spot_img
Monday, June 24, 2024
Homeነፃ አስተያየትየኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት የማን ነው?! 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት የማን ነው?! 

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት

አዲስ ደርበው

አንድ ዜጋ ማንኛውም መስሪያ ቤት አገልግሎት ለማግኘት እንደተገልጋይነቱ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ(ካለ) አሟልቶ እስከተገኘ ድረስ አገልግሎት ማግኝት መብቱ ነው የሚል ህግ አለ መቼስ?! መኖርም አለበት፡፡ 

ታዲያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አግልግሎት : አገልግሎት የሚሰጠው ለነማን ነው? ዜግነት ደረጃ አለው እንዴ? ማለቴ አንደኛ …ሁለተኛ…ሶስተኛ? መቼም እንዲያ ካልሆነ : ከእኔ እኩል ለአገልግሎት የተሰለፈ ተገልጋይ አገልግሎት ሲያገኝ : እኔ : በማንነቴ ተለይቼ አገልግሎት የምነፈግበት ምክንያት አይኖርም። መቼም ሊገባኝ የማይችለው ነገር: የአጥንት ቆጠራው ነገር ነው። 

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት የሚያስፈልጉትን : 

ማስረጃዎች እንደ የታደሰ የቀበሌ ማታወቂያ: የልደት ሰርቲፊኬት: ካሟላሁ በሗላ መጋቢት 12፤2016 ኦንላይን አመልክቼ ፤ ለሚያዝያ 112016 ዓ/ም(አፕሪል 

1፤202) ዋና ቢሮ (አዲስ አበባ)ቀጠሮ ተሰጥቶኝ፤ በቀጠሮውም መሰረት 

ከቀበሌ መታወቂያ ና ልደት ሰርቲፊኬት በተጨማሪ የትምህርት ማስረጃና የምሰራበት መስሪያ ቤት መታወቂያ ይዤ ከጧት እንድ ሰአት ጀምሮ የተሰለፍኩ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰአት አካባቢ ተራዬ ደርሶ ወደ ቢሮ ቁጥር አምስት አመራሁ ። 

ነገር ግን ያስተናግደኝ ዘንድ በወንበሩ የተሰየመው ግለሰብ: ያቀረብኩት ሰነድ አገላብጦ ከመረመረ በሗላ: ያቀረብኩለት ማስረጃ በህጉ መሰረት አገልግሎት አንዳገኝ የሚያስችል ቢሆንም እንደሱ እምነት ያጠገበው አልመሰለኝም። 

የፖሊስ በሚመስል አጠያየቅ : ይጠይቀኝ ጀመር? « የእናት አባት ስም» ጠየቀኝ – ነገረሁት 

ቀጥሎ «የት ተወለድህ?» አለኝ ~ሰሜን 

ወሎ:ወልዲያ:(አማራ ክልል)። 

«አባትና እናትህ የት ተወለዱ?> ራያ ቆቦ። 

ከዚያ የቀጠሮ ቀን የተቀጠርኩበትና ክፍያ መፈፀሜን የሚያሳየው ወረቀት ላይ የሆነ ገር ጫርጫር አድርጎ ሰነዴን ወደኔ ወረወረልኝ ፡ 

ምንድነው? 

«7 ቁጥር ሂድ» አለኝ አለኝ። 

እንዴ እዚህ አይደል እንዴ ሚሰራልኝ? ሊያናገረኝ አልፈለገም። 

የተባለው ቢሮ ቁጥር ሄድኩ: ማንም የለም መሽቷል ። 

ተመለስኩ: ወንድም 7 ቁጥር ዝግ እኮ ነው፡፡ 

«ነገ ተመልሰህ ጠይቅ> 

«ነገ ቅዳሜ እኮ ነው» 

«በቃ ሰኞ ና

«እንዴ ለምን አታስተናግዱኝም እዚህ? ምንድነው 

ችግሩ ወይ ያላሟላሁት ነገር ንገሩኝ » 

ወደ ጥበቃው አንባረቀ። 

«ጥበቃ! ይኼን ልጅ አስወጣልኝ!» 

የዚህን ያህል! 

ምሳ እንኳን በወጉ ሳልበላ: ፀሀይ ላይ ተሰጥቼ መዋሌ፤ :ሰኞ:እንደገና የሚጠብቀኝ ሌላ ሰልፍና : እሰጣገባ ሳስብ:በዚያ ላይ የልጁ ስርአት አልባነት እያናደደኝ ከመሼ ጊቢውን ለቅቄ ወጣሁ። 

ሰኞ መጋቢት 14፣2016 ዓ/ም እንደፈራሁት ገና በጥዋቱ እንደ ሀረጎ መንገድ የተጠማዘዘ ሰልፍ ጠበቀኝ። ተሰልፍኩ እንደምንም ተራ ደረሰኝ። ድጋሚ የፖሊስ የሚመስለው ጠያቄ ቀድሞኝ አገኘሁት። 

«የት ተወለድህ?» 

መለስኩ 

«እናት ናት ወይስ አባትህ ተጋሩ?» 

«ምን?!: አሁን ጫን ያለው መጣ?» 

«ኧረ : ማናቸውም አይደሉም? እኔ እኮ ወደዚህ መስኮት ሂድ ብሎ ወረቀቴ ላይ ስለመራው ነው የመጣሁት።» 

«አይ በዚህ መስኮት : የሚስተናገዱት: የትግራይ ተወላጆች ብቻ ናቸው።> 

«ዋይ ማዕልቲ!» ማለት አሁን ነው? 

ሪፈር ወዳለኝ ሰወዬ ተመልስሁ ። የለም። በቦታው ሌላ ሴት ተቀምጣ ታስተናግዳለች፡፡ 

ይቅርታ የኔ እህት: ባለፈው አርብ ማታ እዚህ ተቀምጦ ይሰራ የነበረ ልጅ : ሰባት ቁጥር ልኮኝ ነበር….ስል ሳታስጨርሰኝ። «አርብ?!» 

አዎ: አርብ አንቺ ያለሽበት ቦታ ነበር። 

እና እባክሽ: ወደ ላከኝ መስኮት ብሄድም አላስተናገዱኝ። እዚህ መስተናገድ እንዳለብኝ ነው የነገሩኝ። 

«አይእኔ ምንም ልረዳህ አልችልም። እሱ ራሱን ጠይቅ፡፡> 

ብላኝ ወደ ተሰለፉት ተገልጋዮች አንገቷን አሰገገች። 

እኔ መሀል ቀረሁ አትሉም?! 

ሰውየው ያቀረብኩለትን ሰነድ አገላብጦ አይቶታል። 

በግልፅ : ሰፍሯል። 

የትወልድ :ቦታ ሰ/ወሎ/ ወልዲያ ራያ ቆቦ 

ክልሉ : አማራ። 

ይህ በግልፅ ታትሟል። 

መታውቂያውም: የልደት ካርዴም ላይ። 

በምን ስሌት ገሸሽሽ እንደተደረግሁ እስካሁን አልገባኝም። 

ድጋሜ ወደዚያ መስሪያ ቤት መሄድ ወደ ሞት የመሄድን ያህል ከበደኝ። ፓስፖርት ባለማግኘቴ ምክንያት: የትምህርትና የስልጣና ዕድሎች እያመለጡኝ ነው፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት : qualify የማደርገው በዘር የየትኛው ዘር አባል ብሆን ነው?! 

_

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉt.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉBorkena

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here