spot_img
Friday, July 19, 2024
Homeነፃ አስተያየትበአብይ አህመድ ትእዛዝ የሚፈርሱ የአዲስ አበባ ቅርሶች ወይንስ “ማንም ያቦካው ጭቃ”  ?

በአብይ አህመድ ትእዛዝ የሚፈርሱ የአዲስ አበባ ቅርሶች ወይንስ “ማንም ያቦካው ጭቃ”  ?

Abiy Ahmed _ chika
ፎቶ ግራፉ ከ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ቪዲዮ ክሊፕ የትወሰደ ነው

ነዓምን ዘለቀ

መለስ ዘናዊ  ይሻል ነበር እንዴ? የሚል ግዜ ይመጣል ብዬ በህልሜም አስቤ አላውቅም ነበር። የሚከበር ጠላትም እለ፣ የሚናቅም እንድሁ፣ ፓለቲካውን ብቻ ሳይሆን ስብእናውን የምትጠየፈው፣ የሚናቅ።  ለቀድሞው ጠ/ሚ ከነበረኝ መጸየፍ የተነሳ ደሜ ሳይፈላ 5 ደቂቃ ማየት እልችልም ነበር። የዚህ ነውረኛ ፣ አጭበርባሪ ብሶ ቁጭ እለ። የአብይ አህመድ ብልግና፣ ትዕቢኢት፣ዕብሪት፣ ለህዝብ ያለውን ንቀት ተደጋጋሚ ውሽትና ማጭበርበር በየግዜው ከማየትና ከመስማት በላይ የሚዘገንን ምንም ነገር የለም። የህዝብን የማሰብ ፣ የማስታወስ አቅም በየጊዜው ይሰድባል። የሌለውን አለ፣ ያልሆነውን ሆነ፣ ትላንት የተናገረውን በሳምንቱ መገልበጥ። በእሱ የበሻሻ አራዳ ጭንቅላት ያለው እሳቤ ግልጽ ነው። በአብይ እህመድ የቅዠት አለም ህዝብ “ሾርት ሚሞሪያም ነው” ። እሱ ደግሞ ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን አድራጊ፣ 7ኛ ንጉስ ነው።

በአለማችን የከተማ ልማት አስተሳሰብና ማእቀፍ/ፓራዳም/ፍሬምወርክ ፣ ዘላቂነት፣ ጽኑነት ፣ አካታችት ፣  ፍታዊነት/Environmental sustainability/Climate Resilience/Socially  inclusive and  just በሚሉ ዋና ዋና ማገሮች የሚመራ እየሆነ ነው፣ ይህም  በበርካታ ሀገሮች ገዢ አስተሳሰብና አሰራር እየሆነ ይገኛል ። በ 2050 የአለማችን ህዝብ 70% የከተማ ነዎሪዎች እንደሚሆኑ የበርካታ ጥናቶች ትንበያ ያሳያል። ስለሆነውም ልማት የከተማውን ኢንፍራስታክቸሮች ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ጽኑ፣ ዘላቂ/እንዲሆኑ ፣ ዜጎች ፣ የከተማ ነዋሪዎች ማህበራዊና አካታችነት፣ ፍትሃዊነት፣ ኢኮኖሚ ጽናትና ዘላቂነት/ሶሻል ኢኮኖሚክ ስስተኔብሊቲ/ሬሲሊያንስ እንዲኖራቸው ማድረግን ታሳቢ ያደረገ የልማት አስተሳሰብ ማእቀፍ/ፍሬምወርክ ነው።  በመሰረቱ  ልማት መዳረሻውም ፣ መነሻውም ሰው ነው። የልማት ግብ የሰዎች፣ የማህበረቦች፣ የዚጎች ልማት ነው፣ የኮንክሪት ጫካ ወይንም  ኮንክሪት ጃንግል ግንባታ አይደለም። አብይ አህመድ እንደሚያደርግው የብልጭልጭ ፎቆችና ግንባታዎች መደርደር አይደለም።  አማራታ ሰን፣ ማርታ ናስባም ፣ ሌሎችም ታላላቅ የኢኮኖሚ ልማት ፈልሳፎችና ሃሳቢዎች እንዳስቀመጡት፣ ልማት መድረሻውም ፣ መነሻውም የሰው ልጅ ነው። የዜጎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ አቅም ማጠናከር ፣ ማዳበር ነው። በእርግጥም ለህዝብ ለዜጎች የሚጨነቅና ፣ በእኩልነትም የምያይ መንግስት ካለ አንድ ሃገር ውስጥ፣ ዋነኛ የመንግስት ተግባር ይህን መተግበር ነው። ሰው ተኮር፣ ዜጋ ተኮር ልማት/human centered development and enhancement of human capabilities.

የእነ እብይ አህመድና የአደነች አቤቤ አገዛዝ ከዚህ በተቃራኒው ፣ ማፈናቀል፣ ማውደም፣ ዜጎችን ለማህበራዊ ምስቅልቅ፣ ትርምስ፣ መከራና እንግልት መዳረግ ዋናው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የአዲስ አባባ ህዝብ የሚገኝባቸው አስከፊ ገጽታዎች ሆነዋል። ለልማት ሳይሆን ለፓለቲካ አላማ የሚፈጸም፣ ግፍና በደል።  የጥቅም አጋሮቻቸውን በብዙሃን ኪሳራ ለማደለብ  የሚፈጸም በደል፣ ኢፍትሃዊነት፣ ጋጠ ወጥነት፣ እብሪትና ትብኢት!! 

ፒያሳንም ሆነ ልዩ ልዩ የአዲስ አበባን አካባቢዎች  ለማፈራረስ፡  ለማውደም፡ ነባር ነዋሪዎችንም ለማፈናቀል  የተሄደበት ርቀት  ምንም የከተማ ልማት ጥናት፣ ፍታዊነት፣ አካታችነትም ፣ ከተሞች ለማዘመን፣ ለማስዋብ ማእክል መደረግ  ያለባቸው ዋና ዋና አምዶች  ጋር ምንም የማይገናኝ መሆኑ ግልጽ ነው።   ከዜጎች ፣ ከነዋሪዎች ጋር ምክክር ፣ ውይይት አልተደረገበትም። በዘፈቀደ፣ በአብይ አህመድና የአዲስ አበባን ህዝብ እንደ ባእድ የሚያዩ፣ ከከተማዋ ጋር ምንም ቁርኝት የሊላቸው ባለግዜዎች የተወሰነ ስለመሆኑ  ከሰሞኑ የወጡ ልዩ ልዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ’’። የጋዜጠኛ  ኤልያስ መሰረትና ሌሎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በየግዜው በልማት ስም የተፈጸሙ የማፈናቀሎች፣ ውድመቶች፣ የተጻፉና የተነገሩ   “የሆረር ታሪኮች” ያረጋግጣሉ።

በአዲስ አበባ ከቅርብ አመታት በፊት የተጀመረውን ነዋሪውን ማፈናቀል፣ ቅርሶችን ማፍረስ ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ለማሳየት በያዝነው ሳምንት የተጠቀመበትን ቃል እስቲ እንመዝነው “ ማንም ያቦካው ጭቃ ታሪካዊ ቅርስ አይደለም” በማለት ሊያሳምን ነው የሞከረው። በእርግጥ እሱ እንደሚለው በኢፍትሃዊነትናጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ  የፈረሱት ጭቃ ቤቶች ብቻ ናቸው? ለአዲስ አበባ ቅርስ መሆናቸው የታወቀ፣ የተመዘገቡ ታሪካዊ እሴት ያላቸው “ቅርስ” ስለመሆናቸው የታተመባቸው ቤቶች እንዲፈርሱ አልተደረገም? ሃቁ ግልጽ ነው። ማስረጃዎች አሉ። አብይ አህመድ በሰጠው ትእዛዝ በርክታ በቅርስነት የተመዘገቡ ግንባታዎች እንዲፈርሱ ተደርገዋል። ስውየው ግን ለህዝብ ያለው ንቀት፣ ማጭበርበርና የውሸት ክምር መደርደር ለከት የለውም።

እንደሚታወቀው ታሪካዊ ቅርሶች መመዝገብ፣ ለህዝብም፣ ለሀገርም፣ ለከተሞችም ያላቸውን ፋይዳ የሚመርመር የራሱ እውቀት መመዘኛ አላቸው። የራሱ ማእቀፍ፣ የራሱ አሰራር አለው። በሰለጠነው አለም ሀገራዊ ቅርሶች አሉ፣ የክፍለ ሀገር ቅርሶች አሉ፣ የከተማ ቅርሶችም አሉ፣ ለምሳሌ በዚህ በአሜካን ሀገር እኔ በምኖርበት በቨርጂኒያ ግዛት በትናንሽ ከተሞች በርክታ ታሪካዊ ቅርሶች ይገኛሉ ፡ ከአሜሪካ ሪቮሉሽን እስከ ሲቪል ዋር መታሰቢያ የሆኑ ቅርሶች፡ ክእነዚህ እንዱ  ኦልድ ታውን/Old Town በሚባል አካባቢ የዛሬ 200 ፣ 100 አመት የተገነቡ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ፋይዳና እሴት የሚያወሱ ቅርሶች ግንባታዎች በቅርስነት ተመዝግበውእንክብካቤ እየተደረገላቸው ተጠብቀው ቆይተዋል። እንዳንዶቹም ለቱሪዝምና ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ውለዋል።

 እነዚህ ቅርሶች ሀገራዊ እይደሉም ከአሚሪካ ፣ ከእንግሊዝ፣ ከቻይና ሀገራዊ ቅርሶች ጋር እይመደቡም፣። በተመሳሳይም በአዲስ አባባ የሚገኙ በቅርስነት የተመደቡ፣ ቅርስ ስለመሆናቸው የተመዘገቡ ቅርሶች ለአዲስ አበባ ከተማ ፣ ለነዋሪዎቿ የጋራ ማንነት፣ ለጋራ ትውስታቸው (collective memory)  የበስተኋላ ታሪካዊ ኩነቶች ፋይዳ አላቸው፣ የከተማው ቅርስ ታሪካዊ ፋይዳና እሴታቸው የከተማዋ ነው። ከቅድመ እያት፣ እያት፣ አባት እናት ጀሞር በከተማዋ የኖሩ ዜጎች የጋራ እሴቶች ናቸው። የግድ ከአክሱም ከላሊበላ ፣ ከፋሲለደስ ቤተ መንግስት፡ ከሌሎች ሀገራዊ ቅርሶች  ጋር መመደብና መነጻጸር እይጠበቅባቸውም። ካለፈው አመት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ  እየፈረሱ የሚገኙ ግንባታዎች፣ “የከተማ ቅርስ” ስለመሆናቸውን ሞያዊ ብይን የተሰጠባቸው ናቸው፣ በእያንዳንዱ ህገወጥ በሆነ መንገድ በፈረስ ህንፃ ላይ  “ቅርስ” ስለመሆኑ በግልፅ ታትሞበታል። እነዚህ ቅርሶች ጭምር እያፈረሰ የሚገኘው ይታያችሁ የአብይ አህመድ፣ የሽመልስ አብዲሳ፣ የአዳነች አቤቤ አገዛዝ እይኑን በጨው ታጥቦ ነው  “ማንም ያቦካውን ጭቃ” በሚል ወንጀሉን፣ ጋጠ ወጥነቱን፣ ህገ ወጥነቱን፣ ኢፍትሃዊነቱን፣ እብሪቱንና ማን እለብኝነቱን ለመሸፋፈን ተራ ወሬ በህዝብ ላይ በየቀኑ የሚወረውረው! ለዚህ ነው ሰውየው ምንም ለከት የሌላው ነውረኝነት፡ አጭበርባሪነትና ከሃዲነት ለከት የለውም የምንለውም።

በእነዚህ ደንቆሮዎች እሳቤ ደግሞ ይሄ ፓለቲካ መሆኑ ነው። መርህና እሴት የሚባል ነገር   የለም። የምትፈልገውን ለማሳካት ምንም ከማንም፣ በየትም እድርሀ ማግኘት ነው ግቡ፣ ስልቱም የአብይ እህመድ ሌላው ጥንድ/ ክፉ ፓሊስ ሆኖ በመልካም ፓሊስ ክፉ ፓሊስ/Good Cop Bad Cop ጨዋታ የክፉ ፓሊስ ሚና የሚጫወተው የአብይ አህመድ ገዳይ አስገዳይ ድብቅ መንግስት/ኮሬ ነጌኛ ሊቀ መንበር ሽመስል አብዲሳ እንደነገረን “ኮንቪንስና ኮንፉስ” በማድረግ ነው። የማይገናኘውን በማገኛነት ፣ የማይወዳደረውን በማወዳደር፣ እዚህ እንድ ነገር፣ እዚያ ተቃራኒውን በመናገር ግቡን ማሳካት ኢላማው ያደረገ ፣ ያፈጀ ፣ ያረጀ ግርድፍ ያማክያቪላዊ ስልት በመጠቀም እክይ አላማን ማሳካት። የምስራቅ አፍሪካ የኦሮሞ ኤምፓየር ቅዠት አካል። የሚተቹትን፣ ሃቁን የሚያገሩንት በመዝለፍና በማስጨብጨብ በድንጋይ ማምረቻ የተመረቱ የብልጽግና ግኡዛን ባለስልጣኖች፣ እንዲሁም ውዳቂ ካድሬዎቻቸውን በየመድረኩ  ማስገልፈጥ፣ ማስጨብጨብ፣ ለምዶበታል። ስለዚህም ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ብሎም የአለም ህዝብ ሁሉ ለማታለል፣ ለማጭበርበር፣ ከነባሪዊው ሁኔታና ከሃቁ በተቃራኒው ማሳመን የሚችል ይመስለዋል።

አብይ አህመድ  በህዝብ ላይ የሚፈጽማቸው ወንጀሎቹን፣ መክሸፉን፣ ውሸቱን፣ ኢ-ፍታዊነቱን ፣ “ትክክል” መሆኖቻውን ለማሳመን፣ ምንም ከማለት እንደማይመለስ በተደጋጋሚ አሳይቷል። ሰውየው ነጩን ጥቁር፣ በሬ ወለደ የመቀባጠር፣ ነጩን ጥቁር የሚልና የማይገናኙ፣ ከነበራዊ ሁኔታው ያፈነገጡና ሃቅ ያልሆኑ ነገሮች አይኑን በጨው ታጥቦ ከመዋሸት ያማይመልስ ለከት የለሽ ወራዳ ነው። እስኪ ወደ ኋላ ሄደን ወደ ስልጣን ሲመጥና በቀጠሉት ሁለት ፣ ሶስት አመታታ ሲደጋግም የነበረውን እናስታውስ “ህዝብን አናፈናቅልም’ “ሳናጣራ አናስርም” “መግደል መሸነፍ ነው”፣ እረ ምኑ ቅጡ ምን ያላላው ፡ ቃል ያልገባው ፡ የህዝብን ልብና ድጋፍ ያልገዛበት ማስመስያዎች ነበሩ?። ስልጣኑን በደምብ ኮንሶሊዴት እስኪያደርግ የተናገረውን መለስ ብሎ ላየ፣ ያ የነበረ ትህትና፣ ያ ለህዝብ የተገባ ተስፋ፣ ነጻነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት እነደ ጤዛ ተኖ ዛሬ ላይ  ስናገኝ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እየተሰማው ያለው ስሜት ግልጽ ነው። በእርግጥም ንዴት፣ ሃዘን፣ ብስጭት የተቀላቀለበት።

ከታሪክ የማይማሩ ፣ ታሪክን በመድገም መቀመቅ ይወራዳሉ ይለናል፣ ፈላስፋ ጆርጅ ሳንታያና። የአብይ አህመድ ብልጽግና የታሪክ ትቢያ ከመሆን የሚያድነው ምንም ነገር የለም እንድን አገዛዝ የሚያድነው ፍትሃዊነቱ፣የመርህ አካል መሆኑና ህዝባዊነቱ ብቻ ነው። በምድረ ኢትዮጵያ ፣ የህዝብ እንባና ደም እንደ ጎርፍ ይወርዳል። የንጹሃን ነብስ በየቤተ አምልኮ፣ በየመንገዱ ፣ በገበሬ ማሳ በአብይ አህመድ አራጆችናነብስ ባላዎች ይቀጠፋል። ይባስ ብሎ በኑሮ ውድነት ፣ በባለጊዜዎች ጋጠ ወጥነት፣ ኢፍትሃዊነት ቁስ ስቅሉን የሚያየውም፣ ጀርባው የጎበጠውን የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የህብረተስብ ክፍል በማፈናቀል ቁም ስቅሉን አበሳውን ያባብሳል። ጣሩን ያራዝማል።

ይህ ህዝብ ተገፍቶ ተገፍቶ   የገድል አፋፍ ላይ ደርሷል። በመጨረሻም ገድል የሚገባው ግን ህዝብ ሳይሆን እብሪተኛና ግፈኛ አገዛዞች መሆናቸውን ታሪክ አሁን አሁንም ደጋግሞ አሳይቷል። የእኛም ሀገር የቅርብ ግዜ ታሪክ የሚያረጋግጠው ይህንኑ ሃቅ ነው። እነ እብይ አህመድ ይህ የታሪክና የህብረተሰብ ጉዞ ሎጊክ እይገባቸውም። አብይ እህመድ፣ “ማንም እይችለንም፣ አቅማችን ተመጣጣኝ አይደለም፣ እኛን መነቅነቅ እይቻልም ወዘተ ” በማለት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በየመድረኩ የሚደነፋው የድንቁርናው ሌላው ምልከት ባዶ የድንፋታን ዲስኩር ለራሱ ሰጋጆችና ለምን፣ እንዴት፣ ብለው ለማይጠይቁና ማገናዘብ ለማይችሉ፣ ትላንትን ማየት የማይደፍሩ፣ ስለዚህም ካለፈው ጥፋትና ክፋት የማይማሩ ባለስልጣኖችንና ካድሬዎችን ለማረጋጋት ይሆን እንደሆነ ነው እንጂ፣ ከነበራዊ እውነታው፣ ሀገሪቷ በእሱ ምክነያት የገባችበትን ሁልተናዊ ቀውስና ዘርፈ ብዙ ቅራኔዎች ጋር የሚጣጣም፣ እብሮ የሚሄድ ሃቅ እይደለም። 

እንደ ቀደሙ እምባገነኖች ሁሉ ድንፋታ፣ ማስፈራራት፣ ማቅራራት፣ መታበይ የአብይ አህመድን መረን የልቀቀ ነውረኛ፣ የከረፋ፣ ግፈኛ፣ ኢ-ፍትሃዊና ፣ እብሪተኛ እገዛዝ ከውድቀት እያድነውም። አብይ አህመድ  አለኝ የሚለው ከወታደራዊ ክህሎት፣ አቅም፣ የሰራዊት ቁጥር፣ የመሳሪያ እይነትና ብዛት በእጅግ የበለጡ መንግስታት ተንኮታክተዋል። በህዝብ የተተፋ፣ ህዝብን የሚጨፈጭፍ፣ ህዝብን የሚንቅ፣  የሚረግጥ፣ ፍትህን ደብዛዋን ከምድሪቱ ያጠፋ አገዛዝ ሁሉ ከውድቀትና የታሪክ ትቢያ ከመሆን ምንም ምድራዊም፣ መለኮታዊም ሃይል አያድነውም። እብይ እህመድ ደርግም፣ ጋዳፊም፣ ሳዳም ሁሴንም፡ የግብጹ ሁስኔ ሙባረክም፣ ሌሎች በአለማችን የተፈጠሩና ህዝብ የተፋቸው አምባገነኖች  የቅርብ ግዜ አሳፋሪ ውድቀቶች ናቸው።  ከእሱ በላይ አውቀትም፣ አቅምም፣ ገንዘብም፣ ወታደራዊ ሃይልም፣ የደህንነት ተቋም የነበራቸው አፈር ድሜ እንደበሉ የማይማር፣ በራሱ ቅዥት አለም የሚዋኝ፣  መረን የለቀቀ ነውረኛ ፡ ክሃዲ ግልሰብ  ነው።

ዛሬ  የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ የደህንነት ዋስትና ፣ ወጥቶ የመግባት ዋስትና አጥቶአል፣ መሰረታዊ የዜጎች መብቶች መርገጥ የእለት ተእለት ክስተት ሆኖአል፣ የህግ የበላይነትና ፍትህ በአገዛዙ የአፈና ተቋማት በአማራ ክልልና በሌሎችም ክልሎች ላይ ጦርነት ራሱ ጀምሮ፣  ዛሬ ላይ ማጠፊያ አጥሮት ነጋ ጠባ የባጥ የቆጡን ይዘባርቃል።  አብዛኛው ህዝብ መሰረታዊ ጤና፣ የኤሊክቲሪክ አቅርቦት ፡ የንጹህ ውሃ አገልግሎት በማያገኝበት፣ በተነፈገበት በዚህች የድሃ ድሃ ሀገር አብይ አህመድ የ15 ቢሊዮን ዶላር ቤተ መንግስት ይገነባል፡፡ ጭቃ ውስጥ ተወልዶ እንዳላደገ ሁሉ፣   “ማንም ያቦካውን ጭቃ” በሚል እብሪት ንቀትና ያሻኝን እያደረኩ ረግጬ እገዛለሁ የፈለኩትንም አፈናቅላለሁ በሚል የድንቁርና  መንገድ ይቀጥላል። እጣ ፈንታውም እይወድቁ አወዳደቅ ወድቆ፣ ተዋርዶ፣  የታሪክ ትቢያ ከመሆን የዘለለ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።

የታሪክና የቅርስ ተመራማሪው ፣ አቶ እዮብ ደሪሎ በኤክስ ያጋራቸው ዛሬ በአብይ አህመድ ትእዛዝ በመፍረስ፣ ላይ የሚገኙ ጥቂቶቹ፣ የሪፖርተር ጋዜጣም ፣ እየፈረሱ ያሉ የታሪክ ቅርሶችን በሚመመልከት ያስነበበው ዘገባ ከዚህ ቀጥሎ ተያይዞአል።

@DerilloEyob

Minas the armenian engineer’s house demolished today. Minas Kerbegian was an armenian roadbuilder and designer of the Taitu hotel opened in 1907 the first hotel to be established in Ethiopia.

In the name of development, the Addis Ababa municipality has demolished a large part of the historic old town, Piazza, known for its architectural heritage from, the 1880s to the Italian-influenced redesign of the 1930s. Piazza was the setting for Evelyn Waugh’s novel “Scoop” in 1938. In the name of development, the Addis Ababa municipality has demolished a large part of the historic old town, Piazza, known for its architectural heritage from, the 1880s to the Italian-influenced redesign of the 1930s. Piazza was the setting for Evelyn Waugh’s novel “Scoop” in 1938.

Addis Ababa Demolition _

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here