጉዳዮች፣ በአንድ በኩል በአንፃር ወይም በከፊል ራሳቸውን ችለው መታየት ሊኖርባቸው የሚችሉና ተመጣጣኝ ምላሾች የሚፈልጉ እንጂ በቀጥታና አንዳፍታ ወይም በጅምላ በአገራዊ ፈርጆች የሚጣጡ ላይሆኑ ይችላሉ። በሌላ በኩል ግን፣ ጉዳዮቹ ስልታዊ በሆነ አቀራረብና አያያዝ በአገር አቀፉ የሥርዓት ለውጥ ዕቅድ ውስጥ በአገባብ የሚካተቱ ናቸው።

ሁለተኛው የጉዳዮች ቀረጽ እርከን ደግሞ ለተለያዩ፣ ተለዋዋጭም ሆኑ ነባ፟ር ችግሮች ጠቅለል ያሉ የጋራ መፍትሔዎች ለማበጀት ስልታዊ ትንተና የሚደረግባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የተለያዩ ችግሮች በመዋቃራዊ ይዞታቸው ጠልቀው ታሳቢ የሚሆኑበትና የሚፈቱበት ዘላቂ የቀረጻ ደርጃ ነው።

ስልታዊ እንቅስቃሴ በአስተሳሰብ መስክ

በጽንሳዊ ፖለቲካ አስተሳሰብ ሜዳ ላይም ስልታዊ ተንቀሳቃሽነትና አመራር አስፈላጊነትም ተገቢነትም አለው። ለዚህ መሠረታዊው ምክንያት የሃሳቦች ራሳቸው ተፈጥሮ ወይም ትርጉም አያያዝና አለቃቀቅ ባህሪ ነው። ሃሳቦች (መርሆችን፣ እሴቶችን፣ እምነቶችንና ሌሎች አእምሯዊ ጽንሶችን ጠቅልሎ) የመንገድ ካርታ እንደሚመራን በቀጥታ የትግል አቅጣጫዎችን አይሳዩንም። 

በቅጡ ሊመሩን የሚችሉት ራሳቸው ለነሱ ታማኝ ከሆኑ ታጋዮች ግልጽ አላማ፣ ይዘታቸውን የማያሰልል ወይም የማያወላግድ ድርጁ (ሥርዓታዊ) አያይዝ፣ እንዲሁም ስልታዊ አተረጓጎም  እና አፈጻጽም ካላገኙ ተገቢ ይዘታቸውን በግብታዊ መንገድ አይለቁም። የፖለቲካ ሃሳቦች ቃል በቃል ወይም በመጠሪያ ስማቸው ብቻ (“የሕግ የበላይነት”፣ “ፍትህ”፣ “ዲሞክራሲ” ወዘተ) ራሳቸውን ፍቺ ሰጪና ፈጻሚ አደሉም።

ስለዚህ፣ የአማራ/ኢትዮጵያ የመኖር አለመኖር ትግል ለበጎ ሃሳቦችና መርሆች ታማኝነት ከሌለው የዘረኞች ፖለቲካ አስተሳሰብም አሠራርም የጸዳና ከትግሉ ጋር የሚግባባ የተሻለ፣ ከአገርና ሕዝብ ነፃነት ጋር የሚጣጣም የአቀራረጽ፣ አተረጓጎምና አፈጻጸም ባህል ማዳበር ግድ ሊለው ይገባል። የአማራ ፋኖ፟፣ ድንቅ የጦር አውድ ተጋድሎውን የሚመጥንና የሚያንጸባርቅ አርበኝነት በአስተሳስብ (በርዕዮት) ሜዳም የማሳየት ተስፋ ተጥሎበታል።

___

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News

ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. ሁሉም የዘር ፓለቲከኞች ተበድለናል ተጨቁነናል እያሉ ነው ያኔ ጫካው እንደዛሬው ሳይመነጠር ከአውሬ ጋር እያደሩ አውሬ ሆነው ከተማ የገቡት። ጦርነት የስልጣኔ ምልክት አይደለም። ሁሌ ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ገና ከትግራይ ወረራና ዝርፊያ ያላገገመን ህበረተሰብ በፋኖና በመከላከያ መሃል አስገብቶ ማገዶ ማድረግ የነጻነት ትግል አይደለም። የሚያሳዝነው አንዳንድ ፋኖ በተናቸው የተባሉ ወረቀቶችን ስንመለከት ትምህርት እንዲቆም ሁሉ መጠየቁ የቱን ያህል ነጻ እናወጣሃለን የሚባለው የአማራ ህዝብ ወደ ጨለማ እንደገባ የሚያሳየን ይሆናል። የመንገድ ሥራው፤ የሃይል ማመንጫ አውታሮች፤ የሰው ለሰው ግንኙነትንና አልፎ ተርፎም አርሶና ሰርቶ መብላትን የነፈገው ይህ የሁለት ሃይሎች ግብ ግብ ትርፋ አልባና በዋንኛነት የአማራን ህዝብ ቀጥሎም ሃገሪቱን እየጎዳ ያለ የፓለቲካ ስር ግብ ነው። ይህ ሲባል የፌደራሉ መንግስት ቀንድ ያወጣ ሰይጣን አይደለም እያልኩ አይደለም። ግን ሁለቱ ዝሆኖች ሲታገሉ የሚጎዳው እናሳልፍለታለን የተባለው ህዝብ ነው። ይህን በቅርቡና በሩቁ የሃገሪቱ ታሪክ መመልከት ይቻላል። የወያኔ ከ 17 ዓመታት መከራ በህዋላ የከተማ አለቃ ሆኖ ሃገርን ማስተዳደሩ ለትግራይ ህዝብ ያተረፈለት አንድም ፋይዳ የለም። ለኦሮሞ ህዝብ እንታገላለን የሚሉት ጥርሳቸው ወልቆ፤ አይናቸው ፈዞ አሁንም ቆንጨራ እንደጨበጡ ናቸው። ለኦሮሞ ህዝብ ግን ከዚህ ግባ የሚባል አንድም ፋይዳ አልተገኘለትም። በብሄር ስም ነጋዴዎች የፓለቲካ ተንኮልና እርስ በእርስ ሰውን ማባላትን የተማሩት ከክፋት ሁሉ ቁንጮ ከሻቢያ ነው። ሲመቸው አረብ ሳይመቸው ደገኛ እየሆነ ይኸው ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኤርትራን ህዝብ ጨቁኖ ያሰቃያል። ባጭሩ ባሩድ እያሸተቱ፤ ድልድይ እያፈረሱ፤ እቃ ተሸካሚ ካሚዎኖችን እያወደሙ፤ የህዝብ ተሳፋሪዎችን እያፈኑና መላሾ እየተቀበሉ መሹሎክሎክ የሽፍታ እንጂ የነጻነት ተዋጊ ባህሪ አይደለም።
    ልብ ላለውና ያለፈውን የፓለቲካ ስልትና ውስልትና ለተገነዘበ ዛሬ በሃገራችን ውስጥ የትጥቅ ትግል አያስፈልግም። የሚያስፈልገው መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ ሃይሎች በጠረጴዛ ዙሪያ መመካከሩ ነው። ግን ይህ የሚሆን አልሆነም። ገና ለገና መንግስቴን ያናጋል፤ እንዲህ እና እንደዚያ ብሎ ጽፏል፤ ተናግሯል እየተባለ ሰው እንበለ ፍርድ ለእስር በሚዳረግባት የሃበሻ ምድር ኡኡታና ለቅሶ የተለመደ ጉዳይ እየሆነ ይገኛል። ሰውም በመከራና በኑሮ ውድነት ከመደንዘዙ የተነሳ መከራው ቤቱ ገብቶ የሃዘን ድንኳን እስካላስጣለው ድረስ የሚኖረው ለራስ ነው። ግን ምን ይደረግ ጥቂቶች በሚፈነጩባት ምድር እልፎች እየተራቡና እያነቡ አይን ያለው የማያይበት፤ ጆሮ ያለው የማይሰማበት ህብረተሰብ ተፈጥሯል።
    እኔን በዚህ ሁሉ የሚያሰጋኝ በእኛ መከፋፈልና መገዳደል የሚነግድት የውጭ ሃይሎች እስክንዳከም ጠብቀው ወረራ እንዳይፈጽሙና ሃገሪቱን ከስር መሰረቷ እንዳያወድሟት ነው። እኔ የምታገለው የምሞተው ላንተ ነው የሚሉኝን ሁሉ የምመለከታቸው ካለፈው የፓለቲካ ክስተት ጋር በማያያዝ ነው።፡ስንቶች ለመሬት ላራሹ ራሳቸውን ሰውተዋል? ዛሬ መሬት የማን ነው? የባለሃብት! ስንቶች ለብሄራቸው ነጻነትና ለህዝባቸው ልዕልና ተፋለሙ። ያ ሁሉ እንደ ጎርፍ የፈሰሰ ደም፤ የወደመ ንብረት ለህዝባችን አንድም የሚበጅ ነገር አላመጣም። የጉልቻ መለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ የጠገበው ወርዶ የተራቡት ናቸው በቦታው የተተኩት፤፡ ይህ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ የፓለቲካ ስልት የ 3 ሺ ዘመን ነጻነት አለኝ የምትለውን ሃገር ከጎረቤት ሃገሮች በታች እንድትሆን አርጓታል።፡ ወረተኛው የሃበሻ ፓለቲካ እንደ ኩራዝ መብራት ብልጭ ድርግም እያለ ስንቱን ወደ ሞት እንዳጋዘ ሰው ሊገነዘብ ይገባል። ዲሞክራሲ፤ የህዝብ ነጻነት፤ በአፓርታይድ አሰራር በተሰመረች ሃገር ውስጥ አይመጣም። ሁሌም ስንፋለም ነው የምንኖረው። ባጭሩ የሃገሪቱ መሰረት ተናግቷል፤፡ ስሌታችን በጎሳና በቋንቋ ሆኖአል፤፡ በክልል ፓለቲካ የተሳከረው ሃገሬ ነው የሚለው በራፉ ላይ ቆሞ ነው። ጦርነት ሊበቃ ይገባል። ከውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ ሆናችሁ ጦርነቱ እንዲፋፋም የምትገፋፉ ሁሉ ልብ ግዙ። የጠ/ሚሩም መንግስት በጉልበት ሁሉን አምበረክካለሁ ከማለት ይልቅ ሰጥቶ መቀበልን ይማር። ብዙም የፓለቲካ እሰጣ ገባ የሚቀጣጠለው ነገርን በግልጽ ባለመረዳት ነው። በሃገራችን ያሉ ግጭቶችና የመብት ፍልሚያዎች ሁሉ መታየት ያለባቸው ከጊዜ ጋር ነው። ጊዜ እየሮጠ ነው። ያመለጠን ጊዜ መልሶ መተካት አይቻልም። ሰው ይማርበት፤ ሰው ሰርቶ ይብላ። ሃገር አቋራጭ ትራንስፓርትና ሌሎችም ነገሮች ሁሉ የሰላም አየር ይተንፍሱ። ፓለቲካ የሽንኮች እይታ ነው። The Achilles Trap – by Steve Coll የኢራቁን ሳዳም ከስልጣን አውርዶ ዛሬ ኢራቅ ላለችበት ገመና የከተታትን ያለመተማመንና በለሌ ነገር ላይ መወዛገብን ከምንጩ ያስረዳል። አንቡት። መገዳደል ይብቃ!

  2. Birru March 19, 2024
    ከ1966 አብዮት ማግስት ጀምሮ ተማሪው፣አስተማሪው፣ወዛደሩ፣ገበሬው በሀገራችን ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመትከል፣ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ብርቱ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን፣ብልጣብልጠ ግለሰቦች በሕዝቡ ውስጥ ተደብቀው ” ከጳጳሱ በላይ ክርስቲያን ” ሆነው በመቅረብ አመራሩን በዘዴ ሲነጥቁ ተመልክተናል። የበለጠ ፍላጎታቸውንም ለማራምድ አምባ ገነን ሲሆኑ ታዝበናል። እነኝህ አገር ሸውደው ሥልጣን የጨበጡ ‘ከሀዲዎች’ ለግላቸው ተልዕኮ እንጅ “ኢትዮጵያ ” ለምንላት ሀገር ጥቅም ሲጥሩ አልታዩም። በይበልጥ የሚያቆስለው ደግሞ የሥልጣናቸውን ዕድሜ ለማራዘም ሀገሪቱን በድህነት አረንቋ ከመዝፈቅ አልፈው፣ሕዝቡ እርስ በርስ እየተፋጅ እንዲኖር መጣራቸው ነው። ሕዝቡ በዚህና በዚያ ተናዶ በትብብር እንዳያወርዳቸው፣ አሀዱ ብለው ሥልጣን ሲቆናጠጡ ጀምሮ፣የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ በመድፋት የጦር መሣሪያ ያከማቻሉ። ከራሳቸ ወገን የሆነ ወታደር በጥንቃቄ በመምሪጥ፣ በሥልጣናቸውን ያስጠብቃሉ። የዋሕ የኢትዮጵያ ሕዝብ የይስሙላ ምርጫ ይሳካልኛል እያለ ሲጠብቅ ይኖራል። ይህ ነው በኢትዮጵያችን በተጨባጭ እየደረሰ ያለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here