spot_img
Saturday, April 20, 2024
Homeነፃ አስተያየትጠባቡ ፤ ጎሰኛውና ፋሽስቱ አቢይ አህመድ የሚያደርገውን አዲስ አበባን የማፈራረስ ዘመቻ ለማስቆም...

ጠባቡ ፤ ጎሰኛውና ፋሽስቱ አቢይ አህመድ የሚያደርገውን አዲስ አበባን የማፈራረስ ዘመቻ ለማስቆም የቀረበ የትግል ጥሪ

አቢይ አህመድ

አስፋው ረጋሳ

አቢይ አህመድና ግብረ አበሮቹ ለውድ አገራችን ኢትዮጵያ ካላቸው ስር የሰደደ ጥላቻ የተነሳ ላለፉት ስድስት ዓመታት በመላው የአገራችን ህዝብ ላይ በታሪካችን ተወዳዳሪ የማይገኝለትን የዘር ማጥፋት፤ የዘር ማጽዳትና ማፈናቀል፤ እንዲሁም የሃይማኖት ተቅዋሞቻችንን የማፈራረስ፤ መሪዎቻቸውን በማባረር በስልጣን መንበራቸውም የነርሱን አገር የማፍረስ ዓላማቸውን በሚያስፈጽሙላቸው ተላላኪና ሆድ አደር ግለሰቦች በመተካት፤ መተኪያ የማይገኝላቸውን ሀገራዊና ታሪካዊ ቅርሶቻችንን በማውደምና በማፈራረስ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ይህንኑ የጥፋት በትራቸውን ላለፉት አንድ መቶ አርባ ዓመታት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥረት በተገነባችው ዋና ከተማችን አዲስ አበባ ላይ ዘርግተው የክተማዋን ታሪካዊ ስፍራዎች በማፈራረስና ህዝብዋንም ያለአንዳች ርህራሄ በማፈናቀል ላይ ይገኛሉ። 

አቢይ አህመድ፤ ሽመልስ አብዲሳ፤ አዳነች አቤቤና የብልጽና (የብልግና፤ የሙስናና፤ አገር አፍራሽ) ፓርቲና ግብረ አበሮቻቸው የሚፈጽሙት ድርጊት ህዝባችንን በተለመደ የማታለልና የቅጥፈት ተግባራቸው እንደሚሉት ልማትን ዓላማው ያደረገ ሳይሆን ይልቁንም ከህጻንነት ዕድሜያቸው ጀምሮ ተኮትኩተው ያደጉበት በኢትዮጵያ አገራችን ላይ ካላቸው ጥላቻ ኢትዮጵያን የማፈራረስና እነሱ ሌት ተቀን የሚቃዡትን ነገር ግን በፍጹም እውን ሊሆን የማይችለውን “ኦሮሚያ” የተሰኘ ሪፐብሊክ የመመስረት ዓላማቸው አካል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። 

ይህ ፋሽስታዊ ቡድን በዋና ከተማችንና በህዝብዋ ላይ የሚያደርሰውንና ታሪክ ይቅር የማይለውን ክፍተኛ ወንጀል ሲፈጽም ህዝባችን በዝምታ ከማለፍ ይልቅ በአንድነት ተነስቶ ሊያስቆም ይገባል።

በመሰረቱ የከተሞች ልማት፤ የኢንዱስትሪዎች፤ የጤና፤ የትምህርትና ሌሎች የመሰረት ልማቶች (የመንገድ ስራ፤ የመብራት፤ የውሃና ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች)፤ ወዘተ ማስፋፋት ብሎም በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ማዘመን ለአንድ አገር ዕድገት አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም እንዲህ ዓይነት የልማትና የዕድገት ስራዎች በተገቢው ሁኔታ በየዘርፉ ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች የአገርና የክተሞችን የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የልማትና የዕድገት ዕቅዶች ባገናዘበ መልኩ በስፋት ተጠንተው የአገርን ታሪካዊ ቅርሶች በሚጠብቁና በህዝብ ላይ መፈናቀልና የኑሮና የአንዋንዋር መናጋትን በማያስከትሉ ሁኔታ የሚዘጋጁ፤ እንዳስፈላጊነቱም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር (ህዝብን ጨምሮ) ውይይት ተደርጎባቸው የሚፈጸሙ እንጂ ህዝብን የሚያፈናቅሉና ታሪካዊ ቅርሶችን የሚያወድሙ መሆን እንደሌለባቸው ይታወቃል።

በሌሎች አገሮችም የተለመደው አሰራር እንደምናየው የክተሞች ልማትና ዕድገት በሚከናወንበት ጊዜ ጥንታዊ ከተሞች ከነቅርሶቻቸው ባሉበት እንዲቆዩና ታሪካዊ አሻራቸው በዘመናት ርዝማኔ እንዳይጠፋ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንክብካቤ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ይልቁንም እነዚህ ጥንታዊና ታሪካዊ ክተሞችና ቅርሶች የአገር ጎብኚዎች መስህብ (tourist attraction) ሆነው የአገሩን ታሪክ ለሌላው ዓለም የሚያስተዋውቁ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ የአገር ሀብቶች ሆነው የሚያገለግሉ መሆናቸው ይታወቃል። ለአብነትም ያህል በመካከለኛው ምስራቅ በጆርዳን የምትገኘውና ከስድስት ሺህ ዓመታት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረችውን ጄራሽን፤ የኢጣልያን ዋና ከተማ የሆነችውንና ሁለት ሺህ ስባት መቶ ሰባ አምስት ዓመታት ያስቆጠረችውን ሮምን፤ በአሜሪካን አገር በቨርጂኒያ ግዛት የምትገኘውንና ሁለት መቶ ሰባ አምስት ዓመታት ያስቆጠረችውን ጥንታዊት ከተማ (Old Town)፤ ለአብነት መጥቀስ ይበቃል።

ክዚህ በላይ እንደተመለክተው የጠባብ፤ ጎሰኛና ፋሽስታዊው አቢይ አህመድ ቡድን ከግብረ አበሮቻቸው ጋር የሚያደርጉት አዲስ አበባን የማፈራርስ ተግባር ውድ አገራችን ኢትዮጵያን የማፍረስና ቅዠታዊ የ”ኦሮሚያ” ሪፐብሊክ የመመስረት ዕኩይ ዓላማቸው አካል መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ፤ በተለይም የአዲስ አበባ ህዝብ ተገንዝቦ ድርጊታቸውን በአፋጣኝ ለያስቆም ይገባል። 

ይህንንም ዕውን ለማድረግ ለኢትዮጵያና ህዝብዋ በቅንነትና በእውነት የቆሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ባልደራስ፤ እናት ፓርቲ፤ ህብር ኢትዮጵያ፤ ኢህአፓ፤ ወዘተ) የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተቃውሞ መግለጫዎችን ከማውጣት ባሻገር ለህዝባችን በተለያየ መንገድ (ለምሳሌ የሰራተኛ፤ የሙያና፤ የሲቪክ ማህበራትን በማስተባበርና በማንቀሳቀስ) የህዝባዊ እምቢተኝነት (Civil Disobedience) የትግል ጥሪ በአፋጣኝ ማድረግ ይገባቸዋል። 

በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በታንክ፤ በመድፍና፤ በድሮን ሲጨፈጨፉ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ለዘመናት ከኖሩባቸው ስፍራዎች ሲፈናቀሉና በረሃብ ሲቆሉ፤ የሃይማኖት ተቅዋሞቻችን ሲፈርሱ፤ ዜጎቻችን በማንነታቸው ምክንያትና በፖለቲካ አቅውማቸው ብቻ ሲታፈኑ፤ ሲታሰሩ፤ ሰቆቃ (torture) ሲፈጸምባቸውና ሲገደሉ፤ ክህጻናት አንስቶ እስከ አረጋውያት ድረስ ያሉ ልጆች፤ እህቶችና እናቶች (መነኮሳት ሳይቀሩ) ሲደፈሩ፤ ገዳማት፤ መስጊዶችና ቤተክርስቲያናት ሲውድሙ፤ ካህናት፤ ሼኮችና የአብነት ተማሪዎች በግፍ ሲረሸኑ፤ ቅርሶቻችን ሲውድሙ እያዘኑ በዝምታ መመልከት በህዝባችንና በውድ ኢትዮጵያችን ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥፋት በፍጹም መፍትሄ ሊሆን አይችልም።

ህዝባችንም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የሚያደርጉለትን ጥሪ ተቀብሎ በአንድነት ሊቆም፤ ሊታገልና ተገቢውን መስዋዕትነት ከፍሎ ክዚህ አረመኔያዊና ፋሽስታዊ ስርዓት ራሱን ነጻ ማውጣት ይኖርበታል። ይህ ፍጹም ጎጠኛ፤ ጠባብ፤ ደንቆሮ፤ ፋሽስታዊ ቡድን በህዝባችንና በኢትዮጵያ አገራችን ላይ በየዕለቱ የሚያደርሰው ግፍ፤ በደልና ሰቆቃ ህዝባችን በአንድነት ተነስቶ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍሎ ማቆም ካልቻለ፤ ከልክ ባለፈ ትዕግስት ወይም ፍርሃት ዝምታውን ከቀጠለ ወደፊት የሚከፍለው መስዋዕትነት እጅግ አስከፊ እንደሚሆንና አያት ቅድመ አያቶቻችን በአጥንትና በደማቸው ክውስጥና የውጭ ጠላቶች ታድገው ያቁዩልን አገር ልትፈራርስ የማትችልበት ምክንያት እንደሌለ መገንዘብ ያስፈልጋል። ፈረንጆች እንደሚሉት “The cost of inaction is far greater than the cost of action.” ከሌሎች አገሮች ታሪክም እንደምንረዳው ነጻነት በነጻ አይገኝምና (“Freedom is not free.) ።

የፍትህና የነጻነት አምላክ እግዚአብሄር ውድ አገራችንን ኢትዮጵያንና ህዝብዋን እንዲታደግልን እለምናለሁ።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here