Advertise Here 


ክፕሮፌስር ጳውሎስ ሚልክያስ
ወይ አዲስ አበባ ወይ ፒያሳ ሆይ
አራት ኪሎ ድረስ አልባስሽ ሲጋይ
ሆድና አንጀትሽ ተዘርግቶ ሳይ
ሙሾ መውረዴ ነው ዛሬ አደባባይ
አጠገብዋ ስታይ እርቃን ቀር ፒያሳ
ቁጭራም በስጋት ጠየቀች እኔሳ
የእስላም መስጊድ ሰፈር ሲያለብሳት አቧራ
ጮሃ እሪ እሪ: ሎሚ ተራ ተራ
መርካቶም እያየች አቀበት ተራራ
ትላለች አስቡኝ አትርሱኝ አደራ
አይዞሽማ ፒያሳ አጥብቀሽ ጸልይ
ገመናሽ እንዲለብስ የኤሚሬት ከፈይ
በለሆሳስ ሆነሽ አቤት አቤት በይ
ለሰባተኛው አፄ ለቀዳማዊ ዐብይ
መርካቶም ለምኝ ምሕረት ከሰማይ
ንግድ ማእከልሽ ሳይኖረው አኩይ
ይገነባልሽ ዘንድ በአምሳለ ዱባይ
አዲስ አበባችን እንዳትሆን ካርቱም
በቁመናው ቆንጆ አጀቡ ለሚተም
ለቱጃሩ መሪ ለኛ አፄ ጡት ዎንድም
አቤቱታ አቅርቡ ለግርማዊ ማክቱም
__
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡ የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com
Ethiopian News – Borkena English
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ




