spot_img
Monday, June 24, 2024
Homeነፃ አስተያየትኦነገደ አምሐራ ወሀገሪትነ ኢትዮጵያ !!  (ከአበባዉ)

ኦነገደ አምሐራ ወሀገሪትነ ኢትዮጵያ !!  (ከአበባዉ)

እምሐራ
ከማህበራዊ ሚዲይ የተገኘ

ከአበባዉThe bihere Gondar

የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማ ዐማራዉ በዉስጡ ያሉትን ጥንካሬዎችና ድክመቶች በመመርመርና በማጥናት በአካሔዱ ላይ ራሱን በማስተካከልና በማዘጋጀት ከዉርደት ወይም ከፈጽሞ ጥፋት ራሱን ማዳን ይችል ዘንድ ለመነጋገሪያና ለዉይይት መነሻ የሚሆኑ ኃሳቦችን  ለማካፈል ነዉ፡፡

መግቢያ

እዉነታዉን ደፍሮና አፍ  አዉጥቶ ለመናገር ከአስፈለገ አማራዉ በጣም አርቆ አሳቢ፤ ጀግና፤ አስተዋይ፤ ፍትህ ፈላጊና አዋቂ ሕዝብ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ለብዙ ሺህ ዓመታት ለራሱ ሳይሆን ለኢትዮጵያ አገሩ፤ ለራሱ ሳይሆን ለአዉነታና ለፍትህ፤ ለራሱ ሳይሆን ለተጨቆኑ ሕዝቦች ሲቆም በመኖሩ ምክንያት በወራሪዎች፤ በጨቋኞች፣  በበዝባዦችና በባንዳዎች ዘንድ እንደ መሰናክልና እንደ ጠላት ሲታይ ኖሯል፤ በመታየት ላይም ይገኛል፡፡ አፍሪካዉያንን   እንዳንበዘብዝና እንዳንጨቁን መሰናክል የሆኑብን አማሮች ናቸዉ፤ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት እንዳንይዝ ሕዝባቸዉን በማስተባበር የጠነከሩብን አማሮች ስለሆኑ እንዴት አድርገን ልናዳክማቸዉና ልናጠፋቸዉ እንችላለን ? የሚል ስተራተጅና እቅድ ሲወጣባቸዉ የኖሩ ሲሆን፤ ይህ ዕቅድም በተለያዩ ጊዚያት እየተሸሻለ ሲወጣና  ተግባራዊ ሲደረግባቸዉም  ኖሯል፡፡ ቅድስት  ኢትዮጵያ አገራችን ደግሞ የዚህ ዘር መገኛና ባለቤት በመሆኗ የታደለች  ናት ተብሎ ይታመናል፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜም ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ ጠላቶች ከሚደቀንባት ጥፋት ሁሉ ሲታደጋትና ሲያድናት ቆይቷልና ነዉ፡፡

ከአማራ የወጡ መሪዎች በዮሐንስና በቴወድሮስ የተጀመረዉን አንዲትና ጠንካራ ኢትዮጵያን የመፍጠር ራዕይ ዉለታቸዉና የመሪነት ጥበባቸዉ በበቂ ሁኔታ ያልተነገረላቸዉ እምዬ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ከዳር አድርሰዉታል፡፡ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ የነበሩ አዳዲስ ሥልጣኔዎችን ወደ አገራችን በማስገባት ሕዝባችንን አይኑን ለመክፈት አስችለዉታል፤ ተጠቃሚም አድርገዉታል፡፡ እምዬ ምኒልክ ጥቁር ስለሆኑና የነጭን የበላይነት በመስበራቸዉ ምክንያት በጠላትነት ስለተፈረጁ እንጂ ምኒልክና ጣይቱ ከጥቁር ቤተሰብ ያልተገኙ ቢሆኑ ኖሮ የዘመኑ ዋና አጀንዳ የሆነዉ የመሪነት ጥበብ (leadership quality) አባት በመባል ስማቸዉ በዓለም ደረጃ ሐዉልት ቆሞላቸዉና የመታሰቢያ በዓላቸዉም በየዓመቱ ሲከበርላቸዉ ይኖር ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ይህ ዉለታቸዉ ተረስቶ ከዚህ ሕዝብና ከእነዚህ ጀግና መሪዎች የተገኙ ልጆቻቸዉ ያልተፈጠረና ያልተሠራ ታሪክና የማይገባ ስም ተለጥፎባቸዉ ለአለፉት 50 ዐመታት አንገታቸዉን ደፍተዉ እንዲኖሩ ከመደረጉም በላይ በዓለም ላይ ከተፈጸሙ የጥፋት ድርጊቶች ሁሉ በባሰ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል፤ ዛሬም እየተፈጸመባቸዉ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህልም በሕወሃት/ኢህአደግ የአገዛዝ ወቅት በማኒፍሰቶ ተደግፎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንዲሳደዱ፤ እንዲገደሉና እንዲፈናቀሉ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በዘመነ ብልጽግና ወቅትም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተልይ ከወለጋ፤ሎሎ ኖኖ፤ በደኖና በሁሉም ኦሮሚያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማሮች ፤ተሳደዋል፤ ተፈናቅለዋል፣ተገድለዋልም፡፡ ዛሬም በአርሲ፣በወለጋና በምሥራቅ ሸዋ በተለይዩ ወረዳዎች ዉስጥ አማሮች ይገደላሉ፤ንብረታቸዉን ይቀማሉ፤  ለብዙ ዓመታት ይኖሩባቸዉ የነበሩ ቦታዎችንም ጥለዉ እንዲሰደዱ በመደረግ ላይ ናቸዉ፡፡ ይህ ድርጊት የሚጸፈምባቸዉም ሌላ እንከን ኖሮባቸዉ ሳይሆን አማራ በመሆናቸዉና ከላይ የተጠቀሱ ዕሴቶች ባለቤት በመሆናቸዉ ብቻ ነዉ፡፤

አማራዉ ይህን የመሰለ የግፍ ጽዋ ይጎነጭ በነበረበት ወቅት በራሱ ልጆች ይመራ ያልነበረዉ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፣ የቅርብ ጊዜዉ አዴፓ እንዲሁም የአሁኑ የአማራ ብልጽግና ለምን የሚል ጥያቄ ሊያቀርብ ካለመቻሉም በላይ ከፖለቲካ አመራሮቹም ብዙዎች በአማራ ላይ ለደረሰዉ የጥፋት ድርጊት ሁሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆናቸዉ ደግሞ የአማራዉን መከራና ስቃይ እጅግ በጣም የከበደና የመረረ አድርጎት ይገኛል፡፡ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህልም በጎጃም የቢቸና ተወላጁ ተመሰገን ጥሩነህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖሰት ዋና አዛዥ በመሆንና የደበረ ወርቁን ተወላጅ አረጋ ከበደን ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ በመሾምና በመቀናጀት በአማራዉ ላይ እየደረሰ ያለዉን እልቂት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ዛሬ በኦሮሚያ ክልል የሚኖር አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ ሐብቱ፤ቤቱ፣መሬቱ እንዲሁም ኢንቭሰትምንቱ በኦሮሚያ ባለሥልጣናት እየተነጠቀ፤ ከስሮ ከሥራ ዉጭ እንዲሆንም ተገቢ ያለሆነ ታክስ እየተጣለበት፤ የዚሁ ክልል መንግሥትም አማራን ለመፍጀት በብዙ ሺሀ የሚቆጠር ልዩ ኃይል እያሰለጠነ በአአለበት በአሁኑ ወቅት እነዚህ ሁለት የአቢይ ለሆዱ አደር ባለሥልጣናት አማራዉን እርስ በዕርሱ እያጫረሱትና ለበለጠ ጥፋት እያዘጋጁት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ወንጀለኛ ግለሰቦች ይህ ግፍና በደል ካልቆመና እኩልነት ከሌለ አማራን አናስጨርስም፤ጦርነቱን በክልሉ ዉስጥ ተሸክሞ እንዲዳከም አናስደርግም የማለት ሰብዕናዉም ሆነ ሞራሉ የላቸዉም?   

የእስራኤል ልጆች ያነን የመሰለ የጉልበት ዕዳ በመክፈል የግብፅ ከተሞችን ማለትም እንደ ፌቶም፤ራምሴንና የጸሐይ ከተሞችን ጽኑ አድርገዉ ቢሰሩም ግብጻዊያን ግን ይንቋቸዉና ያንgሽሿቸዉ እንደ ነበር ሁሉ የቀድሞዉ የኢህአዴግና የጊዜዉ የብልጽግና አመራርም አማራን ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛና ጽንፈኛ የሚል ቅጽል በመለጠፍ ለ40 ዓመታት ያህል እንዲናቅና በዉርደት ዓይን እንዲታይ ሲያደርገዉ ኖVል፡፡ግብጻዊያን የእስራኤልን ልጆች በጽኑ ሥራ፤ በጭቃ ማቡካት፤ በጡብና በእርሻ ሥራም በሚያሰVቸዉ ሥራ ሁሉ ሕይወታቸዉን መራራ ያደርጉባቸዉና ያስመርVቸዉም ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የኢሕአዴግና የብልጽግና አመራርም አማራዎች በአገራቸዉ ላይ በሰላም እንዳይኖሩ በተለያዩ መንገዶች እጅግ አስጨነቋቸዉ፤ አሳደዷቸዉ፤ ገደሉአቸዉም፡፡ እንደዚህ ሆኖም አማራዉ የብዙ ዓመታት የሰቆቃ ኑሮን አሳልòል  እያሳለፈም ይገኛል፤ እነዚህ ረጅም የግፍና የፍዳ ዓመታትም እጅግ ረጅምና አስጨናቂ ሆነዉብናል፡፡ በስቃይ፤ በጭቆናና በሰቆቃ ሕይወት ዉስጥ ኑሮ እንደዚህ ተመሰቃቅሎ፤ ሁሉም ነገር ሚዛኑን ስቶና ደስታ ጠፍቶ ዋይታ ሲበዛ ችግርና መከራ የማይገፋ ግንብ ይሆናል፡፡ ይህ ሲታሰብ ያሳለፍናቸዉና እየገፋናቸዉ ያሉ የመከራ ዓመታትም የብዙ ዘመናትን ያህል ረጅምና እንደ መርግ የሚከብዱ፤ ኑሮም እንደሬት የሚመርና መያዣ መጨበጫ የጠፋበት ሆኗል፡፡የአማራ ዘፋኝም የሚስረቀረቀዉን ቅላጼ ከሚመስጥ ግጥሙ ጋር እያዋሀደና እያዋደደ ‘‘መንገዱ ረዘመ ረዘመ! ረዘመ!፤እንዲያዉ ዜሮ ዜሮ ሁሉም ዜሮ ዜሮ! እና አይነጋም ወይ ሌሊቱ አይነጋም ወይ’’ እያለ ሲያስተጋባ በአዕምVችን ዉስጥ የተለያዩ ሀሳቦችን በመጫር እንቅልፍና እረፍት እየነሳን ይገኛል፡፡አምነነዉና ተስፋ ጥለንበት የነበረዉ የዶ/ር አቢይ አህመድ መንግሥትም ሕግና ጸጥታን በማስከበር የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ከሞትና መፈናቀል ማዳን ካለመቻሉም በላይ ዛሬ ደግሞ ራሱ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ክልል ዉስጥ በመግባት በድሮንና በከባድ መሳሪያ አማራዉን በመፍጀትና ንብረቱንም በማዉደም ላይ ይገኛል፡፡

ዘመንን ከክፉ አገዛዝና ከመራራ ኑሮ ጋር አጣምረን በማዛመድ እንዴት ኖረን ነበር፤ እንዴት እየኖርን ነዉ? እንዴትስ ልንኖር ነዉ? ብለን ስንጠይቅ መልሱ የሚያመራምር አልነበረም፤ አይደለምም፡፡ በአይናችን ያየናቸዉ የሕይወት ገጠመኞች እንደመስተዋት ቁልጭ አድርገዉ እያሳዩን ይገኛሉ፤ የወደፊቱ ግን ከዚህ የተሻለ ይሆናል ብለን በተስፋ ብንጠባበቅም የትንቢቱ ቃል ይፈጸም ዘንድ በአገራችንና በሕዝባችን ላይ መፈጸም የሌለባቸዉ አስከፊ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ግፉን፤ ስደቱን፤ መፈናቀሉን፤ ከሥራ መባረሩንና የሰባዊ መብታችን መገፈፉን ማየት ብቻ ሳይሆን በራሳችን ላይ ደርሶብናል፡፡ በጎሳ የፖለቲካ ሥርዓት ተጠልፈንና ተጠላልፈን የተወገርን፤ ጥቅምና ዘረኝነት ናላቸዉን በአዞረዉ ፖለቲከኞችና የዉጭ ጣልቃ ገቦች እርስ በእርስ እየተበላላን እንድንጠፋፋ የተደረግን ምስኪን ሕዝቦች ሆነናል፡፡እነዚህና መሰል ሰቆቃዎች ስለደረሱብን በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ብናማርርና ፈጣሪ በቃችሁ ይለን ዘንድ ለጸሎተ ምህላ ብንጠይቅም ለምን ታማርራላችሁ፤ ምንስ ጎደለባችሁና ነዉ የምህላ ጸሎት ለማድረግ የጠየቃችሁ ተብለን በደላቸዉ ገዥዎቻችንና በቀድሞ የኃይማኖት አባቶች ተጠይቀናል፤ ተገስጸናል፤ የጠየቅነዉን ጸሎተ ምኅላም ተከልክለናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዚያ በባሰ ሁኔታ ወደ ፈጣሪ አቤት መባያና መጽናኛችን የሆነችዉን ቤተ ክርስቲያናችንን በማፈረስ እናትና አባት እንደሌሉት ህጻን ልጅ ሊያደርጉን ከፍተኛ ጥረት አደረጉ፡፡ኦሮሞዉ ያላሰበዉና ያልፈለገዉን የኦሮሞ ክልል ሲኖደስ መፍጠር በሚል በጣት የሚቆጠሩና ለሆዳቸዉ ያደሩ ጳጳሳትን በመያዝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከፍተኛ ጥረት አድርÒል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይም የቤተ ክርሰትያናችንን ጡት እየጠባ  ያደገዉ የዳንኤል ክብረት ሚናም የሚናቅ አልነበረም፡፡   

የግብጹ ንጉስ እንደ ሲፓራና ፎሓ የመሳሰሉትን የእብራዊያት የልምድ አዋላጆችን ሰብስቦ እንደዚህ ብሎ ተናገረ፤ ‹‹የእብራዊያትን ሴቶች ለመዉለድ እንደደረሱ ባያችሁ ጊዜና ስታዋልዱም ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን አትግደሏት የሚል ትዕዛዝ ሰጣቸዉ፡፡ የኢህአዴግ አስተዳድርም ከዚህ በባሰ ሁኔታ የአማራ ልጆች መዉለድ እንዳይችሉ ከጨቅላ ዕድሚያቸዉ ጀምሮ በወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲታሸጉ መመሪያ ወጣ፤ ትዛዝም ተሰጠ፤ ለስድስት ወር ያህል የሰለጠኑ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን በየቀበሌዉና በየገጠሩ በማሰማራት እናቶቻችን፤ እህቶቻችንና ሚሰስቶቻችን በወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲታሸጉና የመዉለድ ፍላጎት እንዲያጡም በሰፊዉ እንዲሰበኩ ተደረገ፡፡ ይህን ያልተቀበሉ ሴቶችም እንደ ስኳርና ዘይት ያሉ ቁሳቁሶችን ከሚኖሩበት ከቀበሌና ገበሬ ማሕበራት መግዛት እንዳይችሉ ተከለከሉ፡፡ ይህ ድርጊትም የአማራዉን ቁጥር በእጅጉ እንደቀነሰዉ የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ላይ ተጠይቀዉ ሲመልሱ የአማራዉ ቁጥር የቀነሰዉ አማራዉን ኤይድስ ስለፈጀዉ ነዉ የሚል መልስ በመስጠት በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ተሳለቁብን ተዘባበቱብንም፡፡ ይህን መዘባበት ሲፈጽሙብንም ቀድመዉ የሚስቁና የሚገለፍጡ ከአማራ ክልል ተመመርጠዉ የመጡ የፓርላማ አባላት ነበሩ፡፡ የግፍ አገዛዙ በአማራዉ ላይ እጅግ የበረታ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊነትንና የአገር አንድነትን በሚያቀነቅኑት በጉራጌዎች ላይም መከራዉና ስቃዩ የበረታ ነበር ዛሬም ከስቃይ አልወጡም፡፡ ታዲያ አማራዉ ድክመቱን ለማረምና ራሱን ከአንዣበበት ጥፋት ለመታደግ ምን ማድረግ አለበት የሚለዉን እንደሚከተለዉ በዝርዝር  አቀርባለሁ

ዛሬ በኢትዮጵያ አገራችን የሕዝቡ አመለካከት በጎሳ ፖለቲካ የተሳከረ፤ የብዙ ፖለቲከኞች አመለካከት በጭፍን ፖለቲካዊ አመለካከት የተበላሸ በአጠቃላይ አድማጭና ተደማጭ የጠፋበት መሆኑ ደግሞ አገራችንን በከፍተኛ ችግር ዉስጥ ጥሎአት ይገኛል፡፡ ስለዚህ አማራዉ ራሱን ከተጋረጠበት ጥፋት ለማዳንና በአሸናፊነት ለመወጣት በሁሉም መስክ የአማራዉ እንቅስቃሴና ትግል ጥበብና ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መመራት እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይህን የጀመረዉን መራራና አስቸጋሪ ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት ይችል ዘንድ አማራዉ ጥንካሬዉንና ድክመቱን፤ መልካምና አስጊ ዕድሎቹን በማጥናት፤የሥልጣን ጥመኝነቱንና የጎጥ አመለካከቱን አሽቀንጥሮ በመጣልና አንድ ወጥ የሆነ ስትራተጅ በመቀየስ ከፍተኛ ዝግጅት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ይህን በማድረግ መደገፍ ያለበት ደግሞ በመከራና በችግሩ ወቅት አንገቱን ከአሸዋ ዉስጥ ቀብሮ የሚቆየዉና ድሉ ሲቃረብ ሱፉንና ከረባቱን አሳምሮ ለሥልጣን የሚሮሯጠዉ ምሁሩ ክፍል መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ አማራዉ ያሉበትን ድክመቶች ግልጽ ለማድረግና ከፍተኛ ጥፋት ሳይደርስ እርምት ማድረግ ይችል ዘንድ ከአስከፊ ድክመቶቹ መካከል ጥቂቶቹን እንደሚከተለዉ እዘረዝራለሁ፡፡

፩. በተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖችና በየክፍለ ሀገራቱ ተበታትኖ የአመራር ማዕከላዊነትንና አንድነትን አጥቶ መገኘት

ዛሬ በአማራዉ መካከል አማራዉን ነጻ የሚያወጣ ከእኔ የተሻለ የለም የሚሉ፤ በባንዳነት ሥርዓቱን በማገልገልና በአማራዉ ስም በመነገድ የሥልጣን እርካብ ለመጨበጥ የሚንደፋደፉ አካላት የተበራከቱበት ወቅት ሆኗል፡፡ይህ ሁኔታም አማራዉን ጠንካራና አማክሎ ሊመራዉ የሚችል አካል ያሳጣዉ ስለሆነ እንደ አማራ ምሁራን ማኅበር፤ የኃይማኖት ድርጅቶችና የአማራ ሽማግሌዎች ያሉ አደረጃጅቶች እንደነዚህ ያሉ አስጠቂ ሁኔታዎች እንዲታረሙ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸዉ፤ በዚኅ ላይም ጠንክረዉ ሊሰሩ ይገባል፡፡ ዛሬ አማራና የአማራ ልጆች የሚፈልጉት አመራር በትምህርትና በልምድ የዳበረ፣ የረጋ አዕምሮ፣ አስተዋይና ሁለገብ ችሎታ ያለው እንዲሁም የሕዝብ ፍቅር ያለዉ ሆኖ ከጎጠኝነትና ከባንዳነት የፀዳ በቀላሉ ከመደሰት፣ ከመከፋት፣ተስፋ ከመቁረጥና ከመሳሰሉ ነፃ የሆነና አንድ ወጥ የአመራር ስልት በመፍጠር አማራዉ የአሉበትን ስህተቶች አርሞ ከጉዳትና ከጥፋት የሚታደገዉንና በአሸናፊነት እንዲወጣ የሚያስችለዉን ጠንካራ አመራር  መፍጠር ነዉ፡፡

የአማራዉ መከራ እንደዚህ የበዛዉ አንድ ሆኖ ባለመታገሉና አንድ ወጥ የሆነ አማራዊ ድርጅት አምጦ መዉለድ ባለመቻሉ ነዉ፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሁለት ጫፎች ላይ በተንጠለጠሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ተወጥሮ በመወዛወዝ ላይ ይገኛል፡፡ይህዉም በአንድ በኩል በአንድነት ኃይሉና ለኢትዮጵያ አንድነትና ታላቅነት የሚሰሩ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በጥቅም አሳዳጅ ጎሰኞችና የመበታተን አባዜ አዕምVቸዉን በሚያናዉዛቸዉ ቡድኖች መካከል ነዉ፡፡ከዚህ ላይ ከእነዚህ ሁለት መንገዶች መካከል ለአማራዉ የሚበጀዉ የትኛዉን ቢከተል ነዉ?የሚለዉ በጥሞና ሊታይና ሊገመገም ይገባዋል፣ አንዳንድ የአማራ የፖለቲካ ቡድኖች የአማራዉን ልብ በመብላት በአማራዉ ክልል ለጊዜዉ አሸናፊዎች ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ለአማራዉ ሊጠቅመዉ ይችላል ወይ?? በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተበታትኖ የሚገኝ ከ13 ሚሊዮን በላይ አማራን ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ለአማራዉ የሚበጀዉና የሚሻለዉ የአንድነት ኃይሉን ደግፎና አጠናክሮ በመምራት የያዘዉን መራር ትግል ከዳር ማድረስ አማራጭ የሌለዉ መፍትሔ ነዉ፡፡ ይህ ሲባል ደግሞ አሁን አማራዉ የገባበት ጦርነት በአማራ ፋኖ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ አማራዉ ከጥፋት የሚድንበት ሲሆን፤ እየተካሔደ ያለዉ የህልዉና ትግል በአማራ ፋኖ ተሸናፊነት ከተጠናቀቀ ደግሞ አማራዉ ጨርሶ ከገጸ ምድር የሚጠፋበት ባይሆን እንኳ እንደሰዉ ከማይቆጠርበት ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡

እንደሚታወቀዉ ሁሉ አንድ አካል ስትራተጅ (Strategy) በሚቀይስበት ወቅት የስትራተጅ አማራጮች (Strategic Opetions) ይዞ መራመዱ በአሸናፊነት ለመዉጣት ስለሚያስችለዉ አማራዉ የአንድነት ኃይሉን በማጠናከር በአንደኛ ደረጃ አማራጭነት ይዞ መÒዝ፤ ይህ ከከሸፈ ደግሞ የአማራዉ አጋር መሆን ይችሉ ዘንድ ከላይ የጠቀስኳቸዉን የአማራ የክልል ፓርቲዎች በሁለተኛ አማራጭነት ይዞ መራመዱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ለማስገንዘብ አወዳለሁ፡፡ ይህን ስል ግን አማራዉ በአለፉት 40 የመከራ ዓመታት ዉስጥ በደል አልደረሰበትም፤ አልተሳደደም፤ አልተገደለም ማለቴ አይደለም፡፡ ሆኖም አማራዉ በደረሰበት ስቃይና መከራ ተጠናክሮ መቀጠል እንጂ እባብ ያየ በልጥ ደነገጠ እንደሚባለዉ ሆኖ ከነበረዉ የኢትዮጵያን አንድነትና ታላቅነት ማቀንቀን ሊላላ አይገባዉም፤ ይህም መነሻየ አማራነት መደድረሻዬ ግን ኢትዮጵያዊነት የሚለዉ የአማራ ፋኖ  ራዕይ በደንብ ይገልጸዋል፡፡ ስለዚህ አማራዉ የአንድነት ኃይሉን በማስተባበርና አጠናክሮ በመምራት ኢትዮጵያን ከተደቀነባት ችግር ሊታደጋት ይገባል፡፡ ለመሆኑ አማራዉ አባቶቹ ደማቸዉን አፍስሰዉና አጥንታቸዉን ከስክሰዉ በማቆየት ያስረከቡትን አገር ለማን ጥሎ ነዉ በመነጣጠል ለበይ ዝግጁ ሆኖ የሚቀርበዉ? ጠቃሚ ያልሆነዉን የጥቅም፤ የቀበሊያዊና ጠባብነት አመለካከትና አሁን ከሚታየዉ መለካም ጅምር በበለጠ ሁኔታ በአንድ ወጥ አመራር በመደራጀት ዘሩን ከጥፋት ሊያደነዉ ይገባል፡፡

. መደማመጥ አለመቻልና እኔ ልምራ እኔ ልምራ የሚል የመምራት ጥመኝነት መኖር

በተገቢዉ መንገድ መደማመጥ አለመቻል፤ ጥሎ የማለፍና የጥቅመኝነት ጉዳይ የአማራዉ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዋነኛዉ በሽታ ሆኖአል፡፡ ዛሬ ወጣቱ ከአባቶቹ በመማርና ልምድ በመቅሰም ለተተኪነትና ለአገር ተረካቢነት መዘጋጀት ሲገባዉ በዚህ ዉስጥ ሳያልፍና መደማመጥ በሌለበት ለሥልጣን ሲሽቀዳደም ሲታይ ሁላችንም ከመጠምጠም መማር ይቅደም ልንለዉ ይገባል፡፡በአማራዉ መካከል መደማመጥ በመጥፋቱ የተነሳ የደረሱ ጉዳቶችን እንደምሳሌ ለማንሳት ያህልም -በ1967 ዓ.ም በተደረገዉ የመንግሥት ለዉጥ ከፊት ሆኖ በመምራት የአባቱን መሬትና ቤት እንዲነጠቅ ያደረገዉ የአማራ ወጣት ነዉ፤ በ1983 ዓ.ም ህወሃት/ኢህአዴግን አራት ኪሎ ድረስ መርቶ በማምጣት ራሱን ለመከራና ስቃይ የዳረገዉ ራሱ አማራዉ ስለሆነ በማንኛዉም መንገድ ተናቦና ተግባብቶ ለመራመድ መሞከር እንደነዚህ ካሉ ስህተቶችና ጥፋቶች ሊታደግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወጣቱ የአባቶቹን ምክርና የሕይወት ተሞክሮ በጥሞና ሊመለከተዉና የሕይወቱ መመሪያ ሊያደርገዉም ይገባል፡፡ሌላዉና የአማራዉ ከፍተኛ ድክመት ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለሥልጣን መሽቀዳደሙ ነዉ፡፡ አብርሃም ማስሎቭ የፍላጎት ደረጃዎችን  በዘረዘረበት መጽሐፉ ላይ እንደገለጸዉ የሰዉ ልጅ በተፈጥሮዉ ሥልጣን ወዳድ ቢሆንም ቅሉ ይህ ሁኔታ በአማራዉ ላይ ጎልቶ ስለሚታይ ሥልጣንና ኃላፊነት በዕዉቀት፤ በችሎታና በሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን መለመድ አለበት፡፡መምራት እንዳለ ሁሉ መመራትና መሪዎቹን ከታች ሆኖ መደገፍና ማበረታታት ለአማራዉ የሚጠቅም ነዉ፡፡ አማራዉ ሊገነዘበዉና ሊለማመደዉ የሚገባዉ አገልጋይነትን (Stewardship) አንጂ ሥልጣን የጥቅምና የበላይነት መጨበጫ ሆኖ መወሰድ የለበትም፡፡ በወቅቱ ኢየሱስ ክርሰቶስ የዓለምም ሆነ የኃዋርያት መሪና ጌታ ነበር፡፡ሆኖም በአርዓያነት ለዓለም ያስተማረዉ አገልጋይነትን (Stewardship) ነዉ፡፡ ለዚህም ዝቅ ብሎና አጎንብሶ የኃዋርያትን እግር ማጠቡ አገልጋይነትን ለማስተማር ስለሆነ በራስ ሕዝብ ላይ በገዥነት ፊጥ ለማለት ሳይሆን ለአገልጋይነትም መለማመድና መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ላይ በሰሞኑ በዲያስፖራዉ መካከል የምንመለከተዉ የጥቅም ማስጠበቂያ የሆነዉን ሥልጣን ለመያዝ የሚደረገዉን ሽኩቻና ፍትጊያ ስንመለከት አማራዉ ከዚህ ዓይነቱ ችግር ለመዉጣት ገና ብዙ ጊዜ የሚቀረዉ  መሆኑን ነዉ፡፡ የአማራ ፋኖ ከቦታዉ ላይ በመሆን መስዋዕትነትን እየከፈለ እያለ በዉጭ የኒገኙ ወገኖች ለማይተቅም ጥቅም ሲባል እንደዚያ መወነጃጀልና መካስስ በጣም አስከፊና የተሞተለትን ትግል አሳልፎ መስጠት አንደሆነ ልንገነዘበዉ ይገባል

. አማራዉ አጋር ከሆኑ ወገኖች ጋር አብሮ መታገል አለመቻል

አማራዉን ለማዳከምና ለማጥፋት ጥረት ያደርጉ የነበሩ አካላት በየካቲት 1968 ዓ.ም በጻፉት ማኒፌስቷቸዉ ላይ ከቀየሱአቸዉ ሰባት ስትራተጅዎች መካከል አንዱና ዋነኛዉ አማራዉ በሌሎች ብሔረሰቦች ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል እንዲሁም የመግደል ድርጊት እንደፈጸመ የሐሰት ትርክት በማቅረብ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ በአማራዉ ላይ እንዲነሳ ማድረግ አለብን የሚል ነበር፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ኃይማኖትና በአማራዉ ላይ እየደረሰ ያለዉ የጥፋት ዘመቻም የዚያ እኩይ የሀሰት ትርክት ዉጤት መሆኑን ልብ ልንለዉ ይገባል፡፡

አማራዉ እንደነዚህ ያሉ ክፉ ስትራተጅዎችን ለመቀልበስ በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ከሚያምኑና በአgም አንድ ከሆኑ ወገኖቹ ጋር በአንድ ላይ በመሆን ለመታገል ስትራተጅ ቀይሶ መራመድ አለበት፡፡ከእነዚህ አጋር ወንድሞች መካከልም ጉራጌዎች፤ አፋሮች፤ ሶማሌዎችና ደቡቦች የመጀመሪያዎቹና ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ አካላት በተለይ ደግሞ ጉራጌዎች ከአማራዉ ጋር በባህል፤ በስሜት፤ በአስተሳስብ፤ በኃይማኖት፤ በቋንቋ ና በዘር ግንድ አመጣጥም አንድ ናቸዉ፡፡ጉራጌዎች እንደ አማራዉ ሁሉ ኢትዮጵያዊያን ነን በማለታቸዉና ለኢትዮጵያ አንድነት በመቆማቸዉ ሕወሓት/ ኢህአዴግ በአለፉት 30 ዓመታት ዉስጥ ከፍተኛ ጥቃትና በደል ሲያደርስባቸዉ ቆይቷል፡፡

የኒዮርክ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪና ተመራማሪ የሆነዉና ከእንጦጦ ተራራ የባህር ዛፍ ቅጠል ለቅመዉ በመሸጥ ቤተሰባቸዉን በሚያስተዳድሩት ሴቶች ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ማለትም የነጮች ጫና (The white mans’ burden ) በሚለዉ አስደናቂ መጽሐፋቸዉ ላይ እንደገለጹት በደርግ ዘመነ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው ዝቅተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች መካከል የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጆች ሰላሳ አራት በመቶውን ይዘው በመምራት ላይ ነበሩ፡፡ ሕወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ግን እነርሱን ወደ አሥራ ስምንት በመቶ በማውረድ አራት በመቶ የሚወክሉት የቀድሞ ፖለቲከኞች በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚካሔደው የንግድ ሥራ ሠላሳ አራት ከመቶውን (34%) በመቆጣጠር ከሁሉም ብሔረሰብ በቀዳሚነት ላይ ተቀምጠዉ ይገኙ ነበር፡፡ በወቅቱ ማንኛዉንም ቁሳቁስ ከዉጭ በማስመጣት በመርካቶ የጅምላ አከፋፋይነቱን ሥራ ተቆጣጠረዉት የነበሩም የነዚሁ ፖለቲከኞች ቤተሰቦችና ወዳጆች ነበሩ፡፡ በአንዲት ኢትዮጵያ አመለካከታቸዉ የጸኑ በመሆናቸዉም 8% ያህሉ ጉራጌዎች ከመርካቶ ንግዳቸዉ በግፍ እንዲነቀሉ ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩል በየክልሉ በፊትም ሆነ ዛሬ ጉዳት እየደረሰባቸዉ ያሉት በሥራ ምክንያት ከትዉልድ ቀያቸዉ ወጥተዉ በሥራ ላይ በሚገኙ አማራዎችና ጉራጌዎች ላይ ነዉ፡፡ ስለዚህ አማራዉ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በፍቅርና በሰላም አብሮ ለመኖር እስከ ጥግ ድረስ በመሔድ መስራቱ መልካም ሲሆን እንደደቡብ፤ጉራጌ፤ አፋርና ሶማሌ ያለዉን የዐንድነት ኃይል ግን የትግል አጋሩ በማድረግ ቢራመድ የትግል ጉልበቱን አፈርጥሞ ኢትዮጵያ አገሩንም ሆነ ራሱን ከአደጋ በመከላከል ሒደቱ ላይ ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ስለዚህ በዚህ ላይ ጊዜ ሳይወሰድ በጥንካሬ ሊሰራበት ይገባል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ገዳዮቻችን የፋኖን ትግል ለማዳከምና ተሸናፊ ለማድረግ የኦሮሙማ ፖለቲካ አስፋፊዎች አየሰሩት ያለዉ ስትራተጅ ደግሞ  እስካሁን ሲያጠፉን የኖሩት ሴሜቲኮች ማለትም  ትግሬን፤አማራን፤ኤርትራንና ጉራጌን…  ማለት ነዉ ስለሆኑ ኩሾችን በማስተባበር እነርሱን ማጥፋት አለብን የሚል ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ ኦሮሙማን (oromumaa) ለማስፋፋትን በሌላዉ ብሔረሰበ ላይ ለመጫን እንዲያመቻቸዉ እንጂ ለሌላዉ በማስብ እንዳልሆነ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ስለዚህ ይህን መርዘኛ አካሔዳቸዉን ለማኮላሸትና የኢትዮጵያንም አንድነት ለማስጠበቅ አማሮች ሩቅ መንገድ በመሔድ ትግሬዎች የአማራ ፋኖ አጋር እንዲሆኑ ከተደረገ  የፋኖ አሸናፊነት የሦስት ወራት ጊዜ ሊወስድ የማይችል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል 

ኛ. ቸልተኝነት፣በበቂ ሁኔታ አለመደራጀትና ተበታትኖ ለጥቃት ተጋልጦ መገኘት፤

እንደ አማራ በኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ክልሎች ተበታትኖና ተዘርቶ የሚገኝ ብሔረሰብዕ የለም፡፡ የአማራ ድርጅቶች ይህን ሕዝብ በተገቢዉ ሁኔታ አንቅተዉትና አደራጅተዉት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ከፍተኛ ጥንካሬዉና ጉልበቱ ሊሆን በቻለ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም አማራዉን ከሁለት ከፍሎት እናገኘዋለን፡፡ይህዉም ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖር ሆኖ በዘሩ፤ በቋንቋዉና በኃይማኖቱ የተነሳ ትንኮሳ፤ የመሳደድ መከራና የሞት ጽዋን እየተጎነጨ ያለ ሲሆን በአማራ ክልል የሚኖረዉ ደግሞ ዘርን በተመለከተ በወንድሞቹ ላይ እየተፈጸመ ያለዉን መከራና ስቃይ በመገናኛ ብዙኃን በርቀት ከመስማት በቀር ብዙም በጥልቀት እየተረዳ ያለ አይደለም፡፡ይህ ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖረዉ አማራ ተበታትኖ ችግሩንም ሆነ ደስታዉን በአንድ ላይ ለመካፈልም ሆነ በአማራ ክልል ከሚኖር ወገኑ ጋር ተሳስሮ ለመኖር ይችል ዘንድ የሚያስተሳስረዉ አንድም የአደረጃጅት ሰንሰለት አልተፈጠረለትም፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በየሚኖርበት ከተማና ቀበሌ እንኳ የሚሰባሰብበትን መንገድ ፈጠሮ በአንድ ላይ ደስታዉንም ሆነ መከራዉን በአንድ ላይ መካፈል አልቻለም፡፡ ይህ ሁኔታም በተናጠል ጥቃት እንዲፈጸምበት አድርጎት ይገኛል፡፡ ይህም ያልተደራጀ ሕዝብ ሁልጊዜም የተሸናፊነትን ጽዋ ሲጎነጭ ይኖራል የሚለዉን የጠበብት አባባል ያስታዉሰናል፡፡ከዚህ ላይ የእኔ ጥያቄ ይህ ሕዝብ አንድነት ፈጥሮ በዘሩ ምክንያት ከሚደርስበት የመሳደድ፤ የመፈናቀልና የመገደል ጉዳት ራሱን ለመጠበቅ የአማራ ክልል መንግሥትና አመራር ምን ሰራ፤ምን እየሰራ ነዉና ምን ለመሥራትስ እቅድ ይዞአል ለሚለዉ መልስ የለንም፡፡ ይህም የሚያሳየን አማራዉ የአማራ ፋኖ አደረጃጅት ተፈጥሮለት የተስፋ ብርሃን እሰከ ፈነጠቀበት ጊዜ ድረስ የሚቆምለት የተደራጀና ከጥቅመኝነት የጸዳ ጠንካራ ወኪል የፖለቲካ ድርጅት ያልነበረዉ መሆኑን ነዉ፡፡ አንድ በአዴንን ይተካል በሚል በነአቶ በረከት ስሞን የተቆgመዉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ  (አብን) የሚባል ፓርቲ ተgቁሞ የዶ/ር አቢይ መንግሥት ወደ ሥልጣን መጥቶ አስከ አኮላሸዉ ድረስ የአማራዉ ተስፋ ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡ አሁን ግን አመራሩ ፓርቲዉን በጥቅም ስለለወጠዉ ለአማራዉ ቀርቶ ለራሱ ለፓርቲዉ አባላትም  በሚሆን አgም ላይ አይገኝም፡፡

. የአማርኛ gg ለማስፋፋትና ለማሳደግ ከአማራዉ ብዙም ተነሳሽነት አለመኖር

የአማርኛ ቋንቋ በዓለም ላይ የራሱ ፊደል ያለዉ፤እጅግ በጣም የዳበረ፤ አፍሪካዊያን የሚኮሩበትና ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቋንቋቆች አንዱ እንዲሆን የታጨ ከጥንት በቋንቋዎች አንዱ ነዉ፡፡ይህ ቋንቋ ሕወሃት/ኢህአዴግ ሥልጣን እስከያዘበት ቀን ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ በቋንቋ በመሆን ለብዙ ዘመናት የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተሳስሮ ሲያገለግል ኖሯል አሁንም በበብዙ ክልሎች በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡አማርኛ ከአማራዉ ክልል ዉጭ እንዳይነገር፤ በአማራዉ ክልል ዉስጥም ሆነ በፌደራል መንግሥቱ በሥነ ሥርዓት እንዳይነገርና እንዳይጻፍ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ አማራዉ ይህ እየተደረገ ያለዉ የራሱን ባህል፤gንgና ማንነትን ለማጥፋት መሆኑን በመገንዝብ ይህን ለመቀልበስ በትብብርና አንድ በመሆን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ይህን በመስበር በደቡብ ክልል የሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ቋንቋችን አማርኛ ባንዲራችን አረንÒዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ ነዉ በሚል ክልከላዉን በመቃወም በአማርኛ gንg በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ ክልል በብዙ ወረዳዎች ልጆቻችሁን በአማርኛ ቋንቋ አታስተምሩም ተብለዉ በየወረዳዉ የኢህአዴግ ዛሬ ደግሞ በብጽግና የፖለቲካ አስተዳዳሪዎች የተከለከሉ ዜጎች እስከ ፌደሬሽን ም/ቤት ድረስ በመሔድና የአቤቱታ ማመልከቻ በማስገባት ለመብታቸዉ ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡በዚህ ላይ የአማራ ክልል መንግሥት አመራርና አማራን እወክላለሁ ሲል የኖረዉ የቀድሞዉ ብአዴን የቅርቡ አዴፓ እነዚህን አካላት ለመደገፍና ቋንቋዉን በአገሪቱ ዉስጥ ለማስፋፋት ምን ለመስራት ሞከረ? የአማራ ምሁራን ማህበርስ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ያደረገዉ ጥረት ይኑር  አይኑር አላዉቅም፡፡

በአሁኑ ጊዜ እንደራሺያ ያሉ የዓለም ሀገራት በየት/ቤቶቻቸዉ ዉስጥ የአማርኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ወስነዉ ተግባራዊ  አደርገዉታል፡፡ ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ዉስጥ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ እንዳይሰጥና በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይም እንዳይሰጥ  በመንግሥት ደረጃ ሲከለከል አቤት የሚል አንድም የአማራ ባለሥልጣን ወይም አደረጃጀት አለመኖሩ በጣም የሚያሳዝን ሆኖ አግኝቸወለሁ፡፡

የታላቋ ብሪታኒያ መንግሥት የእንግሊዘኛ ቋንቋን በዓለም ላይ ለማሳደግና ለማስፋፋት የብሪቲሽ ካዉንስልን፤ የፈረንሳይ መንግሥት ደግሞ የፈረንሳይኛ ቋንቋን ለማሳደግና ለማበልጸግ አሊያንስ ፍራንሴን በዓለም ላይ በማቋቋምና ባጀት በመመደብ ቋንቋቸዉን ያስተምራሉ፡፡ይህ ደግሞ ቋንቋቸዉን ለማሳደግና ለማበልጸግ ከመርዳቱ በተጨማሪ የበለጸገ ቋንቋቸዉ ለዓለም ሕዝብ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጥ ዘንድም ጥረት በማድረግ ላይ ናቸዉ፡፡የአማራ ክልል መንግሥትም ሆነ ለአማራዉ ተቆርቋሪ ነኝ የሚል አካል ሁሉ እንደነዚህ ካሉ ወገኖች ትምህርት በመዉሰድ የአማርኛ ቋንቋን በኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ በዉጭ ይስፋፋና ይበለጽግ ዘንድ መዋቅር በመዘርጋትና ባጀት በመመደብ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማጠቃለያ

አማራዉ በመደማመጥና የአባቶቹን የቆዩ እሴቶች ጠብቆ በመያዝ ራሱን ጨርሶ ወደ አንድነት በማምጣት ተጠናክሮ የህልዉና የትግል ጉዞዉን በጥንካሬ መቀጠል አለበት፡፡ ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖረዉ አማራም ቸልተኝነቱንና የተበታተነ ሕይወቱን በመተዉ ለሕልዉናዉ ሲል አንድነቱን ማጠናክር ይችል ዘንድም ከፅዋ ማህበር ጀምሮ የተለያዩ አደረጃጅቶችን በመጠቀም ችግሩንም ሆነ ደስታዉን በአንድነት መካፈል ይኖርበታል፡፡

ዛሬ የዓለም ሕዝብ እየደረሰበት ያለዉን ችግር በአንድነት መወጣት ይችል ዘንድ ወደ አንድነት የዕድገት ጉዞ እየተመመ በአለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በጎጥና በቋንቋ በመለያየት እርስ በእርሱ በመጠፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ አካሔዳችን ደግሞ ለጠላቶቻችን ተዳክሞና ለጥቃት ተጋላጭ ሆኖ ከመገኘት ሌላ ምንም የሚያስገኝልን ትርፍ ስለሌለ ጊዜ ሳንወስድ ከዚህ ጥፋታችን በመመለስ ወደ ቀድሞ የአንድነት ሕይወታችን መመለስ አለብን፡፡ለዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ በእዉነት ላይ በመመርኮዝ ከእኩልነትና ከአንድነት ኃይሎች ጋር በመቆም አገሩን ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለልጆቹ ምን አዉርሶ ሊያልፍ እንደሚችል በእርጋታ ሊያጤነዉ ይገባል፡፤

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦን ይባርክ ይጠብቅም አሜን!!
የአማራዉ የህልዉና ትግል በፋኖ አሸናፊነት ይጠናቀቃል !! 

_

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉt.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉBorkena

የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡ በነጻ አስተያየት መድረክ የሚቀርቡ ሃሳቦች የጸሃፊውን እንጂ የግድ የቦርከናን ድረገጽ ሃሳብ ላያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መጣጥፍ ለማውጣት ከፈለጉ ጽሁፍዎትን በሚከተለው አድራሻ በኢሜይል ይላኩልን info@borkena.com

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት እዚህ ይጫኑ፡፡የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ zborkena@borkena.com

Ethiopian News
ትዊተር ፡ @zborkena
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
Ethiopia

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

1 COMMENT

 1. የያኔው ዘመን በዛሬው ነጠላ ጊዜ ሲታይ በባዶ ሜዳ ላይ ኡ ኡ ታ እንደማሰማት ይቆጠራል። የአማራን ህዝብ መከራ ጣራ ላይ ያወጡት ሻቢያና ወያኔ ናቸው። ይህኑ ጥላቻ እንዳለ ከእነ አታላው የተጋቱት ደግሞ ወረፋው የእኛ ነው የሚሉን በኦሮሞ ህዝብ ስም ለዘመናት የሚነግድት የብሄርና የቋንቋ ሰካራሞች ናቸው። አስተውሎ ላየው የአማራው ህዝብ በየዋህነቱና በሃገር አፍቃሪነቱ ያተረፈው መከራን ብቻ ነው። ተምረናል በማለት ለዘመናት ህዝብን እያማቱና እየተማታባቸው ያለፉና አሁንም በህይወት ቆመው የሚውተረተሩ የብሄር ልክፍተኞች ነጻ አወጣንህ ለሚሉት ህዝባችው ያተረፉት ሰቆቃና መከራን ብቻ ነው። ይህ በነፍሴ አውጭኝ ሩጫና በመንገላታት ከሃገር ወጥቶ በየስርቻው ተሸጉጦ ከዚህም ከዚያም እየቃረመ የብሄር ደጋፊ የሆነው ሁሉ አምኖበት ሳይሆን በሁለት ዓለም ለመኖር ለግል ጥቅም የሚደረግ እንደሆነ አይናችን ያያል። የህዝባችን መከራና ሰቆቃ በፍትህ እጦት፤ በዘርና በቋንቋ በተሰመረ የአፓርታይድ ክልል የሚደርስበትን ሃበሳ ልብ ያለው ይገነዘበዋል። የሻቢያ፤ ወያኔና የኦነግ ዓላማ አንድ ነው። የኢትዮጵያን አንድነት መናድ! ለዚህ ዓላማቸው ደግሞ የጋራ ጠላታቸው አማራና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ናቸው። ታሪክ እንደሚነግረን የጣሊያን ወራሪዎችም ስሌት ይኸው ነበር።
  ቄሱ ከመቅደሱ፤ ሼሁ ከመስጊድ፤ ገበሬው ከእርሻው ላይ የውጭ ጠላትን ተፋልመው ለቀጣይ ትውልድ ያስተላለፏት ውድ ሃገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ሰው እንበለ ፍርድ የሚገደልባት፤ የሚታፈንባት፤ የሚፈናቀልባት ባጭሩ እንደ ባቢሎን ከተማ ቋንቋዋ የተደባለቀባት የጉራማይሌ መንደር ሆናለች። ከደቡብ አፍሪቃው የነጭ ዘመን በተቀዳ የአፓርታይድ መንደር ምስረታ የምድሪቱ ሰዎች እንዳሻቸው ተንቀሳቅሰው ሰርተው እንዳይኖሩ አጥር ያጠረው ይህ የብሄር ፓለቲካ በሌቦች ተሰልቶ ለዘራፊዎች ቀዳዳን ያመቻቸ በመሆኑ እልፎችን እያስለቀሰ ጥቂቶችን ቱጃር እንዳደረገ ህዝባችን ይመለከታል። ግን ለዚህም ማብቂያ አለው። እንኳን አፍሪቃዊው ፓለቲካ የዓለም ፓለቲካም በየጊዜው አቅጣጫ እንደጠፋበት መርከብ ሲዋልል ማየት እየተለመደ መጥቷል፡ አሁን የሚያሰጋው በፋኖና በመንግስት የሚደረገው ፍልሚያ ይህን የዋህ ህዝብ ለተራዘመ መከራ እንዳይዳርገው ነው። በዚህ ላይ ወያኔ በዚህና በዚያ ነገሮችን እያማታና እያታለለ ዳግመኛ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ስልፍ እያመቻቸ እንደሆነ አመላካች ነገሮች አሉ። እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እሳት የሚነድበት የአማራ ህዝብ የወደፊት እድል ፈንታው ከአሁኑ የከፋ ወይስ የተሻለ ይሆን? ቆይተን እንይ!
  በማጠቃለያው በኢትዮጵያ ላይ ክፉ ያደረጉ ሃገሮች ሁሉም ባይሆኑ ይበልጡ እሳት በልቷቸዋል። ሊቢያ ለሻቢይ ሙሉ ድጋፍና አጥቂ መርከቦችን ሁሉ ያስታጠቀች፤ ሶሪያ፤ ኢራቅ የሻቢያን ሃይሎች ያሰለጠነች ያስታጠቀች ዛሬ የት እንዳሉ ሁላችን እናውቃለን። ሱማሊያ ለመለስ ዜናዊ ፓስፓርት በመስጠትና በሌሎችም ነገሮች ሲረዱ ዛሬ ላይ ሃገሪቱ ለሶስት ተከፍላ ሰው ከመቋዲሾ በጥቂት ኪሜትሮች ርቀት እንኳን ወጥቶ የማይዝናናባት ሃገር ሆናለች። ወያኔና ሻቢያን የኋላ ደጀን ሆና ያገለገለችው ሱዳን እሳይ እየላሳት ይገኛል። ከፊትና ከህዋላ እየተተኮሰበት ወደ ስደት የሚሸሻት “ሃዳስ ኤርትራ” ደግሞ የእድሜ ልክ ገዢው ሲሰናበት የሚከተለውን አብረን እናያለን። ባጭሩ ጊዜ ሰጠን ብሎ መናጠጥና በሰዎች ላይ ግፍ ማድረግ የማያዋጣ ስሌት እንደሆነ ታሪክ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በተሳከረና በፈጠራ ታሪክ አንድን ወገን ለይቶ ጠላቴ ነው ማለት የበታችነት ስሜት የሚያመነጨው ጥላቻ እንጂ ከተባለውና ከሚባለው ጉዳይ ጋር ተያያዥነት የለውም። የአማራ ህዝብ ቅን፤ አስተዋይና ሃገሩን ውዳድ፤ ሁሉን አቃፊ ህዝብ ነው። በዘርና በቋንቋ፤ በሃይማኖትና በሌላውም የጎጥና የመንደር ፓለቲካ ተሸብሽቦ ከመውተርተር ይልቅ ለሰው ልጆች ሁሉ በጎ የሆነ ነገር ሰርተን ለማለፍ ሰውን በሰውነቱ ብቻ እንመዝን። ከዘመናት በፊት ገሞራ ” በረከተ መርገም” ካሰፈረው አንድ ስንኝ ልዋስና ይብቃኝ።
  አኝኮ አመንዥኮ ከርትሶ ደቁሶ አድቆ ስልቆ ሰልቅጦህ እንዳትቀር
  አስብ ተመራመር ጠንቁል ተፈላሰፍ አጥብቀህ
  ተራቀቅ ላንተነትህ ስትል ሁኔታው ቢረቅም በዘመኑ ነገር
  ይህ ነው የገፋፋኝ ዛሬ ለመናገር!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here