spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeነፃ አስተያየትእያስቀጠሉ ያሉት የአያቶቻቸውን ጅምር ነው

እያስቀጠሉ ያሉት የአያቶቻቸውን ጅምር ነው

አሰፋ ታረቀኝ

የታሪክን ቁርሾ ለትውልድ ላለማስተላለፍ ሲባል፣በአማራው ላይ የተሰራው ግፍ በትምህርት መልክ እንድቀርብልን ባለመደረጉ፣ገዳዮቹ እንደሟች፣አሳዳጆቹ እንደተሳዳጅ፣ወራሪዎቹ እንደተፈናቃይ፣ሆነው ሲቀርቡና ሲወንጅሉን፣ ማስረጃ ጠቅሶ ለመከላከል አቅም አጣን፤ የታሪክ ጠበብቶቹና የብዕር አርበኞቹ እነ ፕ/ር ጌታቸው ኅይሌ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ ሙሉጌታ ሉሌ በሞት ቢለዩንም፣ ወላድ በድባብ ትሂድና ዶ/ር ዮናስ ብሩን የመሰለ የዕውቀት ባለጸጋና ግንባሩን የማያጥፍ ምሁር ወራሪው የገዳ ሥርአት በሀገርና በትውልድ ላይ ያደረውን ውድመት፣ እንደ የኦሮሙማ አራማጆች በተረት  ሳይሆን በማስረጃ የተደገፈ ታሪክ እያስነበበን ይገኛል፡፡ ለምን በትምህርት መስጫ ተቋማት ውስጥ አላስተማሩንም ነበር? የሚል ቁጭት ይቀስቅሳል፡፡ ኦሮሙማ አማራንና አናሳ የደቡብ ጎሳወችን እየፈጀ ያለው፣ የ16ኛውን ክፍለ ዘመን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የማስቀጠል ሂደት ነው፡፡

አጼ ዮሐንስ 4ኛ ወሎንና ጎጃምን እንደት አድርገው እንደፈጁት ከሚከተኩት የህዝብ ሮሮዎች መረዳት ይቻላል፤

ሸህ ሁሴን ጂብሪል፣ 

“ እስላም ይጥፋ ይላል የትግሬዋ ልጅ፣

 “አላህ በብልሀቱ ይገላግለን እንጅ” 

ወሎን ክርስቲያን አደርጋለሁ ብለው የወሎን እስልምና እመነት ተከታዮች ስለ ፈጇቸው የተገጠመ፡፡

ልክ የአሁኑ ዘመን ኦሮሙማ ከሚፈጽምበት እልቂትና ፍጅት ያልተናነሰ፣ አጼ ዮሐንስ የጎጃምን አማራ የዘር ማጥፋት አካሂደውበታል፡፡ የማሳ ላይ አዝመራ፣ የቤት እቃ፣ እንሰሳት ሳይቀሩ ዘርፈው ለመሄድ የመጡትን የሕብረተሰብ ስብስብ ያየች ጎጃሜ፣

“ ዕውሩ በመሪ፣ ቆማጣው በፈረስ የተከተለዎ፣

ዝናብ አይዘንብም ወይ፣ እህል አይበቅልም ወይ ንጉሥ ባገረዎ” ብላ መግጠሟ ተመዝግቧል፡፡ 

ይህም ብቻ አይደለም፣

“ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ 

በሬሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ” 

በማለት ሌላዋ የተቀኘችው፣ በበሬ አስመስላ የወደቀውን የህዝብ አስከሬን መጠን የገለጸችበት ጥበብ ነው፡፡ እነሆ ሁሉቱ ዘረኛ ቡድኖች አማራን መሀል አስገብተው ለመፍጀት የቀደምት አያቶቸቸው ጅምር ለማጠናቀቅ አብረው ተነስተዋል፡፡ወሸትን እንደሙያ ማምታታን እንደ መርህ የሚጠቀመው ጠአላይ ሚንስትር፣ ከአንድ ወር ገደማ በፊት “የአማራ ሕብረተሰብ ተወካይ” ተብለው የተሰበሰቡትን ሰወች ባነጋገርበት ጊዜ፣ የአትጼ ቴዎድሮስን መቅደላ ላይ መውደቅ ሐጢአት ከአጼ ዮሐንስ ላይ አንስቶ ለአማራ፤ የአጼ ምኒልክ ሞት ሳይነገር “ለሰባት ዐመት” መቆየቱን ከኦሮሞ ባለሟሎቻቸው ላይ አንስቶ የአማራ ሤራ አስመስሎ ማቅረቡ፣ የማያውቀውን ታሪክ ከመዘባረቁ በላይ አማራው ላይ ያለውን ጥላቻ ከማጋለጥ ውጭ ሌላ ፋይዳ አልነበረውም፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሦስትም ነገሮች ላይ ዋሽቷል፤

  1. የናፒየርን ጦር ግሸን ማሪያም ጥግ ድረስ አምጥቶና የመቅደላን አምባ ሳይቶት የተመለሰው በአጼ ዮሐንስ የተመደበለት መሪ ቡድን እንጅ አማራ አልነበረም፡፡
  2. የአጼ ምኒልክ ሞት የተደበቀው ለሦስት አመት እንጅ ሰባት አመት አልነበረም፤ 
  3. ሦስቱን አመት እንድደበቅ ያደረጉት በንጉሡ ዙሪያ የነበሩት ታላላቅ የኦሮሞ መኳንቶች አንጅ አማሮችት አልነበሩም፤ እንድህም የሆነበት በቂ ምክንያ ነበራቸው፡፡ንጉሡን ሕዝቡ አንደ አባቱም እንደ አምላኩም ያያቸው ስለነበረ ሞታቸው በአንድ ጊዜ ቢነገር ሀገር ይረበሻል ብለው በመፍራት ነበር፤

አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያስጨረሱትን የትህነግ ወንጀለኞች፣ የአማራ ጥላቻ እስከ አጥንቱ ሰርስሮ የገባውን ሬድዋን ሁሴንና የትህነግ የኮቸሮ አቁማዳ ተሸካሚ የነበረውን ‘field marshal’ ልኮ ናይሮቢ ላይ ከተዋዋለ በኋላ፣ በአለም ፊት በሽልማት አንበሸበሻቸው፡፡በትናንቱ ወንጀላቸው ያልተጠየቁት ትህነጎች በአማራ ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ጀምረዋል፡፡ 

ልብ እንበል! ጠጠር ያልወረወሩት ግን ሕዝባችን አይገደል ያሉት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለውና አማራ አይገደል ያሉ ሁሉ መኖሪያቸው እሥር ቤት ሆኗል፡፡ እሥር ቤቱም ደረጃ አለው፤ አማራ ሲታሰር ወደ ገዋኔ፣ ኦሮሞ ሲታሰር ወደ “ፍንፍኔ”። 

ለትህነግም ለኦሆድድ-ኦነግም፣ ከአማራ ሕዝብ ጋር ብሕብረትም ይሁን በጉርብትና አብሮ መኖር ያበቃለት መስሎ ይታያል፡፡ መሃል አስገብተው ለመፍጀት ቆርጠው የተነሱ መስለዋል፡፡ በብልጽግና ካባ የተሸፈነው ኦሆድድ ከደቡብ በኩል፣ በፈጸመው ወንጀል እንዳይጠየቅ የጠቅላይ ሚንስትሩ ከለላ የተቸረው ትህነግ በሰሜን በኩል አማራው ላይ የፍጅት ነጋሪታቸውን እንደ አድስ እየጎሰሙ ነው፡፡ ምሁር ነኝ ባዩም ቤቱ ነዶ ካለቀ በኋላ አመዱ ላይ ለመነጋገር የወሰነ ይመስላል፤ አልያማ አሁን ጸጥ ብሎ መቸ ሊነጋገርና መፍትሄ ሊያመጣ ነው? እንደቀድሞው ሁሉ፣ አማራው ተጋድሎ ራሱን ማትረፉ የማይቀር ነው፤ ከዚያ በኋላ የምትኖረው ኢትዮጵያ ምን እንደምትመስል ለማየት እድሜ አይንፈገን፡፡

ሀገር መሪዋን፣ ሴት ልጅ ትዳሯን ከተጠየፉ ሀገሪቱም ሀገር ትዳሩም ትዳር አይሆኑም፤ መፍትሄው መሪውንም ማሰናበት ትዳሩንም መፍታት ነው፤ ከዚያ ያለፈ ተያይዞ መጥፋት ነው፡፡ ዶ/ር አብይ አህመድን ኢትዮጵያ ተጠይፋዋለች፡፡ በሁሉም መስክ አሳነሳት፤ ትውልድም እንድተርፍ ሀገርም እንድኖረን፣ ፈገግተኛው ፋሽስት በቶሎ መሸኝት ይኖርበታል፡፡

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉt.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉBorkena

በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

  1. The dreamers are always dreaming how to convince the Ethiopians their forefathers false and fake history of of Ethiopia. The first thing you should know is that Amhara is not Ethiopian and are immigrants from Yemen to Ethiopia. After their immigration they tried alot to destroy the history of the true Ethiopians and modified it as theirs with the assistance of the western and the darkness of the time. Today we’re not in that dark time that you try to convince us your forefathers false history and try to live as them on the shoulders of Ethiopians.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here