spot_img
Saturday, July 13, 2024
Homeነፃ አስተያየትየብልጽግና ወንጌል የክርስቶስ ወይስ የዲያብሎስ ፈተና (ክፍል ሁለት)

የብልጽግና ወንጌል የክርስቶስ ወይስ የዲያብሎስ ፈተና (ክፍል ሁለት)

Prosperity Gospel _ Abiy _ Ethiopia
From Social Media

ክፍል ሁለት: የሁለት ሺ አመት ዋና ዋና ፈተናዎች

ሰይፈ ስላሴ

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ አስተምህሮ ጸንታ በመቆምዋ የሰይጣን ፈተና፣ የፈጣሪ ጥበቃ ተለይቷት አያውቅም።

የፈጣሪ ጥበቃ ስለተደረገላት ነው እንደ ሊቢያ፣ ግብጽ፣ ሶርያ፣ ኢራን፣ ሱዳን የነበሩ ክርስቲያኖች ሲጠፏ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ግን በክርስቶስ ጥበቃ ጸንተው ለኛ የክርስቶስ ቸርነት ያወረሱን። ይህ ማለት ግን ሁሌም መሪዎቿ፣ መምህራን እና አማኞችዋ ልባቸው ከፈጣሪያቸው ጋር ነበር ማለት አይቻልም።

እንደ ዮናስ ኢትዮጵያ ኦርስቶዶክስም የራሱዋን መርከብ ተሳፍራ ስትሸሽሽ ፈጣሪ ነፋሱን እያስነሳ ከእንቅልፏ ይቀስቅሳታል፣ ወደ መንገድ ይመልሳታል። አንዳንዴም ወደ ባህር ይጥላትና በአሳ ነባሪ ያስውጣታል። ከዛ ከአሳ ነባሪ ሆድ ወጥታ የእግዚአብሔርን ቃል እንድትመሰክር ያደርጋታል።

፩: የብልጽግናው ወንጌል የመጀመሪያው የሰይጣን ፈተና አይደለም

ለምሳ ዮዲት ስትነሳ ክርስትና ገነ በዚህ ሀገር ቁጥሩ ጥቂት ነበር። በዛን ዘመን የይሁዳዊ እምነት ጠንካራ በሆነበት ግዜ ዮዲት ጉዲትን ነባሩን መልሳ ለመትከልና ክርስቶስን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት ተነሳች።

 ዮዲት በርካታ ይሁዳውያንን አስነስታ ለ40 ዓመታት ክርስቲያኖችን አሳደደች፣ አቃጠለች፣ ጨፈጨፈች። ጉልበት ባለመመጣጠኑ  ክርስቲያንን አሳዳ ጨፍጭፋ በየጋራና በየ ገዳሙ ተደብቀው ጥቂት ለዘር ተረፏ። ከ40 ዓመታት ጭፍጨፋ ቦሀላ  ለዘር በእግዚአብሔር ያተረፏት የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ሰበኩ። ክርስትናም ተስፋፋ።

ሊቢያ እንደኛ የክርስቲያኖች ሀገር ነበረች። ይሁንና  በሊቢያ በድጋሜ የሚዘራ ዘር ጠፋቶ  መራባት አልቻለም። በቅኝ ግዛት ሊቢያን የገዛችው የካቶሊኳ ፈረንሳይ እንኳን የዘራችው አልበቀለም። ስለዚህ ክርስትና ጠፋ። እኛ ጋ ግን እስከነ ዘር ስላልጠፋ ሲዘንብበት በድጋሜ አፈራ።

፪: ግራኝ

እንደ ዬናስ በድጋሜ መታዘዝ አቆምን። በጎንደር ጥጋብ በዛ። ሰላም ሰለሰፈነ ተመስገን ቀርቶ  ጦር አምጣ ብለው መሬትን ይደበደቡ ነበር ይባላል። ግራኝ መሀመድ ተነሳ። ከትንሽ መንደር ተነስቶ ሀይል አገኘ። ከዛ ክርስቲያኑን አሳደደ። ለ17  አመታት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን አሳደደ፣ ገዳማትን አቃጠለ፣ ክርስቲያኖችን እያየዘ በየመን የባርያ ገበያ ላይ ቸበቸበው። ግን እስከነዘሩ ማጥፋት አልቻለም።

 የግራኝ መሀመድ ሲሞት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ በድጋሜ የክርስቶስ አስተምህሮ ውሀ እንዳገኘ ዘር በድጋሜ በቀለና ሀና ፍሬ ሳያፈራ ሊያግዙን የመጡት ካቶሊኮች ሶስንዮስ አሳምነው ሁላችሁም ሀይማኖት ቀይሩ ካቶሊክ ሁኑ ብለው እንዲያውጅ አደረጉት።

፫፣: ካቶሊክ ግድያ

 ሀይማኖቴን አልቀይርም እንቢ ያለውን አንገቱን በሰይፍ ይቀላ ገባ። ለ8 አመት ሱስንዮስ ቀጠቀጠው። ይሁንና ብዙዎቹ አንገታቸውን ሰጡ እንጂ ሀይማኖታቸውን የቀየሩ ጥቂት ነበሩ። በዚህ ምክንያት አመጽ ተነስቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቶሊክን አሸንፋ እንደገና አበበች። 

ከዛ ደግሞ የኦሮሞ አባገዳዎች ደግሞ ግራኝ ባዳከመው ክርስትና ላይ ዘመቱበት። የደቡብና የምስራቅ ኦርቶዶክስ የወላይታው፣ የጋሞው፣ የሀድያ፣ ዳዋሮ ክርስቲያኖች ተቆርጠው ቅፕሩ ተቋረጡ። ብዙዎቹ ክርስትናን ረስተው በድጋሜ ኦሮሞው ክርስቶስን ከተቀበል ቦሀላ ግንቡ ፈርሶ ክርስትና እስከ ወደ ደቡብ ተመልሶ ገባ።   ደድጋሜ ክርስትና በጋሞ፣ ወላይታ፣ በዶርዜ፣ በሲዳማ፣ በሀዲያ፣ በጉራጌ፣ በደዋርዎ፣ በይፋት እና በኦሮምኛ ተናጋሪ መሀበረሰብ ውስጥ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፍሬ አፈራ።

፬: ሁለተኛው ዙር የቫቲካን ካቶሊክ ጥቃት

የመጀመሪያው የካቶሊክ ሙከራ በፓርቹጋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቫቲካንና በሞሶሎኒ የተመራ ነበር። በጸባይ እንቢ ካሉ በጉልበት እናሳካዋለን ብለው 600 ሺ ባለ ጥቁር ሸሚዝ የፋሺስት ሰራዊት ዘመተ። የቫቲካን ካርዲናሎች (ጳጳሶች) ታንክና የመርዝ ጋዝ የሚረጨውን አይሮፕላን ባርከፍ ቅዱስ ጦርነት ነው አሉ። 

ለዚህ ቅዱስ ጦርነት የካቶሊክ አማኞች በሙሉ የጋብቻ ቀለበታቸውን ለጦርነቱ እንዲያበረክቱ ቫቲካን ጠይቃ የቅዱሱን ጦርነት አወጀች።ስንት ክርስቶስን የማያውቅ ሀገር እያለ፣ እንደ ሊቢያንና ሱማልያን በቅኝ እምትገዛው ሮም አሳምናም ሆነ አስገድዳ አንድ የሊቢያ ወይንም የሱማሌ ዜጋ ስለ ክርስቶስ አላሳመነችም። ይሁንና ከጅንደረባው ክምር ከሮም በፊት ክርስቶስን በምታስተምረው ክርስቲያን ላይ የቅዱስ ጦርነት አወጀች።

የክርስቶስ ቃል የሚዘምሩትን የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በጉልበት ካቶሊክ ማድረግ ያለበለዚያም ማጥፋት ወሰና ይህ ቅዱስን ጦርነት ነውና እባካችሁ የጋብቻ ወርቁንና አልማዙን ቀለበት ለሞሶሎኒ ስጡና በምትኩ ለቃልኪዳናችሁ ማረጋገጫ  የብረት ቀለበት ልስጣችሁ ብላ አሳምና  የኢትዮጵያ ክርስቲያን ለማጥፋት የቅዱስ ጦርነቱን ተቀላቀለች። 

 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖችን እንደ ትንኝ በመርዝ ጋዝ ተረገፈ። ከብቱ፣ አእዋፏቱና፣ አራዊቱ ሳይቀር ከሰዉ እኩል ረገፏ።

አቡነ ጴጥሮስንና በፒያሳ አቡነ ሚካኤልን ደግሞ በጎሬ አደባባይ እንደ ወንጀለኛ ተረሸኑ። “ስጋን እንጂ ነፍስን የማይገለውን ግራዚያኒን ሳይፈሩ ለጣልያን ምድሪቷም ሰውም አትገዛ ብለው አውግዘው ሞታቸውን በጸጋ ተቀበሉ።

አቡነ ጴጥሮስን ረሽኖ ግራዚያኒ አቡነ አብርሃም የፋሺስት ጳጳስ አድርጎ ሾመ፣ ከዛ ዘጠኝ ጳጳሳትን አሹሞ ግራዚያኒ ችግር ተወገደ አለ። ለጣልያን ተገዙ።  ጣልያን ያቃጠላቻቸውን እነ ደብረ ሊባኖስን መልሼ እገነባለሁ ብለው አሽቃበጡ።  ጦርነት ይቁም ሰላም ይስፈን አሉ። ይሁንና የኢትዮጵያ መእመናን አናውቃችሁም አሉዋቸው። ጦርነቱም ቀጠለ።  የአሌክሳንድርያም ጳጳሳት አውግዘው የግራዚያኒን ጳጳሶች አገለሉ። መእመናኑና እውነተኛ ቄሶች ያለ ጳጳስ እና ያለ ሲኖዶስ እምነታቸውን ቀጠሉ።

በመጨረሻ በእግዚአብሔር ሀይል እጣልያን እዚህ ሀገር ብቻ ሳይሆን ጣልያን ሮምም ላይ ድል ተመታች።  ሞሶሎኒም እግሬ አውጪኝ ሲል ተይዞ እስከነ ውሽማው እግሩ ወደላይ ጭንቅላቱ ወደታች ተደርጎ በአደባባይ ተሰቀ።

፭: ሌኒንና የእግዚአብሔር የለም ትውልድ

ከዛ ደግሞ በፈረንጅ ሰይጣን የተለከፏ ወታደሮችና ኮሚኒስቶች እግዚአብሔር የለም ብለው ቤተ ክርስቲያንዋን ወርሰው አደህይተው ጳጳሷን አንቀው ገለው ክርስቶስን ከዚህ ሀገር አባረው የሌኒንን ጣኦት በአደባባይ ሰቅለው በሱ እመኑ፣ በሱ ፎክሩ፣ በሱ ስም አውግዙ አሉ። 

እነ መንግስቱ ኃይለማርያም የኃይለማርያም ልጅ ሆነው ተወልደው እግዚአብሔር የለም ብሎ  በመሀይም አይምሮዋቸው ታበዩ። ይሁንና  ደርግ ውስጥ የተሰበሰቡትና ወታደሩን በእግዚአብሔር የለም ብለው ያሳመኑት እነ ሀይሌ ፊዳ፣ ሰናይ ልኬ፣ ባሮ ቱምሳ፣ ብርሀነመስቀል ረዳ ወዘተ  በመንግስቱ ኃይለማርያም ተረፈረፏ። አብዮት ልጅዋን ትበላለች ብለው ተራማጅ ነኝ ነኝ ባዮች ተጫረሱ። ይህ መቅሰፍት ካልተባለ ምን ይባላል?

 ከዛ የጥጋብ ማማ ሆነው አልቃቸውን ኮ/ል መንግስቱን ተማምነው እግዜር የለም ብለው በማርክስ፣ በኤንግልስ እና በሌኒን ስም ሰራዊት ያዘመቱት በቁምጣ በታጠቁ እረኞች እየተነዱ አዲስ አበባ ገቡ። የነሱ ማርክስ፣ ኤንግልስንና ሌኒን በነጭ ፈረስ ከገሀነም ወጥተው አልደረሱላቸውም።

እንደዛ ትኩር ብሎ ህዝብ ሊያቸው የሚፈራቸው ፓለቲከኞች፣ ካድሬዎች፣ ጀነራሎች ሽጉጣቸውን እንኳን አልጠጡም። ይልቁንም  በሬዲዮ ኑ ሲባሉ እሺ ጌታዬ እያሉ ለእረኞች እጃቸውን ሰጡ።

ከደርግና ሰራዊት ውስጥ ሽጉጣቸውን ጠርተው የሞቱት እነ ጄኔራል አለማየሁና ነፍሰ ገዳይ ቢሆንም አሊ ሙሳ ታሪክ ከተማራኪዎቹ ከፍ አድርጎ ያያቸዋል። ነገም እነ ብርሀኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰ፣ ይልማ መርዳሳ፣ ዳንኤል ክብረት ሽጉጣቸውን የሚጠጡ ይሆን?

ያ ሁሉ ኮሚኒስት ነኝ ብሎ ካኪ ለብሶ ህዝብን ሲያሰግድ የነበረው  ቀበቶዋቸውን ፈትቶ፣ ጫማቸውን አውልቆ እጅ ሰጥተው ባለ ቁምጣዎቹ በዱላ እየተዠለጡ እንደ ከብት በታጠቅ፣ በሆለታ፣ በሀረር፣ በጦላይ፣ በደብረዘይት ካምፕ አሰሩዋቸው። ተዋርደው አየናቸው። አንዳንዶቹ ክርስቶስ እድል የሰጣቸው ከጥጋባቸው ወርደው ተንበርክከው ንስሀ ገቡ።

፮: የህወሓት ሰማይ መርገጥ

ደርግን ተከትለው የመጡት ኢ-አማንያንን እነ ስብሀት ነጋ ኦርቶዶክስን ሰብረነዋል፣ ገዳማቱን ወደ ስኳር ልማት እቀይራለሁ ብለው መናንያንን ሲገርፍ የነበሩት እነ አባይ ጸሀዬ፣ የህወሓትን ተንኮል ሲቀምም የነበረው አስመላሽም ፈጣሪ የሰጠውን ሁለተኛ እድል ሳይጠቀምበት ተገደለ።

ከሞት የተረፏትም እስከአሁን ተንበርክከው ንስሀ ገብተው እንደ እንደ 40ቀን ህጻን መንጻት ሱችሉ አሁንም አደብ አልገዙም። ክርስቶስን ሊያገለግል የተጠሩትን ጳጳሳት አስክድተው የደብረጽዮን ሲኖድስ አቋቁመው በክርስቶስን በህወሓት ተኩ። 

 ለክርስቶስ ሳይሆን እግዚአብሄር የለም ብሎ የትግራይን ህዝብ ከክርስቶስ ለነጠለውን ደብረጽዮንን ካባ አልብሰው በአክሱም ጽዮን ፊት አቁመው ዘመሩለት አመለኩት። ታድያ ብዙም ሳንቆይ እነ ደብረጽዮን እንደ መንግስቱ ካድሬዌች አመድ ለብስው አለምን ምግብካልሰጠን ልናልቅ ነው ሲሉ ይሰማሉ

፯: የብልጽግና ውንጌልና የዲያብሎስ ስገድልኝና ሀብት ልስጥህ ፈተና

ይህ በክፍል አንድ በዝርዝር ቀርቧል። ይሁንና የኦርቶዶክስ እና የብልጽግና ወንጌል አአባቶች ስለ የብልጽግና ወንጌል ገና አልሰሙም፣ አላነበቡም። የኦርቶዶክሶቹ አሁንም በአርዮስ ትምህርት ላይ ናቸው። ፕሮቴስታንት ደግሞ አሁንም በማርቲን ሉተር በካቶሊክ አስተምህሮ ላይ በነበረው ተቃውሞ ላይ እንደቆመ ነው። ሳይኮሎጂስቶች የፈጠሩት የስነልቦና ማነቃቂያ ትምህርት ቀድሞ ሄዶ የሰው ልጅ ለክርስቶስ ሳይሆን ለገንዘብ ስገዱ እያለ ነው። ስለዚህ በጎቹ ከፍየሎቹ እራሳቸውን መለየት አለባቸው። የኦርቶዶክስ ወጣቶች ገብቷቸው ጀምረዋል ጳጳሳቱ ግን አብይ ክርስቲያን ነው ብለው አስበው ብድግ ይሉለታል። ትህትናው ተገቢ ክርስትና ባህርይ ነው። እሱ ግን በእግር ቁጭ በሉ እንኳን አይላቸውም። ብርሀንና ጨለማ እዚህ ጋ ነው የተቀላቀለው።

መደምደሚያ

እነ አብይ ክርስትና የድህነት ስብከት ነው። ወንጌልን አትስሙ ይልቁንም ሀብትን እሹ እያሉ በንዋይ ፍቅር እያማለሉ ነዚህ ሀገር እስልምናን ክርስቲያን ተከታያቸው አድርገው ወደ ገሀነም እየወሰዱ ነው። የሚገርመው ደግሞ መስቀል ባንገታቸው ላይ ያሰሩት እነ አበባው ሳይቀሩ መስቀሉን ትተው መሬት ሲሰጣቸው ክርስቶስን በብልጽግና ቀይረው የክርስቲያን ደም እያፈሰሱ ነው። የክርስቲያን ደም ለ7ተኛ ግዜ እንደ ጎርፍ እዬፈሰሰ ነው። ይሁንና ይሄም የደም መገበር ሀይማኖት ተሳክቶለት ክርስቶስን ከኢትዮጵያ አስወጥቶ የዲያብሎስ የሀብት ፍቅር አይነግስባትም።

ቤተክርስቲያን ብዙ ግዜ ቤተ ቤትዋ በላይዋ ላይ ፈርሷል፣ ተቀብራ ቆይታ  እንደ ክርስቶስ የተጫነባትን ድንጋይ ፈንቅላ ትነሳለች። አሁን ሁሉም አይኑ እየተከፈተ ነው። እንደ ዮናስ ከተኛንበት በግድ ተቀስቅሰን እየነቃን ነው።

በጎቹ ከተኩላዎቹ እየተለዩ ነው። በጎቹን እያረዱ የበሉት እረኞች ወፍረው ሰብተው መንቀሳቀስ የማይችሉ እረኞች የምናይበትን መንፈሳዊ አይን ክርስቶስ ከፍቶልናል። አድርባዩ፣ ጎሰኛው፣ ዘረኛው፣ ሌባው፣  የጥላቻ ሰባኪ ጳጳሱ እየተንጓለ ወደላይ እየወጣ እያሳየን ነው። 

ክርስቶስ  ልጆቹን ከዮዲት፣ ከግራኝ፣ ከካቶሊክ፣ ከአባገዳ ወረራ፣ ከግራዚያኒ ጭፍጨፋ፣ ከእግዜር የለም ከአብዮተኞች፣ ከአባይ ጸሀዬ ግርፊያ መድኃኒተ አለም በደሙ የመሰረታትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቋል አሳልፎናል። አሁንም ኑ ለዳቢሎስ እንስገድናብእንበልጽግ ከሚሉን ይጠብቀናል።   ኑ አብረን ለብልጽግና ለንዋይ እንገብር፣ ብር በሞባዬላችሁ ይገባል የሚሉትን ሀሰተኛ ነቢያት በቴሌቭዥን ሌብነታቸውን እያሳየ እያዋረዳቸው ነው። 

እኔ የፕሮቴስታንት ነብይ ነኝ፣  ክርስቶስ ያዋራኛል የሚል አንድ ክርስቶስን የማያውቀውን  ሰው በዚህ ሀገር፣ በሱዳን፣ በሱማሌ አሳምነው ቀይረው አያውቁም። ሲሞክሩም አይታዩም።    ያው በክርስቶስ ጥምቀት የተወለደውን፣ በክርስቶስ ስጋወወደሙ የቆመውን በማስካድ ጥምቀትን እንዲተው ቁርባንን እንዲጥል  ማድረግ ነው። የተኩላ ንጥቂያ ነው።

ውሸት ግድያ ሌብነት ጉቦ ማጭበርበር በአጭር ቀን ውስጥ የብልጵግና መገለጫ ሆነ። አዛውንቶች ” እግዜር ሲቆጣ ልምድ አይቆርጥም፣ እንዲያው ያደርጋል ነገር እንዳይጥም ይላሉ።

የሚገርመው የሰይጣን ስራ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ሀይል ከዛፍና ከኩሬ እምነት ያላቀቀቻቸውን ህዝቦች ዛሬ ተመልሰው ዛፍና ኩሬን እንዲያመልኩ። በእልህ እውን ጉራቻ ተመልሶ መጣ።  

ክርስቶስ ግን ቤቱን እያጸዳ ነው። ልክ ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት ሲሸሽ ንፋስ ሲያስነሳበት በመርከብ ላይ ያሉት መጀመሪያ ለጣኦቶቻቸው ጸለዩ። የነሱ ጣኦቶች መአበልን ማቆም እንደማይችሉ አሳያቸው። ከዛ ቁሳቁሳቸውን ከመርከብ ላይ አውጥተው ጣሉ። አሁንም መአበሉ አልቆመም። በመጨረሻ ለጥ ወዳለው ዮናስ መጡ። ቀሰቀሱትም። እሱም ከእግዚአብሔር ፊት ማምለጥ እንደማይችል ገባውና እኔን አውጥታችሁ ጣሉኝ አለ። ይህ ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መርከብ ላይ እየሆነ ነው። የንዋይ ፍቅራችንን፣ የግል ሞገስና ጥቅማችንን፣ የሰቡና የወፈሩ እስረኞችን እና  ያግበሰበስነውን የጎሳ፣ የጥቅም፣ የትእቢት ኮተት አውጥተን እስከ ምንጥል እየጠበቅን ነው።  በቤተ መቅደስ ጉቦ እየተቀበሉ የቤት ቁልፍ የሚሸጡ፣ ጉቦ በልተው ሹመት የሚሰጡ፣ ከነፍሰ ገዳዮች ሙገሳን የሚሹትን ከመርከቡ የሚጣልበት ቀን ደርሷል።

 የእግዚአብሔር ትእዛዝ ሸሽተው የተኙትን አባቶችና ምእመን ነፋሱን አስነስቶ እያናወጠ ነውና ከስጋዊ ፍላጎታቸው ነቅተን  ወደ ባህሩ ጣሉኝ የሚሉበት ቀን ቀርቧል። ስለዚህ ክርስቲያኖች እቺን ክርስቶስ በደሙ ያቆማትን ከከበባት ወራሪና እጥፊ ለሁለት ሺ ዘመን ግንብ ሆኖ የጠበቃትን ቤተ ክርስቲያን አያጠፋትም። 

አሁን እያደሳት እንደ ዮናስ መርከብ ላይ ያለውን ፍቅረ ንዋይን፣ አባቴ ውዳሴ ከንቱ መባልን፣ እግዚአብሔር የለም እያልን መታበያችን፣ ዝንጅሮ አባታችን የምንለውን  እስከ ምንተው ንፋሱ አይቆምም።

በየ አውደ ምህረቱ ማስጨብጨብን ትተን የተበተኑ በጎቻችንን ለመሰብሰብ የሚነሱ እስረኞችን ያስነሳል።  ለሀዋርያቱ እንደታዘዙት በነጻ የተሰጠንን ጸጋ በነጻ የሚሰጡ፣ ወርቅ፣ ብር፣ አበል ሳይሉ በጎቹን ፍለጋ የሚወጡ እረኞች እየተነሱ ነው።  

የእውነተኛ እረኞች ግዜ ይመጣል።  የተጠቁትን ማጽናናትት ። ዝቅ ብለን እግር የሚያጥቡ ትሁቶች፣ በወንበዴዎች የቆስያለውን አይተው ወይንና ዘይት አፍሰን ቁስሉን የሚያስሩና  ይፈጠራሉ።  

 መአበሉ ይሄንን እስከምናደርግ አይቆምም። ሊቀ ጳጳስ ተዋርዶ በአንድ በኩታራ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፈትሹት በደንብ በርብሩት የሚባልበት ግዜ ሆንዋል።  

 አንድ የበሻሻ ወጠጤ አያቱ የሚሆኑ አባቶች ብድግ ብለው ቆመው ሲቀበሉት “በእግዜር ቁጭ የማያስብል ትህትና የሌለው እረኛ መሆኑን በቴሌቭዥን እያሳየን ነው። 

ክርስቶስ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ የተሸፋፈነበትን ምጋረጃ ቀዶ የተደበቁትን ተኩላዎች እያሳየን ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ቤቱን ሊያጸዳ ነው ንፋሱን ያስነስቷል። ስለዚህ በዚህ ኮተታችንን መጣል ግድ ይላል።  ለአአብይም የአለምን ሀብት ሁሉ ብትሰጠን ለዳቢሎስ እንስገድለት ማለት ያለብን። ስለዚህ ስጋን እንጂ ነፍን የማይገለውን አንፈራም።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

2 COMMENTS

  1. ቁም ነገር አገኝበት ብዬ ክፍል 1 እና ክፍል 2ን አንኳኳሁ። “እንደ ዮናስ ኢትዮጵያ ኦርስቶዶክስም የራሱዋን መርከብ ተሳፍራ ስትሸሽሽ ፈጣሪ ነፋሱን እያስነሳ ከእንቅልፏ ይቀስቅሳታል፣ ወደ መንገድ ይመልሳታል” የሚል ተረት ተረት አገኘሁበት። እርግጥ ነው፣ የዐቢዮች ብልጽግና ከንቱ ልፈፋ ነው፤ ያንተ ደግሞ ጭራሽ ባሰ። እውር እውርን ቢመራ ሁለቱም ተያይዘው ከገደል ነው።

    • Alem, it is written that for those who doesn’t believe the word of the Cross is foolishness but for those of us who believe it is the power of the almighty God. I agree with the writer because it is based on the wholly Bible (the word of God).

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here