spot_img
Sunday, May 19, 2024
Homeመጽሐፍትፋኖስ እና ብርጭቆው (ገለታው ዘለቀ)

ፋኖስ እና ብርጭቆው (ገለታው ዘለቀ)

ፋኖስ እና ብርጭቆው

ገለታው ዘለቀ

ፋኖስ እና ብርጭቆው የተሰኘው የዚህ መጽሃፍ ዓላማ አዲስ አበባን ሰቅዘው በያዙ መዋቅራዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ መስጠትና ችግሮቹን ማሳየት፣ ብሎም ከነዚህ ከፍተኛ ችግሮች መሃል የመውጫውን መንገድ መጠቆም ነው።

እንደ መግቢያ “ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት (Democratic Ethno-Nationalism)” የሚባለውን ጽንሰ ሃሳብ ከመረመርን በኋላ ሃገሪቱን በከፍተኛ መተሳሰሪያ መርሆነት የሚመራውና የህገ መንግስቱ ሁለንተና የሆነው ይህ የብሄርተኝነት አስተምህሮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ ያሳደረውን ከፍተኛ ችግር እያነሳን እንወያይበታልን። በተለይ በዚህ በብሄርተኝነት መርህ በተቀረጸ መተሳሰሪያ መርሆ ውስጥ የአዲስ አበባ ራስን በራስ የማሥተዳደር መብት ጉዳይ ምን ምን ችግሮች ላይ እንደተጣደ በትንታኔዎቻችን ላይ በትኩረት እንሄድበታለን። የከተማዋ አስተዳደር በቻርተሩ ላይ እንደገለጸው የራሱ ህግ አውጪ፣ ህግ ተርጓሚና አስፈጻሚ ቢኖረውም እነዚህ የመንግስት አካላት ያላቸውን የነጻነት ደረጃ እንመዝናለን። ህገ መንግስቱ በማንነቶች ላይ የፖለቲካ ድንኳኖቹን ሲጥል ከዚህ ከማንነት አንጻር አዲስ አበባ ምን ዓይነት ውዥንብር ገጠማት? የሚል ጥያቄ አንስተን እንመክርበታለን። ከዚህ በተጨማሪ ከብሄርተኝነት (Ethno-Nationalism) አስተምህሮ ጋር ተያይዞ በከተማይቱ ላይ የሚታዩ የፍላጎት ግጭቶችንም አንስተን እንገመግማለን። በተለይም አዲስ አበባ ላይ ካሉ የልዩ ልዩ አካላት ፍላጎቶች ውስጥ የኦሮምያ ክልል ያደረበትን እላፊ ፍላጎትና ይህ ፍላጎት ከአዲስ አበባ ህዝብ ፍላጎት ጋር ያለውን ግጭቶች በሚገባ ከውስጥ ወደ ውጭ፣ ከውጭ ወደ ውስጥ እያገላበጥን እንወያይበታለን። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ በተለይ በብልጽግና ጊዜ ያለችበትን ሁናቴ እናነሳለን። የሸገር ከተማ ጉዳይና የዜጎች መፈናቀልና የድሃ ቤት ፈረሳ ጉዳይ ከስርዓቱ ጋር ያለውን ግንኙነት እናሳያለን። 


የከተማይቱን ታሪካዊ ቅርሶች አያያዝ በተመለከተ ይህ ጽሁፍ ትኩረት ሰጥቶ ይመለከተዋል። አዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እንደመሆኗ የብዙ ታሪካዊ አሻራዎቻችን መገኛ ብትሆንም በዚህ ዘመን በተለይ ቅርሶቻችንና ትውፊቶቻችን ከፍተኛ ስደት በዝቶባቸው ይታያልና ለምን ቅርሶቻችን ይሳደዳሉ? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ የመንግስትን ፍላጎት እንመረምራለን፣ እናጋልጣለን። 

የከተማይቱን የሙስና ችግሮች፣ የህዝቡን ኑሮ፣ በተለይም የሰራተኛውን ምንዳ በሚመለከት የውይይት ምዕራፎች ደግሰን የሰራተኛውን ትዳር የማሸነፍ አቅም እንገመግማለን። በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ሃገሪቱ በሥራ አስቀጣሪ ኤጀንሲዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ወገኖቻችን ምንዳ በአስቀጣሪ ኤጀንሲዎች አማካኝነት የሚደረገውን ዘረፋ አበጥረን እናጋልጣላን። የከተማዋን የጎዳና ላይ ኑሮና የመንግስትን የሃብት አጠቃቀም ችግሮች እያነሳን እንሞግታለን። እንግዲህ አንባቢ ሆይ ወደ ትንታኔዎቻችን እናምራ! መልካም ንባብ ይሁንልዎ!

__

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

መጽሃፍዎን በዚህ ዓምድ ለማውጣት በዚህ አድራሻ ይላኩልን ፡ info@borkena.com 

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here