spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትየብልጽግና ወንጌል የክርስቶስ ወይስ የዲያብሎስ ፈተና (ክፍል አንድ)

የብልጽግና ወንጌል የክርስቶስ ወይስ የዲያብሎስ ፈተና (ክፍል አንድ)

Prosperity Gospel Ethiopia

ሰይፈ ስላሴ
ክፍል አንድ

ስለ ሀይማኖት በቅርብ ግዜ ነው መጻፍ የጀመርኩት። ምክንያቱም የፕሮቴስታንትም የኦርቶዶክስ የእምነት አባቶች ገና ስለ ብልጽግና ወንጌል ምንጭና ግብ አላነበቡም። ምን እንደሆነም ገና አላወቁም። እንደ ክርስቶስ አስተምህሮ ተቆጥሮ ከሱ ጋር ህብረት ለመፍጠር እየተሞከረ ነው። አብይ እንዳለው ብርሀንና ጨለማን ለማስታረቅ ጳጳሳቱና ወንጌላውያን እየሞከሩ ነው። ይሄንን ጽሁፍ በሀይማኖት ድህረ ገጾች ማውጣት እችላለሁ ይሁንና እየተታለለ ያለው እስላሙም፣ ፕሮቴስታንቱም ኦርቶዶክሱም ነውና በዚህ አይነት ሚዲያ ሁሉም እንዲያነበው ጽፌያለሁ

በእርግጥ ፍቅረ ንዋይ -ብልጽግናን መሻትናንት ማምለክ የክርስቶስ አስተምህሮ ነውን? 

በማቲዎስ ወንጌል ም4 ቁ 1-11 ይሄንን ይላል ። “ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተም ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። አርባ ቀን አርባ ሌሊት ከጦመ በኋላ ተራበ።ፈተኙም ቀርቦ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆን በል አለው።  እርሱም መልሶ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል አለው። ……ከዛም ዲያቢሎስ እጅግ ረዥም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፣ የዓለምን መንግስታት ሁሉ ከክብራቸው  አሳይቶ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ  እሰጥካለሁ አለው። ያን ግዜ ኢየሱስ ሒድ አንተ ሰይጣን ከፊቴ ለአምላክህ ስገድ እሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፏልልና አለው።” 

ይህ ቃል የተጻፈው ዲያቢሎስ እንዴት የሰው ልጅን በጥቅምና በዝና እንደሚፈትሸውና የሰው ልጅም ለሀብትና ጥቅም ብሎ ለሰይጣን መስገድ እንደማይገባው ለማስተማ ነበር። ይሁንና በ20ኛው ክፍለዘመን ብዙ የአነቃቂ ንግግር ጸሀፊዎች የሰው ልጅ እንዴት ሀብታም ይሆናል የሚለውን መጻፍ ጀመሩ። ይህም  የአዲሱ ዘመን ንቅናቄን ፈጠረ (The New Age Movement) ተወለደ። ይህ ስነ ልቦና መሆኑ ቀርቶ ሀይማኖት/እምነት ሆነ አሁን አብይ ክርስቲያንም እስላሙንም የዚህ እምነት ተከታይ አድርጎ ብዙውን ሀይማኖቱን አስቀይሮታል። 

የብልጽግና ወንጌል ማርቆስ፣ ማቲዎስ፣ ሉቃስ ወይንስ ዮሃንስ ጻፈው?

የብልጽግና ወንጌል የተጻፈው መጀመሪያ በስነ ልቦና አነቃቂዎች ነው። እነ ናፖሊዮን ሂል “Think and Grow Rich”  እነ ኖርማን አንስት  “The Power of Positive Thinking” ነው የጀመሩት። ይሄም ፓዘቲፍ ማሰብና መመኘት ጤናና ሀብት ይሰጣል በማለት ነው።  

ይህን ወስደው እነ Joel Osteen, የ Lakewood Church ባለቤት ትልቁ. በአሜሪካ ቤተ እምነት ባለቤት  እና Oral Roberts, a pioneering televangelist,  ወደ ቤተ እምነት ወስደው ሳይኮሎጂውን ወደ ቅዱስ መጽሀፍነት አሳደጉት።  አስተምህሮውም ሀብታም እንድትሆኑ መጀመሪያ ለፓስተራችሁ ለዘር የሚሆን ብር ስጡ እሱ ይጸልይላችሁና ያባዛልችሀል ነው ። ልክ እነ እስራኤል ዳንሳ ብር ስጡኝና እኔ በሞባዬላችሁ ክርስቶስ በሞባዬላችሁ ሚሊዮን ያስገባል እንደሚሰብኩት ማለት ነው።

 የብልጽግና እና የጤና መጽሀፍ ቅዱስ የሚባለው በእንግሊዘኛ (The prosperity gospel, also known as the health and wealth gospel or name it and claim it, is a teaching within Protestant Christianity”. ብዙ የፕሮቴስታንት እምነት የተታለሉትና አብይ ሺ አመት ንገስ ብለው በአደባባይ የጸለዩት አብይ የሚከተሉትን መጽሐፍ ቅዱስ ከነሱ ጋ አንድ  ስለመሰላቸው ነው። ይህ የብልጽግና ወንጌላውያን ማታለል በአደባባይ እየታየ ነው። 

አሁን በሞባዬላችሁ ከንግድ ባንክ ሚሊዮን ብር እንዲገባ ያላችሁን ሁሉ ለኔ ስጡና  ልጸልይላችሁ የሚሉ እንደ እስራኤል ድልንሳ፣ አዩ ጩፋና፣ ዮናታን በእኛ ሀገር ተፈጠረዋል። አብይም የዚህ እምነት ተከታይ እንጂ የክስቶስ ተከታይ  አይደለም።  ክርስቲያን ማለት የክርስቶስን ቃል የሚያከብር ነው። በማቲዎስ ም4:8-11 የተጻፈው ዲያቢሎስ እንዴት ሰውን በፍቅረ ንዋይ ጠልፎ ሊጥለው እንደሚችል ለማሳየት ነው ክርስቶስ በፈቃዱ ተፈትኖ ያሳየን። የሰውም ልጅ መልስ “ወጊድ ስልጣን” ማለት እንጂ ብር ላሳየን ዲያብሎስ መስገድ አይደለም። 

በሉቃስ ወንጌል ደግሞ ም6: 20-26. ይህንን ይላል “እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና። እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና።  እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና ታለቅሱማላችሁ።  ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።”

የብልጽና ወንጌል ከላይ የተጠቀሱትን የክርስቶስ ቃል አይቀበልም። ሳትሰራ፣ ሳትጥር፣ ሳትደክም ሀብት በሞባዬልህ ይገባል። ለድሆች አታስብ፣ በመንገድ ላይ ወንበዴዎች ደብድበው የጣሉትን አትመልከት፣  ለሚሞቱት ለሚሰቃዩት አታስብ። አንተ ደግ ደጉንና  ሀብታና ንብረት ብቻ እሻ። እሱን ታገኛለህ።  መስረቅ፣ መዋሸት፣ ጉቦ መብላት ፣ ድሆችን ለማየት መጠየፍ፣ ቤታቸውን ማፍረስ የብልጽግና ወንጌል መገለጫ ነው። ዛሬ እነ ሽመልስ ወንድሙ በቢሊዮን በጉቦና በሲሚንቶ ንግድ ከብረዋል። እነ አዳነች አቤቤ ልጆቻቸውን በዶላር ያስተምራሉ፣ ግን ማታ ተሰብስበው ተንበርክከው ለአባታቸው ይጸልያሉ።  ይህ አባታቸው የሌብነት፣ የጥላቻ፣ የግድያ አባት ክርስቶስ ይመስላችኋል? አይደለም አፋቸው እንጂ ተግባራቸው ሀብትን የዲያብሎስ ነው። በማቲዎስ ወንጌል ም4:8-11 ላይ እኮ ዲያቢሎስ በምድር ላይ ሀብትና ንብረት መስጠት እንደሚችል ተጽፏል። 

ስለዚህ የብልጽግና ፓርቲ ተከታይ ክርስቲያኖች ንቁ። የተቀላቀላችሁት እምነት እንጂ የምድራዊ ፓለቲካ ፓርቲ አይደለም። አርማውብን ተመልከቱ ከአሜሪካ የብልጽግንና ወንጌል አርማ የተቀዳ ነው።  እበላለሁ ብላችሁ በዘላለማዊ እሳት እንዳትበሉ። የማቲዎስ ወንጌል 6:24 “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው አገልጋይ የለም፣ አንዱን ይወዳል ሁለተኛውንም ይጠላል፣ ወይንም አንዱን ይታዘዛል፣ ለሁለተኛውም አይታዘዝም፣ እንግዲህ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብመገዛት አትችሉም። 

ሙስሊሞችም የተቀላቀላችሁት የብልጽግና ” መጽሐፍብ ቅዱስ”  እንጂ አለማዊ ፓርቲ አይደልም። አናውቅም ነበር እንዳትሉ ይሄው ተነግሯችሀል። አብይ Charismatic የሆነና ብዙ ተከታዮችን ማሳሳት የሚያስችል የክፏ መንፈስ ጸጋ ያለው ነው። 14 ሚሊዮን አስክጂያለሁ ይላል። ሁሉንም ሀይማኖቱን ሳያስቀይር አይቆምም።

የኦርቶዶክስና የብልጽግና ወንጌል ግጭት

አብይ ከልጅነቱ ጀምሮ ሀብት ንብረት ዝናን ለማግኘት እንደተጋ ነግሮናል። በማቲዎስ ወንጌል 4:8-11 እንደተጻፈው ዲያቢሎስ ከሰገዱለት በምድር ላይ ስልጣንና ሀብትም ይሰጣል። ስለዚህ በድህነት ሰቀቀን ስነ ልቦና ለሚሰቃይ ሀብት ስጠኝ እንጂ እሰግድልሀለሁ ይላል። የብልጽግና ወንጌል ልክ እነ መንግስቱ ለማርክስ ኤንግልስና ሌኒን ሰግደን ገነት እንገባለን ብለው እንዳሳመኑት አሁንም ለዲያቢሎስ ብንሰግድ እንበለጽጋለን፣  ብልጭልጭ ህንጻ ውስጥ እንኖራለን፣ ገነት ማለት የአበቦች ቦታ ናት ብለው ብዙ ክርስቲያንና ብዙ የእስልምና ተከታዮችን ወደ ገሀነም አስከትለው እየሄዱ ነው። 

ዲያቢሎስ ደግሞ ግብር ይጠይቃል። ይህም ሀጥያትን መስራት ነው። ይሄም ሀጥያት ነፍስ ማጥፋት ነው፣ የንጹሀንን ደም ማፍሰስ ነው። ወይን መጠጣት ሀጥያት ነው የሚሉት የብልጽግና አማኞች የሰው ደም ማፍሰስ ግን ሀጥያት መስሎ አይታያቸውም። በአደባባይ ወይን አንጠጣም. ብለው ጻድቅ መስለው የሚታዩት በጭለማ ደግሞ ህጻናትን ያሳርዳሉ፣ እናቶችን ይገላሉ፣ በሰራዊታቸው ሴቶችን ይደፍራሉ፣ ዘር ለማጥፋት ይተጋሉ። ደሆችንን ያሳድዳሉ። ዲያብሎስ እንዳለው ጉልበትና ሀይል ይሰጣቸዋል። እርስቲያኑን እስላሙን፣ መኑኩሴን፣ ሼኩን፣ አባ ገዳውን ህጻናትን ማረድ ግን ይጠበቅባቸዋል። ለዚህ ለዲያቢሎስ ቃብድ የሚሰጡት በመጀነሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኞችን በማረድ ነው።

 ሰይጣን ክርስቶስን ሲፈትነው የአለምን ሀብት ሁሉ አሳይቶ ለኔ ብትሰግድልኝ ይሄንን ሁሉ እሰጥሀለሁ እንዳለው ለአብይና ለሽመልስም ሀብት ለማግኘት የማያደርጉት ነገር  ያለም። 

አብይ ላይ የተዳበለውም የክርስቲያንን ደም የሚጠጣው ዲያብሎስ ኑና ለሰይጣን እንስገድ ሀብትና ብልጽግና ይሰጠናል ሲባሉ እሺ ብለው የሚከተሉት ክርስቲያንና እስላም ነን የሚሉ ብዙ ናቸው።

ክርስቶስ ለደቀ መዝሙሮች ማስጠንቀቂያ ደግሞ  በመንገድልችሀ ላይ ወርቅና ብር አትያዙ ነበር ። 

ክርስቶስ  በማቲዎስ ወንጌል 10:7-10 “ሄዳችሁም። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትን አውጡ፣ በከንቱ የተቀበላችሁ፣ በከንቱ ስጡ። ወርቅ ወይንም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፣ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይንም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ”

ይህ ቃል ሁሉ በሁሉም ወንጌሎች ውስጥ ተደጋግሟል። ይሁንና የብልጽግና የዲያቢሎስ ወንጌል ደግሞ ሀብትን፣ ሞገስን እሹ፣ ወርቅና ዶላርን አጋብሱ ነው የሚላቸው። ዲያቢሎስ ለኔ ስገዱ ብልጽግናን እሰጣችሀለሁ ነው።   ይሄንን ባለማውገዛቸውና ባለ መለየታቸው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ፈተናውን ወድቀው ለሀብት ስገዱ ለሚለው እየጸለዩ ነው። ሎጂክ ስንማር A ከ B ጋር እኩል ከሆነና B ደግሞ ከ C ጋር እኩል ከሆነ A ደግሞ ከ C ጋር እኩል ይሆናል። 

አሁን ያለው ፍቅረ ንዋይ ወዳጅና በንጹሀን ደም የሚታጠበውን አለማውገዝ ከተጠያቂነት አያድንም። መደገፍ ደግሞ እጅን በደም ማነካካት ነው። ይህ ደግሞ የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ጳጳሳትንና የሙስሊሞችም የሀይማኖት አባቶች ያካትታል።

ለጥያትን አውግዙ። ስሙን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ ተብሏል። ሁላችንም ለፍርድ ስንቀርብ እንጠየቅበታን ።

በክፍል ሁለት የ ሁለት ሺ ዘመኑን የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ፈተና እናያን ።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here