spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeነፃ አስተያየት“አምሓራውን ምን በላው? ብአዴንንስ ማን ወለደው?

“አምሓራውን ምን በላው? ብአዴንንስ ማን ወለደው?

Amhara _ Ethiopia

ራሴላስ ወልደማርያም

አምሓራው በኢትዮጵያ ረጂም ታሪክ ውስጥ ብዙ አኩሪ ታሪክ ያለው ብልህና አስተዋይ ሕዝብ ነበር። ለነጻነቱ ለመብቱ የሚሞት፣ ከሆዱ ነጻነቱ የሚያስቀም፣ ለማንም ሎሌና ባርያ ከመሆን ሞቱን የሚመርጥ ኩሩ ህዝብ ነበር። አሁን ማን ብአዴንን ወለደ? ማንስ ከለሰው ? እንዲህ ለምን ጉራማይሌ ሆነ?

ነቡረዕድ ኤርምያስ ከበደ ነፍሳቸውን ይማርና ““አም” ማለት በግዕዙ “ህዝብ” ሲሆን “ሓራ” ደግሞ ነጻ ማለት ነው ብለው ጽፈው አልፈዋል። ለምሳሌ “ሓርነት ግንባር” ማለት የነጻነት ግንባር እንደሚባለው ማለት ነው። “አም’ሓራ” ማለት እንግዲህ “ነጻ ህዝብ” ማለት ነው። ማንም ነጻ ሰው “አምሓራ” ይባላል።

ባለፏት 36 ዓመታት ግን ነጻ መሆኑን ትቶ ባርነትን የሚሻ፣ ወንድሙን በመሰለል፣ በማስገደል እንደ ውሻ አጥንት እንዲጣልለት ጭራውን የሚቆላ አማራ ተባዝቶ የተበትኗል።

ዛሬ ለ10  ሺ ብር ደሞዝ ኢንሳና ደህንነት ተቀጥሮ የወንድመን ስልክ የሚጠልፍ፣ ለሶስት ሺ ብር ደሞዝ ደግሞ ወታደር ተብሎ ራሱ ላይ የሙተኩስ፣ የእናቱን ገበና የሚሸጥ። በፊት አማራነት በትውልድ የሚተላለፍ ይመስለኝ ነበር። አሁን ግን አምሓራነት በትውልድ የሚወረስ ሳይሆን በእድገት፣ በተግባርና በስም ምግባር የሚወረስ ነው። ነቡረዕድ ኤርሚያስ አንድ ሰው ከማንም ይወለድ፣ ከጋሞም ይምጣ ከከገመሚራ “ነጻ ሰው” ወይንም አምሓራ ይባላል ነበር ብለዋል።  ነጻ ያልሆነ በምንም አይነት “አምሓራ” አይባልም። 

 እኔ ተዳፈርክ እንዳልባል ይሄንን ሀሳብ ለአንድ አመት በውስጤ ይዤው ቆይቻለሁ። በማስታወሻ ደብተሬ ላይ አምሓራን ምን በላው ብዬ ጽፌ ነበር።

የአምሓሮች አመጽ፣ የአድማ በታኝና የባርህር ዳር ጉዞ

የዛሬ 11 ወር ልክ በፋሰካ ቦሀላ የአማራ ልዩ ሀይል ትጥቅ ፍታ የተባለበት ግዜ ነበር።  ሰዎችን ለማግኘት በዛውም ለመታዘብ ባህርዳር  ሄጄ ነበር። በርካታ የአምሓራ ወጣቶች ልዩ ኃይላችን መፍረስ የለበትም ብለው መንገድ ዘግተው ከመከላከያ እና ከብአዴኖች ጋር ገጥመው ህይወታቸውን ነበር።  ህዝቡ በመላው የአማራ ክልል ግልብጥ ብሎ ልዩ ሀይላችን ትጥቁን እንዳይፈታም። ልዩ ኃይልም አምሓራውም ለአደጋ ይጋለጣል ብሎ ነበር ይተናነቅ ነበር። ይሁንና ባህርዳር ሆጄ ያየሁዋቸው ሰዎች አማራውን ምን በላው አስባለኝ? ሲታረድ ዝም፣ ቤትህን አፍርስ ሲባል እሺ፣ የነፍ አባቱ ሲታረድ ሻማ የሚያበራ፣ ተነስ ሲሉት የሚነሳ ሆነ። በኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥር ትልቁ ብሄረሰብ ነው ይሁንና ግብረ መልሱ ግን እንደ አንድ አናሳ ቡድን ነው። 

የዛሬ 11 ታጣቂዎች እንደ ዶንያ በሚኒባስ ጣራ ላይ ተደራርበው ተጭነው አየሁ። ከዛ አብሮኝ የነበረውን ጠየቅከት።  እነዚህማ ባለፈው ፈርሳችሀል ተብለው የተበተኑት የአማራ ልዩ ሀይሎች ናቸው። አሁን ብአዴኖች  ሲጨንቃቸው ወደ ካምፕ ግቡ ተብለው ነው አለኝ። አሁን አምሓራው ለነሱ መብት ብሎ ይሞታል እነሱ ደግሞ ለሽመልስ አብዲሳ የተሀድሶ ስልጠና እየገቡ ነው አለኝ።

ይሄንን ስሰማ አንድ ነገር ከሰውነቴ ውስጥ ሲፈርስ ተሰማኝ። አሀን ህዝብና ወጣት ለእነዚህ የአማራ ልዩ ኃይል መብት ህይወቱን ሰጥቶ እየሞተላቸው እነሱ የሽመልስ አብዲሳንና የአብይ አህመድን ትእዛዝ ተቀብለው ጠመንጃቸውን ለማስረከብ ነው መኪና እንኳን አቅርቡልን ሳይሉ በሚኒባስ ጣራ ላይ ተጭነው የሚሄዱት ብዬ አዘንኩኝ።  በዛ ሳምንት ደግሞ በጣም የማከብረው የሞቀ ስራውንና ትቶ ለአምሓራው መብት ሊታገል ወደ አምሓራ ክልል የመጣ ሰው እነ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለና ደሳለኝ ጣሰው አፍነው ይዘው ለኦፒዲኦ ሰጡት ከተባለበት ሳምንት ነበር።

ከዛ በማስታወሻዬን አውጥቼ በተሰበረ ልብ “አምሓራውን ምን በላው?” ብዬ ጻፍኩኝ። ይህ ጽሁፍ የዚህ ርዕስ ሆነ።

አምሓራ

ይህ አምሓራ /ነጻ ህዝብ/ ብለው ሌሎች ስም የሰጡት፣ የነ ጣይቱ ብጡል፣ የነ ምኒሊክ፣ የነ ቴዎድሮስ፣ የነ አክሊሉ ሀብተወልድ፣ የነ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን፣ የነ ቴዎድሮስ ፣ የነ ፋሲለደስን፣ የነ አበበ አረጋይ ብልህነት የት ገባ? እንዴትስ ልጅ መውለድ አቃታቸው ብዬ አሰብኩ?  ታድያ የነዚህ ብልሆች የልጅ ልጆች ምን በላቸው? ዘር አልተኩም ማለት ነው?

እንዴት ከሁሉ ብሄር በታች ይህንን ተንኮል እንኳን መረዳት የሚያስችል ህሊና ያጡ ሰዎች በአማራው ውስጥ በዙ አልኩኝ? እዚህብ ክፍለ ሀገር በላይ ዘለቀ በተዋደቀበት ምድር እነ በረከት ስምዖን እንኮኮ ተብለው ክቡርነቱ እየተባሉ ኖረው ሄዱ። አሁን ደግሞ የራሱ ልጆች ታግለው አሸንፈው የሚያርዱትን እነ ሽመልስ አብዲሳ ጃኖ የሚያለብስ ተንበርክኮ ተፈናጠጥብኝ የሚሉትን አማሮች ማን ወልፕዳቸው? እንዴት ለውርደትና ለእርድ እየተጠራ መሆኑን መረዳት የሚያስችል ህሊና ያጣ አማራ ተፈጠረ አልኩኝ?

ህዝብ ለልዩ ሀይሉ ብሎ እየተናነቀና እየሞተ እያለ እንዴት ለራሳቸው መብት ለመታገል ቢያቅታቸው እንዴት ከገዳያቸው ጋር ለመተባበር መረጡ አልኩኝ። 

ደግሜ ደግሜ እንዴትስ እንዲህ ማሰብ የማይችል አማራ በአማራ ውስጥ ተፈጠረ አልኩኝ? ለራሱ ነጻነት ወንድሙ ሲሞት እሱ ለራሱ ሰጻነት መሞት ቢያቅተው ለሱ ነጻነት የሚታገለውን ወንድሙን ለመግደል ቃታ የሚስበው ጋር ይተባበራል አልኩ?

ቁጭ ብዬ ማልቀስ አማረኝ። አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ አማራውን ዘር ማንዘሩን ለማጥፋት ቆርጠው እየሰሩ ነው። የፕረቶርያ ስምምነት ብለው አማራውን ትጥቅ አስፈትተው፣ ራያንና፣ ጠገዴን፣ ሁመራን ለህወሀት ሰጥተው አማራውን ማዋረድና ማስጨፍጨፍ ነው አላማቸው። ታድያ ይሄንን እንዴት እነ ደመቀ መኮንን፣ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ፣ እነ ተመስገን ጥሩነህ፣ እነ አገኘው ተሻገር፣ እነብአረጋ ከበደ፣ እነብደሳለኝ ጣስው መረዳት አቃታቸው። እንዴትስ እራሳቸውን ቤተሰባቸውን የሚከላከሉበትን ጠመንጃ አስረክቡና ተሰልፋችሁ ታረዱ ይላሉ የሚል ሙግት በውስጤ መጣ። ቅስሜ ተሰበረ። በእርግጥ “አም’ሓራ” ጠፍቶ አማራ ተራባ አልኩኝ? በአምሓራ ወጣቶች ትግልና ትልልቅ ብኮራም፣ በህወሓት አማሮች አዘንኩኝ። ማንም ስንናገር ወደ ሆቴሌ ተመልሼ ሻንጣዬን ይዤ ባህርዳርን ለቀቅኩ።

ይሄንን ስሜት በውስጤ የተቀበረውን ለማንም አልተናገርኩም። በግል ማስታወሻዬ ላይ “አማራውን ምን በላው?” ብዬ የጻፍኩት ዛሬም ማስታወሻዬን ሳገላብጥ አያታለሁ።

የህወሓት አማሮች

ለመሆኑ ያ ነጻ ህዝብ አምሓራ ተብሎ የተጠራው የኢትዮጵያ መስራች ህዝብ የት ገባ? የተባለውን ቀርቶ  የታሰበውን የሚረዳ ብልህና ኩሩ ህዝብ እንዴት እንደ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ? ጀነራል አበባው ታደሰ፣ ደመቀ መኮንን፣ አገኘው ተሻገር፣ ሰማ ጥሩነህ፣ በለጠ ማላ፣ ዳንኤል ክብረት፣ አረጋ ከበደ፣ ደሳለኝ ጣሰው፣ ጄኔራል መሀመድ ተሰማ፣ አቶ አብዱ ሁሴን፣  አቶ አህመዲን መሀመድ፣ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ፣ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ፣ ዶ/ር በጋሻው አወቀ፣ አቶ ብርሀኑ ጎሽም፣ ዶ/ር ሰቡህ ገበያው፣ አቶ ክብረት አህመድ፣ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ፣ ዶ/ር ደመቀ ቦሩ ከማን ዘረመል ተፈጠሩ አልኩኝ?

እንዴት ለራሱ መብት የሚታገልለትን ወንድሙን ይሰልላል፣ ይገላል? በወለጋ በአርሲ እያሰለፈ ምንም ሀጥያት የሌባቸውን ህጻናት፣ እናቶች፣ መነኩሴዎችና ሼኮች የሚያርድ ሀይል ትጥቅ ፍቱልኝና አሰልፌ ልረዳችሁ ሲል እሺ ይባላል? እናታቸውን የሚያሳርዱ፣ እህታቸውን የሚያስደፍሩ ከየት መጡ?

ሳይገባቸው ሳያዩ ቀርተው ይሆን አልኩኝ? ከወለጋ ዩኒቨርስቲ 17 ልጃገረዶች ተጠልፈው ሲወሰዱ ንጉሱ ጥላሁን እያወቀ ለምን ለነሽመልስ አብዲሳና ለነ ጃን መሮ ገጽታ ግንባታ ዋሸ?  እውነቱን መናገሩ ለአለቆቹም መፍትሄ እንዲሹ፣ ራሱም እንዲከበር፣ ለልጆቹም ቤተሰቦች እርማቸውን እንዲያወጡ ይረዳ ነበር። ይሁንና የጃል ማሮና ጭካኔና ለአብይ መሰሪነት ለመሸፋፈን  ዋሸ። አሁን ንጉስ ጥላሁን የት ነው ያለው?  እስር ቤት። 

አብይ አህመድ እንኳን ለአማራ ወዶ ገብ ስልጣኑን ለለቀቀለት ለለማ መገርሳ አልራራም። ቄሮን ቀስቅሶ ለስልጣን ላበቃው ለጃዋር አህመድ ያልራራ ለወዶ ገብ ለአበባው ታደሰ ይተኛል? ከአብንና ከጃዋር ጋር ሲተናነቅለት ለነበረው ታዬ ደንደአ ያልተኛ ለወዶ ገብ ሎሌ ጀነራል መሀመድ ተሰማ ይመለሳል።

እነዚህን ሰዎች ሳይ ነው እንዲህ አይነት ሎሌዎች በአማራ ዘረመል ተፈጠሩ የምለው?

ታዛዥ ብሆንለት አጥንት ይጥልልኛል ብለው የሚያስቡ ውሾች በአማራ ማህጸን ተፈጠሩ? ለምንስ በዙ?። 

በወለጋ “ወላሂ ሁለተኛ አምሀራ አልሆንም” ካለችው ልጅ የዳንኤል ክብረት ሀጥያት በላይ ሆኖ ይሆን? ስንት ዳንኤል ክብረት ከኦሮሙማ ፍርድ ያመልጣ?   እንዴት እነ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ስህተት እነ አረጋ ከበደ መማር አቃተው?  ጣሰው ለአማራው ህዝብ እኩልነትና ነጻነት ብለው የሸፈቱን የአማራ ልጆች እያነቁ በመስጠት በሽመልስ አብዲሳ ለመወደድ የሚመርጡ ሆኑ? አሁን የዶ/ር ይልቃል ህይወት እሱ ፈቅዶ አንቆ አሳልፎ ከስጣቸው በታች ነው? እነሱ በህግ እስረኞች እሱ ደግሞ የግል እስረኛ ነው? እነሱ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ለአማራው ይዘምራሉ፣ እሱ ግን እንደ ሸለምጥማጥ የተቆፈረት ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ ይውላል። 

የዛሬ ሁለት አመት ከአበባው ታደሰ ጋር ጎንደር ጥምቀት ላይ ነጭ ለብሶ በህዝብ ታጅቦ ሰው እጅ ሲነሳይ የነበረ የትልቁ ብሄረሰብ መሪ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ እራሱን ዝቅ አድርጎ ለሽመልስ አብዲሳና ጃል ማሮ  አገልጋይ ልሁን በማለቱ ተዋረደ። የአበባውም፣ የአረጋ ከበደም፣ የደሳለኝ ጣሰውም የሳህለወርቅ ዘውዴም እጣ ፈንታ ከዶ/ር ይልቃል ከፍያለ የባሰ ነው።

አአማራና በአምሓራነት መሀከል ያለው ልዩነት ተለይቶ ነጥሮ መውጣት ያለበት። እንደነ ናሁሰናይ ያለ አምሓራ እንዳለ ሁሉ እነ አረጋ ከበደም ተወልደዋል።

ለኔ ይልቃል ከፍያለ፣ ዳንኤል ክብረት፣ ደመቀ መኮንን፣ አረጋ ከበደ፣ ደሳለኝ ጣስው፣ ተመስሽገን ጥሩነህ አምሓሮች አይደሉም። በምርጫው ባሮች ናችው።  ለኔ እነ መምህር ፋንታሁን ዋቄ፣ መምህር ዘመድኩን በቀለ፣ ቶሎሳ ኢብሳ፣ ታዬ ቦጋለ፣ ታልዲዎስ ተንቱ፣  ፕሮፌሰር ሀይሌ ላሬቦ፣ ወዲ ሻምበል፣ ዶ/ር አረጋዊ (የአጋዚያን መሪ) ባርነትን የጣሉ እውነተኞቹ አምሓሮች እነሱ ናቸው።

በጥቅል ገዳዩም ማቹም፣ ባርነት የመረጠውም ነጻውም ሁሉ ጎጃም ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ስለተወለደ ብቻ አምሓራ አይሆንም። እራሱን ነጻ ያላደረገ ነው አም’ሓራ የሚባለው። 

ሁሉም በተግባር እኔ አምሓራ ወይስ ባርያ ብሎ ራሱን መጠየቅ አለበት። ለምንስ አምሓራ ሆኜ ተወልጄ ባርነትን በተግባር መሻት መረጥኩ ብሎ እራሱን ይጠይቅ አለበት? ባርነት ለነ ንጉሱ ጥላሁን፣ ለነመቀ መኮንን፣ ለዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ምን አመጣላቸው? ለህዝባቸው ለወገናቸው ጽምጽ ሆነው ቢሄን ኖሮ ህዝብ መከታ ይሆንላቸው ነበር። የመረጥኳቸው ልጆቼ እነሱ ናቸው አትንኩዋቸው ብሎ ሰልፍ ይወጣ ነበር፣ መንገድ ይዘጋ ነበር። ገዱ አንዳርጋቸው ብአዴን ቢሆንም ኮለኔል ደመቀን አሳልፌ አልሰጥም ስላለ በህወሓት ተፈራና ተከበረ እንጂ አልተዋረደም።  

 እነ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ግን ለህዝባቸው ድምጽ ከመሆን ይልቅ ቤትና መኪና ፈልገው የሺንት ቤት ወረቀት መሆን መረጡ?  ተጠቅመው አቆሽሸው ጣልዋቸው። ነገ የይልቃል ከፍ ያለም የናሁሰናይም ልጆች ያድጋሉ። ታሪካቸው ይጻፋል። ነጻነት ሲመጣ ለጣልያን ያደረና ፓስታ ሹታ የበላ ልጆቹን አዋረደ ቆሎ ቆርጥሞ ጫካ ገብቶ ለነጻነቱ የቆሙት ራስ መስፍን ስለሺ፣ ራስ አበበ አረጋይ፣ በላይ ዘለቀ ተብለው ልጆቻቸው እስከዛሬ እኔ የእንትና የልጅ፣ልጅ፣ልጅ ነኝ ብለው የመንፈስ ኩራት ይለብሳሉ።

በከተማም በስደትም ለኦሮሙማ ባርያ ለመሆን ትንሽ መሬት ትንሽ አጥንት እንዲጣልላቸው ለነሱ ነጻነት የሚታገሉትን የሚሞቱትን የሚሰልሉ ወሬ የሚያቀርቡ መንፈሰ ባርያዎች ሚሊዮኖች ናቸው። እነዚህ ደግሞ የብአዴን ብልጽግና ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን በየ ትንንሽ ቢሮ ይገኛሉ። በገቢዎች፣ በክፍለ ከተማ፣ በደህነት፣ ቢሮ፣ በኢንሳ፣ በአድማ ብተና፣ በሰራዊት፣ በኢምግሬሽን ውስጥ ያሉትንም አማራ ይጠቀልላል። እነዚህ ሌቦች አምሓራ መባል የለባችፕውም። 

ዮቲዩቡንም የያዙት እውነትን ተናግረው የአምሓራን ዳግም ውልደት ከማምጣትና ድክመታችንንና ህጸጻችንን እያስወገድን ወደ አምሓራነታችን እንድንመለስ ክመጣር ከንቱ ውዳሴ፣ የተጋነነ ዜና፣ የሚታገለውን ሳይሆን የሚያወራውን በማንገስ የሱ ጭፍራ ለመሆንና አንድ ቀን ፍርፋሪ ለመልቀም የሚመኙትንም ይጨምራል። አምሓራነት ባህርና ተግባር ነው።፣

አምሓራነት ያልገባው አምሓራ መሆን አይችልም። እራሱን ነጻ ያላደረገ አማሓራ ነኝ ማለት አይችልም። አምሓራ የነጻ ዜጎች ስብስብ እንጂ የአድርባዮች፣ ለዳረጎት ገዳዮች፣ የሰላዮች፣ ለአድማ በታኞች፣ ለብአዴን አሽቃባጮች፣ ጋዜጠኖች፣ አቃቤ ህጎች፣ ዳኞች መገለጫ አይደለም።

አምሓራ ነኝ የሚል ወንድሙን ሰልሎ፣ አስገድሎ፣ እህትቱን አስደፍሮ ቁራሽ መሬት፣ የመንግስት መኪና፣ የመንግስት ቪላ ውስጥ መኖር የሚመኝ አይደለንም። 

 እነዚህ ችጋራሞች እጣ ፈንታቸው የነ ንጉሱ ጥላሁን ነው። አብይን ቆዳው እንዳይሸጥ አድርጎ ሲሰድብ  የነበረው ጌታቸው ረዳ ህዝብና ደጋፊውን አሳልፎ ስላልስጠ ተከብሮብ ከአብል አጠገብ አስቀምጦ ከወለጋ ተወስደው ግፍ የተፈጸመባቸውን ልጃገረዶች ድምጽ ከመሆን ለኦነግ ሸኔ አሽከር የሆነው ንጉሱ ጥላሁን እስር ተጥሏል። ሲታስር እንኳን እንደ ታዬ ደንደአ ለዜና አልብቃም።

የራያ ዳግም ወረራ

አሁን ደግሞ አረጋ ከበደ እና ደሳለኝ ጣሰው ታዘው መቀሌ ተልከው እነ ጌታቸው እንዲያስፈራሩዋቸው ተደርገው የራያን ህዝብ እንዲሰጡና አስተዳደር አፍርሰው ለህወሓት አስረክበው መጡ። ነገ ደግሞ ከጠገዴ፣ ከሁመራ ህዝብ አፈናቅለው አስወጥተው ይሰጣሉ። ከዛ ደግሞ ውሎ እኮ ኦሮሞ ነበር ብለው ፈርመው ያፈናቅላሉ። ከዛ አማራ ነኝ በትውልድ እንጂ በባህሪ “አምሓራ” መሆን ያልቻልክ ከአዲስ አበባ፣ መላው እትዮጵያ፣ ከጎጃም ትነቀላለህ። ከዛ ጥቂት ሰው መንዝ ተራራ ላይ ተንጠልጥለህ የኦሮሙማ ባለ ጸጋ ልጆች ቱሪስት እያመጡ እንደ ሙርሲ ያስጎበኙታል።

ይህ እቅድ በጽሁፍም በቃልም ተነግሮሀል ስለዚህ አማራ ነኝ ብለህ የምትመጻደቅ መጀመሪያ እኔ በእውነት አምሓራ ነኝን በል። የባሪያ የይሁዳ ህሊና ይዘህ ወንድምህን እየሸጥክ አምሓራ ነኝ አትበል። ከዛሬ ጀምሮ እኔ አምሓራ ነኝ ወንድሜን ገድዬ፣ ሰልዬ፣ አፈናቅዬ፣ ወታደር፣ አድማ በታኝ፣ ፌዴራል ፓሊስ ሆኜ ወገኔን ፈጅቼ መጨረሻ እኔም ከምፈጅ ከዛሬ ጀምሮ እኔ ባርያ ሳልሆን አምሓራ ነኝ በል። የራስህን ሽክም እራስህ ተሸከም፣ የራስህን ነጻነት እውጅ፣ ማስመሰሉን ትተህ አምሓራ ሁን።

__

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena 

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here