spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeመጽሐፍትየእመቤቴ መንግስቴ አራተኛ መጽሐፍ - “ዝም ከምል ብዬ”

የእመቤቴ መንግስቴ አራተኛ መጽሐፍ – “ዝም ከምል ብዬ”

Emebet Mengiste - ዝም ከምል ብዬ

አቤል ጋሽ
ደራሲ

“ዝም ከምል ብዬ” በሚል ርዕስ ደራሲ እመቤት መንግሥቴ ያሳተመችው ይህ የትምህርታዊ ትዝብቶች ስብስብ ጠቃሚ የሆኑ የሕይወት መነጽሮችን ያካተተ ነው፡፡ መነጽር እይታን የሚያስተካክሉበት፣ ለሚጠቀምበት ሰው አይኑ ላይ አድርጎ የማየት ችሎታውን የሚያሻሸልበት ወይም ከፀሐይ የሚከላከልበት መሳሪያ ነው፡፡ 

እመቤት ከህይወት ተመክሮዋ ተነስታ ለአንባቢ እንዲጠቅሙ አድርጋ ከሽና ያቀረበቻቸው መጣጥፎች ለአንባቢው በራሱም ይሁን በአካባቢው የሚያጋጥሙትን የህይወት ገጠመኞች እንዲመረምራቸውና እንዲማርባቸው የሚያስችሉት የአመክንዮ መነጽሮች ናቸው፡፡ 

ደራሲዋ በዚህ ስራዋ ውስጥ ከተጨባጩ አለም ልምድዋ ተነስታ ያቀረበቻቸው ማህበራዊና ግላዊ ሂሶችና ትዝብቶች በይዘታቸው የደራሲዋንና የአካባቢዋን እውነታ በቅርብ ስለሚዳስሱ እንዲህ ያለ ትዝብትን ለሕዝብ የማካፈል ጉዞ ድፍረትንና የውስጥ ጥንካሬን የሚጠይቅ ኃላፊነት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ራስንና አካባቢን ተመልክቶ በሂስና በግለሂስ ለማስተማርና አካባቢን ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራና ጥረት የሚያስከትለውን ወቀሳና ተጠያቂነት ተቁዋቁሞ “ታዝቤ ዝም አልልም” በማለት ራስንና አካባቢን ለመለወጥ መሞክር ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመንና ብሎም የሞራልና የሕሊና ሚዛንን ጨብጦ ሳያንጋድዱ ማመላከትና መለካትን ይጠይቃል፡፡

 ደራሲዋ እመቤት ይኽንን ፈተና ተፈትና ካየችው ከታዘበችው ተነስታ በግል ሕይወትና ማንነት፣ በቤተሰብ፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በፖለቲካ፣ በእምነት፣ በባህል፣ በታሪክ፣ በሀገርና በመሳሰሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ አስተማሪ የሆኑ ተግሳጾችን፣ ምክሮችን፣ ወቀሳዎችን፣ ብሎም አዳዲስ አመለካክቶችን ጀባ ብላናለች፡፡ አጫጭር ሆነው ቀርበው ሳይሰለቹ የሚነበቡት እኒህ ስራዎች ለሚያነበው ሁሉ ራሱን አካባቢውን እንዲቃኝ ይረዱታል፡፡ ብሎም እመቤት እንዳደረገችው እያንዳንዱ ሰው በኑሮውና በአካባቢው ከሚያየው ከሚታዘበው ተነስቶ ራሱንም ሆነ አካባቢውን የሚያስተምርበትና የሚለውጥበት ምህዳርንና መንገድን ይማርበታል፡፡ 

ከሁሉም በላይ የእመቤት ጽሁፎች “ራስን ለማወቅ” የራስንና የአካባቢን ሕይወት ማየት፣ መመርመርና ጥንካሬን አጎልብቶ፣ ከድክመት ተምሮ የተሻለ ሰው መሆንን ያስገነዝባሉ፡፡ ይህ ደራሲዋ ራስዋንና አካባቢዋን ተመልክታ ወገኖችዋን ለማስተማር የደከመችው ድካምና ስራ ለሺዎች ዘመናት አዋቂዎችና ጠቢባን ያስተማሩትንና የሰበኩትን ብሂል የሚያጸና ነው፡፡ ይህ ስራ የፈላስፎች ቁንጮ ሆኖ የሚታወቀው ሶቅራጥስ ተናገረ የሚባለውን “ያልተመረመረ ሕይወት ባይኖሩት ይሻላል፡፡” (The unexamined life is not worth living.) የሚል ብሂል የሚያስታውስ ነው፡፡ 

እመቤት በዚህ ስራዋ ያሳየችን መልካም መንገድ የሕሊናንና የልቦናን አይን ከፍቶ ራስንና አካባቢን መመርመር፣ መገሰጽና ብሎም ወደ ተሻለው ደረጃ ለመለወጥ የራስን አስተዋጽኦ ማድረግን ነው፡፡ ራስንና አካባቢን አግባብ ባለው ተግሳጽ መርምሮ የተሻለ ሰው መሆንና፣ የተሻለ ማህበረስብ ለመገንባት የራስን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀት የእያንዳንዱ ግለሰብ ምርጫ ነው፡፡ ፈረሱን እመቤት አቅርባለች፣ መጋለብ የአንባቢ ነው፡፡ መልካም ጉዞ፣ መልካም ንባብ፡፡

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here